የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች በነበሩባቸው የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ይካሄድ እንደነበረ መረጃው ነበረኝ አለ።
የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም እንዳለው ከወራት በፊት ከስደተኞቹ መካከል አንዳንድ ጊዜ በኃይል ጭምር ተዋጊዎችን ለመመልመል የሚደረጉ ጥረቶች እንደነበሩ “ተአማኒ ሪፖርቶች” ደርሰውት እንደነበር ለቢቢሲ ገልጿል።
በጥቅምት ወር ማብቂያ 2013 ዓ.ም. ላይ ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ድንበር ተሻግረው ወደ ምሥራቅ ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል።
የስደተኞቹ ከፍተኛ ኮሚሽን ወታደራዊ ምልመላ መኖሩን እንደተገነዘበ ጉዳዩን በተመለከተ ለሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት እና ለአካባቢ ባለሥልጣናት ስጋቱን መግለጹን አመልክቷል።
ይህንንም ተከትሎ ሁኔታዎች የተሻሻሉ ይመስሉ እንደነበር የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም ለቢቢሲ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ ገልጿል።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች በነበሩባቸው የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ይካሄድ እንደነበረ መረጃው ነበረኝ አለ።
የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም እንዳለው ከወራት በፊት ከስደተኞቹ መካከል አንዳንድ ጊዜ በኃይል ጭምር ተዋጊዎችን ለመመልመል የሚደረጉ ጥረቶች እንደነበሩ “ተአማኒ ሪፖርቶች” ደርሰውት እንደነበር ለቢቢሲ ገልጿል።
በጥቅምት ወር ማብቂያ 2013 ዓ.ም. ላይ ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ድንበር ተሻግረው ወደ ምሥራቅ ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል።
የስደተኞቹ ከፍተኛ ኮሚሽን ወታደራዊ ምልመላ መኖሩን እንደተገነዘበ ጉዳዩን በተመለከተ ለሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት እና ለአካባቢ ባለሥልጣናት ስጋቱን መግለጹን አመልክቷል።
ይህንንም ተከትሎ ሁኔታዎች የተሻሻሉ ይመስሉ እንደነበር የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም ለቢቢሲ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ ገልጿል።
የሰላም አስከባሪ አባላት በጦርነት መሳተፍ
ከጥቂት ቀናት በፊት ብሉምበርግ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ከትግራይ ኃይሎች ጎን ተሰልፈዋል የሚል ዘገባ አወጥቶ ነበር።
ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ትገባኛለች በሚሏት የአብዬ ግዛት ተሰማርተው ከነበሩት ሰላም አስከባሪዎች መካከል ሚያዚያ አጋማሽ 2014 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ አንመሰለስም ያሉት የትግራይ ተወላጆች ቁጥር ወደ 500 እንደሚጠጋ ከመካከላቸው አንዱ በወቅቱ ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር።
ብሉምበርግ በዘገባው ለደኅንነታችን እንሰጋለን በሚል በሱዳን ቀርተው ጥገኝነት ጠይቀው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቀድሞ የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት፣ ከሌሎች የትግራይ ተወላጆች ጋር በመሆን በሁመራ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መቃረባቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ነግረውኛል ብሏል።
የብሉምበርግ ዘገባን ተከትሎ ተመድ ለቀድሞ የሰላም አስከባሪ አባላት የስደተኝነት እውቅና ከሰጠ በኋላ ወደ ጦርነት ተሰማርተዋል የሚሉ ክሶች ሲሰሙ በተደጋጋሚ ሲሰሙ ቆይተዋል።
የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ግን የስደተኝነት እውቅናን የሚሰጠው የሱዳን መንግሥት መሆኑን ገልጾ፤ በዚህ ላይ የደርጅቱ ተሳትፎ የቴክኒክ ምክር እና ድጋፍ ማድረግ ብቻ መሆኑን አመልክቷል።
“ቁጥራቸው ወደ 650 የሚጠጋ የቀድሞ ሰላም አስከባሪ አባላት በሱዳን የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው 247ቱ” የስደተኝነት እውቅና ማግኘታቸውን ከፍተኛ ኮሚሽኑ ገልጿል።
ነገር ግን የስደተኝነት እውቅና የማግኘት ሂደቱን ሳያጠናቅቁ ከሚኖሩበት አካባቢ ጥለው ስለሄዱት ግለሰቦች የሚያውቀው መረጃ እንደሌላው ድርጅቲ ለቢቢሲ በኢሜይለ በሰጠው ምላሽ ገልጿል።
“ዓለም አቀፍ ሕጎች የስደተኝነት እውቅና ከማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ እንደማይሄድ እና አንድ ወታደር ጥገኝነት ለመጠየቅ ከፈለገ ወታደርነቱን መተው እንዳለበት ይደነግጋሉ” ሲል ከፍተኛ ኮሚሽኑ አክሏል።
ግጭት እንደ አዲስ መቀስቀስ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንደ አዲስ መቀስቀስ “ብዙ በተሰቃዩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ተጨማሪ ሰቆቃን የሚያመጣው ነው” ይላል።
ግጭቱ እንደ አዲስ ማገርሸቱ ተጨማሪ ሰዎች ደኅንነት እና ሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ሊያደርግ እንደሚችል ድርጅቱ ተንበያውን ያስቀመጠ ሲሆን፤ በሱዳን እና በመላው ዓለም ተፈናቅለው ለሚገኙ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ያጋጠመው የገንዘብ እጥረት እንዳሳሰበው ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን የእርስ በእርስ ጦርነት በመሸሽ በሱዳን የተጠለሉት አብዛኛዎቹ ሰዎች የሚገኙት ሩካባ እና ቱናያዳባህ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ መሆኑን የጠቀሰው ድርጅቱ፤ እነዚህ መጠለያ ጣቢያዎቹ ከኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛሉ ብሏል።
የግጭቱን ማገርሸት ተከትሎ አዲስ ተፈናቃዮች ስለመኖራቸው ክትትል እያደረገ እንደሆነ የገለጸው ኮሚሽኑ፤ እስካሁን ድረስ በተጠቀሱት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያም ሆነ ሃምዲያት ስደተኞች መቀበያ ጣቢያ ግጭት መድረሱን የሚያሳይ ምንም ሪፖርት የለም ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት በሱዳን በሚገኙ የሰብዓዊ ድርጅት ሠራተኞች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ያለው ድርጅቱ፤ እንደ አዲስ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ግን በቅርበት እንደሚከታተል ገልጿል።
BBC
ይህ ተመድ የተባለ ድርጅት ዝም ብለው ነገሮች ሲፈፀሙ ሲመለከት ቆይቶ አሁን ሪፖርት ማድረግ ምንድነው ጥቅሙ???? እሰከመቼ ነው በአገራችን ላይ የሚቀለደው???
Where were been this UN, comes with non-sense of report at this time???? Hummmmm, a good alliance of terrorist TPLF in which they violate the law & charter of the organization.
ወያነ 10 ልብ ይዞ ነው የሚንቀሳቀሰው። ኣንደኛ ለኣሚሪካኖች፡ ሁለተኛ ለኢትዮጵያኖች፡ ሰውስተኛ ለኤርትራውያን፡ ኣራተኛ ለሩሱ ህዝብ፡ ኣምስተኛ ለኣፍቃውያን፡ ስድስተኛ ለኤውሮፓ፡ ሰባተኛ ለዜና ሰዎች፡ ስምተኛ ልብ የማይል ህዝብ፡ ዘጠነኛ ለቻይና፡ ኣስረኛ UN እና የUN ግብረኣበሮች የተላለየ እንደ እስስት ሁኖ ይቀርባል። 1 ዋናው ተላላኪ ነው። 2 እንደ ተላለኪዎች ስራ ሰው ይገድላል፡ የለምንም ኣለብኝ ንብረትና ገንዘብ ይዘርፋል፡ ኣውሬውነቱ ግን ለሌላው ይሰጣል። ውግያ ራሱ ጀምሮ ለሌላው ይሰጣል። የ90 ሺ ኤርትራውያን ንብረትና ገንዘቡ ለመዝረፍ ሲመቸው፡ በለሌት ከኢትዮጵያ ኣባርረዋል። ደግሞ በውግያ ከተሸነፈ ብሃላ ወድሞሞች ነን ይላል። በኢትዮጵያ የኤርትራውያን ንብረትና ገንዘብ የነበረው በትሪሎን ይቆጠራል፡ ግን ወያነ ዘርፈዋል። ከኣመሪካን በመሆን ብዙ ሰው በእስር ኣሰቃይተዋል። ብኣመሪካን ድጋፍ በኣለም ሙሉ በሚኖሩ ኤትራውያን ስንት በደልና ስቃይ ኣድርሰዋል፡ ሃብቱንና ንብረቱ እንዳይቀሳቀስ ኣግደዋል። ለISS ኣሳልፎ ሰጥተዋል። ገድለዋል። UN እንዳላየ ዝብ ብሎ ኣልፈዋል። ወያኔዎች የኣባታቸው ልብ የዘው ነው የሚኖሩ። የኤርትራ ራስ ወልደንኪኤል ወያኔዎች ብኣስመራ (ሓዝሓዝ) ከሸነፈ ብሃላ፡ ራስ ኣሉላ እና ኣጸይ የውሃንስ ኣንተ ጀግና ነህ፡ እና ኣምነናል ብሎ ለእርቅ ወደትግራይ ከጠሩት ብሃላ፡ ገደሉት። ለዚ እና ለሌላው የትግራይ ልብ የሚገልጽ፡ ብኣስመራና እና ከረን የሚገኝ ጠመዝማዛው እና ኣሸጋሪው መንገድ ልቢ ትግራይ ተብሎ ይጠራል። ዛሬም ሃይል ስያገኝ ኣማራ ይበቀላለሁ ሲል፡ ከተሸነፈ ደግሞ ኣማራ እና ትግራይ ወድሞሞች ናቸው ይላል። የኤርትራ ነጽነት ማግስት፡ በኤርትራን ህዝብ ላይ የ30 ዓመታት ውግያ የወደመው ንብረትና የተጉድውን ሰው ለመጠገን ሲባል፡ የወያነ መሪ መለስ ዜናዊ የኤርትራ ቁስል ኣብቅተዋል ብሎ ነበር። ወያነ ብሻእብያ ድጋፍ ቤተመንግስት ሲገባ እና ቤተመንግስቱን ብሻእብያ ኮማንዶ ለ27 ዓመት ሲጠበቅ እንደነበር ሁሉን ያውቀዋል። የወያነዎች ልብ ግን ከኣመሪካኖች በቢሎን ዶላር ሲፈሰለት ወደ ጦርነት ገባ። የኣይናቸው ቀለም ካልማረን ከኢትዮጵያ የውጡ ሲል ኤርትራውያን ከቅያቸው ኣባረረ። ህጻን ከውላጅ፡ ወንድ ከሚስቱ እየለየ ሰው በግፍ ተባረረ። ይህ ብኣመሪካና ብUN በኣፍሪቃ ህብረት፡ ኢጋድ ፊትና ዓይን እየተመለከተ የተፈጸመ የሰይጣን ተግባር ነው። ለዚ ሁሉ ኤርትራውያን ይበቀላሉ፡ የተደረገውን ሁሉ በዓለም ፊትም የሙሴን በትር በላያቸው ያርፋል። (በኤርትራ ኣንድ ኣባባል ኣለ (ኣድጊ ዝገበረካ ጠይቂ ግበሮ!)