በኢትዮጵያ ድፍን ሁለት ዓመት ሊያስቆጥር በጣት የሚቆጠሩ ቀናት የቀረዉ በኢትዮጵያዉያን እና በኢትዮጵያ ግዛት ስር በሚገኘዉ ትግራይ ክልል አስተዳደር ዛሬም ቀጥሎ ለያዥ ለገናዝዥ አስቸግሯል፡፡
ለዚህም የእርቅ ስምምነት ላይ ለማድረስ ይቻል ዘንድ በአፍሪካ ህብረት ሸምጋይነት ጥቅምት ፲፬ ቀን ሁለት ሽ አስራ አምስት ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ መሆኑ ይወራል ፡፡
እዚህ ጋር ይስማል ለማለት በግልፅ እና በጊዜዉ ለባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የሁለት ዓመት የዋይታ ዓመታት ግንባር ቀደም ግንባር ቀደም የመከራ እና ሞት ቀንበር ለተሸከመዉ የዓማራ እና አፋር ህዝብ ተሳትፎም ሆነ የመረጃ ተደራሽነት ባለቤት ሊሆን እንደሚገባዉ ስለሚታወቅ ነዉ ፡፡
የአለፉት ሁለት ዓመታት የሞት ነጋሪት የተጎሰመበት እና በቁም እንዲሞት የተፈረደበት የዓማራ እና የአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት በትህነግ ሲታወጂበት ዛሬ እንደሚባለዉ ግጭት ወይም በማዕከላዊ መንግስት እና ይህን ለመገዳደር ባልተደራጀ ወይም ህጋዊ ባልሆነ ስብስብ የሚካሄድ ጦርነት(Civil war )ማለት በኢትዮጵያ ላይ የደረሰዉን እና እየደረሰ ያለዉን ዘርፈ ብዙ የመከራ ቋጥኝ የተሸከመዉን ህዘብ መስዋዕት ማቅለል እና ለመፍትሄ የሚደረገዉን ጥረት ማደናቀፍ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡
ይህን በሁለቱ ህዝቦች በተለይም ለዘመናት በጠላትነት ፈርጆ ከእናት አገር ምድር ለማጥፋት ከፍተኛ የማንነት እና ዘር ተኮር ጥቃት ሲደረግበት የነበረዉን ኢትዮጵያዊ ዓማራ ህዝብ በግልፅ እና በዕብሪት በመዉረር እና በመመዝበር ከፍተኛ ሠባዊ ፣ ተፈጥሯዊ ፣ ባህላዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ በደል እና ምዝበራ በማድረግ በከፍተኛ ደረጃ ለይቶ ጥቃት ፣ ስደት ፣ዉርደት እና ሞት ያደረሰዉን ጦርነት ግጭት ወይም የመንግስት እና የተወሰኑ ቡድን ጉዳይ አድርጎ መዉሰድ ለዕርቅ ሳይሆን ለትዉልድ ጠንቅ ማስተላለፍ ነዉ ፡፡
ጦርነቱ በሦስት ዓለማ የተጀመረ እና የተካሄደ መሆኑ ሲታወቅ ይህም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ለማናጋት ከመቀሌ አስከሙያሌ የተነዛዉ ጥላቻ ዓማራን በማዳከም እና በማክሰም በዓማራ ሞት እና በኢትዮጵያ ፍርስራሽ አዲስቷን ትግራዋይ መቀለስ፣ የኢትዮጵያን መሰረት ለማናጋት ዕንቅፋት በሚሆኑ እና በታሪክ፣ በመልካምድር ፣ በብሄራዊ ስሜት እና ዕምቢ ባይነት የሚገመተዉን ህዝበ ኢትዮጵያ እና ለመስፋፋት እና ለመቀራመት ቅርበትም ፤ ፍላጎትም ያለበት የትግራይ አዋሳኝ የኢትዮጵያ ግዛቶችን ማመስ፣ማተራመስ፣ መድምሰስ የአፍራሽ ጦርነት የታወገበት እና የተካሄደበት ዓማራ እና አፋር አካባቢ እንደመሆኑ ከቅድመ ጦርነት አስከ ዛሬ የሚታዩ ሁነቶች ዋና አመላካቾች ናቸዉ ፡፡
