September 30, 2022
11 mins read

ብአዴን የዝንጀሮን ያህል እንኳ ኢፍትሐዊነትና ጥቃት አይሰማውም! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ ([email protected])

የሃያ ሰባቱ የህወሀት በምድር ታይቶ የማይታወቅ የስግብግብነት ደዌና የአሁኑ ተኢቦላ የከፋ “የኔ” ወረረሽኝ በሽታ በአማራ ጫንቃ እንደ ቀንበር የተጫነውን ብአዴንና አለቆቹን ተመራማሪዎች ስለፍትህ ታጠኗቸው ዝንጆሮዎች ለማወዳደር የሚያስገድድ ነው፡፡

Biadenበአሜሪካን አገር ጆርጅያ የሚገኘው ኤሜሪ ዩንቨርስቲ ጥናት ዝንጀሮ ኢፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንደሚያበሳጨውና አጥብቆ እንደሚታገል አመልክቷል፡፡ [1-2] የዚህ ጥናት ተመራማሪዎች በመጀመርያ ዝንጀሮዎች የወይን ፍሬ ተኩከንበር ፍሬ የበለጠ እንደሚወዱ የወይን ፍሬና የኩከንበር ፍሬ በመስጠት አረጋገጡ፡፡ ቀጥለውም ተመራማሪዎች ዝንጀሮዎቹን ለሁለት ከፍለው በሳንቲም የወይን ወይም የኩከንበር ፍሬ እንዲገዙ ሙከራውን አደረጉ፡፡

ዝንጀሮዎች የሚወዱትን የወይን ፍሬ ሲያሳዩአቸው ሳንቲም ለተመራማሪዎቹ ለመስጠት ፈቃደኛ ሆኑ፡፡ የማይወዱትን ኩከንበር ሲሰጧቸው ግን ሳንቲም ለመስጠት አቅማሙ፡፡ ምርምሩን በመቀጠል ተመራማው ሳንቲሙን ተዝንጀሮዎች ተቀብሎ ለአንደኛው ዝንጀሮ የወይን ፍሬ፤ ለሌላኛው ግን የኩከንበር ፍሬ ሸጠለት፡፡ ይኸንን ኢፍትሐዊ ግብይት የተመለከተ ኩከንበር የተቀበለው ዝንጀሮ ደሙ እንደተጣደ የብረት ድስት ውሀ ተፍለቅልቆ በተቀበለው ኩከንበር ተመራማሪውን ደለዘው፡፡ ይህ እውነታ የሚያሳየው ኢፍትሐዊነትና ጥቃት የዝንጀሮን አንጀት ሳይቀር እንደ አሻሮ የሚያሳርር እርኩስ ተግባር መሆኑን ነው፡፡

222rrተዝንጀሮዎቹ በተቃራኒ ኢፍትሐዊነት በምቾት ጉንጫቸውን እንደ ዱባ የሚያሳብጣቸውና ሆዳቸውን እንደ ተነፋ ፊኛ  የሚወጥራቸው ሎሌዎችን ብአዴኖችና ሰውበላ አለቆቻቸውን ነው፡፡

ለሰላሳ ዓመታት አማራ ተደጁ ሞፈር እየተቆረጠና በሥሙ እርጥባን እየተለመነ ሌሎቹ ፋብሪካቸውን፣ ትምህርት ቤታቸውን፣ ሆስፒታላቸውን፣ መንገዳቸውን፣ ድልድያቸውን፣ መብራታቸውንና የንፁህ ውሀ አቅርትቦትን ሲገነቡ አሳማው ብአዴን ይህ እንደ ሰሃራ በረሃ የተዘረጋ ኢፍትሐዊነት አልተሰማውም። የአማራ ልጆች ከሌሎች በከፋ ሁኔታ በጠኔና በበሽታ ሲያልቁ፣ ተድንጋይ ተቀምጠው ተዛፍ ሥር እንደ ጦጣ ሲማሩና በመላ አገሪቱ ስደተኛ ሲሆኑ ፍትህን ቀርቶ ይሉኝታን በማያውቁት ጅብ አልቆቹ ብአዴን የግመር ዝንጀሮን ያህል እንኳ የኩከንበር ናዳ አልጣለም፡፡ ይኸንን የሚያህል የአካል፣ የምጣኔ ሐብት፣ የጤናና የማህበራዊ ዘር የማጥፋት ግፍ ሲፈጠም የብአዴኑ ጉልቻ ደመቀ መኮነን ሊጋልብ ስልጣን የሰጠውን አለቃውን ለገሰ ዜናዊን “ለዘመናት በጨለማ የተሸሸገውን ድህነት በልማት ፀሐይ የገለጠ መሪ!” እያለ በፌስ ቡክና ትዊተር ሲያደንቅ የጫኑበት የኮርቻ ልጓም ትንሽ እንኳ አልገታውም፡፡

ብአዴኖች በአማራ መቃብር መንደር ለመገንባት እድሜ ልኩን የቃዠውን እርጉም “ድህነትን በልማት ፀሐይ የገለጠ” እያሉ በሚያሞካሹበት ወቅት የብአዴን አለቆች በወልቃይትና ራያ አማራን በመጥረግ  ሰይጣናዊ ዘመቻ እያደረጉ ነበር፡፡ ብአዴኖች አልቆቻቸውን በሚያደንቁበት ሰዓት ይህ አድግ ህጻናትንና ወጣቶችን አምባ ጊዮርጊስ፤ ጎንደር፣ ደብረታቦር፣ ቡሬ፣ ማጀቴ፣ ዳንግላ፤ ወልዲያና ሌሎችም ቦታዎች እንደ ዱር ሲጨፈጭፍ የተረፉትንም እየጎተተ ሲያስር ነበር፡፡ ብአዴን የአለቆቹን ዲያብሎሳዊ “ገድል” በሚሰብክበት ሰዓት አለቆቹ ከብአዴን ቢሮ ጣራ ተፈናጠው ፈረንጅ የረጠባቸውን ባሩድ በባህርዳር ሕዝብ እንደ ዝናብ ሲያርከፈክፉ ነበር፡፡ ይህ ሰቆቃ የሚያሳየው ብአዴኖች ፍትህን የዝንጀሮን ያህል የማያውቁ፤ የወገኖቻቸውን ደም እየጠጡና ሥጋቸውንም እየበሉ የሚደልቡ አሳማዎች መሆናቸውን ነው፡፡

በሎሌነት የሰላሳ ዓመታት ልምድ ያካበተው ብአዴን ዛሬም ገጣባው ሳይደርቅ በአዲስ ኮርቻ አዳዲስ ጌታዎቹን ተሸክሞ  እንደ አለሌ አህያ እየተጋለበ ነው፡፡ መጋለብ የሚጥመው አህያው ብአዴን የሚበትኑለትን እንክርዳድ እየቃመ አለቆቹ በትእዛዝ አለንጋ ሲጠበጥቡት የአማራን ሕዝብ ባልተጣፈረ ሸኮናው እንደልማዱ እየረገጠው ነው፡፡ “ኢፍትሐዊነትና ጥቃትን እምቢኝ” ያለውን ፋኖ ተአለቆቹ በሚሰጠው ትዕዛዝ በምንግጭሉ እየነከሰው ነው፡፡ የዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ተጥልፈው የውሀ ሽታ ሆነው ሲቀሩ ትንኝ እንኳን የሞተበት ሳይመስለው እርምን ቆርጥሞ የበላ ጉድ ነው፡፡ እናቶችና ህፃናት ቅደመ-አያቶቻቸው በደማቸው ታስከበሩት አገራቸው “መጤ” እየተባሉ ሲታረዱ፣ ሲቃጠሉና የተረፉትም ተባረው ጎዳና አዳሪ ሲሆኑ ብአዴን የዝንጀሮን ታህል እንኳ ኢፍትሐዊነትና ጥቃት ምንም አይሰማው፡፡

እንኳን ኢፍትሐዊነትና ጥቃት ሊሰማው ኢፍትሐዊትነትና ጥቃት ተሰምቷቸው ፍትህን የጠየቁትና ጥቃቱን የሚከላከሉትን ጀግኖች አማራን ሲያደማ በኖረበት ምንግጭሉ ዛሬም ነግንጎ እየነከሰ ነው፡፡ ሰፊውን የአማራ ሕዝብም ፍርፋሪ እያበላ ባሳደጋቸውና ባሰማራቸው ካድሬዎቹ በሃይማኖትና በጎጥ የመከፋፈል ሴራውን እንደቀጠለ ነው፡፡

እርጉሙ ብአዴን በወፌ ቆመች ተአህያነት ወደ አንበሳነት ይቀየራል ብሎ ተስፋ እሚያደርግ ቅንቡርስ በአዝጋሚ ለውጥ ሰው ይሆናል ብሎ እንደሚጠባበቅ ጅል እሚቆጠር ነው፡፡ “የዚህኛው ጎጥ ብአዴን ተዚያኛው ጎጥ ብአዴን፤ የዚህኛው ሃይማኖት ብአዴን ተዚያኛው ሃይማኖት ብአዴን፣ የተማረው ብአዴን ታልተማረው ብአዴን፣ የዚህኛው ጾታ ብአዴን ተዚያኛው ጾታ ብአዴን፣ የምድሩ ብአዴን ተማርሱ ብአዴን ይሻላል!” እያለ ተዝንጀሮም ታነሰው ብአዴን መልክ እየመረጠ የሚቧቀስ ከንቱም ወይ ብአዴን ድንግልናውን የወሰደው ካድሬ አለዚያም የዝንጀሮን ያህልም ፍትህን የማያውቅ ሎሌ አፍቃሪ ወለወልዳ ነው፡፡

የሰላሳ ዓመቱ እጅ እግር የሌለው ታሪክ እንደሚያሳየው ብአዴንም ሆነ አልቆቹ የዝንጀሮን ያህልም የፍትህ ግንዛቤ የሌላቸው አሳማዎች ናቸው፡፡ አሳም ከንፈሩን የምርግ ያህል የከንፈር ቀለም ቢቀቡት ያው አሳማ ነው፡፡ ተኢህዲን ወደ ብአዴን የተቀየረውን አሳማውን ብአዴንም አንዴ አዴፓ ሌላ ጊዜ ብልጥግና የሚል የተውሶ ከንፈር ቀለም ቢቀቡት ያው አሳማው ብአዴን ነው፡፡

ጆርጅ ኦርዌል እንዳለው አሳማ ሆዱን ለመሙላት እንሰሳትን እርስ በርሳቸው የሚያፋጅ፣ አፋጅቶችም ስጋቸውን የሚበላና ደማቸውን የሚጠጣ ከርሳምና እርኩስ ፍጡር ነው፡፡ ተብአዴን  አሳማዎች ነፃነትን፣ ፍትህንና ብልጽግናን የሚጠብቅ በጆርጅ ኦርዌል የእንሰሳት አብዮት ሲንዘላዘል የኖረው ቦቅሰር የተባለው መጋዣ ብቻ ነው፡፡ [3] አመሰግናለሁ፡፡

ዋቢ:-

  1. van Wolkenten M1, Brosnan SF, de Waal FB, Inequity responses of monkeys modified by effort.Proc Natl Acad Sci U S A. 2007 Nov 20;104(47):18854-9. Epub 2007 Nov 13.
  2. Patricia S. Churchland, Conscience,  The Origin of Moral Intution, Social Norms and Expectations
  3. George Orwell, Animal Farm, http://www.huzheng.org/geniusreligion/AnimalFarm.pdf(Last accessed in January, 2020)

 

 

ጥር ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop