ሀ) ወያኔ የእኔ ናቸው የሚላቸውን በሰሜኑ የአማራ ታሪካዊ ርስቶችና ቦታወች መሆናቸውን ማረጋገጫ፦
ማረሻው ሚንሽር መጎልጎሊያው ጓንዴ
የአባ ስበር አገር ወልቃይት ጠገዴ
አለማጣ ዉዬ መልሼ አለማጣ
በበሽታዬ ላይ በሽታ ላመጣ
ለ) ጥቃትን በሚመለከት፦
እልም ነው ጭልጥ ነው ዉሀ አይላመጥም
ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም
በለው በሚንሽር አስኪደው በዋንዛ
በአባት መሬትና በሚስት የለም ዋዛ
ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው
አስቀድሞ መግደል ፊርማቶሪውን ነው
ፊርማቶሪ ማለት ለጠላት የተሸጠ የውስጥ ሰው ማለት ነው፡፡ ይህ አባባል ከራስ ወገን ሆነው በጣሊያን ወረራ ወቅት ለጣልያን ሲሰሩ ለነበሩ የአማራ ባንዳወችና ከሀዲወች በአርበኞች የተገጠመ ግጥም ነው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁኖቹ የተረኞቹ የኦሮሙማውች አገዛዝ ድረስ ያሉትን ከአማራ ውስጥ ወጥተው አማራን የሚያስጠቁትን ሁሉ ይመለከታል፡፤
በእኛ ዘመንም ይህንኑ ነውረኛ ስራ የሚሰሩትን በተለይም አሁን ላይ ለኦሮሙማ አሽከር ሆነው የአማራ አስጠቂ የሆኑትን የብአደንና የአብን ሆዳሞ አመራሮችን ለይቶ ይመለከታል፡፡ አማራው በአማራነቱ እየታደነ ከማለቁ በፊት አማራውን በተናጠልም ሆነ በጥምረት እየተናበቡ የሚያጠቁትን ጠላቶቹን ማለትም እየተንፈራገጠ ያለውን ወያኔንና በተቃራኒውም እያበጠ ያለውን ኦሮሙማን ስልት ነድፎ ሊያስወግዳቸውና ነጻ ሊሆን የሚችለው አስቀድሞ በውስጡ ያሉትን የአብይ አህመድ ምስለኔወች ሲያስወግድ ብቻና ብቻ ነው፡፡
አማራው አንዲነቱን አጠናክሮና በፋኖ ዙሪያ ተሰባስቦ ቆሞ ሁሉም አማራ በየሰፈሩ፣ በየመንደሩ፣ በየከተማው፣በየወረዳውና በየዞኑ ብሎም በክልል ደረጃ ያሉትን ሆዳሞ የኦሮሙማ ምስለኔወች እየመነጠረ መቀጣጫ በማድረግ ለፋኖ ደጀንነቱን በተግባር ካላረጋገጠ መቼም ቢሆን ከተደገሰለት የኦሮሙማ ወጥመድ አያመልጥም፡፡ እነዚህ የአብይ አህመድ ወደል አህዮች እያሉ አማራ ነጻ ይሆናል ርስቶቹንም ያስመልሳል የፖለቲካ ጥያቀወቹም መልስ ያገኛሉ ማለት ዘበት ነው፡፤
እንድገመው፡፡ አማራ ፍዳውና እዳው ገና እጅግ በጣም ገና ነው፡፡ መፍትሄው ህዝቡን ደጀን ያደረገና ከሆዳሞች የጸዳ የፋኖ(የአማራ ህዝባዊ ሀይል) ትግል ነው፡፡የተግባር ተሳትፎ ነው፡፤ ይህም መደረግ አያለበት ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው ; አሁን ነው፡፡ ነገ ይጨልማል፡፤ አማራን ባርያ አድርጎ የሚያስገዛው ወጥመድ በኦሮሙማ ተዘርግቶ አልቋል፡፡ ስለሆነም ፋኖን አማራው እንደአይነ ብሌኑ ከኦሮሙማና ከምስለኔወቹ ጠብቆ ካላዳነውና ፋኖ ሲመታ ወይንም ትጥቅ እንዲፈታ ሲደረግ ህዝቡ ዝም ካለ የአማራ ትግል ለረዥም ዘመን ወይንም ጭራሹኑ ተዳፍኖ ሊቀር ይችላል፡፡