ኦሮሚያ ክልል፡ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ በታጠቁ ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት

በሲቪል ሰዎች ላይ ለደረሰው ግድያ፣ ጉዳት እና መፈናቀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ፣ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ስምሪትን የተመለከቱ እርምጃዎች የሰዎች ደኅንነት ላይ ስጋት በማያሳድር መልኩ ሊሆን ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ
ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም.

Amuru displacement

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ስር በሚገኘው ኡሙሩ ወረዳ ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ነዋሪዎች የተገደሉ፣ የቆሰሉ እና ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ወደ ኦቦራ ከተማ መፈናቀላቸው በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳስብ መሆኑን ገለጸ። ኮሚሽኑ ጥቃቶቹን ተከተሎ ነዋሪዎችን እና የመንግሥት አካላትን አነጋግሯል።

በዚህም መሰረት በአካባቢው ተሰማርቶ የነበረ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሌላ አካባቢ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ፣ በኡሙሩ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል፡፡

በነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ቀበሌ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ የሚጠራ) ታጣቂዎች የወረዳው ዋና ከተማ የሆነችውን ኦቦራ ከተማን ለመያዝ ባደረጉት እንቅስቃሴ ሦስት የአማራ ብሔር ተወላጆች መግደላቸውን ተከትሎ ከኡሙሩ ወረዳ፣ ሀሮ አዲስ ዓለም ከተባለ ቀበሌ እና አጎራባች ከሚገኘው የአማራ ክልል፣ ቡሬ ወረዳ የተውጣጡ ታጣቂዎች በኡሙሩ ወረዳ በሚገኙና አገምሳ፣ ጆግ ምግር፣ ታም ኢላሙ፣ ጀቦ ዶባን፣ ጦምቤ ዳነጋበ፣ ጃዋጅ፣ ኛሬ፣ ለገ ሚቻ፣ ሉቁማ ዋሌ በሚባሉ ቀበሌዎች የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ነዋሪዎች ላይ ነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ጥቃት ፈጽመዋል።

በእነዚህ ሁለት ቀናት በተደረጉ ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ70 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የነዋሪዎች የቤት ንብረቶች እና የቀንድ ከብቶች መዘረፋቸውን ኮሚሽኑ ካነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እና የመንግሥት ኃላፊዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ቀበሌዎች መካከል አሁንም ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን እና በጥቃቱ ምክንያትም ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በኦቦራ ከተማ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በተጨማሪም በጥቃቶቹ ምክንያት የተፈጠረው የደኅንነት ስጋት ያልተቀረፈ መሆኑን እና በዞኑ ውስጥ ካሉት ወረዳዎች መካከል በጃርደጋ ጃርቴ፣ ኪረሙ እና በአቤ ዶንጎሮ ወረዳዎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊፈጸሙ እንደሚችሉ ስጋቶች መኖራቸውን ኮሚሽኑ ከነዋሪዎች ያሰባሰባቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ኮሚሽኑ ጥቃት በተፈጸመባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እንዲሰማሩ እና ሰላምና ደኅንነትን በማረጋገጥ ነዋሪዎችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት የመመለስና ተገቢውን ምርመራ አድርጎ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠራ ያሳስባል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኮሚሽኑ ክትትል ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑንና በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመው አሳዛኝ ጥቃት ያሳሰበው መሆኑን ገልጸው በማንኛውም ጊዜ የፀጥታ ስጋት ካለባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሌላ ቦታ በሚዘዋወሩበት ወቅት የነዋሪዎች በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት እና የንብረት መብቶች ለአደጋ እንዳይጋለጡ ተገቢ የሆኑ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ እንደሚገባ በድጋሚ አስታውሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop