ስኬታማ ትዳር ከአንድ ሰው ጋር ደግሞ ደጋግሞ በፍቅር መውደቅን ይጠይቃል

የቅርብ ጊዜ የፍቅር እና ትዳር ትስስር

በልጅነታችን ሁላችንም ፍቅር ካለ ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ይሆናል የሚል ህልም ነበረን፤ እውነታው ግን ትዳር ቀላል የማይባል መመቻመች የሚጠይቅ ነገር መሆኑ ላይ ነው፡፡ ፍቅር እና ትዳር ልክ እንደ ፈረሱና ጋሪው ኋላና ፊት ሆነው ነው የሚጓዙት የሚለው እምነት አሁንም ድረስ ሰፊ ቢሆንም ይህንን ሃሳብ የሚሞግቱ ሃሳቦች በአንፃሩ እየተጠናከሩ መጥተዋል፡፡ ይህንን ጥያቄ አብራርቶ ለመመለስ ጥልቅ ፍቅር እንዴት ያለ ነው? የሚለውን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

“ትዳር ለመመስረት የጦፈ ፍቅር አስፈላጊ ነው” የሚል ድምፅ ጎልቶ መደመጥ የጀመረው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፡፡ ስቴፋኒ ኮንተዝ “ይህ እሳቤ ከሁለት ክፍለ ዘመን ወዲህ የመጣ ነው፡፡ ሰዎች ሁልጊዜ በፍቅር ይወድቁ ነበር፤ እርስ በእርሳቸው ከልብ ይፋቀሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ፍቅር ለመጋባት እንደ ቅድመ ሁኔታ ይቀመጥ የነበረው ከስንት አንዴ ነው” ይላል፡፡ ኮንትዝ ቀጠል ያደርግናም እንዲህ ይላል “ፍቅር የትዳር የጎንዮሽ ተፈላጊ ውጤት እንጂ ወደ ትዳር መግቢያ ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ በብዙ ባህሎች አይታሰብም ነበር” በተመሳሳይ ሁኔታ ፓስካል ብሩክነር የሚከተለውን ይላል፡፡ “ትዳር በብዙ ባህሎች ውስጥ የተቀደሰ ትስስር መሆኑ ይታመናል፡፡ ከዚህ ውጭ ፍቅር ኋላ ላይ የሚመጣ ከሆነ እንደ አንድ ተጨማሪ ቦነስ ብቻ ይወስዳል፡፡ አሁን አሁን ግን ትዳር ለመመስረት ፍቅር ቅድመ ሁኔታ ሆኖ በመቀመጡ ከትዳር ይልቅ ፍቅር ቅዱስ ሆኗል፡፡ በምትኩ ትዳር ሁለተኛ ደረጃን እየያዘ ነው” በዚህ ምክንያት በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተጋቢዎች ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ሲሆን የፍቺ እና ያለ አባት ወይም ያለ እናት የሚመሩ ጎጆዎች ቁጥርም በአንፃሩ እያሻቀበ ነው፡፡ ብሩክነር ከዚህ በተጨማሪ ፍቅር ከትዳር ይልቅ ቅድሚያ ቦታ እየተሰጠው ቢሆንም እውስጥ ሆኖ ግን አጥፍቶ እየጠፋ ያለ ይመስላል ይላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን በዶሮ ሾርባ

ትዳር ለመመስረት የጦፈ ፈቅር ቅድመ ሁኔታ ሆኖ በመቀመጡ የትዳር ዋጋ ከፍ ብሏል፡፡ ይህም ትዳር የብዙዎች ቀዳሚ አጀንዳ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ይኸው አይነት ፍቅር መልሶ ትዳር መቅኖ ቢስ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የጦፈ ፍቅር የለም በሚል ምክንያት ባለትዳሮች እና ጥንዶች መለያትን እንደ ሁነኛ አማራጭ ተያይዘውታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኮሮናቫይረስ አምስት ደረጃዎች እንዳሉት ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን? - ቡሩክ ተሾመ

ፍቅርን እንደ ትዳር መሰረት ስናስብ ሁለት አይነት ተቃዋሚ ሃሳቦች ነፍስ ዘርተው ይነሳሉ፡፡

ትዳር ከፍቅር በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ነገሮችን ግምት ውስጥ እያስገባን የምንኖርበት ማዕቀፍ ነው፡፡

የጦፈ ፍቅር አጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ በመሆኑ በረጅም የጊዜ ሂደት የሚመጡ የፍቅር ሌሎች ገፅታዎች ይበልጥ ግንዛቤ ውስጥ ሊገቡ ይገባል፡፡

የመጀመሪያው ሙግት ትዳር በአንድ አይነት ማህበረ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ስርዓት ውስጥ የሚኖር ቁርኝት እንደመሆኑ መጠን የጥንዶቹ አጠቃላይ የደህንነት ይህንን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ማዕቀፍ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን መቻል አለበት የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው የመከራከሪያ ሀሳብ በሌላ በኩል የጦፈ የሚባለው ፍቅር አይነት ያልተረጋጋ፣ እና ለውስን ጊዜ ብቻ ደስታ የሚሰጥ መሆኑ ላይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለረጅም ጊዜ የተረጋጋ ህይወት ምንጭ ሊሆን ከሚችለው ትዳር ጋር ይጋጫል፡፡ እነዚህ ሁለት መከራከሪያ ሃሳቦች ሲጨመቁ ትዳር በሚመሰረትበት ወቅት ለፍቅር ብቻ ቅድሚያ የሚሰጥ ከሆነ መጨረሻው ሲያልቅ አያምር ይሆናል የሚል ነው፡፡

