“ ለችግሩ ምክንያት የሆነ አስተሳሰብና አሰራር
ለመሰረታዊ ችግሮቻችን መፍትሄ አይሆኑንም ”
ጥላቻን የዘራ ጥላቻን እንጂ ፍቅርን አያመርትም!!
አንባቢያን በሁለቱ ግለሰቦች አማካኝነት በቀረበው መጣጥፍ ላይ የተቃውሞ አስተያየት ለመሰንዘር የገፋፋኝ በሁለት ምክንያቶች ነው። እነዚህም አንደኛው በያ ትውልድ ባጠቃላይ ምንም አይነት ልዩነቶችን ሳያደርጉ በጅምላ የጥላቻ ዘመቻ ማካሄዳቸው በተለይም ደግሞ በምንም ሁናቴ ምንም አይነት ግላዊ ትውውቅ ሳይኖራቸው ራሳቸውን ከበላይ ኮስፈው ዋለልኝ መኮንን ግን ንቀት በተሞላበት መልኩ የእውቀቱን ደረጃ ለመፈታተን ያደረጉት ፍረጃ በፍፁም ሕሊናዬ ሊቀበለው የማይችል ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸው ነበር። እስቲ ያቀረቡትን አብረን እንመልከተው። እንዲህ ይላሉ ሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬ።
“ብሔረተኞች/ዘውገኞች ለጥቅማቸው ሲሉ ዋለልኝ መኮንን ከስታሊን ፍልስፍና ገልብጦ ያቀረበውን ጽሑፍ ወይም ሌላ ሰው የጻፈለትን /አንዳንድ ሰዎች ስለሚገምቱ ነው/ ይጠቅሳሉ፡፡ ለመሆኑ ዋለልኝ በወቅቱ ስለ ኢትዮጵያ ወይም ስለ አፍሪካ ታሪክ በቂ አውቀት፤ የሥራና የሕይወት ተሞክሮ ነበረው ወይ? የኢትዮጵያን ሕዝብ ማሕበራዊና እኮኖሚያዊ ትስስር በቅጡ ሊረዳበት የሚችልበት የእድሜ፣ የሕይወትና የሥራ ተሞክሮ ነበረው ወይ? የሚል ጥያቄ አቅርበው እንዲህ ሲሉ ይመልሳሉ። “መልሱ አልነበረውም ነው፡፡” በመቀጠልም “ አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወጣት የሌላ አገር ችግር ፍልስፍና ያውም የአውሮፓ /የአፍሪካ እንኳን ቢሆን ጥሩ/ገልብጦ ስለ ጻፈ የኢትዮጵያ ችግር ባልሆነበት ችግር መፍቻ ብሎ በመውሰድ (ላም ባልወለበት ኩበት ለቀማ እንደሚባለው) የዘውግ ፖለቲከኞች የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የተጠቀሙበት ነበር እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ አይደለም፡፡” በማለት የተሳሳተ ትርከታቸውን በአነጋገር ዘይቤ አጅበው የማጠልሸትና ሰብዕናን የማቆሸሽ እኩይ ተግባር ዘመቻቸውን መሰረት ለመስጠት ሲቅበዘበዙ ይታያሉ።
እንግዲህ በቅድሚያ “ከስታሊን ፍልስፍና ገልብጦ” ና “ የኢትዮጵያ ችግር ባልሆነበት ችግር መፍቻ ብሎ መውሰድ “ የሚሉትን ሁለት ሀረጎች በሚገባ ተመልከቱልኝ። በቅድሚያ ግን መታወቅና ከግንዛቤ መግባት ያለበት “አንዳንድ ሰዎች ስለሚገምቱ“ የምትለዋ ሀረግ ምንም አይነት ማስረጃ ለማቅረብ ባልተቻለበት በምክንያታዊነት ሸጉጦ አንድን ዜጋ መተቸት ክወንጀልም ወንጀል ነውና በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አልተገነዘቡም። ጠንቀቅ እንበል የሚል ምክር መስጠቱ አግባብነት ያለው ነው። ኃይማኖተኛ መሆን በሕግ ከመጠየቅ አያድንምና። በሁለተኛ ደረጃ ወጣት የእድሜን ንቅታና ከፍታነት የሚያመላክት እንጂ የአስተሳሰብንና የእውቀትን መጠንና ደረጃ ጨርሶ የሚገልፅ አለመሆኑን አለማወቅ የተቺዎችን ምንነት ገላጭ እንጂ በሌላ በምንም አይነት ሊተረጎም አይችልም። የእውቀትን መገኘትና ውስጣዊ ይዘቱን በሚመለከት በሌላ ጊዜ በሰፊው የምንመለስበት ይሆናልና ለጊዜው የእድሜ መጨመር ያሸብታል እንጂ አዋቂ እንደማያደርግ ብቻ ጠቅሰን ወደ ዋናው ርዕሳችን እናልፋለን።
ዋለልኝን ለመተቸት የተነሱበትንና ያቀረቧቸውን ምክንያታዊ አስተሳሰቦች ስንዳስስ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ዋለልኝ የፃፈውን በጥልቀት እንዳላነበቡትና እንዳልገባቸው ብቻ ሳይሆን ከየትም ያምጣው ራሱ ያመንጨው በወቅቱ እንደ አሎሎ እሳት የሚፋጀውን የፖለቲካ ጥያቄ በጓሮ ሳይሆን በአደባባይ ግልጥልጥ ባለ ሁናቴ ችግሩን እንመለከተውና መፍትሄ እንፈልግለት በማለት ያበጠው ይፈንዳ ብሎ ለውይይት ፅሁፉን ማቅረቡ ምንድን ነው ስህተቱ? እንዴት ነው አንድ ጤናማ አዕምሮ አለኝ የሚል የሰው ፍጡር ያውም ከኃይማኖት ክበብ ውስጥ ነን ብለው ከሚመፃደቁ በቅርበት አግኝተው የማያውቁትን፣ በጥሞና የርስ በርስ ውይይት ተደራርገው ለመተዋወቅ ምንም አይነት ሁናቴ ባላገኙበት፣ የአንድን ኢትዮጵያዊ ዜጋ የእውቀት ደረጃ አግባብ ባልሆነ መልኩ መፈታተንና መዝለፍ ስለ ፀሃፊዎቹ ጤንነት የሚያጠያይቅ ብቻ ሳይሆን አንድን ዜጋ ለማጥላላት ምን ያህል ርቀት እንደተጓዙ የሚያመላክትና ስለ ሞራል ያላቸው ግንዛቤም የተወለጋገደ እንደሆነ የሚጠቁም ነው። ከሰው ፍጡር የማይጠበቅ ነውና። የምሁራንነት ካባ ራሳቸው በራሳቸው ስላጠለቁ ዋለልኝን በዚህ ሁናቴ ለመገዳደር መሞከር በሱ ግላዊ ሰብአዊነት ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን የመንፈስና የትግል አጋሮቹ የሆኑትን የዛ ትውልድ አባላትና እኔንም ጨምሮ በሌለንበትና ባልዋልንበት ቦታ ወሽቀው ባልሰራነው ኃጢአት መዝለፍ በቸልታ የምናልፈው ጉዳይ ሊሆን ከቶ አይችልም።
ዋለልኝ „On the question of Nationalities in Ethiopia. Arts IV, HSIU Nov. 17, 1969” በሚል ርዕስ ባቀረበው መጣጥፉ ሊያስከትል የሚችለውን እንካ ሰላንቲያ ቀደም ብሎ በመገንዘቡ “The main purpose of this article is to provoke discussions on the “sacred”, yet very important issue of this country-the Question of Nationalities. The article as it was prepared for a special occasion (where detailed analysis was due time and other inconveniences impossible) suffers from generalizations and inadequate analysis. But I still feel it is not mediocre for a beginning. I expect my readers to avoid the temptation of snatching phrases out of their context and capitalizing on them. Instead every point raised here should be examined in the light of the whole analysis.” የፁሁፍን አላማና አንዳንድ ሀረጎችን ከይዘታቸው መንጭቆ በመውሰድና በነሱ ላይ ብቻ ትኩረት እንዳይደረግ ማሳሰብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ይዞታው ላይ እንዲተኮር በፅሁፉ መጀመሪያ ላይ ማስፈሩ ያለምክንያት እንዳልሆነ የሚጠቁም ነበር። ለመረዳት ቅን ፍላጎትና ክፍት ልቦና ካለ ማለት ነው። ድንጋይ ሁሌም ድንጋይ ሆኖ የሚቀረው ለካ ያለምክንያት አይደለም ወዳጆች!!
የዋለልኝ ፅሁፍ ለውይይት መነሻ እንዲሆን በማለት እጥር ምጥን ተደርጎ የተዘጋጀ እንደሆነ ራሱ ዋለልኝ ቢገልፅም ስለ ብሔር ትርጉም ሆነ ወስጣዊ ይዘት የነበረውን አስተሳሰብ “ And what else is a nation? It is not made of a people with a particular tongue, particular ways of dressing, particular history, particular social and economic organization? Then may I conclude that in Ethiopia there is the Oromo Nation, the Tigrai Nation, the Amhara Nation, the Gurage Nation, the Sidama Nation, the Wellamo [Wolayta] Nation, the Adere [Harari] Nation, and however much you may not like it the Somali Nation. “ ተብሎ በፅሁፉ ተገልፆ እያለ በሀገራችን ችግሩ መኖሩን ከነጭራሱ መካዳቸው ሳያንስ “የብሔርን ጥያቄ አመጡ ተብዬዎችና አቅራቢዎች ትክክለኛዉን ትርጉም ያኔም የገለፀም፣ የጠየቀም፣ የለም፤ አሁንም ድረስ ትርጉም አልባ ግን የአንድነት ችግር መንስኤ ሆኗል!” እያሉ በውሸት የተሞላ ግን ምኞታቸው ውነት ሆኖ በአንባቢያን ዘንድ ከግንዛቤ እንዲገባ ሲቀባዥሩና ሲዘላብዱ ይስተዋላሉ። ስለ ተማሪዎች ትግልም ሆነ በብሔር ጥያቄ ቀርበው የነበሩትን ለምሳሌ በወቅቱ በአልጄሪያ በስደት ይኖሩ በነበሩት የዋለልኝ የትግልና የመንፈስ ጓዶቹ በእንግሊዝኛ ከትበው ያቀረቡትን፣ እንዲሁም በአሜሪካና በአውሮፓ በሚገኙት የተማሪዎች ማህበራት የትግል መፅሄቶች ታጠቅና Struggle ውስጥ ታትመው የተሰራጩትን እንዲሁም ተባራሪ ወረቀቶች ለምሳሌ „Fetishism of „Ethiopian Colonialism“ A Ciritical Remarks on the National question in Ethiopia, 1988 By ZT ሌሎችንም አፈላልገው ቢያነቡና በጥሞና ቢመለከቷቸው ኖሮ ከተሳሳቱና ትርጉም አልባ ከሆኑት ድምዳሜያቸው ባልደረሱ ነበር። ለነገሩ ” የኢትዮጵያ ችግር ባልሆነበት ችግር መፍቻ ብሎ መውሰድ “ በማለት ችግሩ እንደሌለ በመቁጠር የፖለቲካ ክህደት ከፈፀመ ምንስ ይጠበቃል? ከሁሉ በላይ “ አንድን ነገር ከመደገፍም ወይም ከመቃወም በፊት ከሥረ መሰረቱ የመመርመር ባሕል ሊኖረን ይገባል” ባሉበት ምነዋ ታዲያ ይህንኑ ምክራቸውን ራሳቸው በመገልገያነት ለመጠቀም ለምን አልፈለጉም?። በርግጥም ፁሁፉ ደፋር፣ እውነቱን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ የቆረጠና በሕዝቦች መከከል ሊፈጠር የሚችለውን የትግል አንድነት አቅጣጫ ለመቀየስ የሞከረ ፁሁፍ ነበር። ይህንን ነው እንግዲህ አጠልሽተውና አጥላልተው ወደጎን ለመግፋት አሁንም ድረስ እየተጣረ ያለው።
በተመሳሳይ ሁናቴም ያረድ ኃይለመስቀል የተባሉ የአንድ የማማከርና የኮሚዩኒኬሽን ኤጀንት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናቸው የተባሉ በአራት ክፍል ስለ “ምክንያት አልባው ፅንፈኝነት” በሚል ርዕስ በ ጁን 29 ቀን 2022 ባቀረቡት መጣጥፍ “ስታሊን የጻፈውን ሳያነቡ፣ ዋለልኝ ያልጻፈውን ወይም ጻፍኩት ያላለውን ጽሑፍ ዋለልኝ ስለብሔር የጻፈው እያሉ ዛሬም ብዙ ደፋሮች ይሰማሉ፡፡ ዋለልኝ ፈረንጅ ጽፎ የሰጠውን ነው ያነበበው፡፡ የብሔር ጥያቄ ደጋፊ አልነበረም፡፡” በማለት ያንን ትውልድ ብቻ ሳይሆን ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ሆነው ተግተርትረዋል። ታዲያ ውስጥ አዋቂ ከሆኑ ለምንድን ነው የፈረንጁ ስምና ማን እንደሆነ ለመግለፅ ያልተደፈረው? ምንድንነው ደፋፍኖ ማለፍ? እነ እንግዳሸት እኚህን ደራሲ ነው እንዴ “አንዳንድ ሰዎች ስለሚገምቱ ነው” በማለት በምስክርነት ለመግለፅ ያልደፈሩት? ለነገሩ “የሚገርመው ነገር ስታሊን ‹‹የብሔር ጥያቄ›› የሚለውን ጥንብ እርኩሱን አውጥቶ የብሔር ጥያቄ እንደ ኮሌራ ወረርሽኝ ነው፣ አብዮተኞች በዓለም አቀፋዊ ወዝ አደርነት ሊያወድሙት ይገባል ብሎ በብሔርተኞች ላይ ጦር ያወጀበትን ጽሑፍ በሩሲያኛም ሆነ በጀርመንኛ፣ ወይም በእንግሊዝኛ ትርጓሜ ሳያነቡ እንደ እውነት ቆጥረው እነ አቶ መለስ፣ እነ አቶ ሌንጮና እነ ዋለልኝ በስማ በለው የሰሙትን ይዘው አበዱ፡፡ ከዚህ የስማ በለው ትርክት ውጪ የሚቀርበውን ሁሉ ፀረ ብሔረሰቦች፣ ብሔር ጠሎች፣ ትምክህተኞች፣ ፀረ ሕገ መንግሥት፣ ፀረ ሕዝብና ትምክህተኛ እያሉ ፈጅተው የአንድ ትርክት አገር ፈጠሩ፡፡” ካሉና አንብቢያለሁ በማለት የምስክርነት ቃላቸውን ካሰፈሩ በወቅቱ ለሚኖረውና የወደፊቱ ትውልድም እንዲማርበት ጠቆም አድርጎ ከማለፍ ምነዋ ታዲያ የመፅሃፉን ርዕስና አመተ ምህረት ለመግለፅ አልደፈሩም? እኔ ግን የነመለስንና ሌንጮን ለነሱ እንተውና ለያሬድ ኃይለመስቀል መግለፅ የምፈልገው በዩኒቨርሲቲ መማር ብቻ ሳይሆን የስታሊን፣ የሌኒንን፣ የማርክስ ኤንግልስ የተሰበሰቡና ምርጥ ፅሁፎች(collected and selected works) ሌሎችንም በርካታ መፅሃፍቶችንና ጥናታዊ መጣጥፎችን በማንበብና በመረዳት እንጂ ከሀገራችን ሁናቴ ጋር ሳናገናዝብ ትግል አልጀመርንም አልቀጠልንምም። ወቅቱ የግራውን ርዕዮተ አለም ማጠልሸት እየተለመደ መጥቷልና ይህም በያሬድ ኃይለመስቀል መንፀባረቁ የሚያስገርም አይሆንም። የቆምነው ለጥቂቶች ሳይሆን ለብዙሃኑ ነውና ያኔም ያነሳናቸው የዴሞክራሲ፣ የነፃነትና የመብት ጥያቄዎች፣ የእኩልነት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላም፣ የሰርቶ አደሩ ሕዝብ መብት መጠበቅ፣ የንግግርና የነፃነት መረጋገጥ፣ የህግ የበላይነት መረጋገጥ፣ የሕዝብ ሉዐላዊነት እውን መሆን፤ የመደራጀት ነፃነት፣ ነፃ የዳኝነት ሥርአት፣ የሥልጣን ክፍፍል፣ የብሄሮች እኩልነት፣ የፌዴሬሽን ስርአተ አስተዳደር፣ የሀገር አንድነት በእኩልነት፣ የመንግስትና ኃይማኖት መለያየት፣ የኃይማኖት እኩልነት፣ የፆታ እኩልነትና ሌሎችም እስካሁን ድረስ መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎቻችን ናቸውና ከወቅቱ ጋር የሚስማማ የትግል ዘዴ በመቀየስ በትግል የመገኘታችን ትርጉሙ ይህ ነው እንጂ ሌላ አይደለም፣ አልነበረምም። ይህ የማይናወፅ መታገያችን በመሆኑ በግራነት ማጠልሸት ለሚፈልጉ አይሳካላችሁም እንጂ ይመቻችሁ እንላለን። ምን ቢመጣ ምን ግን ከትግል እንደማያሸሸን ለጠላትም ለማይወዱንም ሆነ በሕይወት መኖራችንን ለማይፈልጉ ሁሉ ይህንን ግልፅ መልዕክታችንን ባለፉት ጊዜያት እንዳደረግነው በአሁኑ ወቅትም ደግመን እንገልፃለን። አራት ነጥብ።
ለመሆኑ “ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በቂ ግንዛቤ መኖር አለመኖር፣ የሥራና የሕይወት ተሞክሮ ማግኘት አለማግኘት የኢትዮጵያን ሕዝብ ማሕበራዊና ኤኮኖሚያዊ ትስስር በቅጡ መረዳት አለመረዳት “ የምስክር ወረቀት ለመስጠትም ሆነ የአዋቂነት ወይንም ደግሞ የብልህነት መመስከሪያ መረጃ ለመሸለም ሥልጣን የተጎናፀፈው ማነው? በምንስ ማጠየቂያ? የ ያ ትውልድ አባላት በወቅቱ እኮ ሰፍኖ የነበረውን የጭቆና ሥርአት መፍትሄ አፈላልጎ ለማግኘትና ለማስወገድ በምትኩም በመብት እውቅና ላይ የሚመሰረት፣ ነፃነትን በተጎናፀፈ አዲስና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመተካት ነበርና ነውናም በጊዜው በአርአያነት የሚመለከቱትና ተመክሮን ሊቀስሙበት የሚችሉበት የፖለቲካ ድርጅትም ሆነ ኃይል አልነበረም። በመሆኑም የሌሎች ሀገራትን ህዝባዊ ትግሎችን፣ ፍልስፍናዎችን ወዘተ. በማንበብ ግልባጭ ለመሆን ሳይሆን ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁናቴ ጋር እያዛመደ እራሱን በጠለቀ ሁኔታ ያነጸ ነበር ያ ትውልድ፡፡ የኢትዮጵያ ተማሪዎችም ሆኑ የ ያ ትውልድ አባላት ወገናቸውን፣ የተገፋውን ገበሬ፣ የተመዘበረውን ላብ–አደር ከግፈኛና ጨቋኝ ስርዐቶች ነፃ ለማውጣት ትግሉን ሲጀምሩ በሂደት ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ውጣ ውረዱን፣ አቀበት ቁልቁለቱን፣ ረሃብ ጥማቱን ለድል የሚሆናቸውን ስንቃቸውን ሰንቀው፣ የግዴታ ሲሆን ደግሞ ወድ ህይወታቸውን ለመሰዋት ቆርጦ የተነሱ እንጂ በድንገት ዘው ብሎ የገቡበት አልነበረም። የትግሉን ግብና አላማ፣ ስትራተጂውንና ታክቲኩንም በነጠረ ሁኔታ የጎደለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለሟማላት የትግል ጉዟቸውን የተያያዙት። የ ያ ትውልድ አባላት ሰፍኖ የነበረው ክፍተት በደንቃራነት ሳይሆን ለውስጣዊ ግፊት መሰረት እንዲሆናቸው ተጠቀሙበት፣ ይቻላልን አነገቡበት። ራሳቸው በራሳቸው ጥረው ግረው ይሆናል የሚሉትን መፍትሄ ሰፋ ባለ ጥናታዊ ምርምርና ውይይት ለማግኘት ከፍተኛ ትግል ያደረጉና ታግለውም ከፍተኛ የሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል ክንዳቸውን ተንተርሰው ዘላለማዊ የእረፍት እፎይታቸውን የተጎናፀፉ ናቸውና ስማቸውም ሆነ ገድላቸው በሀገር ወዳዱና ለሕዝብ ቀናኢ በሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ምንጊዜም እንክብካቤ የሚሰጣቸው፣ ገድላቸው ሁሌም የሚታወስ ብቻ ሳይሆን በአርአያነት የሚመለከቷቸው እንደሆኑ በኔ በኩል ፍፁም እምነቴ ነው። የነ ሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬ ሆነ የመሰሎቻቸው ጫጫታ ይህንን ሀቅ በምንም ሁናቴ አይቀይረውም። ሊቀይሩት እንዳይችሉም ማድረግ የሚቻለኝን ሁሉ ከማድረግ ወደኋላ አንልም። ቃል ኪዳናችን የኢትዮጵያዊነት መገለጫችን፣ ማህተባችን፣ ለፅናታችንም መሰረት ነውና ጫና ሲበዛብን አውልቀን የምንጥለው አይደለም።
የኩረጃ ጉዳይን ካነሱማ ሁለቱ ግለሰቦች ምንም አይነት የራሳቸውን ጥናታዊ ምርመራ አስተዋፅዖ ባላበረከቱበት ከመጀመሪያ ገፅ ክፍል አንድ ዝግመተ ለውጥና ፍጥረት አንስቶ እስከ ክፍል ሶስት ማጠቃለያ ሃሳቦች እስከሚለው ድረስ በኢትዮጵያ በባዕዳን አጀንዳ አስፈፃሚነት የተመደቡ እስከሚያስመስላቸው ድረስ በአማርኛ ቃል በቃል ተርጉመው የከቱቧቸው ኬን ሃም (Ken Ham) የተባለ የቀድሞ አውስትራሊያዊ, የኋላ አሜሪካዊ በሆነው የተመሰረተና በሱም መሪነት የሚንቀሳቀስ „Young Earth creationist“ በተሰኘ ማህበርና በሱ ዙሪያ የተሰባሰቡ ደጋፊዎቹ ይፋ የሚያደርጓቸውን አስተያየቶች መፅሃፍቶች የተወሰዱ እንደሆኑ በግልፅ የሚታይ ነው። እነሱ ያነበቡትን ሌላው የሚያነብ ስላልመሰላቸው ተንደርድረው ከተሳሳተ ጉድጓድ ውስጥ መግባታቸውን ሊረዱት አልተቻላቸውም። ለዚህም ነው በዋለልኝ ላይ የቀሰሩት ጣት የእጃቸው ሶስቱ ጣቶች ግን በነሱ ላይ የተቀሰሩ መሆናቸውን ሊታያቸው ያልተቻላቸው። እነሱ አማኝ ነን ብለው ለራሳቸው የመስካሪነት ካባ ስለለበሱ የሌላን ፅሁፍ ጥቅስ ሲገለብጡና ሲኮርጁ ከስህተት የሚፀዳው በምን ማጠየቂያ ነው? በውነቱ ለዚህ ምንም አይነት ማሳመኛም ሆነ ማረጋገጫ ሊያቀርቡልን አይቻላቸውም። ለነገሩ እምነታችን ብለው እንዲህ የሚብከነከሉለትና እንዳሻ በዋቢነት የሚጠቅሱት ሥረ መሰረቱም ሆነ ፅንሰቱ በኢትዮጵያ ነበር እንዴ? የሚል ጥያቄ ማንሳትን የግድ እንደሚል እነሱን ቢያንቃቸውም፣ ቢያበሳጫቸውም፣ ጫጫታ ማንሳታቸው የማይቀር ቢሆንም፣ ኬይሲ ተግባራቸው የሚያስገድደን መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል።
ሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬ እንዲሁም የበላይ አቀንቃኛቸው ኬን ሃም (Ken Ham) በሀገራችን ለማስተናገድ የሚሞክሩትን የኃይማኖት እይታ እስቲ ጠጋ ብለን እንመልከተው። በድረ ገጹም ሆነ በተለያዩ ግን ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን መጣጥፎቻቸውን፣ ያሳተሟቸውን መፅሃፍቶች ላገላበጠ ማንኛውም ዜጋ በግልፅ ለመረዳት እንደሚቻለው የሚያቀነቅኑት እይታ ሌላ ሳይሆን በተፈጥሮ ሳይንስ ጥናታዊ ምርምር የተደረሰበትን የአለም ስዕላዊ ገፅታ ለማጠልሸትና ለነሱ እይታ ተስማሚ መስሎ እስከሚቀርብ ድረስ በተሳሳተ መልኩ ለመተርጎም ከፍተኛ ጥረት ማድረግ የወጠኑት የመጀመሪያ ተግባር ነበር አሁንም ነው። በሩቅ አላማ ደግሞ የነሱን የመፅሃፍ ቅዱስ አተረጓጎም ከዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ጋር በእኩሌታ እንዲታይና በየትምህርት ቤቶች በተለይም በጂኦሎጂ ስነ መስክ እንዲሰጥ መታገል ሌላው የስምሪታቸው አካል ነው። ከሁሉ በላይ በተቻላቸው መጠን የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ተወግዶ የራሳቸው እይታ ብቸኛ የስርአተ ትምህርት አካል እንዲሆንላቸው መጣር የሞት ሽረት ሕልማቸው ነበር፣ አሁንም ነው። ጥረታቸው ግን በገንዘብ ኃይልና በመጠነ ሰፊ የፕሮፓጋናዳ ዘመቻ የታጀበ ስለነበር ውጤት አልባ ነው ለማለት አይቻልም። በተወሰነ ደረጃ የተሳካላቸው ሀገሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። በምሳሌነትም በአሜሪካ በተወሰኑ ክፍለ ሀገሮች፣ በፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ሥር ባለቺው ቱርክ፣ እንዲሁም በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ እንደሚታየው ማለት ነው።
እርግጥ ነው ሽፈራው ሉሉ፣ እንግዳሸት ቡናሬና የነሱ የበላያቸው የሆኑት እይታቸውን የሚመለከቱበት ሁናቴ ራሱን የቻለ የሳይንስ ዘርፍ አድርገው በመጠነ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የታጀበ ጥረት ቢያደርጉም ይህንን ሚና ግን ቢያንስ በአሜሪካ በ 1925 ዓ.ም. “የዝንጀሮ ችሎት” በሚል ሥያሜ የሚታወቀው ከፍተኛ ትኩረት በሳበ የፍርድ ቤት ችሎት ቅሌትን ተከናንበውበታል። በፍርድ ቤት ውስኔው መሰረት ስለ ፍጥረታት ታሪክ አስመልክቶ ያላቸው እይታ በተፈጥሮ ሳይንስ አረፍተ ነገሮች ተቆናጃጅቶ የቀረበ እንጂ የተፈጥሮ ሳይንስ መሰረታዊ መመሪያን ሆነ መመዘኛ የማይከተል እንደሆነ በወቅቱ በፍርድ ቤቱ ተረጋግጦ ጥያቄያቸው ውድቀትን ተላብሷል። በዚህም የተነሳ የእይታቸውን ውስጣዊ ይዘት አንዳችም ሳይቀንሱና ስይደልዙ ፈጣሪ/እግዚአብሄር የምትለውን ቃል ብቻ አውጥተው (Intelligent Design) በብልህ/ አዋቂ ኢንጂነር በሚለው ቢተካም እውነተኛነትን/ትክክለኛነትን ወይንም ደግሞ የእርግጠኛነትን ካባ በምንም አይነት ሊላበስ አልተቻለውም:: ስለሆነም ክሬያሺናዊነት በብልሁ እንጂነር ተሸፋፍኖ ቢመጣም በሚመኙት ደረጃ ተቀባይነትን አልጨመረላቸውም፤ ከኬይሲነቱም አልተላቀቀም፣ በምንም አይነት የነሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬ ጫጫታም ተዳብሎበት ሳይንሳዊነትም ሆነ የኃይማኖት ጠባይንም ሆነ ካባ ሊደርብ አልተቻለውም። ለምን ቢባል? መልሱ ከእውነት ጋር በመጋጨት፣ ከተፈጥሮ ሳይንስ ጋር በመቃረኑ ብቻ አይደለም። የሚከተሉት ዶክትሪን ሂሳዊ ምርምር እንዲደረግ ጨርሶ አይፈቅድም። የሚታሰብም አይደለም። ትቀበላለህ አትቀበልም ዋና መመሪያቸው ነው። እነሱ ብቻ ብልህና አስተዋይ፣ ሁሉ ነገር በእምነታቸው ቡራኬ የእውቀት ብርሃን የፈነጠቀላቸው፣ ሌላው ግን በድንቈርና አለም የሚኖር፣ በኃጢአት ተግባር የተጨማለቁ የሚል እምነት የሚያስተጋባ ነው። አሁንም የተለወጠ ነገር የለም።
በሌላ በኩል ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ በመሰረቱ በጥናታዊ ውይይት የሚደርስበት ውሳኔ ከመመዘኛዎቹ አንዱ የሆነውን የሚያሟላና በሙያው የተሰማሩ ከዚህም ውጭ ላሉ ፍላጎት ያላቸው ተመራማሪዎች ለውይይት/ለእርምት ክፍት ነው። ይህም ማለት ማንኛውም ግለሰብ ሆነ ቡድን ስለሚኖርባት አለም፣ እንቅስቃሴዋና ውስጣዊ ይዘቷን ለማወቅ ፅኑ ፍላጎት ስላለው በጥናታዊ ምርምር የየራሳቸውን ግንዛቤ በማዳበር የመረዳት ችሎታቸውን ያሳድጉበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ክሬያሺናዊነት የሚያቀነቅነው የተለየ አላማ ሲሆን እሱም መፅሃፍ ቅዱስን የመተርጎም እውቀት እነሱ ብቻ እንዳላቸው፣ ማናቸውም የተፈጥሮ ሁኔታዎችና ምልክቶች ለመፅሃፍ ቅዱሳቸው እይታ የሚስማማ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው፣ የማይስማማ ከሆነ ደግሞ ክፉኛ ተቃውሞ የሚገጥመው አተረጓጎም የሚቀነቀንበት ነው። በነሱ አመለካከት ስህተት የሚባል ነገር ጨርሶ በእምነታቸው መዝገበ ቃላት ውስጥ በባትሪ ተፈልጎ የሚገኝ አይሆንም። ጥያቄ ማንሳትና መጠራጠር ጨርሶ የሚታሰብም አይደለም። ሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬም በዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ላይ ያላቸው የጥላቻ ማጠንጠኛቸው ከዚሁ የሚመነጭ ነው። ለዚህም ነው ህይወት ምን ማለት እንደሆነ፣ የመኖር ትርጉምም ሆነ ውስጣዊ ይዘቱን ለመገንዘብ የሁሉም ነገር ፈጣሪ እግዚአብሄር ነው ተብሎ የውይይት መሰረት የሚያስቀምጥ ወይንም ደግሞ የፈጣሪ ተግባር በምርምር የሚታወቅ አይሆንም በማለት ለውይይት በምክንያታዊነት የሚያቀርብ ምንጊዜም ቢሆን ከተፈጥሮ ሳይንስ ጋር የሚጋጭ እንደሆነ ልዩ እውቀት የሚያስፈልገው አይደለም ተብሎ በፅናት የሚገለፀው።
ለዚህም ነው “ፍጥረት በዝግመተ ለውጥ አልመጣም ሊመጣም አይችልም” በማለት ያቀረቡትን አስተያየት ስለ ቀለማት ከእውር ጋር አይወያዩም ወይንም ደግሞ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነሳም ብለን እንለፈውና “የታሪክ የመፅሃፍ ቅዱስ፣ የአርኪዎሎጂና፣ የስነ ሕዝብ መረጃዎች ግን የሰው ልጅ በዝግመተ ለውጥ፣ በአጋጣሚዎች ጋጋታ በአፍሪካ እንደተገኘና ከአፍሪካ ለመውጣቱ አያረጋግጡም። በመፅሃፍ ቅዱስ መሰረት የተደረጉት የታሪክ የአርኪዎሎጂና የስነ ሕዝብ ጥናቶች የሰው ልጅ ሥልጣኔ የቅርብ ጊዜ መሆኑን ነው የሚያረጋግጡት” በማለት በርግጠኝነት ያልተጣራ ድምዳሜ በዋቢነት ማስቀመጥ ከታሪክ የተጣላና ነጭ አምላኪነታቸውን የሚያረጋግጥ ነው የሚል ትችት እየቀረበባቸው የሚገኘው ያለምክንያት አይደለም።
“በአብዛኛው የዴሞክራሲ ጠበቃ ነን በሚሉት በአውሮፓና በአሜሪካ አገሮች ውስጥ ያለው ወጣቱ ትውልድ እግዚአብሔር አልባ ሆኖ ራሱን ከዝንጀሮ መሰል እንስሳ እንደመጣ አምኖ ተቀብሏል። ከዚህም የተነሳ የእምነት ተቋማት የእሮጊትና የሽማግሌዎች መሰብሰቢያ ሆነዋል።” ማለትም ሆነ ዳርዊንን ከእንስሳ ጋር የሚያመሳስል ፎቶ መለጠፍ ግን የውሃ ጠብታ ታህል እንኳን ተቀባይነቱንና የተከበረ መሆኑን አልቀነሰበትም። እንዲያውም በተቃራኒው በተለያዩ አመታት ለሱ ክብርና እውቅና ለመስጠት ሲባል በ ፒተር ብራንድሁበር የዳርዊን 200ኛ የልደት አመቱና እንዲሁም „On the origin of Species” የታተመበት 150ኛ አመት በማክበር በአለም አቀፍ ደረጃ የተዘጋጁ ፎቶዎችን የመታሰቢያ ቴምብሮችና ሌሎችንም በመረጃ አጠናቅረው ያቀረቡትን የተለያዩ በርካታ ፎቶዎችን መመልከቱ ብቻ በቂ ነው።
ኬን ሃምም በተደጋጋሚ እንደሚገልፀው „When it comes to biblical authority, the question of the age of the earth is just as vital as the question of whether evolution is true or not. The chronologies in the Bible and the length of the days of the Creation Week (they were 24 hours each) show that the earth is young. Why try to reinterpret the very clear teaching of Scripture to accommodate the fallible ideas of man that say the earth is old? Such reinterpretations undermine the authority of the Word of God.“
ለዚህም ነው ከመጀመሪያውኑ “የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ የሚያስረዳን ፍጥረት ሁሉ በብዙ ሚሊዮን አመታት ራሱን በራሱ ቀስ በቀስ አዘጋጀ በማለት ነው። ታዲያ ይህንን በእምነት ከመቀበል በስተቀር ሌላ መንገድ የለም። ለዚህ ነው የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ፈጣሪ የሌለበት ኃይማኖት ነው የሚባለው።” ይህን የመሰለ አቀራረብ የሚያመላክተው ስለ ኃይማኖት ትርጉምና ውስጣዊ ይዘት የጠለቀ እውቀት አለመኖርን የሚገልፅ ብቻ ሳይሆን የፅንሰ ሃሳቡን ሳይንሳዊነትን ለመገዳደርና መጠነ ሰፊ የጥላቻ ዘመቻ ለማስፋፋት ጥረት ማድረጊያ ሆነው የሚገኙት። አልተሳካላቸውም እንጂ። ቀጠል አድርገውም “የዝግመተ ለውጥ እምነት ግን ሁሉም ነገር የሌሉት ባዶ እምነት ብቻ ነው። ራሱን መግለጥ የማይችል እግዚአብሄርን የካዱ ሰዎች /የዲያቢሎስ ሽንገላ ክምችት ነው።” ሲሉም ደጋግሞ መዋሸት ጠብታ እውነት ያስገኝልናል የሚል ምኞት በማስተናገድ የዝግመታዊ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ሳይንስ መሆኑን ክደው ጥግ የነካ ጥላቻቸውን በፅንሰ ሃሳቡ ላይ የሚያዝረከርኩት ያለ ምክንያት አይደለም። የአለቆቻቸውን አጀንዳ ለማስፈፀም ከመወራጨት ሌላ በገሃድ ለመታዘብ እንደሚቻለው ምንም ትርፍ አያመጣላቸውም። ኬን ሃምም እኮ የሚለው እንዲሁ ነው። እንጠቅሰው።
“Evolution has no scientific basis at all, it is a belief system from the past” “All the fossils that we find, all the living animals, all plants, our planet, the universe – everything exists in the present.” And no one was there when life began.”
በግርድፉ ሲተረጎም “ዝግመተ ለውጥ ምንም አይነት ሳይንሳዊ መሰረት የለውም። ስላለፈ ሁናቴ የሚገልፅ የእምነት ስርአት እንጂ። የምናያቸው እንስሳቶች፣ እፀዋቶች፣ መሬታችን፣ አፅናፈ አለም ማናቸውም በአሁኑ ወቅት የሚኖሩ ናቸው። ሕይወት ሲፈጠር ማናችንም በዚያን ወቅት አልነበርንም።” እንደ ማለት ነው። ሌላ ጥቅስ እንጨምር።
“The theory of evolution is the root of many evils in the world.” የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ በአለም ለተከሰቱት ኃጢአቶች ምንጭ ነው።
„We aren’t going to convince the majority, but we need to do business until [Jesus] comes.“ ይህም ሲተረጎም “ብዙሃኑን እንዲረዱን ለማድረግ አንሰራም። ነገር ግን ኢየሱስ እስከሚመጣ ድረስ ተግባራችንን እንተገብራለን” “
„When it comes to biblical authority, the question of the age of the earth is just as vital as the question of whether evolution is true or not. The chronologies in the Bible and the length of the days of the Creation Week (they were 24 hours each) show that the earth is young. Why try to reinterpret the very clear teaching of Scripture to accommodate the fallible ideas of man that say the earth is old? Such reinterpretations undermine the authority of the Word of God.“
እነዚህን የመሰለ አስተያየቶች ገዝተው ነው እንግዲህ ሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬ መሰሪ ተንኮል የተሞላበትና በተፈጥሮ ሳይንስ ምርምር ውድቅ የተደረገ ሃሳብ ተሸክመው ነው ኬይሲ ተግባራቸውን ከፖለቲካ ጋር በማጣመርና ከኃይማኖት ጉያ ተሸጉጠው ሕዝባችንን ሊበክሉ የሚጥሩት። የነ ሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬ ትልቁ በሽታቸው የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ሳይንሳዊ መሆን አለመሆን ወይንም ደግሞ የተሳሳተ እሳቤ መያዝ አለመያዙ ሳይሆን በግብረገብነት የበላይነት ለመያዝ ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት ቦታ ስለሚያሳጣቸው እንደሆነ በራሳቸው አንደበት በተደጋጋሚ ድፍረት በተሞላበት መልኩ ገልፀውልናል። የመንግሥትና ኃይማኖት መለያየት፣ የኃይማኖቶች በእኩልነት መታየት፣ ስለ ሰው ፍጡር ሥዕላዊ ገፅታ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ በሕብረተሰቡ ውስጥ ሰርፆ መግባትና ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘት፣ ማንኛውም ህብረተሰብ መድበላዊነት ጠባይ ያለው ስለመሆኑ፤ ሌሎችም በስጋት ላይ ስጋትና ጭንቀት እየጨመሩባቸው መሆኑ ሌላው በምክንያትነት የሚጠቀሱና ጤናና እንቅልፍ የነሳቸው መሆኑ ነው።
„Secularism, with its moral relativism, is in direct opposition to Christianity and its absolute morality. The battle is between these two worldviews—one that stands on God’s Word and one that accepts man’s opinions.“
„What President Obama is talking about—this idea that all faiths are equal, especially Islam and Christianity, and that all people serve God in some way—is a dangerous misconception. It is increasingly becoming common in our pluralistic and inclusive culture. But nothing could be farther from the truth. A quick study of God’s Word and key Christian doctrines makes it clear that Islam and Christianity are utterly incompatible.“
“The author sees the “reason of the problem” in the consequences that have to be drawn from the two worldviews. “The theory of evolution entitles people to make their own rules.” In doing so, however, man commits the same sin as Adam: rebellion against God and his commandments. If there is no creator, man is not a creature either, but makes his own rules. “The public has been truly misled into thinking that, on the one hand, the theory of evolution is science alone, while belief in God is the sole domain of religion.”