ለዚህም ነዉ ጦርነቱ በዋና ነት መነሻዉም ሆነ መዳረሻዉ በትግራይ ፣በዓማራ እና በአፋር ሲሆን ከማዕከላዊ መንግስት ጋር የነበረዉ ጦርነት በሶስተኛ አማራጭ“ ሀረጉን መገዝገዝ ዛፉን ማወዛወዝ ” መሆኑን በመገመት የተካሄደ ጦርነት በመሆኑ እንጂ ትህነግ ሸዋ ደርሶ ወይም በሌላ አቅጣጫ ቢመጣ መንገዱ የመሪያም መንገድ መሆኑን አጥቶት እንዳለነበር መረዳት አይገድም ፡፡
እንዲያዉም የትህነግ በጦርነት ክሽፈት የጀመረዉ ገና ከ1983 ዓ.ም በፊት እና የማዕከላዊ መንግስት ስልጣን ተቆጣጥሮ እያለም ያስተገባ የነበረዉን በኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት ስር የሠደደ ጥላቻ ከጥቅምት ሀያ አምስት ሁለት ሽ አስራ ሶስት አስቀድሞ እና አሳልሶ የጦርነት ክተት አዋጂ እና ጦር አምጣ ምድር ድብደባ ሲያደርግ የነበረዉ ዓማራ ፣ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያ እና አስከሌለንበት ሲኦል ይግባ በማለት ይህን ዕኩይ ምኞት ዕዉን ያደረገዉ በዚሁ ነበር ፡፡
እኮ ጦርነቱ መቋጫ ያገኝ ዘንድ ከተፈከገ የበደለ ሊክስ ፤ የተበደለ ሊካስ ይህም ሲሆን ዕርቅ ከሆነ የዚህ የበደል ቋጥኝ የተሸከመዉ እና በአናቱ የተጫነበት ህዝብ ዉክልና በሌለበት በዳይ እና ገዳይ ከሳሽ በሆነበት የሚጠበቅ ዕርቅ ይሁን ድብቅብ ከዚህ ትዉልድ ወደ ቀጣይ እንዳይተላለፍ ተበዳይ የዓማራ እና የአፋር ህዝብ ከበዳይ ትህነግ ጋር ፊት ለፊት ሊነጋገሩ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር ፤ሊመቻች ይገባል፡፡
ይህ ካልሆነ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆኖ ነገሩን ቂም ይዞ ፀሎት ፤ ሳል ይዞ ስርቆት እንዳይሆን ቢታሰብበት የሚበጂ ሲሆን ይህም ጦርነቱ ሶስት መልክ ይህም በክልሎች( ትግራይ፣ዓማራ እና አፋር) ሆኖ ይህም የማዕከላዊ መንግስት በሌላ ገፅ የሚመላከት እንደመሆኑ አሁን ላይ በአፍሪካ ህብረት የሚደረገዉ ሽምግልና ጥረቱን እየፈጩ ጥሬ እንዳይሆን ነዉ ፡፡
ሟችም ገዳይም ኢትዮጵያ ሆነ በዳይ ተበዳይ በኢትዮጵያ ሠማይ ስር አስከሆኑ ሸምጋይም ፤ተሸምጋይም ኢትዮጵያዉያን በተለይም የጉዳዩ ባለቤት መወከል ነበረባቸዉ ፤ነዉም ፡፡ “ሲታጠቡ ከክንድ፤ ሲታረቁ ከልብ ”ይሏል እንዲህ ነዉ ካልሆነ የሰነፍ እርሻ እንዳንሆን አሁንም በራሳችን ጉዳይ ዝም አንልም ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ
NEILOSS Amber.
https://youtu.be/5Qy6nJEL3mQ