ጥ ያ ቄ – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

እረኝነት …

ትልቅ ኃላፊነት …

መሆኑንን አውቃለሁ ።

ግን እኔ

ለወንድሜ መልካም እረኛ ሆኛለሁ ?

ወይስ እኩይ ቅናት ስላደረብኝ

የመጥፊያውን ጉድጎድ እቆፍራለሁ ?

” ከእኔ ቀድሞ በሞተ ! ” ቢዬ እፀልያለሁ ።

………………………………..

ግን ፣ ግን ፣ መቼ ነው ?

ሰው ለሰው መልካም እረኛ የሚሆነው ?

አንዱ ለሌላው ሥኬት ፣ እንቅፋት የማይሆነው ?

መቼ ነው ?

ከጠብ መንጃ አጥር ወጥቶ …

ህይወትን የሚኖራት በጋራ ተስማምቶ ?

መቼ ነው ፤ ሰው አለማወቁን የሚየውቀው ?

ሰው ከአፈር ተፈጥሮ ፤ አፈር እንደሚሆን የሚረዳው ?

……………………………………………………………………..?

ሰው አፈር እስከሚሆን በተራ ፤ በተራ …?

የፈጠረውን ፈጣሪውን ካልፈራ …?

” የክርስቶስ ነኝ ፡፡ ” እያለ በገዳይነት ከተሰማራ…?

” አላህ ! ክበር ! ” እያለ ፣ በአላህ  ካልተመራ …?

እግዚአብሔር …

ከእመ አልቦ ሁሉን እንደፈጠረ ካለወቀ …?

ፈጣሪውን በመፍራት ሰው፣ለሰው ካልተጨነቀ ?

ፈጣሪን የመፍራት ጥበብ በውሰጡ ካልደመቀ

ሰው በተግባሩ ገሃነም አይሆንም ወይ ፤ ከፍቅር ከራቀ ?

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሻለቃው ማስታወሻ ከረሃብ አድማ እስከ ሽምግልና ትዝብት | Hiber Radio Special Program Oct 02, 2023

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share