“Building on this godless worldview, Ham explains in the book, man lived without a foundation and without a moral compass. If you don’t have Jesus as the foundation of your life, your life will collapse at some point, while a life based on faith not only makes sense, but will endure. Instead of lawlessness, homosexuality, pornography, and abortion through evolution, belief in creation gives you laws, marriage, standards, and meaning in life. ሲያጠቃልልም Likewise, National Socialism and predatory capitalism can be traced back to a belief in the theory of evolution. The two different ways of looking at it also give death completely opposite meanings: “Adherents to the theory of evolution claim that struggle and death led to human existence,” ካለ በኋላ “The Bible says that man’s rebellion brought death.” Even a life after death, the “eternal life” that Jesus brought, makes no sense from an evolutionary point of view. በማለት ሃሳቡን ያጠቃልላል።
ከዚህም ሌላ ሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬ በኃይማኖት ጉያ ተሸጉጠው የነሱን የአስተሳሰብ ሕግ ተግባራዊ የማያደርግ “በምድራችን የተረገመና ከፍተኛ የማህበረሰብ ቀውስ ከመፍጠሩም በላይ ሰው ለዘለአለሙ ከእግዚአብሄር ተለይቶ የዘለአለም ሞት እጩ ይሆናል” በማለት የሽብር ፍርሃትና ሰቀቀን በሰው ሕሊና ውስጥ በማሰራጨት የራሳቸው ተከታይ ለማድረግ ያላቸውን ኬይሲ አላማ ለማሳካት መሆኑ ምንም ጥርጥር የለም። በዚህ ብቻ አያቆሙም ። „የዝግመተ ለውጥ አስተሳሰብ/ፅንሰ ሃሳብ የክፉው የዲያቢሎስ ሃሳብ መሆኑን ተገንዝበን፣ ሶዶማዊነትን በዚህ ሃሳብ ላይ ተመስርቶ እየተስፋፋ በመሆኑ ልንለየውና ልናወግዘው ይገባል” በማለት የመብት ጥሰት እርምጃ ለመውሰድ ረግረጉን ያመቻቻሉ። መወገድ ከሚኖርበት አገዛዝ ከበድ ያል ቅጣት የሚያስከትል የሕግ አንቀጽ በአገዛዙ መተዳደሪያ ሕግ ውስጥ እንዲካተት እየተማፀኑ የሚገኙት። ከነሱ ወይንም ደግሞ ከሚያስተምሩት የተለየ የግብረስጋ ግንኙነት ዝንባሌያዊ ስሜት ባላቸው ላይ የዘለፋ መጠሪያቸው (ሶዶማዊያን) ላይ እየነዟቸው ያሉት አስፀያፊና መጠነ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። ዋና ዋና አቀንቃኞቻቸውም ይህንኑ እይታ የሚያንፀባርቁ ናቸውና እስቲ በዋና ወኪልነት ኬን ሃም እያንፀባረቃቸው ያሉትን እንመልከታቸው።
„Bible-believing Christians who oppose same-sex marriage are not discriminating against homosexual people—they are taking a stand on the authority of God’s Word. They are applying God’s holy standards—as recorded in the Bible—to correctly identify sin as sin. Homosexual behavior is sin. All sin is evil. People need to understand what sin is, and not justify it and dress it up as something good and acceptable.“ አንድ ልጨምር_
„1 Corinthians 6:9–10 lists homosexual behavior as a sin that will bring judgment by God on the unrighteous. The beautiful truth of Christ’s gospel is found in verse 11, “And such were some of you. But you were washed, but you were sanctified, but you were justified in the name of the Lord Jesus and by the Spirit of our God.” Yes we should be welcoming of practicing homosexuals with the love of Christ, but with a clear presentation of His death for their sinful perversion of God-ordained sexuality between one man and one woman in Genesis 2:24. Anything less misses the meaning of what the love of God really is, not an inclusive message but a saving gospel (John 3:16). The church shouldn’t encourage people who struggle with same-sex attraction to engage in sinful sexual practices. No, church leaders like those at Highland Baptist should be finding ways to share the gospel with unbelievers and encourage Christians to live in a way that’s pleasing to God.“
„You see, when we’re talking about origins, we’re talking about the past, we’re talking about our origins. We weren’t there, you can’t observe that, whether it’s molecules-to-man evolution or the creation account. When you’re talking about the past, we like to call that origins or historical science: knowledge concerning the past. Here at the Creation Museum, we make no apology about the fact that our origins or historical science is actually based upon the biblical account of origins. When you research science text books being used in public schools, what we found is this: by and large the origins or historical science is based on man’s ideas about the past, for instance the ideas of Darwin.“
“What evolution does is teach people that there is no God and that we’re a result of natural processes – then ultimately who does decide right and wrong? It is all subjective, it all depends on your opinion, it all depends on who can control the culture and who determines whose rules are to be obeyed.”
እነ እንግዳሸት ቡናሬም በተመሳሳይ ሁናቴ “ሰው በፈጣሪው ተጠያቂነት እንዳለበት ካላመነ፤ ፈጣሪ የለም የመጣሁት በዝግመተ ለውጥ ነው ብሎ ከተቀበለ ማንኛውንም ነገር ከመፈጸም የሚያቆመው ነገር የለም፡፡ ለዚህ ነው በአውሮፓና በአሜሪካ የዝግመተ ለውጥ እምነት ትውሉዱን በማጥለቅለቁ ሰዎች ከፈጣሪያቸው ተለይተው ሰዶማዊነት በስፋት በመስፋፋቱ፤ ሰዶማዊነትን የሚደግፍ ህግ እስከማውጣት የደረሱት፡፡” በማለት ሲገልፁ በርግጥም ይህ ከሀቅ የተጣላና የሚመለከታቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ጊዜያት ያቀረቧቸውን የእምነት ተቋማት ውስጥ የተሰሩ እጅግ አስፀያፊ ተግባራትና ይህንንም ሸፋፍኖ እንዳይታወቅ ያደረጉት የባለሥልጣናቱ ጥረት እንደሆኑ ለነሽፈራው አልተገለፀላቸውም ወይንም ደግሞ ለማወቅ ፍላጎቱ የላቸውም። ይህ በራሱ ብቻ የተሳሳቱ መረጃዎች ማስራጨትና ብሎም ከወንጀለኛ ድርጊቶች ጋር መተባበር እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። ወይንስ ባለስልጣናቱ ሲወቀሱበት የነበርውና በሕግ እንዲጠየቁ በተለያዩ ግለቶች እየተደረጉ ያሉ የአማኞችን እንቅስቃሴ ለማወቅ ባለመፈልግ ከነሱ የወንጀል ድርጊት ጋር ተባባሪ ለመሆን ሸር ጉድ ማለት ነው? ምንስ ፋይዳ ለማግኘት? መልሱን ለነሱ መተዉ የሚበጅ ነው።
ኬን ሃምም በበኩሉ የሚከተለውን የቆመበትን እምነት ተመርኩዞ ሲገልፅ፣–
“What did the President of the United States say, in his autobiography published before the election? Whatever we once were, we’re no longer a Christian nation! We are also a Jewish nation, a Muslim nation, a Buddhist nation, a Hindu nation, a nation of non-believers. He’s not just talking about a nation where you have freedom of religion. He really means we are no longer a nation that build our thinking on the bible. For instance he declared that June 2009 was gay lesbian transgender month and called upon Americans to support homosexual marriages and so on.”
God’s people need to unashamedly and uncompromisingly stand on the Bible. We need to unashamedly proclaim a Christian worldview and the gospel, all the while giving answers for the hope we have.”
“We need to attack the false foundation of autonomous human reasoning that leads to evolution and millions of years, and proclaim that God’s revealed Word is authoritative and its history of the world is foundational to Christian morality and the gospel of Jesus Christ.”
እነዚህ ስብስቦች ያልተገነዘቡት አንድ ቁም ነገር መብታቸውን ለማፈን ስለሚያቀነቅኑባቸው ዜጎች ነፃነታቸውን ለመጎናፀፍ የቻሉት በፆም፣ በፀሎት ሳይሆን ለበርካታ አመታት ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግልና በከፈሉት ከፍተኛ መስዋዕትነት መሆኑን ነው። ታዲያ ዛሬ ከዚህ ሁሉ በኋላና የተጎናፀፉትን የነፃነት ፍሬ እያጣጣሙ ባሉበት፣ ወደነበሩበት የመብት እጦት ዘመን ሊመልሷቸው የሚፈልጉትን ባላንጣዎቻቸውን፣ የጥላቻ አቀንቃኞችንና መብት አፋኝ ኃይሎችን በቸልታ ሊመለከቷቸው የማይፈልጉ መሆናቸውን ለመገንዘብ አለመቻላቸው ወደ ተሳሳተ ጎዳና እንዲጓዙ አድርጓቸዋልና ቢችሉ የነሱኑ ቃል ልበደርና በንስሃ አባታቸው ፊት ተጸጽተው ከስህተትና ከኃጢያታቸው ቢፈወሱ ጠቃሚ ነው። ያደርጉታል የሚል ተስፋ ባይኖረንም እድሜ ከሰጠን የምናየው አንድ ኃቅ ቢኖር በኢትዮጵያም ሆነ በሌላ የአፍሪካ ሀገራት ምንም ቢሆን ምንም መብታቸው በሁለመናና ጠንካራ ትግል የሚከበርና የገዢዎቻቸው ኬይሲ አላማና ተግባራቸው እንደማይሳካላቸው በርግጠኝነት መናገር የሚቻል መሆኑን ነው። በዚህ በኩል የሰላም ወዳድ ኃይሎች ትብብርም እንደማይለያቸውና ከነሱ ጎን የሚቆሙ መሆናቸውን በርግጠኝነት መናገር የሚቻል ነውና።
ሌላው ደግሞ የእምነታቸውን መፅሀፍ ቃል በቃል ከመተርጎም የሚነሳው ስለ (የስጋ ሩካቤ /ግብረ ሥጋ ግንኙነት) የተዛባ አመለካከትን ማቀንቀን፣ ባጠቃላይ በሽታን ሆነ ጤንነት አስመልክቶ የሚኖር ግንዛቤን በየጊዜው በሚገኙ የሳይንስ እውቀት ጋር አለማዛመድ፣ ከተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ፅንሰሃሳብ ውስጣዊ ይዘትና ምንነት ጋር አገናኝቶ አለመመልከትና የሚያስከትሉትን አሉታዊ ገፅታዎችን አለመረዳት፤ ሁለመና የሰውነትና የአዕምሮ ጤንነት እንዲሁም በንፅህና የታጀበ የተሟላ ኑሮ አለመኖር በግብረሥጋ ግንኙነት ስለሚያስከትሉት በሽታዎችን አለማጤን፣ መብትን ባለማክበር የሚያስከትለው ጭንቀት፣ ስጋትም ሆን የአዕምሮ እውከት ተገቢ ትኩረት ባለመስጠትም ሆነ ባለመገንዘብ የታጀበው የሰው ልጅ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ጠለቅ አድርጎ ባለማጤን የሚሰጥ የተዛባ አመለካከት የሚያስከትለው ችግር ነው።
ገና ሲጀምሩ አግባብነት የሌለውና በጥላቻ ያልተበከለ ምንም አይነት የስታቲስቲክ መረጃ ሳያቀርቡ የነሱን እይታ ከፍታ ለማስገኘት ሲሉ ብቻ “የዝግመተ ለውጥ አስተሳሰብ ለሶዶማዊነት መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል” በማለት ያው የተለመደ የጥላቻ ናዳቸውን ያወርዳሉ። ይህንን ለጊዜው ወደጎን እንግፋውና ላቀረቡት አስተያየት ግን ዋቢ ሊሆናቸው የሚችል የት ሀገር? መቼ? ጥናታዊ ትንታኔ ተደርጎ ከዚህ ድምዳሜ ለመድረስ እንደቻሉ መግለጽ ተገቢ ነበር፣ ግና ምንም የገለፁት የለም። ቢኖራቸው ኖሮ ለመግለፅ የሚያቅማሙ እንደማይሆኑ መገመት ይቻላል። ለማንኛውም ሶዶማዊነት በዝግመተ ለውጥ ሳቢያ እንደዚህ ማራኪና ተቀባይነት ካገኘ ለምንድን ነው ቢያንስ ከ 90 በመቶ በላይ የሚሆነው ዜጋ በማንኛውም ሀገር በወንድና በሴት ግብረስጋዊ ግንኙነት ብቻ ተወስኖ የቀረው? በበኩሌ ያየሁት በ 2001፡ 2016ና በ2021 ዓ.ም. የሕዝብ አስተያየት እይታ የምርምር ተቋማትና የተወሰኑ ሌሎችም ለናሙና ባደረጉት ቃለ መጠይቆች የተገኘው ውጤት መረጃ ይህንኑ አሃዝ የሚያመላክት ነው። የወሊድ እንከን ያለባቸውን ዜጎች አስመልክቶ ምስጋና ለተፈጥሮ ሳይንስ ይድረሰውና የእውቀት ደርጃ ማደግና የቴክኖሎጂ መዳበር ለዚህ ችግር መፍትሄ አስገኝቷልና ለዘር መራባት የግዴታ የግብረስጋ ግንኙነትን በብቸኛነት ማቅረቡ ትክክል ሊሆን አይችልምና እነ እንግዳሸት ቡናሬ ለሚያቀርቡት የተቃውሞ እሳቤ በመረጃ ማስደገፍ ለሁሉም ጠቃሚ በሆነ ነበር። ያለበለዚያ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ከመሆን አያልፍም።
ሌላው የመከራከሪያ ነጥባቸው በኢትዮጵያም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የወሊድ ችግር እንደሌለ ግልፅ ሆኖ ሳለ እነዚህ ቁጥራቸው በማንኛውም ስሌት ቢመዘን “ትውልድ ከምድር እንዲጠፋ መንገድ” የሚያመቻቹበት አቅሙም፣ ጉልበቱም ፍላጎቱም፣ የሚገኙበት ተጨባጭ ሁናቴም በዚህ ለተባለው ፍራቻ አስተዋፅዖ ያበረክታሉ ብሎ ማሰብ በውነትም የፍራቻ ሰቀቀን የለቀቀባቸው ለመሆናቸው ማመላከቻ ነው። በመሆኑም “የሰው ልጅ በምድር ላይ እንዳይራባ ያደርጋል” ብሎ መከራከሪያ ማቅረብ ሃቅን በአፍጢሙ መድፋት ካልሆነ በስተቀር በሌላ በምንም ሊተረጎም አይችልም።
ለጥቆም “የሰው ልጅ በተለያዩ በሽታዎች እንዲሰቃይ ምክንያት ይሆናል። ለምሳሌ በምድራችን ፈውስ የሌላቸው በሽታዎች እየተከሰቱ ያሉት አንደኛው ምክንያት እግዚአብሄር ለመራባት ካስቀመጠው ሕግ ውጪ በሚደረጉ ግንኙነቶች ምክንያት ነው” በሚል ጠቅሰው አስፋፍተው ሲያቀርቡም “ሰዶማዊነት ለተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጥ መንገድ መሆኑ በተለያዬ ጊዜ የተጠኑ ጥናቶች ለማረጋገጥ ችለዋል61፡፡ እነዚህም በሽታዎች በዋናነት በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ፤ አካለዊ ጉዳትን፤ የአእምሮ ችግርና፤ የዕድሜ ማጠር ናቸው62፡፡ ሰዶማዊያን የሁሉንም ዓይነት በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታዎችን (ኤድስ፤ ቂጥኝ፤ ጨብጥ፤ ወዘተ) እንዲሁም በግብረ ስጋ ግንኙነት የማይታወቁ በሽታዎችንና ካንሰርን ጨምሮ ከአሥራ አምስት ዐይነት በላይ በሽታዎች ከጤናማው ሰው ይልቅ እንደሚያስተላለፉና እንደሚጠቁ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰዶማዊያን በተለያዩ የአእምሮ በሽታዎች በተለይ በድብርትና፣ ራስን በመግደል ይተወቃሉ፡፡ የሰዶማዊያን ዕድሜ ከጤናማው ሰው እስከ 20 ዓመት እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡” በማለት ላቀረቡት አስተያየት፣–
-
በትንሹም ቢሆን የተሟላ ንፅህናን ስለተላበሰ ኑሮ ጥቅምና ጉዳት ከሕክምና ሳይንስ የጤና መፅሄቶች አገላብጠው እንዲያነቡ፣
-
የእምነት ተቋማት የሰጡትን መግለጫዎች እንዲመለከቱ፣
-
ጊዜና ገቱ ካላቸው የአለም አቀፍ የጤና ድርጅት ርዕሱን አስመልክቶ ከ 1984 1993 ዓ.ም. ያወጣቸውን ይፋዊ መግለጫዎች ቢያገላብጡ ጠቃሚ ትምህርት ይቀስሙበታልና ይህንኑ አበክሬ ከመምከር በሰተቀር አምብዛም የምለው የለኝም። ምክንያቱም በሰብአዊ ሳይንስ (Human Science) ላይ ለበርካታ አመታት በተደረጉ ጥናቶች የተገኘ ውጤት መሰረት አለም አቀፍ የጤና ተቋም ሶዶማዊነትን በበሽታ ለመቁጠር ምንም አይነት አሳማኝ መረጃ ባለመገኘቱ በበሽታ ከተመደቡት ዝርዝሮች ውስጥ መሰረዙ ተገልጿል።
ለማንኛውም የተለያዩ ገፅታዎች ያሉትን የስጋ ሩካቤ የግብረስጋ ግንኙነት (Sex) አጠር ባለ መልኩ ማብራራት ጥራት ላለው አስተሳሰብ መኖር ጠቃሚ ነውና እስቲ አብረን እንመልከተው።
በሁለመናው የሰው ልጅ የሕይወት/የኑሮ ሁናቴ ላይ ጫና አሳራፊ ናቸው ከሚባሉት የተለያዩ ርዕሶች ውስጥ የግብረስጋ ግንኙነትን የሚስተካከል የለም ቢባል ከእውነቱ መራቅ አይሆንም። ግብረስጋዊ ግንኙነት ከፍትወተ ስጋ ግንኙነት በላይ ትርጉም ያለው ነው።
ግብረ ስጋዊ ግንኙነት ውስጣዊ ይዘቱ የተለያዩ ስሜቶችን ተግባራዊ ከማድረግ በላይ ትርጉም ያለው ነው። ርዕሱ በርካታ ገፅታዎች ያሉት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ አንስቶ ያለ ጋብቻ ከአንድ ሴት ጋር በፍቅር ተጋምዶ አብሮ በመኖር የሚያገኙት ተመክሮን ሁሉ ያጠቃልላል። ይህ ተግባር ማንኛውንም የሰው ፍጡር እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ድረስ ከሰውነቱ ጋር ተቆራኝቶ ያለ ሲሆን የሰው ልጅ ለሚፈጥረው የርስ በርስ ግንኝኑነት ከፍተኛ እሴት የሚሰጠው ነው። ላንዳንዱ ፍቅርና ፍትወተ ሥጋ ግንኙነት ተጣምረው የሚገኙ ሲሆኑ ለሌላው ደግሞ አለያይቶ የሚያያቸው ናቸው። ላንዳንዱ ሴተኛ አዳሪ አካባቢን ጉብኝት አድርጎ ዝሙት መፈፀም ፈፅሞ የማይታሰብ ሲሆን ለሌላው ደግሞ እምብዛም ግድ የማይለው ነው።
አብዛኛው የፍትወተ ስጋ ግንኙነትን አስመልክቶ ያሉት እሳቤዎች በዋናነት ግለሰብን የሚመለከቱ ቢሆንም ገደብ ያለው ነው። ማንም ሰው ለፍትወተ ሥጋ ግኝኙነት ተግባር ያለ ፍላጎቱና ስሜቱ ተካፋይ እንዲሆን ወይንም ደግሞ አስገድዶ ተካፋይ ማድረግ ወንጀል በመሆኑ በሕግ ሊከለከል የሚገባው ነው። በተለይም ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ወይንም ደግሞ ማንኛውም ወጣት ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሙሉ ኃላፊነት ለመውሰድ የሚያስገኘው የእድሜ ገደብ በታች እስከሆነ ድረስ ከህጋዊ አንስቶ ማህበረሰባዊ ጥበቃ ማድረግ የግድ እንደሆነ ከፍተኛ አፅንዖት በተሞላበት ሁናቴ በተደጋጋሚ ሳይታክቱ እየተገለፀ የሚገኘው አለምክንያት እንዳልሆነ በመረዳት ነው። ለዚህም ነው ማንኛውም አይነት የወሲብ ጥቃት (ድርብ ሰረዝ ይጨመርበት)የሚወገዝ ብቻ ሳይሆን ይዘቱ በግልፅ ተደንግጎ በህግ ሊወገድ የሚገባ ተግባር ነው። የሰለባዎቹ ምንነት የሚጨንቀን ከሆነ በዚህ በኩል ምንም አይነት ብዥታ ሊኖር አይገባም። በተለይም በንፁሃን ህፃናት ለይ የሚፈፀም የወሲብ ጥቃት በጣም አሰቃቂ ነውና። አንዳንድ ለናሙና የወጡ መረጃዎች አንደሚጠቁሙት ለምሳሌ በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ከሚደርሱት የወሲብ ጥቃቶች ውስጥ ሰላሳ ስምንት ነጥብ አምስት በመቶ (38.5 %) ህፃናት ላይ እንደሆነ ነው። ከነዚህም ውስጥ ስድሳ ስምነት በመቶ (68 %) ጥቃቶች የሚደርሱት ህፃናቱ በሚያውቋቸው ሰዎች ሲሆን ሃያ ዘጠኝ በመቶ (29%) ደግሞ በህፃናቱ ዘመዶች ነው። The African Child Policy Forum, 2006, ባወጣው ጥናታዊ ዘገባ በኢትዮጵያ በወጣት ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት 39.1 በመቶ በወንዶች የሚደረግ ሲሆን 45.3 በመቶ የሚሆነው በእናቶች አማካኝነት ነው።
ዩኒሴፍ የተባለው ተቋም ባደረገው ተደጋጋሚ ጥናት የሚያመላክተውም በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ አንድ ሚሊያርድ የሚሆን ሕፃናትና ወጣቶች እድሜያቸው ከሁለት እስከ አስራ ሰባት አመት በሚሆኑት ላይ የወሲብ፣ የአካል፣ የመንፈስና የአዕምሮ ጥቃት ሰለባ እንደሚሆኑ ነው። በግምት አንድ ነጥብ (1.1) ሚሊያርድ የሚሆኑ ወላጆችና የጥበቃ እንክብካቤ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች በሕፃናት ላይ አካላዊ ቅጣት መፈፀም ስነስርአት ለማስያዝ በአዎንታዊነት እንደሚቀበሉት ታውቋል። ስለሆነም ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ይቻል ዘንዳ፣–
1. ከየትኛውም አቅጣጫ የሚከሰቱ ጾታዊ ጥቃትን ያለመታገስ አረዳድና ግንዛቤ በህብረተሰቡ ውስጥ ሰርፆ እንዲገባ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር፣
2. ከኅብረተሰቡ አባላት በዋናነት የሚጠበቀው ተግባር ደግሞ፣
ሀ. ጾታዊ ጥቃትን መጸየፍ፣
ለ. ጥቃት የሚያደርሱ አካላትን ማጋለጥና ለፍትሕ ማቅረብ፣
ሐ. የጥቃቱ መንስዔዎችን ሆነ የመከላከል እርምጃዎችን በጥናታዊ ትንተና አስቀድሞ በግልፅ መለየት፣