ትዳር ከፍቅር ውጪ የሚያስገኛቸው ሌሎች በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ትዳር ሲመሰረትም ሆኖ የመፍረስ አደጋ ሲያንዣብብበት እነዚህን ከጦፈ ፍቅር ውጪ የሚገኙ ተጨማሪ ሁኔታዎችንም ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ፣ ትዳር ሲመሰረት ጥንዶቹ በጋራም ሆነ በተናጠል ቤት ውስጥ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት እና ጥሩ ወላጅ መሆን መቻላቸው በቀዳሚነት ሊነሳ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ እውነትም በታሪክም ቢሆን ትዳር የጥንዶችን ጤናና ሀብት የሚያሻሽል ቢያንስ ቢያንስ እንኳን የማይጎዳ አብሮነት እንደሆነ ነው የሚታመነው፡፡ ለፍቅር ብቻ ሲሉ ትዳር መመስረት ግን ጥንዶቹ እነዚህን ተጨማሪ ገፅታዎች እንዳይመለከቱ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ እንደውም እንዲህ የሚነበብ አባባል አለ፡፡ ለጦፈ ፍቅር ብቻ ሲሉ የሚጋቡ ጥሩ ምሽቶችን እና መጥፎ ቀኖችን ያሳልፋሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: በኢትዮጵያ ቪያግራ ገበያ ደርቷል፤ * የቪያግራ ተጠቃሚዎች ሊያውቁት የሚገቡ እውነታዎችና ጥንቃቄዎች

ትስስር መፍጠር በፍቅር እና ትዳር መካከል ትስስር ለመፍጠር በጊዜያዊ የጦፈ ፍቅር ስሜት እና ዘለቄታ ባለው ጥልቅ ፍቅር መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘብ ያሻል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: የወሲብ አፈፃፀም ለጡንቻ፣ ለወገብና ለጀርባ ህመም ይዳርጋል እንዴ?

ጥልቅ ፍቅር እንደ ጊዜያዊ የጦፈ የፍቅር ስሜት ለተወሰነ ጊዜ ያህል ብቻ የሚጎበኘንን ጠንካራ የመፈለግ ስሜት ብቻ ሳይሆን አመለካከታችንን እና ጠባያችንን ዘለቄታ ባለው መንገድ ይቃኛል፡፡ ጠንካራ የሆነ ስሜታዊ ወሲባዊ ፍላጎት ብልጭታ ለተወሰነ ጊዜ ውስጣችን ይቆይ ይሆናል፡፡ በአንፃሩ ጥልቅ ፍቅር ግን ያለማቋረጥ እያበራ ስሜታችንን ያሞቃል፣ ጠባያችንን ያንጻል እንዲሁም ከጊዜ እና ቦታ ጋር የሚኖረንን ቁርኝት መልክ መልክ ያስይዛል፡፡ የጦፈ የፍቅር ስሜት የሚያሳየው አጭር ጊጊ የሚቆይ የስሜት ኃያልነትን ብቻ ነው፡፡ በሌላ በኩል ጥልቅ ፍቅር ግን በረጅም የጊዜ ሂደት ውስጥ የሚፈጠርን፣ በሁሉም መልኩ የሚያበራን፣ የሁለቱንም ጥንዶች ህይወት እንዲያብብ እና እንዲያፈራ የሚያደርግ ፍቅር ነው፡፡ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ህይወት ጥብቅ ከሆነ ጊዜያዊ ስሜት የተለየ ነው፡፡ የአፍታ ወሲባዊ ፍላጎት ከዘመናት የፍቅር ህይወት በላይ ጥብቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ጥልቀቱ እዘህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

ለጦፈ ፍቅር ብቻ ሲባል ትዳር መመስረት በ3 ምክንያት ብልህ ውሳኔ አይደለም፡፡

ፍቅር የሚለዋወጥ ስሜት ነው፡፡

ፍቅር ብቻውን ጠንካራ መሰረት ሊሆን አይችልም፡፡

ከፍቅር በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ነገሮች ያስፈልጉናል፡፡

የአንድን ሰው እንበልና አዕምሮአዊ ብቃቱን ወይም ደግነቱን ግምት ውስጥ ሳያስገቡ ትዳር መመስረት ለጊዜው አፍቃሪ ውሳኔ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን በረጅም ጊዜ አብሮነት ውስጥ ዋጋ ባላቸው ማገናዘቢያዎች ሲፈተሽ ግን አስፈሪ ውሳኔ መሆኑ ግልፅ ይሆናል፡፡

ትዳር ለመመስረት በምንነሳበት ወቅት ፍቅር ቦታ ሊኖው ይገባል፡፡ ይሁን እንጂ የዛሬም ሆነ የወደፊት ህይወት ደስታ እና ትርጉም ጊዜዊ የጦፈ የፍቅር ስሜት ላይ ብቻ ሊመሰረት አይገባም፡፡ ይልቁንም መተሳሰብን፣ መመሳሰልን፣ መጋራትን፣ እና በመጠኑም ቢሆን ስሜታዊ መፈላለግን መሰረት ያደረገ ጥልቀት ያለው ፈቅር ላይ ሊደገፍ ይገባል፡፡ ስኬታማ ትዳር ከአንድ ሰው ጋር ደግሞ ደጋግሞ በፍቅር መውደቅን ይጠይቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዘጠኙ የአማላይ ሴቶች ባህሪይና እነሱን መልሶ ማማለያ ምስጢር

ሰዋሰው

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: ባለቤቴ እኔ የማደርገው አይጥማትም፤ ሁሌ እንጨቃጨቃለን ለምትለው ወንድ 7ቱን ከሚስት ጋር ተስማምቶ የመኖር ጥበቦችን እንካ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share