September 28, 2022
6 mins read

የምንኖረዉ ለዕዉነተኛ ለዉጥ መሆን አለበት

r4444444አገር እየጣመሰ ፤ ህዝብ ደም እያለቀሰ በኢትዮጵያ የግለሰብም ሆነ የቡድን እና የህዝብ መብት የሚከላከል ህገ-ብዙኃን ባለመኖሩ ከሶስት አስርተ ዓመታት በላይ የዘለቀዉ አድሎ እና መድሎ የበዛበት የፖለቲካ -ህገ መንገስት ፖለቲከኞችን እና ጥቅማቸዉን ጠባቂ መሆኑ የህግ መከበር እና መታፈር ስጋት ዉስጥ ከጣለዉ ዓመታት ተቆጥረዋል ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ተነቅሎ በቦታዉ አረም -ኢትዮጵያ መትከል ፤ ዜጎችን በአገራቸዉ ባይተዋር የሚያደርግ ፣ በተፈጥሮ በህይወት የመኖር እና ሠርቶ ሀብት እና ንብረት የማፍራት መብት መግሰስ፣ ዜጎች በማንነታቸዉ ጠላት እና ወዳጂ አድርጎ የመለየት ፣ በልዩነት ማሳደድ እና ማዋረድ እና መግደል አንዲሁም የኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የሚያስችል ግልፅ እና ተዓማኒነት የሚጎድልበት  ህግ የህዝብ እና የአገር ጥቅም ለመከላከል እና ለማስጠበቅ የህግ ቅቡልነት እና በላይነት ለማስጠበቅ ይሆናል ብሎ ማለት ልማድ ነዉ ፡፡

ማንኛዉም ህግ ከተፈጥሮ መርህ የሚቃረን  እና ከአገር ጥቅም በላይ የሚሆንበት ለስልጣን ማስጠበቂያ እና የፖለቲካ ስልጣን ስርዓት ዕድሜ ለማራዘም ዓላማዉ ከሆነ ህግ የአገርን እና የህዝብን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሳይሆን ለመንጠቅ ጠንቅ መሆኑ የማይቀር ነዉ ፡፡ ይህም በአገራችን በህግ የበላይነት ሽፋን ለሠላሳ ዓመታት በአገር አንድነት እና ነፃነት ላይ የነበረዉን ትተን ላለፉት ሶስት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ -ትግራይ እና በኢትዮጵያ ናዕከላዊ መንግስት በተከሰተዉ አለመግባባት የሆነዉ ጦርነት የሕግ የበላይነት ጉዳይ እንደነበር በተደጋጋሚ ሲነገር የነበረዉ በሁለቱም በኩል ነበር ፡፡

ርግጥ ነዉ ኢህአዴግ ይሁን ትህነግ ሁለቱም የህግ የበላይነት የሚሉት እና የማስፈራሪያ ዱላ ህገ -ኢህአዴግ (መንግስት) ነዉ ፡፡ የትግራይ ህዝብ በህገ-ኢህአዴግ የራሱን ዕድል በራሱ ህዝበ ዉሳኔ አካሂዷል ሲል ፤ ኢህአዴግ /መንግስት ህገ- መንግስቱ ተጥሷል በሚል የህግ የበላይነት ለማስከበር ጦርነት ሲነደረደር ካለንበት ጊዜ እና ሁኔታ ላይ ደርሰናል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በግንቦት ወር የተከሰቱ 11 ታሪካዊ ሁነቶች

ከ1987  ዓ.ም ጀምሮ ህገ መንግስት/ህገ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የብዙኃን ኢትዮጵያን  ጥቅም የማያስከብር ይልቁን ተፈጥሯዊ እና ሠባዊ መብት እና ነጻነት የሚያሳጣ እና የሚያሳፍር መሆኑን በመገንዘብ በተለይም የዓማራ ህዝብ እና የዓማራ ህዝብ የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ሙሴ“ፕ/ር አስራት ወ/የስ ” አስቀድመዉ ዉድቅ በማድረግ የመጣንዉ ለህዝብ እና ለአገር ለዉጥ እንጂ ለመገልበጥ አይደለም በማለት ኢትዮጵያ እና ህዝቧን ከተዘጋጀላቸዉ የስደት ፣ዉርደት እና ሞት  ወጥመድ በመበጣጠስ ለማሻገር  መሪነታቸዉን በተግባር አሳይተዋል ፡፡

ለለዉጥ እና ለነፃነት በሚደረግ  ጉዞ በህገ- ኢህአዴግ  ፈቃድ እና ይሁንታ የሚጠበቅ ከሆነ የኢትዮጵያ ሆነ የዓማራ ህዝብ ያንን ጠላፊ እና አጥፊ የሆነዉን ህግ ዓሜን ብሎ መቀበል የነበረበት በዉልደቱ አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሠባት ነበር ፡፡

ሆኖም ዛሬ አገሪቷ እና ህዝቧ ቢያንስ 1/3ኛዉ በፀረ-ኢትዮጵያዉያን ቁጥጥር ስር ሆኖ  ዜጎች በህይወት መኖር አለመኖር በክፉዎች ፈቃድ በሆነባት አገር ህዝብ ራሱን እና አገሩን የመከላከል ተፈጥሯዊ እና ብሄራዊ መብቱን ለመከላከል እና ለማስቀጠል የኢትዮጵያዉያንን እና የዓማራ ህዝብ የመደራጀት ሠባዊ እና ተፈጥሯዊ  ማንነቱን የመዋጀት ትግሉ ከየትኛዉም ሠዉ ሰራሽ  የዓለም ህግ በላይ ክቡር የሖነዉ የሰዉ ልጂ እና የጋራ  ጎጇችን -ኢትዮጵያ በላይ ናቸዉ ፡፡

ስለዚህ ህግ  ከሠዉ ለሠዉ እንጂ ከፖለቲካ ጥቅም እና ስም የሚቀዳ የአገርን እና የህዝብን ጥቅም እና ስም የሚያሳጣ መሆን የለበትም ፡፡

ሁላችንም በምድር ላይ የምንገኘዉ እና በህይወት ለመኖር ዓምላክ ዕድል የሰጠን ለለዉጥ እንጂ  በዚህ ዓለም ከምናገኘዉ መናኛ ነገር የምንገላበጥ መሆን የለብንም ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop