September 28, 2022
10 mins read

ከአማራ ህብረት በሙኒክ (ጀርመን ) የተሰጠ የአቋም መግለጫ

የአማራ ኅብረት በሙኒክ (ጀርመን)
Amhara Union in München (Deutschland)

 

Municየአማራ ማህበር በሙኒክ (ጀርመን) ህዝባችን የገጠመውን፣ ውስብስብ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍና ፈታኝ የሆነውን የህልውና አደጋን ለመከላከል የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ትግል ለመደገፍ የተቋቋመ ህዝባዊ ማህበር ነው። መንግስት እና ጸረ-አማራ ጎራው የአማራን ህዝብ አንገት ለማስደፋት ከዚህ ቀደም “ህግ ማስከበር” በሚል ሽፋን አማራን እንደ ህዝብ፣ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ከጥፋት የታደጉ ከ12ሺ በላይ የፋኖ አባላትን በግፍ አስሮ የሚገኝ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ይህ ሳያንሰው ፋኖ ዘመነ ካሴን መንግስት በሽምግልና አታሎ ቅዳሜ እለት መስከረም 7. 2015 ዓ.ም. ትጥቁን ፈቶ እንዲገባ ካደረገ በኋላ ምክክር እየተደረገ ባለበት መካከል በ11.01.2015 ነውረኛው የኦሮሞ ብልጽግና መንግስት ከበባ በማድረግ “የተደበቀበት ቤት ውስጥ በህዝብ ጥቆማ አገኘነው” በሚል የክህደት ድርጊቱን እንደፈጸመበት መረጃችን ያመላክተናል። የአማራ ህዝባዊ ሀይል መሪ የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሴን “በድርድር” ሰበብ በሽምግልና ስም አስቀርቦ “በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር አዋልነው” የሚል ተራ የውሸት ዜና ማሰራጨት የአማራንም ሆነ የኢትዮጵያን የሽምግልና ባህል ያረከሰ የህዝባችን እምነት የናቀ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊት ነው። የዚህ ነውረኛ የመንግስት ድርጊት ሆን ተብሎ እቅድና ፕላን ተይዞለት አማራ የተከፈተበትን ወረራና ጭፍጨፋ እንዳይመክትና መሪ አልባ አድርጎ ለማስቀረት የሚፈጸም ጸረ-አማራ እንቅስቃሴ አካል መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ዛሬም በወለጋ፣በራያ፣በቆቦ፣ በማይጸምሪ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ንጹሃን አማሮች በፋሽስቱ ኦነግ ሸኔ እና በትሕነግ ጨፍጫፊዎች በጅምላ እየተገደሉና ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ ይገኛሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተፈጽመውን ወንጀል ለመርመር ገለልተኛ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የላከ ቢሆንም በአማራ ላይ የደረሰውን ጉዳት ተዘዋውረው በቂ መረጃ እንዳይሰበስቡ እና የጥቃት ሰለባዎችን እንዳያገኙ በማድረግ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማሳሳት ወንጀሉ ተዳፍኖ እንዲቀር ብዙ ደባዎች ተፈጽመዋል። ለአማራ ህዝብ ዓይንና ጀሮ የሆኑ ጋዜጠኞችን እና የማህበራዊ እንቂዎችን ያለ አንዳች ምክንያት የሚያስረውም በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድቀት ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ እንዳይደርስ ለማድረግ ነው። ባጭሩ ለውጥ መጣ ከተባለበት ግዜ ጀምሮ የአብይ መንግስት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው መጠነ ሰፊ ጉዳት ለሶስት አስርት ዓመታት አማራን በጠላትነት ፈርጆ ይገዛ ከነበረው የትሕነግ አገዛዝ ያልተናነሰ ምናልባትም ከዚያ የከፋ እንዲሆን አድርጎታል ብንል መሳሳት አይሆንም።

በመሆኑም የአማራ ህብረት በሙኒክ :-

1ኛ. በመላው የአማራ ክልል ከልጅ እስከ አዋቂ በተለያዩ መንገዶች ቁጣውን ማሰማት እንዲችል የትግል ስልቶች ተቀይሰው ዘመነ ካሴን፣ የተለያዩ የአማራ አንቂዎችን፣ ጋዜጠኞችንና በብዙ እስር ቤቶች በግፍ የታገቱ ፋኖዎችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ በመንግስት ላይ ጫና መደረግ ይገባዋል ብለን እናምናለን።

2ኛ. ዘመነ ካሴ ለአማራው ህዝብ በፋኖነት ብቻ ሳይሆን በፖለቲካው መድረኩም አማራው ያለበትን የመሪ አልባነት ክፍተት በመሙላት ትልቅ የፖለቲካ ሚና የመጫወት አቅም ያለውና በርካታ የአማራ ወጣትን ከጀርባው ያሰለፈ በመሆኑ እንደ አንድ ጠንካራ ብሄራዊ መሪያችን በማየት ልዩነታችን በይደር አስቀምጠንና ከአውራጃዊነት አስተሳሰብ ወጥተን በአንድነት ከዘመነ ካሴ ጎን እንድንቆምና ጠላትን እንድናሳፍር ጥሪያችንን እናስተላልፋልለን።

3ኛ. በሁሉም አቅጣጫ ያሉ የፋኖ መሪዎች፣ የአማራ ወጣቶች፣ የሴቶችና የሌሎች ማህበራት መሪዎች፣ የዘመነ ካሴን መታሰር አውግዘው የአቋም መግለጫ ማውጣቸውን እየደገፍንና እያደነቅን ሌሎች ድርጅቶች፣ ህዝባዊ ተቋማት፣ እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦችና በልዩ ኃይሉና በመከላከያው ያሉ ለሃገር ዋጋ እየከፈሉ ያሉ የአማራ ተወላጆች በለዘመነ ካሴ ያላቸውን አጋርነትን በሚችሉት መንገድ እንዲገልጹ ጥሪ እናስተላልፋለን ።

4ኛ. ዘመነ ካሴንና መንግስትን በሽምግልና እናስታርቃለን ብለው ወደ ባህርዳር እንዲመጣ ያደረጉና በጉዳዩ ውስጥ አውቀውም ሳያውቁም የተስተፉ የአገር ሽማግሌ ተብየዎች የሕዝብና የታሪክ ተጠያቂ ከመሆናቸው በፊት የነበረውን የሽምግልና ሂደት ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። ይህ ሳይሆን ቢቀር የሴራው አካል በመሆናቸው የአማራ ሕዝብ እንደሚፋረዳቸው ማስገንዘብ እንወዳለን ።

5ኛ. በውስጥም በውጪ ያሉ የአማራን ጉዳይ ይዘው የሚሰሩ ሚዲያዎች በየዕለት ፕሮግራማቸው የዘመነ ካሴን በግፍ መታሰር እና በአጠቃላይ በአማራ ላይ ያንዣበበውን አደጋ አጀንዳ አድርገው በመወያየትና በመቀስቀስ ህዝቡ በመንግስት ላይ ቁጣውን እንዲያሰማና መንግስት ከያዘው የተሳሳተ አቅጣጫ እንዲመለስ ወገናዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ እናደርጋለን ።

6ኛ. መንግስት ዘመነ ካሴን እና የአማራ ተቆርቋሪዎችን በማሰር የአማራን ትግል አፍናለሁ ከሚል የተሳሳተ እኩይ አስተሳሰብ ወጥቶ በህገ መንግስትና በመዋቅር የተደገፈውን አማራ ጠል ሰርዓት እና ስሪት ለመቀየር የሚያስችለውን መንገድ እንዲከተል እና የአማራ መሪዎችን ከማሰርና ከማሰደድ እንዲቆጠብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

7ኛ. በመጨረሻም በመንግስት ካድሬዎችና በአንዳንድ ተላላ የአማራ ፖለቲከኞች “በዘመነ ካሴ መታሰር አብይ የለበትም፣ ይህ ድርጊት በአካባቢ መሪዎች ፈቃድ የተፈጸመ ነው።” እየተባለ የሚወራው የማጨርበሪያና የመከፋፈያ ቅጥፈት እንጂ ፣ እውነታው የተረኛው መንግስት ፍላጎት፣ ፈቃድና ቀጭን ትዕዛዝ የፈጠረው ቀውስ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለንም። ስለዚህ ዘመነ የታሰረው በኦህዴድ/ኦነግ ስር የሰደደ ጥላቻና አማራን የማሳደድ የማፈናቀልና እንደ ህዝብ የማጥፋት ዓላማን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው እናስገንዝባለን።

 

የአማራን ህዝብ እረፍት መንሳት ይቁም!!!

ዓማራነት አሸናፊነት ነው።

መስከረም 16/2015 ዓ.ም

የአማራ ህብረት ሙኒክ/ ጀርመን( Amhara Union Munich)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop