የዋለልኝ ልጆች እግዚአብሔር ይይላችሁ!

በአልነካም ባይነታቸው አባቶቻችን አድዋ ላይ የቀበሩት የነጭ መንጋ አስከሬን የሙት መንፈስ እዚያው ተራራው ስር በባንዳነት ባህሪያቸው በታወቁት ወላጆቻቸው ተወልደው ላደጉና የበታችነት መንፈስ ለተናወጣቸው የሙት መንፈስ ልጆቻቸው ክፋት አገራችን ኢትዮጵያን አሳልፋችሁ በመስጠት ለዚህ ሁሉ የብሄረሰብ ክፉ የብጥብጥ በሽታ አሳልፋችሁ የሰጣችሁን የዋለልኝ ልጆች (ተከታዮች) እግዜር ይይላችሁ

እግዜር ይይላችሁ!

ተጨማሪ ያንብቡ:  አገዛዙ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ተጠየቀ | እስክንድርና አንዷለምን ጨምሮ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ዛሬም አልተፈቱም

10 Comments

 1. የሰው ልጅ መመዘን ያለበት በኖረበት ዘመን ነው። ዛሬ ላይ ቁጭ ብለው በየዘመናቱ የተነሱና የወደቁ አጼዎችን፤ በአመራር ቦታ ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሥፍራ የነበራቸውን የመጎነትሉ ሾተላዪች ራሳቸውን ማየት የቅድሚያ ምርጫቸው ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። የሃበሻ የፓለቲካ በሽታ ተላላፊ ነው። ግን ያም መጣ ይህ ሄደ ሁሌ የሚነገረን ለሃገር፤ ለህዝብ፤ ለሰንድቅ ዓላማ እየተባለ ነው። ችግሩ የሚነገረን ላይ ሳይሆን እየነገሩን የሚሰሩት ተግባር ከሥራቸው ጋር አለመጓዙ ነው። እንሆ በቅርቡ ወደ 100 ሚሊዪን ዶላር በህጋዊ መንገድ ሲያተራምስ የነበረ ሰው ተይዟል። የዘረፋና የማጭበርበር ስልታቸው ከቤተ መንግስት እስከ ውጭ ሃገራት ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች የተጠጋ በመሆኑ አሁን ያዝን የተባለው ግለሰብ ጅራቱ እንጂ የዚህ ዝርፊያ ቡድን ጭንቅላት አለመሆኑን ሰው ሊገነዘብ ይገባል። የወያኔው አምባሳደር ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ ከአውሮፓ እስከ ቻይና ይሰራ የነበረው ይህኑ የገንዘብ ማዘዋወር ስልትና ዘረፋ ነው። ከዚያም አሜሪካኖች መንግስት ይሆናሉ ብለው ለማደናገሪያ ያዋቀሯቸውን በአይነ ቁራኛ እንዲከታተል ሙሉ ባለሥልጣን ያደረጉት ያለፈና የአሁን የዘረፋ ስልቱን እያወቁ ነው። ዛሬ የስቴት ዲፓርትመንቱ የበላይ አንቶኒ ብሊንከን ሙሉ ጊዜውን ለወያኔ ጠበቃነት የሰጠው እንዲሁ በነሲብ እየተመራ አይደለም። ከአፍሪቃ እንደ ዪጎዝላቪያ ፍርክርኳን የሚያወጡት ሃገር ፈልገው እንጂ። አሜሪካ ሃገር ስታፈርስ እንጂ ሃገር ስትገነባ የታየበት ጉዳይ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በህዋላ የለም። የኢትዮጵያ መንግስት ም ዕራባዊያንን በመለማመጥ እውነትን እንዲጋቱ ማድረግ አይችልም። አቋሙን ግልጽ በማድረግና አልፎ ተርፎም ግልጽ በሆነ መልኩ እነዚህ ሃገራት በሃገሩ ጉዳይ ላይ የቀጥታና የተዘዋዋሪ ጣልቃ ገብነት እንደሚበጠብጡ ለዓለም በግልጽ በማስታወቅ እንጂ። ከሶስት ጊዜ በላይ የምሥራቅ አፍሪቃ ተወካይ የቀየረችው አሜሪካ እንዲህ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አይኗን የጣለችው ለምንድ ነው? በእውነት የወያኔ ግፍና ሥራ ጠፍቷቸው ነው? በጭራሽ። ሆን ብለው ሃገር ለማፍረስና ለማተራመስ ካቀድት ጉዳይ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው። ለዚህም ነው አሁን በደ/አፍሪቃ የሚደረገው የሰላም ድርድር የሰላም ድርድር ሳይሆን ለወያኔ የጊዜ መግዣና የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና ለማድረግ እንዲቻል ብቻ ነው። ሲጀመር ወያኔዎችን ለማንሳት ወደ መቀሌ የተጓዘው ወታደራዊ አውሮፕላን ምን ጭኖ ነበር? የሚያውቅ አለ? ትላንት ታደሰ ወረደ ዳግም እንዲደነፋ ያደረገው ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው። ለወያኔ ጥፋትን ማመን ሽንፈት አለመሆኑ አይገባቸውም። ያው በሰው ደም ሲጫወቱ ለዘመናት የኖሩ ስለሆኑ ደንዝዘዋል እንጂ የሚያገዳድሉን አይዞአቹ የሚሏቸው መሆናቸውን መረዳት ነበረባቸው።
  ለሃገራችን ቅጥ ያጣ መከራ ተጠያቂዎቹ በህይወት ያለን ሁሉ እንጂ የዋለልኝ ልጆች አይደሉም። እነርሱ በመሰላቸው ተፋልመው አልፈዋል። ከእነርሱ በህዋላ ሌሎችም በግፈኞች በቁማቸው ታንክ ተነድቶባቸዋል፤ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። ለሃገር ለህዝብ ነው ተብለው በየምድረበዳው ወድቀው ቀርተዋል። አሁንም በዘርና በቋንቋ እንዲሁም በክልል በተሰመረቸው ኢትዮጵያ የአፓርታይድ አሰራር ተዘርግቶ አንተ ውጣ አንቺ ኑሪ እሱን አቃጥል ያንን ግደል የሚባልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ስለሆነም የአሁኑን ክፋትና ክርፋት ዘንግቶ ከዘመናት በፊት የወደቁ ጀግኖችንም ሆነ ባንዳዎች መውቀሱ “ሟችን ወቃሽ” መሆን በመሆኑ በዛሬና ወደፊት በሚሆነው የሃገራችን ጉዳይ ላይ እናተኩር። በቃኝ!

 2. ወይ ጉድ አንተ አገር ገደሉ ትላለህ እነሱ ገልብጠው ላገር ሞትን ይላሉ። እንግዲህ የስድብ መአት ይዘንብብሀል ቻለው።

 3. ተስፋ እንደፈራሁት የመጀመሪያው ፍላጻ ወርዋሪ አንተ ሁነህ ተገኘህ። ትንሽ ትንሽ ነገር እያነሳህ ግዙፉን ነገር መከላክልና ማለባበስ ምን ይጠቅማል? ታንክ ተነዳባቸው ተጨፈጨፉ ትለናለህ ይህ ነገር ዛሬ ትግሬዎች ከሚያደርጉት ግፍ ሳይምታታብህ አልቀረም። ለዚህ እልቂት ከዋለልኝ መዝገብ ውጭ ማስረጃ ማቅረብ ትችላለህ? ታንክ የተነዳበትን ኢህአፓ ብታስነብበን። ወደድክም ጠላህም የናንተን ነቀፋ ሳይፈሩ ያስነበቡን ነው ሀቁ። የችግራችን ምንጭና መሰረቱ ያ ትውልድ ነው አመራር ላይ የነበሩት ያመኑትን አንተ ለማንሻፈፍ አቅጣጫ ለማስቀየር የምታደርገው ድካም ብዙም አይፈይድም። ባለፈውም በዚህ ጉዳይ ካንዱ ጋር አተካራ ገጥመህ ነበር። ትክክለኛ የፖለቲካና ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ያለህን አቋም ለማወቅ ተቸግረናል ያ ሊሆን የሚችለው ከእውቀትና ልምድ አኳያ በሌላው ደግሞ ከሌላው ጠርዝ ጋር ያለህ ስበት ሊሆን ይችላል ። አንተን ማለቴ ሳይሆን ሊሆንም ይችላል ትግሬዎች አንዱ የሚደግፈውን አምርረው ይቃወማሉ የሚቃወመውን ይደግፋሉ አላማው ህዝብ አብሮ እንዳይቆም ማድረግ ነው። በተረፈ ያልኩትን ካልሆንክ ወይም ዋቄ ፈና ወደ ተጣመመ መንገድ ወስደውኝ ከሆነ እኔ አይደለሁም ማለት ነው ሀላፊነት አልወስድም።

 4. I completely aggrege with the very rational, powerful, realistic… comment of Tesfa!

  The very simplistic political culture and mentality of blaming and accusing that generation not only without doing our own historic mission of this century but also horribly failing and being victims of a terribly brutal and criminal ruling circle of EPRDF/Prosperity is, I am sorry to say but I have to say is a very iodic political thinking and discourse!
  With all its weaknesses and mistakes that generation did what it believed was good for the advancement of the country based on a political ideology of the world that was divided into two camps and based on the very hard fact of an internal political system that was characterized by a very rigid, hypocritic, and of course had no true or genuine sense of behaving and acting for the sake of the wellbeing of the society at large!

  I Don’t really know why and how we do not have a real sense of shame or guilty conscience when we simply try to blame and condemn a generation that had tried to get something it had believed that it was the right to do despite its own weaknesses and failures! It is absolutely nonsensical to keep trying hard to make that generation an excuse to distance ourselves from our own responsibilities and accountabilities instead of trying to understand what went wrong in the past, learn a bitter lesson from it and do what is right and productive!

  Blaming and cursing that generation while we totally failed at least to slowdown the very political mad dogs our own ruling elites who keep causing unprecedently unbearable sufferings in all aspects of peoples’ lives is idiotic and deeply disturbing!!!

 5. አሁን ምን ይባላል ከ53አመታቶች በላይ ያስቆጥረው በጌዚአቸው እና ወቅቱ በፈቀደው ለኢትዮጵያ ህዝብ ስታገሉ የተሰው ታጋዮችን የዋለልኝ ልጆች በማለት ወቀሳ መሰንዘሩ ዋጋው ምንድን ነው? ለመሆኑ አንተ ጸሃፊው በጊዜህ ምን አደረግህ? የሀሰት ወሬ ከማማሰል በስተቀር፤ ከመቀቀል በስተቀር ፤መሠረተ ቢስ ወሬ ከማንፈር በስተቀር አለፍ ካለም በየጣሳ ቤቱ አንቡላ እና ቅራሬ እንዲሁም ቡሃቃ ከመገልበጥ በስተቀር እኔ ምን ሰራሁ ብለህ ራስህን ጠይቅ? ወያዬን ለማዳን የአውሮፓ እና የአሜሪክ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ እያደረጉ ያለውን ተጽዕኖ በመቃወም ኢትዮጵያውያን/ዊት ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ተቃውሞአቸውን በሰልፍ ሲገልጹ አንተ ግን ከፍሪነትህ የተነሳ ከደጃፍህ ሳትደርስ መቀመጫህ በገማው ነገር ተተትርኮ እንድነበር አንተም ተውቀው ነበር። ታዲያ ከላይ ፎቶአቸውን የለጠፍካው ብርያን መስቀል ዋለልኝ ጌታቸው ማሩ እና ማርታ በዚያ በጨለማው ዘመን አይምሮ ብርቱ አስተዋይ ቆርጥ ታግሎ አታጋዮች ለአላማቸው ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ እንጂ እንዳንተ ድውይ እና ሆዳም አልነበሩም በመሆንም በታጋይነታቸው ስማቸው ሲነሳ ይኖራል።

 6. ተስፋ የመጀመሪያዋን የስድብ አብሪ ጥይት ተኮሰ ማለት ነው በምክር አስመስሎ?

 7. አይኑ እያየ ልቡ ለታወረ ሰው መድሃኒት የለም። በተለያየ ስም ተፍረክራኪ ሃሳብ ማቅረቡ ቀላማጅነት ነው።

 8. የኢትዮጵያን ህዝቦች የግፍና የሰቆቃ ህይወት የማያውቅ ወይንም ህዝባችንን በግፍ ሲያሰቃዩ የነበሩ በባዥ ግፈኞች የልጅ ልጆችና የጥቅም ተካፋዮች እኒያን በህይወታቸው ተወራርደው የተሰዉትን ብርዬ ታጋዮች ይነቅፋሉ::
  እነዋለልኝ መኮንን ማርታ መብራቱ ጥላሁን ግዛውና መሰሎቹ ከንጉሱ ባለስልጣኖች የተወለዱና የተዛመዱ ሆነው የህዝባቸውን ሰቆቃ ማየት ባለመፈለጋቸው የታገሉና ህህይወታቸውን የሰጡ ለመሆናቸ በቅርብ የማውቃቸው ጄነራል መብራቱ ሲገኙ የሌሎቹም የታወቀ ነውና ጀግና ሰማእታቱን በሃሰ መክሰስ ይቁም::ወያኔ ዛሬ ለሚሰራው ደባ እኒያ ድንቅ ታጋዮች ያቀዱት ፈጽሞ አልነበረም ይልቅስ ፈኛውን ወያኔ ተባብረን እንፋለም ባለተረኛጽንፈኞችንም እንፋለም::

 9. አምባው ነህ ማነህ? ለአስተያየት የምትልከውን ስድብ ቀደም ብለህ ለሰዎች አሳየው ምናልባት እርምት ሊሰጡህ ይችላሉ ለነገሩ ስንቱ ይታረማል? የድፍረትህ ጥግ ያሳቅቃል የስድብህና ዘለፋህ ክብደት ልጆች እንዳያዩት ልዩ ጥንቃቄ ይጠይቃል። ሁኔታህ ሲታይ አንተ ሳትሆን ሰዎች የሚያስቡልህ ይመስላል። ትላልቅ ለሀገር የሚጠቅሙ ጨዋዎች የድር ገጹን ስለሚጠቀሙ ለቃላት አጠቃቀምህ ጥንቃቄ አድርግ ነገር ግን እድ ገትህ እንትን ተራ ከሆነ ምን ማድረግ ይቻላል በር ትተህ ተሳደብ።

 10. የማያውቁትን ለማወቅ ጥረት ማድረግ የትክክለኛ ተማሪዎች መንገድ ነው፡፡ ትንሽ ጫፍን ይዞ አዋቂ መስሎ ለመታየት የራሥን ፍላጎትና ምኞት ደርቦ መተረክ የአስመሳዮች መንገድ ነው፡፡
  ኢሕአፓ በነበረበት ወቅት፣ ዋለልኝ ያቀረበው ሃሳብ፣ እና በተማሪዎች እንቅስቃሴ ያለው ትርከት ከእውነታው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ነው፡፡ በርግጥ በዚህ የአጭር ሃሳብ ማቅረቢያ ላይ ሙሉውን ትክክለኛ ታሪክ ማቅረብና ማስረዳት አስቸጋሪ ነው፤ ሆኖም ግን መሠረታዊ የሆነውን ሀቅ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ ይሄን ተመርኩዘው ሌሎች መረጃዎችን በማፈላለግ ሙሉውን መረዳት ይቻላል፡፡
  ኢሕአፓና “የብሔረሰብ የብጥብጥ በሽታ!”
  ኢሕአፓ ከመላ ኢትዮጵያ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን ፓርቲ ነበር፡፡
  ኢሕአፓ የኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅቶች “የቅኝ ግዛት ድርጅት ነውና ተቀበል!” ያሉትን ባለመቀበሉ፤ ሸዓቢያ ቡችላውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርን እንዲወጋው አደረገ፡፡
  ኢሕአፓ የኢትዮጵያዊያን ፓርቲ በመሆኑና የብሄረሰብ ድርጅቶችን መብት ቢቀበልም፤ በትግራይ ምድር የመታገል መብት አለኝ ብሎ ቢንቀሳቀስም፤ የብHኤር ድርጅት አይደለህምና ከዚህ ጥፋ ብሎ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ድርጅቶች ወግቶታል፡፡
  ኢሕአፓ የብሄር ክልል አልመሠረተም፡፡
  ኢሕአፓ የብሔር መገነጣጠያ ሕገ መንግሥት አላስቀመጠም፡፡
  በወቅቱ የነበሩ የነፃ አውጪ ድርጅቶች ኢሕአፓን ወግተውታል፡፡
  ኢሕአፓ የአመራር ድክመት ስለነበረበት፤ መሪዎቹ ሁኔታው ለሚጠይቀው ወቅታዊ መልስ መሥጠት ባለመቻላቸው ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡
  ኢሕአፓ የማንንም ብሄር መገንጠል አላቀነቀነም፡፡ መብት አላቸው ብሎ ማለትና በፖለቲካ መድረክ መፍትሔ ይፈለግ ብሎ ማለት፤ ለብጥብጥ በሽታ መዳረግ አይደለም፡፡ ኢሕአፓ በወቅቱ ለሴቶች እኩልነት፣ ለሃይማኖት ተከታዮች እኩልነት፣ ለጭቁን ሕዝብና ለአገር እድገት የታገለ ድርጅት ነው፡፡
  ዋለልኝ ድርጅት አልመሠረተ፣ ጠመንጃ አላነሳ፣ በመንግሥት ሥልጣን አልነበረው፣ ማንም እንደሚያስበው ለአገሩ መፍትሔ ብሎ ሃሳብ አቀረበ! ለምን ሃሳብ አቀረብክ ነው ወንጀሉ?በወቅቱ የነበረው ዓለም አቀፍና የአገራችን ሀቅ ምን ያህል ለቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት ነበረው? ይሄን ማጤን ያስፈልጋል፡፡ለጊዜው በዚህ አቀኦማለሁ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share