የወያኔ አመራሮችን ግፍ ለማጋለጥ እጄን ሰጠሁ ESAT [እውነት እና ንጋት] Oct 26 2022

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን ..! ከሁሉም በፊት

3 Comments

  1. በቅድሚያ ጋዜጠኛ አርአያ ተ/ማሪያም በአዲሱ ፕሮግራምህ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል። እህታችን የነገረችን የወያኔ የግፍ ሰበዝ ሞልቶ ከሚፈስ ጽዋ የተጨለፈ እንጂ የወያኔ ግፍና የመከራ ተግባር ተዘርዝሮ አያልቅም። መድፈር፤ መዝረፍ፤ መግደል፤ ማፈንና ማሰቃየት የሰውን ገላ እንደ ቄራ ከብት መግፈፍና መቆራረጥ የተካኑበት የግፍ ስልጣኔአቸው ነው። ገና ከጅምራቸው ጀምሮ ለትግራይ ህዝብ ያልቆሙ ለጥቂቶች ሲባል እልፍ ትግራዊያንን ለመከራ የዳረጉ ድርቡሾች ናቸው። FAU: An Ethiopian Famine by James Waller በ1980ዎቹ የትግራይ ወገኖቻችን በሱዳን የደረሰባቸውን ግፍና ገመና ቆንጥሮ ያሳያል። እኔን እጅግ የሚያስገርመኝ የአሜሪካ የጭፍን እገዛና የአውሮፓ ህብረት አሜሪካን ተከትሎ ወያኔን በመደገፍ ኡኡታ ማሰማት ነው። ያኔ ደብረብርሃን ወያኔዎች ደረሱ ሲባል ኤምባሲያቸውን ዘግተው የወጡት የክፋት ተባባሪዎቹ አሜሪካውያን አሁን አስታራቂ ሆነው መገኘታቸው የአሜሪካን የተንጋደደ የውጭ ፓሊሲ አሰራር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በየመን እልፎች በረሃብና በሳውዲና በተለጣፊ ሃይሎች እየተቀጠቀጡ አንድም ነገር የማይሉት አሜሪካኖች አሁን አንዴ ዘጠኝ ሴናተር ለዶ/ር አብይ ደብዳቤ መጻፍ፤ ሌላ ጊዜ የካናዳው መሪ መደወል፤ ሌላም ሌላም የቀጥታና የእጅ አዙር ተጽዕኖ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚያደርጉት ለኢትዮጵያ ህዝብ አዝነው ነውን? ጭራሽ። እናውቃለን አሜሪካና አውሮፓ ያሉ የዘር ፓለቲካ ሰልፈኞችን እያደኑ በማሰባሰብ መንግስት ለመፍጠር እኮ ዲሲ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሰጡ አድርገው ነበር። ያ አልሞላ ሲላቸው ሌላ ስሌት ይዘው ብቅ ብለዋል። በየትኛውም የዓለም ክፍል ቢሆን አንድ የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን በግፍ እጃቸው የተነከረ ጠባብ ብሄርተኞችን ለማዳን መቀሌ ድረስ ገብቶ ጅቡቲ ያረፈበት ታሪክ የለም። ይህ የሚያሳየው አሜሪካኖች ልክ እንዳለፈው ታሪካቸው ከደም አፍሳሾች ጋር በጥቅም የሚያስተሳስራቸው ጉዳይ መኖሩን ነው።
    አሁን የሰሜኑ ጦርነት መቋጫ ላይ እያለን ጦርነት ይቁም፤ ለድርድር ተቀመጡ፤ ኤርትራ ከትግራይ መሬት ትውጣ ገለ መሌ የሚሉት ለትግራይ ህዝብ አስበው አለመሆኑን ልብ ያለው ሊያስተውል ይገባል። ከፓርቹጋላዊው የተመድ መሪ ጀመሮ እስከ አውሮፓ ህብረት አይናቸውን ጨፍነው ከአሜሪካ ጎን የቆሙት እውነቱ ጠፍቷቸው ሳይሆን ስውር ሴራቸውን ለማሳካት ነው። ጠንካራና ሃብታም የነበሩ ሃገሮችን በውሸትና በሴራ ፓለቲካ የናድት እነዚህ ምዕራባዊያን ለምን በኢትዮጵያ ፓለቲካ ላይ እንዲህ ባለ መልኩ ጊዜና ሃብታቸውን ያፈሳሉ? ሚስጢሩ ግልጽ ነው። የኢትዮጵያን እድል ፈንታ መወሰን የምንችለው እኛ ነን ብለው ያምናሉ። እንደ ሊቢያ፤ ሶሪያ፤ የመን፤ ኢራቅ ወዘተ ማፈራረስና ከሩቅ ሆነው እያዪና እየሰሙ እኛ ስንጋደል የወሬ ማሟያ ያደርጉናል። ተርበው አበላናቸው፤ ታርዘው አለበስናቸው እያሉ የምጽድቅና እኛ ብቻ ለዓለም ሰላም ቆመናል እያሉ ያማታሉ። የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር። ጊዜው ተቀይሯል፡ ትላንት ዛሬ አይደለም። ሰው የሚነቃው ነቅቷል። በጅምላ አስተሳሰብ የሚነዳውም እንደ እንቁራሪት በደቦ ይጮሃል። ግን በእውነት ይህ በወሎ፤ በአፋር፤ በጎንደር፤ በትግራይ፤ በወለጋ ወዘተ የሚፈጸመው ግፍ ይገታ ይሆን? ወይስ ዝንተ ዓለም እንደተገዳደልን እንኖራለን። አታድርስ ነው። በቃኝ!

  2. ልጅቱ ቀላምጅ የምትናገረው የሚታመን አይደለም ባንዳ ሲጨንቀው ወደ ወገን ጦር እጁን ሰጥቶ የቀላመደውን ሳንመረምር መቀበሉ አግባብ አይመስልም ይልቅስ ልጅቱ ደም በእጇ ያለ ይመስላል ጎበዝ አንዘናጋ ለእስኛ መኖር በዛ ቦታ ብዙዎች አልቀዋል።

  3. አርአያ አይ መከራህ ከማይታመነው አብይ አህመድ ጎን ቁመህ ለጠላቶችህ አጋልጦ ይሰጥሀል እግዜር ይሁንህ ትግሬዎቹም አያስቀምጡህም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share