በፊደራል ደረጃ  ልዩ ትኩረት የተደረገበት  የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፣ የ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ  ፈተና ልዩ መረጃ  –  በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

በመሥከረም 28/ 2015 ዓ/ም በሶሻል ሣይንሥ ተማሪዎች ፈተና ይጀመራል ። ይህ በፈተና አሰጣጡ ልዩ የሆነው አገር አቀፍ ፈተና ፣ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ጥንካሬ እና ደካማ ጎን በግልፅ እና በተጨባጭ የሚያመላክት ፣ በትምህርት ጥራት ላይ በትጋት እንዲሰራ የሚያደርግ ነው ። ተብሎ ይጠበቃል ። እንደሚታወቀው ገንዘብ ተኮር የትምህርት አሠጣጥ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መኖሩን ( በግል ትምህርት ቤቶች በክፍያ በመንግሥት ተምህርት ቤቶች ኮራብት በሆኑ መምህራን የተነሣ … )  በይፋ የሚያሳውቀን ይኽ በየዩኒቨርስቲ የሚሠጠው ፈተና በመሆኑ ፣ የትምህርት ሚኒሰትር  እና መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጡት ይታወቃል ።

ይህ ፈተና በአገር አቀፍ ደረጃ ፣ በፊደራል  ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ነው የሚካሄደው ። ፈተናው ልዩ ጥበቃ ይደረግለታል ። ፈታኝ መምህራንም በዕጣ ነው ፣ ለየዩኒቨርሥቲዎቹ የሚመደቡት ።   እያንዳንዱ አሥፈታኝ ትምህርት ቤት ፤ ተማሪዎች  እና ዩኒቨርስቲዎችን የሚመለከት ግዴታ ና መብትም በግልፅ ወጥቷል ። ይህንን በተመለከተ ያገኘሁትን መረጃ አሣጥሬ ለተማሪዎች እና ለወላጆች አሣውቃለሁ ።

 የአሥፈታኝ ተምህርት ቤቶች ግዴታ

  1. የተፈታኝተማሪዎችንሥም ዝርዝር አሥቀድሞ ለሚመለከተው ክፍል ፕሮቶኮሉን በጠበቀ መልኩ ያሳውቃል ።

2 . በበቂ ሁኔታ ተፈታኙን ሥለ ዩኒቨርስቲው እና ሥለ ፈተናው ህግ ያሣውቃል ።

3 . በሳይኮሎጂ የተጎዱትን ተማሪዎች ( በኮቪድ እና በሶሻል ሚዲያ ውዠንብር ) ሞራል መገንባትና ከኩረጃ ይልቅ በራሳቸው አእምሮ መሥራት አማራጫቸው መሆኑንን በወጉ ያሥረዳል ። አቅማቸውን ሣይጠቀሙ ቀርተው ጠባቂ በመሆን እንዳይወድቁ አሥቀድሞ ያነቃል ።

4 . የትምህርት ቤት እና የአድሚሽን ካርዳቸውን እንዳይረሱ ያሳስባል ።

5 . እያንዳንዱ አሥፈተኛ ት/ቤት ፤ የማህበራዊ ሣይንሥ ተፈታኞችን በመሥከረም 28/01/2015 የተፈጥሮ ሣይንሥ ተማሪዎችን ደግሞ በጥቅምት 6/ 2015 ዓ ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲዎች ቀጥሮ የማሥረከብ እና ፈተናቸውን ሲጨርሱ ቆጥሮ የመረከብ ግዴታ አለበት  ።

 

የተፈታኝ ተማሪውች ግዴታ 

  1. አንሶላ፣ብርድልብስ እና የሌሊት  ልብሶች ( ቱታ እና ፒጃማ ) ይዘው መምጣት አለባቸው ።
  2. ማንኛውንም ብልጭልጭ ቁሣቁሥ ፣ የመዘነጫ መነፅር ፣ የጆሮ ጌጥ ፣ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ሌላ የጌጥ ቀለበት ማድረግ የለባቸውም ።
  3. ማንኛውም  ሞባይል ሥልክ ፣ ላፕቶፕ ፣ ታብሌት ፣  ይዞ ወደ ዩነኒቨርስቲ መግባት ክልክል  ነው ።
  4.  እርሳስ ፣ ላቢስ፣ መቅረጫ ፣ ማሥመሪያ መያዝ አለባቸው ።
  5. የትምህርት ቤታቸውን እና የመፈተኛ መታወቂያቸውን  የመያዝ ግዴታ አለባቸው ።
  6.  ዩኒቨርሲቲከገቡበኋላ በሚገለፅላቸው  በዩኒቨርሲቲው ህግ የመተዳደርና ህጉን የመጠበቅ  ግዴታ አለባቸው ።
  7. እርጉዝተማሪዎችመፈተን አይቹሉም ። ከወለዱ በኋላ የሚፈተኑበትን ሁኔታ መንግሥት ያመቻቻል ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ብልጽግና ከወያኔ ጋር ቢደራደር ምንድን ነው የሚኮነው ? - ግርማ ካሳ

የዩኒቨርስቲዎች ግዴታ

  1. አሥቀድሞ  በተጠቀሰው ተማሪዎችን የመቀበል ቀን ፣ ከሚመለከተው አካል አሥቀድሞ በተረከቡት ሰነድ ፣ አንድ በአንድ ተማሪዎችን ማንነታቸውን በማረጋገጥ እና ከላይ የተጠቀሰውን ግዴታ ተማሪው ማሟላቱን በማረጋገጥ ፣ ህጋዊ ፍተሻ አድርገው ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው የማሥገባት ግዴታ አለባቸው ።
  2. ለተፈታኝ ተማሪዎች ፣ የሚያድሩበት ክፍል ፣ አልጋ እና ፍራሽ አሥቀድሞ አዘጋጅተው የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ።
  3. ለተማሪዎቹቁርስ፣ ምሣና እራት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ። ( በምግብ የሚነሳን ቅሬታ ከወዲሁ ለማሶገድ ዩኒቨርስቲዎቹ ትኩረት ሊያደርጉበት ይገባል ።)
  4. የተማሪዎቹ ፀጥታ እንዳይናጋ ፣ ማንኛውንም የፀጥታ ሥጋት እንዳይኖር ከፍተኛ ጥበቃና ምሥጢራዊ ክትትል ያደርጋል ።
  5.  ፈተናውንበተመለከተለተማሪዎቹ መብራሪያ እንዲሰጥ አደራሾችን ያመቻቻል ።

3 Comments

  1. ይህ አዲስ የፈተና አሰጠጥ ዘዴ ለቀጣይ በቂ ትምህርት ሊሰጥ የሚችልና የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያግዝ መሆን አለበት፡፡ ይህንን ለማስተጓጓል የሚሞክሩት ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት በጥቂቶች የአጠቃላይ የልፋት ውጤትና አገር መበላሸት የለበትም፡፡ ትምህርት ሚኒስቴርም ልክ ፈተናው እንዳለቀ ከመምህራን እና የኒቨርሲቲዎች ጋር አጠቃላይ ግምገማ በማድረግ የማሻሻያ መረጃ መሰብሰብ ያለበት ይመስለናል፡፡ በዚህ ፈተና ምደባ ላይ መምህራን በዕጣ ከተመደቡ ጥሩ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎችም የሚመደቡት ክፍልና የመቀመጫ ዴስክም በዕጣ ወይም በማይታወቅ ኮድ ቢሆን ጥሩ ነበር የተማሪ ትውውቅን ሊያስቀር ይችላል፡፡ ፈተናው የስውር ካሜራ ክትትል ቢኖርበትም ጥሩ ነው፡፡ ሌላው በሚዲያዎች የተወሰነ የመረጃ ሽፋን ቢኖርም በቀጣይ ግን ት/ሚኒስቴር በራሱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ አማከይነት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በመላ አገሪቷ በሁሉም ሚዲያዎች Aggressive የሆነ የማስተማርና ቅስቀሳ ስራ በደንብ ቢሰራበት ጥሩ ነው፡፡
    በመላ አገሪቷ ያሉ ት/ቤቶችም በቀጣይ የወላጅ ስብሰባ ሲያደርጉ የዚህን አመት የ12 ክፍል ፈተና አፈፃፀምን በአጀንዳ ይዘው እንደ ተሞክሮ ሊወያዩበት ይገባል፡፡ ት/ሚኒስቴርም በስብሰባው ላይ ተወካይ በመመደብ ሊከታተል ይገባል፡፡ አንድ አንድ የግል ት/ቤቶች ይህን አሰራር ስለማይወዱት ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል ምክንያቱም እነሱ ለቢዝነሳቸው ሲሉ በግሩፕ እንዲኮራረጁ በማድረግ ብዙ አሳለፉ እንዲባሉ ስለሚፈልጉ ለጥቅማቸው ስሉ አሁን የተጀመረውን ስራ አይፈልጉትም፡፡ ስለዚህ ት/ሚኒስቴር ጠበቅ ያለ ክትትል የማድረግና እርምጃ የመውሰድ ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል፡፡ ካልደፈረሰ አይጠራም ነውና ነገሩ ሁሉም በዚህ የጅማሮ ስራ ላይ ጠንክሮ በመሳተፍ ይህን የፈተና ስርቆት፣ የትውልድ ዝቅጠት እና ብሎም የአገር ውድቀት ነቀርሳን ማስወገድ ይጠበቅበታል፡፡

    የት/ሚኒስቴር አመራሮች በርቱ ግፉበት!!

  2. ይህ አዲስ የፈተና አሰጠጥ ዘዴ ለቀጣይ በቂ ትምህርት ሊሰጥ የሚችልና የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያግዝ መሆን አለበት፡፡ ይህንን ለማስተጓጓል የሚሞክሩት ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት በጥቂቶች የአጠቃላይ የልፋት ውጤትና አገር መበላሸት የለበትም፡፡ ትምህርት ሚኒስቴርም ልክ ፈተናው እንዳለቀ ከመምህራን እና የኒቨርሲቲዎች ጋር አጠቃላይ ግምገማ በማድረግ የማሻሻያ መረጃ መሰብሰብ ያለበት ይመስለናል፡፡ በዚህ ፈተና ምደባ ላይ መምህራን በዕጣ ከተመደቡ ጥሩ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎችም የሚመደቡት ክፍልና የመቀመጫ ዴስክም በዕጣ ወይም በማይታወቅ ኮድ ቢሆን ጥሩ ነበር የተማሪ ትውውቅን ሊያስቀር ይችላል፡፡ ፈተናው የስውር ካሜራ ክትትል ቢኖርበትም ጥሩ ነው፡፡

    ሌላው በሚዲያዎች የተወሰነ የመረጃ ሽፋን ቢኖርም በቀጣይ ግን ት/ሚኒስቴር በራሱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ አማከይነት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በመላ አገሪቷ በሁሉም ሚዲያዎች Aggressive የሆነ የማስተማርና ቅስቀሳ ስራ በደንብ ቢሰራበት ጥሩ ነው፡፡ በመላ አገሪቷ ያሉ ት/ቤቶችም በቀጣይ የወላጅ ስብሰባ ሲያደርጉ የዚህን አመት የ12 ክፍል ፈተና አፈፃፀምን በአጀንዳ ይዘው እንደ ተሞክሮ ሊወያዩበት ይገባል፡፡ ት/ሚኒስቴርም በስብሰባው ላይ ተወካይ በመመደብ ሊከታተል ይገባል፡፡ አንድ አንድ የግል ት/ቤቶች ይህን አሰራር ስለማይወዱት ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል ምክንያቱም እነሱ ለቢዝነሳቸው ሲሉ በግሩፕ እንዲኮራረጁ በማድረግ ብዙ አሳለፉ እንዲባሉ ስለሚፈልጉ ለጥቅማቸው ሲሉ አሁን የተጀመረውን ስራ አይፈልጉትም፡፡ ስለዚህ ት/ሚኒስቴር ጠበቅ ያለ ክትትል የማድረግና እርምጃ የመውሰድ ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል፡፡ ካልደፈረሰ አይጠራም ነውና ነገሩ ሁሉም በዚህ የጅማሮ ስራ ላይ ጠንክሮ በመሳተፍ ይህን የፈተና ስርቆት፣ የትውልድ ዝቅጠት እና ብሎም የአገር ውድቀት ነቀርሳን ማስወገድ ይጠበቅበታል፡፡

    የት/ሚኒስቴር አመራሮች በርቱ ግፉበት!!!

  3. ይሄ ሰውየ በሄደበት ቦታ በሚመራው ድርጅት የነካው ነገር ሁሉ ወይ ምስቅልቅሉ ይወጣል ወይ ላይመለስ ይሰናበታል፡፡ ኢህ አፓ፤ግምቦት7፤ቅንጅት፤ቀስተ ዳመና፤አሁን ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴር፡፡ በመገላገያው ካልተገላገልነው ነገር እንዳበላሸ ይኖራል፡፡ አሁን አሁን ደግሞ ይሄ የመጀመሪያው ስራ ነው እየተባለ ነው በስተርጅና የስራ ልምድ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share