መ. ይህንን ተገባራዊ ለማድረግ የሚረዱ ዕቅዶችንና የማስፈጸሚያ ሥልቶችን አውጥቶ ከሁሉም በላይ ሳይታክቱ በመመራት በዕውቀት፣ በተቀናጀ ደረጃና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰራ እነ እንግዳሸትና መሰሎቹ ከጥላቻ ስምሪት ተቆጥበው በዚህ ጎዳና ቢሰማሩና የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ቢያበረክቱ ለጥቃቱ ሰለባዎች ከፍተኛ ባለውለታ ሊሆኑ እንደሚችሉ ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ።
በተለይም የመኖር ህልውናቸው አደጋ ላይ የወደቁ ሴቶችን፣ አረጋውያንን፣ አካለ ጉዳተኞችንና ሕፃናትን እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በበጎ ፈቃድ መደገፍና መንከባከብ የአዕምሮ ዕርካታና የህሊና እረፍት የሚሰጥ ምግባር መሆኑን መገንዘቡ ወሳኝ ነው:: ማንኛውም ሰው (ፆታ፣ ዘር፣ እድሜ፣ እምነት፣ በማንኛውም የመንግስት ተቋማትም ሆነ በተለያዩ ሕዝባዊ ድርጅቶች ያሉ ሰራተኛ፣ ገበሬ፣ ላብ አደር፣ አርብቶ አደር፣ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ይሁን ተራ አባል፣ ክፉ ወይንም ደግ፣ ተማሪ ሆነ አስተማሪ፣ ባለ ዲግሪ ይሁን አይሁን፣ ተራ ሰው ይሁን ባልሥልጣን ወዘተ ሳይለይ) የወሲብ አጥቂ ወይም ተጠቂ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው። በተለያዩ ሀገራት የተገኙት ተመክሮዎች ይህንኑ የሚያረጋግጡ ናቸው። ወንጀል በምንም አይነት በባህል ተስታኮም ሆነ ተቆነጃጅቶ ቢቀርብ ወንጀል መሆኑን አይሰርዝለትም። ከግንዛቤ እጥረት የተነሳም የሚደረግ ወንጀል ምንጊዜም ወንጀል ነውና። በመሆኑም አንድን ሁናቴ በጥልቀት ሳይመረምሩ እንዲያው በደፈናው ምንም አይነት ማረጋገጫ በሌለበት ሁሉንም በአንድ ሙቀጫ መውቀጥ ትክክል አይሆንም። ለዚህም ነው በመስኩ በርካታ ጥናታዊ ምርምር ባደረጉ ባለሙያዎች ግብረ–ሶዶሟዊነት እና የሩካቤ የግብረስጋ ግንኙነት ተመርኩዞ ለአቅመ አዳምና ሄዋነት ባልደረሱ ወጣቶች ላይ ያለ ፍላጎትና ስምምነት ኃይል በተመረኮዘ ሁናቴ ከሚደረግ የወንጀል ተግባር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው የሚገለፀው።
የመብት መከበር ጉዳይ በፆምና በፀሎት ወይንም ደግሞ በወቅቱ ከሥልጣን ማማ ላይ የሚገኘውን ቡድን በመለመን የሚገኝ ባለመሆኑ አገዛዙን ይህንን ያንን ሕግ እያሉ በሕገ አገዛዙ እንዲካተት መጠየቅ አገዛዙን ከነግሳንግሱ ለማስወገድና ለዴሞክራሲ መመስረት በሚደረገው ሕዝባዊ ትግል ላይ ቀዝቃዛ ወሃ በላዩ ላይ ከመቸለስ ሌላ በምንም አይተረጎምም። በተጨማሪም አገዛዙን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከመደገፍ ወይንም የስልጣን እድሜው እንዲራዘም አስተዋፅዖ ማበርከት ነውና የሚደገፍ እሳቤ አይሆንም። ከዚሁ ጋር በተያያዘም የተለየ የፍትወተስጋ ዝንባሌና አመለካከት ያለውን “ኢሰብአዊና ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ ተግባር በማለት ጥላሸት እየቀቡ፣ በሽታ ያልሆነው በበሽታ እየሰየሙ በፀሎትና በልምምድ ብሎም ለነፍስ ኃኪም ንስሃ በመግባት ይፈዋሳል” እየተባለ የሚነዛውም ተሞክሮ ያልሰራ፣ የጤንነትና የአዕምሮ ጭንቀት ሥረመሰረትን አለማወቅ በመሆኑ በጭንቀት ላይ ጭንቀትን፣ የአዕምሮ መታወክን፣ ጨማሪ እንጂ መፍትሄ አይሆንም። በፍትወተ ስጋ ግንኙነት ይህ መጥፎ ነው ያ ትክክል ነው የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም። ሁሉንም ነገር በተፈጥሯዊነቱ ከማየት በተጨማሪ ከግለሰብና ከራስ የእሴት ግንዛቤ ጋር ተስማሚ መሆን አለመሆኑ ነው በመሰረታዊነቱ መታየትና ከግንዛቤ መወሰድ ያለበት።
“የሶዶማዊነት ባሕሪይ በፀሎት ሲለቃቸውና ሲፈወሱ የምንመለከተው አንዳንዴም ይህ አጋንንታዊ መንፈስ ጮሆ ሲለቅ እናስተውላለን። ምክንያቱም አጋንንት በሰው ውስጥ ያስቀመጠው ማንኛውም ተፅዕኖ መልቀቅ/መፈወስ የሚችለው በእግዚአብሄር ኃይል ስለሆነ ነው። ” ወረድ ብለውም “በወቅቱ በየአካባቢው የዛር መንፈስ የነበረባቸው፣ ወቅትን ጠብቆ የሚነሳባቸውና የጥንቆላ መንፈስ የነበረባቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ በወቅቱ ለመንፈሱ ካልገበሩ ይታመሙ ነበር አንዳንዶችንም ደም ያስተፋቸው ነበር፡፡ ሁለቱም፤ ማለት ባለዛሮችና ጠንቋዮች በአጋንንት መናፍስቶች የተያዙ ስለነበሩ በውስጣቸው ያለው መንፈስ የተለያዩ አስገረሚ ነገሮችን በማድረግ ሰውን የሚስደንቁ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን በኮሚዩኒዝም ፍልስፍና መሠረት ሰይጣንም፣ እግዚአብሔርም የለም ተብሎ ስለታመነ እነዚህ ባለዛሮችና ጠንቋዮች እንዲገረፉ፤ የጥንቆላና/የዛር እቃዎቻቸው እንዲቃጠሉና እንዲዘረፉ ተደረገ፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ በፊት ለመንፈሱ አስፈላጊውን መስዋዕት ካላቀረቡ ይታመሙና ደምም ይተፉ የነበሩ ሁሉ ምንም ሳይሆኑ ቀሩ፤ ማለትም መታመም የለም ደም መትፋትም አልነበረም፡፡ በዚህ ምክንያት ወጣቱና ካድሬው እንደተጨባጭ ማስረጃ በመቁጠር ይሄው ተመልከቱ ሰይጣንም እግዚአብሔርም የሚባል ነገር የለም ድሮም ቢሆነ ሲያታልሉን ነው የኖሩት፣ እውነት ቢኖር ኖሮ አሁን ለምን አልታመሙም በማለት በኩራት ሰበኩ ብዙ ተከታይም ማፍራት ቻሉ፡፡ እንግዲህ አስተውሉ ዲያብሎስ ምን ያክል አሳሳች እንደሆነ፡፡” በማለት ይህን የመሰለ አስተሳሰብ እየያዙ ነው እንግዲህ የዝግመተ ለውጥ አስተሳሰብ ምን ያክል አደገኛ እንደሆነ በአገራችን ኢትዮጵያ ያሳለፍነው ታሪክ ማስረጃ ነው፡፡” እያሉ ማንን ለማሞኘት እንደፈለጉ ግራ ማጋባቱ አንሶ ከታሪክም ተጣልተው እኛንም እንድንጣላ የሚጨቀጭቁን።
ስለ አጋንነትም ሆነ ስለ ዛር ሁናቴ የዝግመተ ለውጥ አስተሳሰብ ምንነቱ ባላታወቀበት ጊዜ በስፋት በተለይም በገጠሩ ይከናወን እንደነበረና በወቅቱ በማደግ ላይ የነበሩ ወጣቶች በቅርበት ያዩትን ለመታዘብ የቻሉት በመሆኑ ልዩ ምስክር ማምጣት የሚሻ አይደለም። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ዘመናዊ ትምህርትና የእውቀት ብሎም የፖለቲካ ንቃት በዳበረበት ይህን የመሰለ ተረት ተረት ማቅረብ አቅራቢን ከማስገመቱ ውጭ ምንም ትርፍ የለውም። ከእንግዲህ ወዲህ 500 እስከ 600 አመት ወደኋላ የሚመለስ ያስተሳሰብ ጉዞ ፈፅሞ ሊኖር እንደማይችል መገንዘቡ ይጠቅማል ምንም እንኳ ይህንን ተረት ተረት የሚያምን ባይጠፋም። ከሁሉ በላይ ይህ ክስተት በፈጣሪቸው ከልብ እምነት ያላቸውን ዜጎች የእውቀት ደረጃም መገዳደር ፈጣሪያቸውንም ማኮሰስ ነውና የተሳሳተና ወደኋሊት ጉዞ አስተናጋጅ ግንዛቤ ማስፋፋት ማንንም አይጠቅምምና በነሱ አነጋገር “ወደ መልካሙ እንዲመለሱ ፈጣሪ ቀጥቶም ቢሆን ምህረት እንዲያገኙ” ደጋግመው ንስሃ ቢገቡና ፀሎት ቢያደርጉ መልካም ይሆናል።
የሰው ልጅ የግብረስጋ ግንኙነትና ተግባር በተለያዩ የሰውነት አካላት እንቅስቃሴ፣ ለምሳሌ በመነካካት፣ በመዳራት የሚገኝ ስሜት፣ ፍላጎት ማግኘት፣ የራስ ግላዊ የሆኑ አካላዊ ስሜቶች መንፀባረቅ፣ የጤና ጉድለት፣ ከበሽታ ለመፈወስ የሚያገለግሉ መድኃኒቶችንም ሆነ አልኮሆልን የያዘ መጠጥ መጠጣትና ሲጋራን ማጬስ ፣ ሰውነትን አደንዛዥ የሆኑ እፀዋትን መጠቀም እነዚህ ሁሉ በግበረ ሥጋ ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተፅንዖችን ያሳድራሉ። ባሕላዊ፣ ሕብረተሰባዊ እንዲሁም ልጆች የሚያድጉበት ከበባዊ ሁናቴዎችና የወላጆች ኃላፊነት፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት ተመክሮዎች፣ ፍላጎት፣ ከሴትም ሆነ ከወንድ ጋር ያለ የግብረስጋ ግንኙነቶች፣ ከጋብቻ በፊት አብሮ በፍቅር መቆየት የተፈቀደ/ያልተፈቀደ በህብረተሰቡ ዘንድም ተቀባይነት መኖር/ አለመኖር ምልክቶች እነዚህ ሁላ ተፅዕኖ አሳዳሪ ናቸው። ስለሆነም እነ አንዳርጋቸው ስለ ግብረስጋ ግንኙነት ያላቸው አረዳድ በተሳሳተ መረጃ ላይ በመሆኑ “የሶዶማዊነት ወጥመድ ውስጥ የገቡና በእግዚአብሄር ኃይል መፈወስ እንደሚችሉ ተገንዝበው ወደ እግዚአብሄር እንዲቀርቡ እንመክራለን” የሚል ለበርካታ አመታት ተመክሮ ያልሰራን ይበልጡኑ በጤንነትና በመንፈስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተልውን እንደ አዲስ ሲያቀርቡ በርግጥም ምክር የሚያስፈልጋቸው እነሱ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንጂ ሌላ ምንም ትርጉም አይሰጥም። እንዴት ነው ታሪክንና ተመክሮን ወደኋላ መለስ ብሎ መራመር እንዴት ይገዳል?
ጤናማ የፍትወተ ስጋ ግንኙነት
ይህንን አስመልክቶ የአለም የጤና ተቋም እንዲህ በማለት ያቀርበዋል። ከግብረስጋ ግንኙነት አንፃር አካላዊ፣ ስሜታዊ፣ ሕሊናዊና ማህበራዊ የኑሮ ምቹነትን ማግኘት፣ አዎንታዊና ክቡርነትን የተጎናፀፈ የርስ በርስ ግንኙነት መኖር፣ እንዲሁም ደስ የሚልና ግዴታ የሌለበት፣ ለባይተዋርነት የማይዳርግ፣ ከጉልበት ጥቃት የፀዳ ጥሩ የግብረስጋ ግንኙነት ተመክሮን የሚያስገኝ በሚል ይተረጉመዋል። የሰው ልጅ የነፃነት መብትን ከተጎናፀፈ ፍላጎቱን ያለምንም እንከን ሆነ ጫና እንዲሁም ያለ አድሏዊነት ጥቃት ስሜቱን መገለፅ ሲችል፣ ይህንንም ሕብረተሰቡ ከሚጠይቀው፣ ከሚጠብቀው፣ ከሚፈልገው ወይንም ደግሞ የባይተዋር ስሜት አያሳድርብኝም የሚል አስተማማኝ ከበባዊ ሁኔታ ውስጥ ከተገኘ ለአካላዊና ለአዕምሮ ደህንነቱ፣ ስለ ሰውነቱ እንክብካቤ መኖር በአዎንታዊ መልኩ ስለሚመለከቱለት ምቹ የሆነ የግብረሥጋ ግንኙነት ያለው መሆኑ ይረዳል፣ ይገነዘባል።
የግብረስጋ ግንኙነት መብት መሰረቱ አለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ነው። በአሁኑ ወቅት ይህ መብት በብዙ ሀገራት እውቅና ተሰጥቶት በሕገ መንግስታቸው ውስጥ የተካተቱ ናቸው። ይህ መብት ማንኛውም ግለሰብ በፆታው፣ በውልደቱ፣ በሚከተለው እምነትና ርዕዮተ አለም፣ በእድሜው፣ በጤንነቱ ወይንም ደግሞ የግብረሰጋ ግንኙነት ዝንባሌው የመብት ጥሰትም ሆነ የባይተዋርነት፣ የመገለል ስሜት ሊደርሰብት አይገባም። በሕግ የተከለከለ ነው። ማንኛውም ዜጋ የግብረስጋ ግንኙነቱን ያለምንም አድልዎ በራሱ ግላዊ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሕይወቱን ለመምራት ሕጋዊ መብት ይኖረዋል።
በግብረስጋ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ አድሏዊነት፣ በዝቅተኛነት መመልከት ክቡርነቱን የመዳፈር ተግባር ነው። ይህ በተለይ እየተቃጣ ያለው በዋናነት ከግብረስጋ ግንኙነት ተግባር ላይ ሳይሆን የሚያነጣጥረው በሌላው ላይ የበላይነት ለመያዝና ለመቆጣጠር፣ ሥርአት የማሲያዝ የስልጣን ባለቤት ከመሆን/ከመያዝ ጋር የተቆራኘ ነው። ይህ በአደባባይ በተለይም ከጉልበተኛነት ጋር ተቆራኝቶ ሲንፀባረቅ የግለሰብን መብት ከመጋፋቱ በላይ ጥሰቱ የደረሰበትን ግለሰብ ሰብአዊ ክቡርነቱን የመዳፈር ተግባር ነው። ይህ በተለይ እየተቃጣ ያለው ውጫዊ እይታቸው እንዳለ ሆኖ በእድሜ፣ በአለባበስ፣ በማህበራዊ ምንጫቸው፣ በሚከተሉት እምነታቸው ከቁጥር ሳይገባ በዋናነት በሴቶች ላይ ነው። በተለያዩ ምክንያቶች ፍላጎታቸውን ለማንፀባረቅ የሚቸግራቸው፣ የመከላከል አቅማቸው ደካማ የሆነና እምቢታቸውን ለመግለፅ የሚቸገሩ ሕፃናትና ወጣት ልጆችም የዚሁ ክስተት ሰለባ ናቸው።
ማጠቃለያ
ሽፈራው ሉሉና እንግዳሸት ቡናሬ ሙግት የሚያደርጉት ከፊትም ከኋላም፣ ከግራም ከቀኝም ”ዲያቢሎስ፣ ሰይጣን ሉሲፈር፣ አጋንንት” ወዘተ) የተሰኙ የማስፈራሪያ ጭራቆችን አንዳንዴም በምናባቸው በኢራን እንዳሉት ግብረገብ/ ስነምግባር ጠባቂ ፕሊሶች ታጅበው ነው። በሰው ፍጡር ላይ አንዳችም እምነት የላቸውም። የሰው ልጅ ክፉ ወይንም ደግ፣ ፃዲቅ ወይንም ኃጢአተኛ ሆኖ ወደዚች አለም አልመጣም። በአለም ላይ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ ሕይወትን በሚመለከት አንድ ሲሆኑ የግብረስጋ ግንኙነት ግንዛቤያቸው እንደሚኖሩበት ከባቢ፣ ስለራሳቸው ያላቸው አረዳድ፣ ስለሚያድጉበት፣ ስለሚኖሩበት፣ ስለሚከተሉት እምነትና አረዳድ/ግንዛቤ ግን ይለያያሉ። አንደኛውን በጥሩነት ሌላውን በመጥፎነት ሊወሰድ አይቻልም። ኬን ሃም እንዳቀረበው የሱ ፈጣሪ ትክክለኛ የሌሎቹ የተሳሳተ አድርጎ መቁጠር ለወደፊት ጠብጫሪነት እንጂ በሰላም፣ በመከባበር፣ ለመኖር የሚጋብዝ አይደለም።
ብዙ ማንበብና ጠልቆ አለማየት፣ ብዙ መብላትና አለማኘክ መሆኑን የተገነዘቡ ባለመሆናቸው በራሳቸው የእምነት አስተሳሰብ ዙሪያ ታጥረው ሰክረዋል። ሁሉን ነገር የሚያዩት በነጭና በጥቁር ቀለማት ነው። ለዚህም ነው ስለ ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ ነፃነት ያላቸው ግንዛቤ በእጅጉኑ የተሳሳተ የሚሆነው። ከዚሁ ጋር ተደምሮ ስለ ግብረሥጋ ግንኙነት ያላቸው አመለካከት በተፈጥሮ ሳይንስና በሕክምና የምርምር ውጤት የተደገፈ ሳይሆን በጭራቆች ማስፈራሪያዎች፣ የሰው ፍጡር ስሜትን በሚገድሉ ሕግ ተብዬዎች የተደገፈ፣ በሰው አካላት ውስጥ ፍራቻን የሚለቅ ምንም አይነት በራስ መተማመን እንዳይኖር የሚያደርግና የማሸማቀቂያ፣ የማስበርገጊያ ዘዴ የተሞላበት ነው። ዋናው አላማ የሰው ስሜትን ለመግዛት፣ ለመቆጣጠር ነው። ለዚህም ነው ከነሱ እሳቤ ውጭ ሌላው የተለየ አመለካከት ያለው ሁሉ የሰይጣን ሰለባ ተደርጎ የሚቆጠረው።
ከዚሁ ጋር ተደምሮ ስለ ግብረስጋ ግንኙነት ያላቸው አረዳድም ቢሆን በተሳሳተ መረጃ ላይ በመሆኑ “የሶዶማዊነት ወጥመድ ውስጥ የገቡምና በእግዚአብሂር ኃይል መፈወስ እንደሚችሉ ተገንዝበው ወደ እግዚአብሄር እንዲቀርቡ እንመክራለን” የሚል ለበርካታ አመታት ያልሰራን ይበልጡኑ በጤንነትና በመንፈስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ብቻ ሳይሆን ሕይወትንም ለማጣት የዳረገን እንደ አዲስ ሲያቀርቡ በርግጥም ምክር የሚያስፈልጋቸው ሌሎች ሳይሆኑ እነሱ መሆናቸውን ድርጊታቸው የሚያመላክት ነው።
ከሁሉ በላይ የሚያስገርመው “በአሁኑ ወቅት” ይላሉ እነ እንግዳሸት “ሰው ሁሉ ከታዳጊ እስከ አሮጊትና ሽማግሌ ድረስ በአገራችን ሁሉም ስለ ዲሞክራሲ ይዘምራል፤ ያወራል፤ ይጮሀል፡፡ ነገር ግን የዲሞክራሲ አስተሳሰብ በተለይም የሊበራል ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሊያመጣ የሚችለውን ታላቅ ማሕበራዊ ቀውስ አስቀድመን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ በዘመናችን የዲሞክራሲ አስተሳሰብ በዲያብሎስ ተጠልፏል፡፡ በመሆኑም ይህ አስተሳሳብ ለኢትዮጵያችን ሲባል ታላቅ ገደብ ካልተበጀለትና፤ ኢትዮጵያዊ የሆነ ዲሞክራሲ ካላመጣን ዝም ብለን የምዕራባዊያንን አስተሳሳብ እንደዘመናዊነት ተቀብለን ማቀንቀንና ወደተግባር መሄድ ውሎ አድሮ የማንወጣበት አዘቅት ውስጥ እንደሚያስገባን ተረድተን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል።” መታወቅ ያለበትና እነ እንግዳሸት ያልገባቸው ነገር፣–
-
ዴሞክራሲ ያለ ሁሉ ተመሳሳይ አረዳድ የሌላቸው መሆኑ፣
-
ጥፋቱ የዴሞክራሲ ፅንፀሃሳብ ሳይሆን የዴሞክራሲን ካባ በማጥለቅ አምባገነኖች የመሰረቱት ሥርአት ችግር በችግር ላይ እየቀፈቀፈ ያለ እንደሆነ፣
-
ሰላም መስፈን ያልቻለው መሰረቱ የሆነው የመብት አለመከበር ውጤት እንደሆነ፣
-
ሕዝብ እየታገለ ያለው የምዕራቡም ሆነ የምስራቁን አመለካከት እንዳለ ለመገልበጥ እንዳልሆነ፣ አለመገንዘብ በዴሞራሲና በነፃነት ላይ ያላቸው ግንዘቤ እንዲንሸዋረር ሆኗል።
በመሆኑም “ኢትዮጵያ በዕምነታቸው የጸኑ ሕዝቦች የሚኖሩባት፤ በማሕበራዊና ግለሰባዊ ግብረገብነት የተገነባ ባሕል ያላት አገር ነች፡፡ የዲሞክራሲ አስተሳሰብ ገደብ ካልተበጀለት ወይም የአገራችንን ባሕል መሠረት ያደረገ ኢትዮጵያዊ የሆነ ዲሞክራሲ ማምጣት ካልቻልን፤ እንደ ምዕራባዊያን ሀገራት እኛም የዲያብሎስን ዕቅድ በማስፈጸም ትውልድንና አገርን ወደሚገድል ማሕበራዊ ቀውስ ውስጥ መግባታችን አይቀርም፡፡ በመሆኑም የሁሉም የዕምነት ተቋማት፤ እንዲሁም ሁሉም ዜጋ ዲሞክራሲን ከለላ አድርጎ ሊመጣ የሚችለውን የሰዶማዊነትንና እንዲሁም ሌሎች የክፋት ሀሳቦች ማስተማርና መከላከል ይኖርብናል፡፡” የሚል ምክርን ይለግሳሉ። ምክራቸው ግን ለምሳሌ “እምነተ ፅኑ መሆን፣ በማህበራዊና ግለሰባዊ ግብረገብነት የተገነባ ባህል ያላት መሆኗ” ግን በጎሳና ዘረኝነት የተላበሰ አገዛዝ ከመመስረትና ትውልድንና ሀገርን እየገደለ ከአንድ ማህበራዊ ቀውስ ወደ ሌላ ማህበራዊ ቀውስ ከመግባት አላዳናትም። ያለፉት ከ50 አመታት በላይ የተገኙት ተመክሮዎች የሚያሳዩት ይህንኑ ነው።
ሥልጣን ለመጨበጥ የሚቋምጡ ቡድኖች መብትን ለመገደብ ሲያስቡና ሲያውጠነጥኑ በመሰረቱ ሕዝብን ረግጠው ለመግዛት ካላቸው ፅኑ ፍላጎት እንጂ ሌላ አይደለም። ሕዝቡ ባለሙሉ መብት ከሆነ አገዛዛቸውን ይቃወማል፤ ውሎ አድሮም ያስወግዳል። ስለዚህም የመብት ሞግዚት ሆነ ለመቅረብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም። ይህንን ነው የሕዝብ ታጋዮች ነቅተው መታገል የሚገባቸው። በሀገራችን ዴሞክራሲ ለጭቁኖቹ አለገደብ ከተከበረ ሕዝብ የመረጠውን መንግሥት የሚደግፉ ብቻ ሳይሆኑ በተለይም የሚቃወሙት ጭምር መብታቸው የተከበረ ይሆናል። ውሳኔዎች በሕዝብ ድምፅ ስለሚረጋገጡ ዴሞክራሲን ለመገደብ ማሰብና ማሰላሰል ከወዲሁ ፀረ ዴሞክራሲ ነውና የማይፈልጉትን ቡድን ሆነ ተቃዋሚ ለመገደብ ነውና በኛ በኩል ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። እውነተኛ ዴሞክራሲ፣ እውነተኛ ነፃነት ትክክለኛ ነፃነት ሊኖር አይችልም። ሁሉም የየራሱ ግንዛቤና አረዳድ ይኖረዋል። ዴሞክራሲ፣ ነፃነት ያለ ሁሉ ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው ማለት ጨርሶ አይደለም። ሁሉም አስተሳሰብ በአደባባይ ወጥተው የሚመለከተው ሕዝብ ይሁንታውን እንዲሰጥ ማስቻል ነው መሰረታዊው ጥያቄ፡፡ ለዚህም ነው “ዴሞክራሲ ያለ ገደብ” የትግል መርህ ሆኖ በማታገያነት፣ በማደራጂያነት በማንቂያነት እየተገለገልንበት የሚገኘው። ለዚህም ነው ዴሞክራሲያዊ ሥርአት እናውቅልሃለን በሚሉት ሳይሆን በራሱ በሕዝቡ መራራ ትግል ገና ሳይመሰረት ከወዲሁ ገደብ ለማበጀት ማሰብና ደፋ ቀና ማለት ሂደቱ ወዴት እንደሆነ የሚታወቅ ነውና በምክንያትነት ሶዶማዊነትም ሆነ የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብን ማቅረብ ትርጉም የለሽ ነው የሚሆነው። ይህ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥቅሙን በሚገባ ጠንቅቆ እንደማያውቅ አድርጎ መቁጠርና አለማመን ጭምር ብቻ ሳይሆን የሚበጅህን እኔ ብቻ አውቅላሃለሁ ከማለት ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። ይህ ደግሞ በበኩላችን ወደ አምባገነናዊነት ጎዳና የመሄድ ነፀብራቅ ነውና አጥብቀን የምንታገለው የነበረ፣ አሁንም የምንታገለው፣ ወደፊትም በዚሁ የምንቀጥልበት ነው።
ለዚህም ነው “„ ፖለቲከኞች ሙሉ በሙሉ ተገልለው የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ከፖለቲካ ገለልተኛ ከሆኑ ምሁራን፣ የኃይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎችን በማቀናጀት፣ የኃይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎች ሕዝቡን በማስማማትና በማቀራራብ፣ የአስተዳደርና ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ ሥረዓት እንዲዘረጉ ቢደረግ በሁሉ ሕዝብ ተቀባይነት ስለሚኖረው ዘላቂ የሰላምና የአንድነት መሰረትን ለመጣል ያስችላል፡፡“ ተብሎ እንደ መፍትሄ ሃሳብ የቀረበው ጠጋ ብለው ሲመረምሩት ምኞትና እውነታው የተቀላቀለበት መሆኑን ያልተገነዘበና ውሃ የማይቋጥር ሆኖ የሚገኘው።
አንባቢያን እንግዲህ እነ እንግዳሸት የጥላቻ ተረታቸውንና ትርከታቸውን ዘርዝረው፣ ከኋላ ቀር የፍልስፍና አስተሳሰብ ተንደርድረው ነው “ፖለቲከኞች የኢትዮጵያን ችግር ይፈታሉ ብለን አናምንም። የኢትዮጵያን ችግር ሊፈቱ የሚችሉት የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው” በማለት የጅምላ ወቀሳና የጅምላ ሙገሳ ያላበሷቸውን በመፍትሄነት ያቀረቡልን።
በመቀጠልም “ፖለቲከኞች ሙሉ በሙሉ ተገልለው የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ከፖለቲካ ገለልተኛ ከሆኑ ምሁራን፣ የኃይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎችን በማቀናጀት የኃይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎች ሕዝቡን በማስማማትና በማቀራራብ የአስተዳደርና ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲዘረጉ ቢደረግ በሁሉ ሕዝብ ተቀባይነት ስለሚኖረው ዘላቂ የሰላምና የአንድነት መሰረትን ለመጣል ያስችላል፡፡ “ ሲሉ ዴሞክራሲን በአፍጢሙ ደፍተውና በጫማቸው ረግጠው ምርጦች ለሆኑ የኃይማኖትና የሽማግሌዎች ስብስብ የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ የመወሰን ሥልጣን ለማስረከብ የሚቋምጡት። ለመሆኑ በምን ማጠየቂያ ነው “ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆኑ ምሁራን” በኃይማኖት መሪዎች ሥር በጋራ የፖለቲካ ተግባር ሊያከናውኑ የሚጠበቀው? የኃይማኖት አባቶችንና ሽማግሊዎችን ማክበርና የራስንም ሆነ የቡድን ጥቅም ለማስከበር የሚደረግ ትግል እጅግ በጣም የተለያዩ መሆናቸው እንዴት ይረሳል? ፖለቲካ ማለት እኮ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በሚገኙ እሴቶች ላይ ያሉትን አለመግባባቶች ለመወሰን(ሕጋዊነት ለመስጠት) ላይ ያነጣጠረ ማህበራዊ ተግባር/ እንስቃሴ መሆኑ እንዴት ይጠፋናል? የፖለቲካ አላማና እምብርቱ ልዩነቶችንም ሆነ አሉ የሚባሉ ጥቅሞችን በማጣጣም፣ የፖለቲካ ሥልጣኑንን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በማደራጀት ሰላም ማስገኘት እንደሆነ መረዳት ለምንድን ነው የሚሳነን? ሰብአዊ ተግባር ከስነሥርአት፣ ከመደበኛ ደንብ፣ ከእሴት ግንዘቤና ከርዕዮተ አለም አረዳድ የሚቀረጽና የርስ በርስ ግንኙነቶች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳራፊ መሆኑን መገንዘብ እንዴት ያቅተናል?
ፖለቲክኞች ይገለሉ ከተባለም ሊያገል የሚችለው እኮ ሕዝቡ በራሱ ከራሱ ከጉያው አውጥቶ በትግል ሂደት ውስጥ እንደ ብረት በእሳት በተፈተኑ መሪዎቹ አማካኝነት እንጂ በሌላ ከቶም ሊሆን አይችልም። ትግሉ በድል ሲጠናቀቅ ደግሞ የሽግግር ሂደቱን እናውቅልሃለን በሚሉት ሳይሆን ለድሉ አስተዋፅዖ ባባረከቱ እንጂ ከዚህ ውጭ የሚታሰብ ሊሆን አይችልም። ሕዝብ ታግሎ ወደ ድል ሲቃረብ በተለያዩ የማነሆለሊያ አረፈተ ነገሮች በፕሮፓጋንዳነት በመጠቀም በሕዝቡ ትከሻ ተረማምደው ሥልጣን ለመጨበጥ የሚቋምጡ እንዳሉ ያለፉት ተመክሮዎቻቸን የሚያሳዩን ናቸውና በበኩላችን በቸልታ የምንመለከተው አይደለም። የደርግ “ኢትዮጵያ ትቅደም ያለምንም ደም”፤ ሆነ የወቅቱ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” የሚሉ ፈሊጦች ስንቱን እንዳነሆለሉና ትግሉን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን እንደጎዱ ያለንበት ወቅት የሚያመላክተን ነው። ስለሆነም ምንም ገደብ የሌለው ነፃነታችንንና ድላችንን ለመጎናፀፍ ከራሳችን እልህ አስጨራሽ ትግል ውጪ በሌላ በፆም በፀሎት በልመና የሚገኝ እንዳልሆነ ጠንቅቀን የምናውቀው ነው። ሕዝብ ደሙን አፍሶ አጥንቱን ከስክሶ በታገለ ማን በማን ትክሻ ላይ ተንጠልጥሎ ከስልጣን ማማ ለመቆናጠጥ እንደሚቀላውጥ የወቅቱን እናውቃቸዋልና የወደፊቶቹን በጋራ የምናያቸው ይሆናል። እነ እንግዳሸት ከዚህ ተርታ ለመመደብ የሚያስችላቸውን የመቀጠሪያ ደብዳቤ አሳይተዋልና ከንግዲህ ወዲያ አናስጨንቃቸውም። አውቀናል ጉርጓድ ምሰናል ከማለት ውጪ።
እነ እንግዳሸት “ፖለቲከኞች የኢትዮጵያን ችግር ይፈታሉ ብለን አናምንም “ ሆነ “ የኢትዮጵያን ችግር ሊፈቱ የሚችሉት የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡” ማለታቸው መብታቸው ነው። ነገር ግን “የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎችን ሕዝብ ይሰማቸዋል፣ እነሱም ሕዝቡን ያዳምጣሉ፡፡ ሕዝብ ያከብራቸዋል እነሱም ሕዝቡን ያከብራሉ፡፡ ከሕዝቡ የሚጠብቁት ልዩ ጥቅም ወይም ሥልጣን የላቸውም፡፡ ሰጪነትን እንጂ ተቀባይነትን አያስተምሩም፡፡ ሕዝብን ማስታረቅ እንጂ ፀብን አይዘሩም፡፡ የተለየ ዘውግን/ቡድንን አይወክሉም፡፡ ኃይማኖት ዘውግ የለውም፤ ቀለም የለውም፤ ወሰን የለውም ሁሉንም ሕዝብ ያዋሕዳል፡፡ የሀገር ሽማግሌዎች እንደቃሉ የሚወክሉት ሀገርን ነው ጎሳን ወይም ቡድንን አይደለም፡፡ በአስተዳደሩም ሆነ በማሕበራዊው የህዝቡን ስነልቦና በደንብ ይረዳሉ፤ ለህዝብ የሚጠቅመውን ለይተው ያወቃሉ፡፡ ህዝብን አቻችሎ አብሮ የሚኖረበትን መንገድ ከማንም በላይ ይረዳሉ፡፡ ሕዝብን የማስተዳዳሪያ ዘይቤዎችን ከማንኛውም ፖለቲከኛና ሊሂቅ የበለጠ ይረዳሉ፡፡ በሕዝብ ስነልቦና ላይ የተመሠረተ የአስተዳዳር ዘይቤ መቀየስ ይችላሉ፡፡ „የኃይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎች ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በተለይ ለሕዝብ የቀረቡና ለሕዝብ የሚሠሩ ናቸው፡፡“ ማለት በጥሩ የተሰራ ሰላጣ ውስጥ ቅመምና ቃሪያ መጨመር ካልሆነ በስተቀር ትርጉም የለውም። ስለማር ስለተወራ ከአፍ ውስጥ ጣፋጭ የመፍትሄ አስተያየቶች ነጥረው ይወጣሉ ማለት አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ስብከትን ሳይሆን ሲቻል ከጎኑ መቆም ካልተቻለ ደግሞ ትግሉን ለማደናቀፍ በእንቅፋትነት አለመቆም ፍላጎቱ እንደሆነ በተደጋጋሚ አሳይቷል። ሕዝብን ማዳመጥ እንጂ መዳመጥ መቼም ቢሆን የሚዋጥልን ሊሆን አይችልም።
የነ እንግዳሸት ቡናሬ የጅምላ ስብከት ከላይ እንደተመለክትነው የሚያመላክተው የራሳቸውን ግምት እንጂ በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠ አይደለም፣ ሊሆንም አይችልም። የራስን ስሜትና እምነት እንደመጨረሻው እውነተኛ መንገድ አድርጎ ከመውሰድ ሌላ ለብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስገኘው ጠቀሜታ የለም። ሰውን ማክበር የግዴታ ለኃይማኖት አባቶችና ለሽማግሌዎች ብቻ በተለይ የሚሰጥ ክስተት አይደለም። በሀገር ጥበቃና ደህንነት፣ ድንበርን በማስከበር፣ በጠላት እንዳይደፈር ሌት ተቀን በረደን ሞቀን፣ በረሃብና ጥማት ተጎዳን ሳይሉ፣ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረከቱ በሕዝብ ዘንድ ከበሬታን ተነፍገው አያውቁም። በተለያዩ ደረጃዎች ለሀገር ከፍታ አስተዋፅዖ ያበረከቱ በስፖርት፣ በሳይንስ በተለያዩ የግንባታ ዘርፎች፣ በእርሻና ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረከቱ ሁሉ የሚከበሩ ናቸው። ሌላም ሌላም። በመሆኑም የኃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ከሌላው ሁሉ በተለየ “በአስተዳደሩም ሆነ በማህበራዊ የሕዝቡን ስነልቦና በደንብ የሚያውቁበት፣ ለሕዝብ የሚጠቅመውን ለይተው የሚያውቁበት፣ ሕዝብን አቻችሎ አብሮ የሚኖርበትን መንገድ ለይተው የሚያውቁ ከማንም በላይ የሚረዱ፣ የማስተዳደር ዘይቤዎችን ከማንኛውም ፖለቲካኛ ልሂቅ የበለጠ የሚያውቁ “ በማለት አንድን የሕብረተሰብ ክፍል በዚህ ሁናቴ ማቆለጳጰስና ከዙፋን ለማስቀመጥ መመኘትና መጣር ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ወይንም ደግሞ ሊበሏት ያሰቡትን ዥግራ ቆቅ ይሏታል አይነት ነውና የመለሳለስ ፕሮፓጋንዳ ትርጉም የለሽ ነው። ከሁሉ በላይ የሕዝብን የፖለቲካ ንቃት አሳንሶ መመልከት ነው የሚሆነው። የህዝብን ሚና ከግምት አለማስገባትም ነውና ተቀባይነት ጨርሶ ሊኖረው የማይችል ነው።
ከላይ የተጠቀሱት ማቆለጳጰሻዎች በርግጥም ለግለሰብ እንጂ በጅምላ መጠቀሚያ ሊሆን አይችልም ከኋላው ሌላ መሰሪ ተንኮል ካልታሰበ በቀር። ማንኛውም ግለሰብ በጠባዩ፣ በተግባሩ በአመለካከቱና በቀና ባሕሪው ተፈትኖና ተመርምሮ ይፈርዱታል እንጂ የጅምላ ፍረጃ መስጠት ትርጉም የለሽ ነው። በወንጀልም ቢሆን በድርጊት ተከፋይነትን እንጂ የዚህ ወይንም ደግሞ የዛ የሕብረተሰብ ክፍል አባልነት አይደለም ከጥያቄ የሚገባው። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የብሔር ተወላጆች (ለምሳሌ በኦሮሞም ሆነ ትግራይ አማካኝነት) እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ጭፍጨፋዎችና የመብት ጥሰቶች በዜጎቻችን ላይ ተደርገዋል። ለዚህ ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉት ድርጊቱ እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጡ ባለሥልጣን/አዛዥ፣ በድርጊቱ ተካፋይ የሆኑትና ተባባሪዎች እንዲሁም መቃወም ሲችሉ ዝምታን የመረጡትን እንጂ ጠቅላላ ብሔራቸው ሊሆን አይችልም።
ስለሆነም በጭፍን ወገንተኛነት ስሜት አንዱን አጥፊ ኮንነን ሌላውን አጥፊ ለማመስገን ካልፈለግን በስተቀር በወቅቱ እየታዘብን እንዳለው ማለት ነው፣ በተቃራኒ ወገኖች በተካሄደው የረዥም ጊዜ ጦርነት በትውልድ፣ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በባህል በሥነ ባህሪና በኢኮኖሚ አንዱ ከሌላው ጋር በጥብቅ የተሳሰረና የተጋመደ እህትማማችና ወንድማማች መሆናችንን ከታሪክና ከተመክሮም በመጥቀስ ጥግ የነኩ አስተሳሰቦችንና ጥላቻን የሚያስወግዱ መፍትሄዎችን በመለገስ፣ በማሳየት፣ በማመላከት ብሎም በመብት መከበር ላይ የተመረኮዘ ወደ ብሔራዊ አንድነት የሚወስደውን መንገድ በማስተማርና በመምራት ፈንታ በሥልጣን ጥማት በሰከሩና ባበዱ በራስ ወዳድ አገዛዞችና ሃይማኖት መሪዎቻችን አማካይነት ጥላቻና ደመኛነት መሰበኩን (ድርብ ሰረዝ ይጨመርበት) እነ እንግዳሸት ቡናሬና መሰሎቹ ተገንዝበው ለሌላው የሚሰጡትን ምክር በቅድሚያ በራሳቸው ላይ አድርገው ንስሃ ቢገቡ ለአብሮነት የመጀመሪያው ድል ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ይጠበቅባቸዋል።
ለዚህም ነው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በመሰረታዊነት ግልፅ ሊሆን የሚገባው የፖለቲካና ሕዝባዊ ድርጅቶች ከሁሉ በፊትና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ምናልባትም በድልነት ሊቆጠር የሚችለው ይህ ወይም ያኛው አማራጭ፣ ወይም ፓርቲ ወይም አቋም ወይንም ደግሞ ግንባር/ጥምር አሸንፎ የራሱን አጀንዳ ለመፈፀም ሆነ ለማስፈፀም ደፋ ቀና ማለቱ አይደለም፡፡ ባለፉት በርካታ አመታት የተጓዝንባቸው ሂደቶች ያገኘናቸው ተመክሮዎቻችን ይህንኑ የሚያመላክቱን ናቸው። ስለዚህ በመጀመርያና በቅድሚያ ለሕዝብና ለሀገር ቀናኢ የሆኑ ኃይሎች በሙሉ ልናተኩርበት የሚገባው አማራጮች በሰፊው እንዲሰራጩና የሚመለከተው ሕዝብ በራሱ አረዳድና ግንዛቤ ፍላጎቱንና ስሜቱን ለመገለጽም ሆነ ድጋፉንም ሆነ ነቀፌታውን ለመስጠት ይችል ዘንዳ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያለምንም ገደብ እንዲያብቡ፣ ፍላጎታቸው፣ ለችግሮች መፍቻ ብለው የሚያቀርቧቸው መፍትሄዎች፣ አቋሞች በህዝቡ ፊት ነጥረው እንዲወጡ ማድረግ የሚያስችል ያለውን አገዛዝ በህብረት በተቀናጀ ትግል አስወግዶ በምትኩ ነፃና ገለልተኛ የሆነና ዴሞክራሲያዊነትን የተላበሰ የተቋም ግንባታ ውስጥ መሰማራት የሞትና የሽረት ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበን ለዚህ ስኬታማነት ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅዖ ማበርከት ይጠበቅብናል። ይህ ተሟልቶ ሲገኝ ይሄኔ ከፊታችን ተደቅነው ለሚገኙ መጠነ ሰፊ ችግሮቻችን በሕዝባዊ ነፃ ውይይትና የምርጫ ውሳኔ ያለምንም ጥርጥር መፍትሄ ያገኛሉ የሚል ጠንካራ እምነት አለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሁሉም በየፊናው በራሱ ብቸኛ የእውነት ጎዳናዬ የሚለውን ለማቅረብ ቢንፈራገጥ ድርጅቶቹም ሆኑ ሕዝብም የሚያተርፉት መላላጥ ቀጣይ ይሆናል። ይህ ግን በማናቸውም ዘንድ ፈፅሞ የማይፈለግ ነው። የድል ጊዜን ያራዝምብናል እንጂ። አበቃሁ መልካም ንባብ።
የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሃሳብም ሆነ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ብሩህ ተስፋ ናቸው!!
በሽተኛ ለሌላ በሽተኛ የሕክምና መፍትሄ ሊያስገኝ ከቶም አይቻለውም!!
ጥላቻን ዘርቶ ማን ፍቅርን ያመርታል!!