August 19, 2022
26 mins read

የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስና የአይኤምኤፍና የዓለም ባንክ  ፕራይቬታይዜሽን ሴራ!! – (ክፍል 3)  

ሚሊዮን ዘአማኑኤልና ፂዮን ዘማርያም
(ክፍል 3)  ሚሊዮን ዘአማኑኤልና ፂዮን ዘማርያም  (ኢት-ኢኮኖሚ

5433cvc

በዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ በሪፖርተር ጋዜጣ እሁድ ሰኔ 17 ቀን 2010ዓ ም በፁሁፍ ያቀረቡት ‹‹ኢኮኖሚው ያጋጠሙትን የማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ለማቃለል የቀረበ የመፍትሄ ሐሳብ›.(1)

የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ስለ ‹‹ዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ በሪፖርተር ጋዜጣ እሁድ ሰኔ 17 ቀን 2010ዓ ም በፁሁፍ ያቀረቡት ‹‹ኢኮኖሚው ያጋጠሙትን የማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ለማቃለል የቀረበ የመፍትሄ ሐሳብ›› ላይ አንድም የፖለቲካ ፓርቲ ድጋፍ ወይም ነቀፌታ የሠነዘረ የለም፡  ኢዜማ፣ ኦፌኮ፣ ባልደራስ፣ አብን፣ ወዘተርፈዎች ስለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ያላቸው ዕውቀትና ግንዛቤ አናሳነት፣ ስልጣን ስትይዙ ያደናግራልና ከአሁኑ የኢኮኖሚውን ዘርፍ ጠንቅቆ መረዳት አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት የኢኮኖሚ አጥኝ ኮሚቴ  አቆቁሞ በማጥናት ለህዝብ ማስተማር ይጠበቅባችኃል፡፡ የአራት አመታት ዝምታችሁን ስበሩ፣ ስለቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ መልስ መስጠት ይጠበቅባችኃል፡ስለ ጦርነት ኢኮኖሚ አቆማችሁን ግለፁ፡፡ እንዲሁም የሃገሪቱ ኃብት በፕራይቬታይዜሽን መርሃ-ግብር ተሸጦ ከማለቁ በፊት ድምፃችሁን አሰሙ እንላለን፡፡

{5} የፈስካል ፖሊሲ (Fiscal policy)  አፈፃፀም ጥራት ማሳደግ:- ‹‹የአገሪቱ በጀት በየጊዜው እያደገ መምጣቱ ይታወቃል (በዋጋ ግሽበት ምክንያት የተፈጠረውን ዕድገት ሳይጨምር) ይሁን እንጂ በዚያው መጠን ብክነትና ምዝበራ  እየጨመረ ሄዶል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንግሥት የካፒታል በጀቱን ይጨምር እንጂ ጥራቱ ከመጨመር ይልቅ የወደቀ ሆኖል፡፡ ለአብነት የኢህአዴግ አባል ድርጅት የሆነ አንድ ክልል የሚመራ ድርጅት  በቅርቡ ባወጣውና ሥራ አስፈፃሚው የተወያየበት ሪፖርት እንደሚያመለክተው  በክልሉ  ካሉ 800 ትምህርት ቤቶች ለመማር  ማስተማር ሥራ ብቁ የሆኑት 80 ብቻ ወይም አሥር በመቶ መሆኑን አጋልጦል፡፡ይህ የሚያመለክተው  ብክነትና በጀትን በሚገባ በጥራት መጠበቅ አለመቻሉ ነው፡፡ ሰሚ ያጣው የዋናው ኢዲተር ሪፖርትም የበጀት አጠቃቀም  ላይ ያለውን ክፍተት ለመድፈን አለመቻሉን ነው፡፡ በዚህ ረገድ የበጀት ጥራት (Quality budget) ማረጋገጥን መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ የታክስ መሠረቱን (Tax base) ማስፋት ከአገር ውስጥ የሚገኝ ተጨማሪ ገቢ (Domestic resource mobilization) የማግኘት ሥራ የአገር ውስጥ የብድር ጫናን  በመቀነስ ለኢኮኖሚው ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ የመንግሥት ሥራ ነው፡፡››

  • ዓመታዊበጀት መሟጠጥ (Draining the budget:) የተባበሩት መንግሥታት ሴክሬተሪ ጀነራል አንቶኒዩ ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ጦርነት  አንድ ቢሊዮን ዶላር ከአመታዊ በጀታቸው ጎተራ አሞጠዋል ብለዋል፡፡ ወታደራዊ ወጪውን ይጨምራል፡፡  እንደ ስቶክሆልም ኢንተርናሽናል ፒስ ሪሰርች ኢንስቲቲውት ዘገባ መሠረት በ2020 እኤአ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ 460 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ተዘግቦል፡፡ እንደ ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ የዓለም የማክሮ ሞዴሎችና ትንተና ግምቶች መሠረት ኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ  በ2021 እኤአ መጨረሻ ድረስ ወታደራዊ ወጪዋ  502 (አምስት መቶ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር ወይም ሃያ አምስት ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ ተተንብዬል፡፡
  • የዶክተር አብይ መንግሥት ትልቁ የገንዘብ ምንጩ የህዝብ ገንዘብ የሆነው ተቀማጭ ገንዘብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመበደር ባንኩን በማክሰር ላይ ይገኛሉ፡፡ አዳነች አቤቤ የምትመዤርጠው መቶ ሚሊዮን ብር እና ሽመልስ አብዲሳ ጢባ ጢቤ የሚጫወትበት መቶ ሚሊዮን ብር ምንጩ ከየት ይሆን? በበጀት ለስጦታ የተያዘ እቅድና አፈፃፀም ይሆን፡፡የኢትዮጵያ የ2013 ዓ/ም በጀት 561(አምስት መቶ ስልሳ አንድ) ቢሊዮን ብር ሲሆን በጦርነቱ ወቅት 122 (መቶ ሃያ ሁለት) ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት በፓርላማ ፀድቆል፡፡ የብልፅግና መንግሥት 100 (መቶ) ቢሊዮን ብር የትግራይን ኢኮኖሚ ለመገንባት ወጪ ማድረጉ ተገልፆል፡፡ በአንፃሩ ለትግራይና ለአፋር ክልሎች አምስት ቢሊዮን ብር የበጀት ድጎሞ ተፈቅዶል፡፡ የዓመታዊ በጀት መሟጠጡን ያሳያል፡፡
  • የ2015ዓ/ም በጀት 786.61 ቢሊዮን ብር ሲሆን አስረሰአምስት ቢሊዮን ዶላር (a budgetof about 15.1 billion U.S. dollars for the country’s 2022/2023 fiscal year) ሲሆን For the upcoming fiscal year, the Ethiopian Parliament approved a government budget with planned expenditures of Birr 787 billion (11 percent of GDP), to be funded by revenue collections of Birr 439 billion, grants of Birr 39 billion, foreign borrowing of Birr 43 billion, and domestic borrowing of Birr 266 billion.
  • የ2015ዓ/ም በጀት 786.61 ቢሊዮን ብር አስርቱ የበጀቱ ወጪዎች ዝርዝር The top 10 budget expenses for the upcoming Ethiopian fiscal year, according to the Cepheus report, are listed below.

(1) የአገልግሎት ወጪ 126.0 ቢሊዮን ብር (Debt service: ETB 126.0 bn with a share of 22.4%)

(2) መከላከያ ሠራዊት ወጪ 84 ቢሊዮን ብር (Defense: ETB 84.0 bn with a share of 14.9%)

(3) መንገድ ሥራ 66.2 ቢሊዮን ብር (Roads: ETB 66.2 bn -11.8%  )

(4) ትምህርት 64.7 ቢሊዮን ብር (Education: ETB 64.7 bn – 11.5% )

(5) ውኃ ኃብትና የኢነርጂ ልማት 24.7 ቢሊዮን ብር (Water & Energy: ETB 24.7 bn – 4.4%)

(6) ጤና 19.3 ቢሊዮን ብር  (Health: ETB 19.3 bn – 3.4% )

(7) የከተማ ልማት 18 5 ቢሊዮን ብር (Urban Development: ETB 18.5 bn – 3.3%)

(8) ግብርና ልማት 18.5 ቢሊዮን ብር (Agriculture: ETB 18.5 bn – 3.3% )

(9) የፍትህና ደህንነት 17 ቢሊዮን ብር  (Justice & Security: ETB 17.0 bn – 3.0%)

(10) የአደጋ መከላከልና መልሶ ማቆቆም  13.1 ቢሊዮን ብር (Disaster Preparedness: ETB 13.1 bn – 2.3%) ………………………(2)

መደምደሚያ  የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፅፀም  የዘንድሮ በጀት ለካቻምና ልማት

  • የአማራክልላዊ መንግሥት መረጃ መሠረት በአማራ ክልል 380 ቢሊዮን ብር ንብረት መዘረፉንና መውደሙን ዳግም መሠረተልማቶቹን ለመገንባትም ብዙ አመታት እንደሚፈጅ በተደጋጋሚ አሳስበው ከፌዴራል መንግሥቱ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ የዘንድሮ በጀት ለካቻምና ልማት!!!
  • በአማራ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 100 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ለፓርላማ አባላት ገልፀዋል፡፡ ከወደሙት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1200 ትምህርት ቤቶች በጦርነትና በሌሎች ምክንያት የወደሙ፣ 5000 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ ሶሰት ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፣ መቶ ሃምሳ ሽህ መምህራን ከመማር ማስተማር አገልግሎት ውጪ ሆነዋል፣ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች በከፊልና በሙሉ ወድመዋል በማለት የደረሰውን ጉዳት ገልጸዋል፡፡ በአማራ ክልል ብዙ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ብዙ 11.6 ሚሊዮን ህዝብ በጦርነቱ ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ ዜጎች ሆነዋል፡፡
  • በአማራና በአፋር ክልሎች ለተዘረፉና ለወደሙ 36 ቢሊዮን ብር መልሶ ለማቆቆም እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል በህወኃት የተዘረፉ የጤና ተቆማት ተፈታትተው የተዘረፉ የህክምና መሣሪያዎችና የላብራቶሪ እቃዎች ግምት 36 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ታውቆል፡፡በአፍር ክልል እስከ አምስት መቶ ሽህ ህዝብ በጦርነቱ ተፈናቅሎ ይገኛል፡፡
  • በሃገሪቱመንግሥት የለም!  የብልፅግና መንግሥት የጦር ግምጃ ቤቱን መሳሪያዎች ታንኮች፣ ሞርታለች፣ ቢኤሞች፣ ብሬኖች፣ ዲሽቃዎች ሚሳኤሎች፣ ሮኬቶች ፣አዘርፎል፡፡ የሃገሪቱን  ባንኮች፣ ፋብሪካዎች፣ ከባድ መኪኖች፣ አዘርፎል፡፡ በምድረ ኢትዮጵያ ዓየር በዓየር የጦርነት ንግድ ተጦጡፎል፣ አንድ ክላሽን አንድ መቶ ሃያ ሽህ ብር ይሸጣል፡፡ በየሐሙስና ቅዳሜ ገበያ ውስጥ ጥይት እንደ ቆሎ ከሜዳ ላይ ይለቀማል፣ይሸጣል፡፡ እቃ እቃ የሚጫወቱ ህፃናት ቦንብ ቀጥቅጠው ዓይን እጅና እግራቸው ተቆራረጠ፣ ዓየር በዓየር  ንግድ ተጦጡፎል፣  ህገወጥ የጦር መሣሪዎች ዝውውርና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር  ከቁጥጥር ውጪ ሆኖል፡፡

{6} የውጭ ብድርን የመክያ ጊዜ እንዲራዘም መጠየቅ (Debt rescheduling):-

‹‹ የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ የክምችት አቅም እየተፈታተኑ ብቻ ሳይሆን በዓይነቱ ልዩ ወደሆነው የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም አገሪቱ እንድትገባ ካስገደዱ ምክንያቶች አንዱ በፍጥነት እያደገ የመጣው የውጭ ዕዳ ጫና ነው፡፡  የውጭ ዕዳ ጫናው በመንግሥት በጀት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የፈጠረ ብቻ ሳይሆን  ለልማት ሊውል የሚችል ገንዘብን ለዕዳ ጫና ማቃለያ እንዲውል አድርጎታል፡፡  የፕራይቬታይዜሽን የውጭ ምንዛሪ አቅም ከመፍጠር አኳያ የራሱ የሆነ አዎንታዊ ሚና ቢኖረውም መንግሥት የዲፕሎማቲክ መስመሩን በመጠቀም የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘም መጠየቅን እንደ አንድ አማራጭ ሊጠቀምበት ይገባል፡፡ በነገራችን ላይ እኤአ በ2014 ቦንድ  (Sovereign bond) በማቅረብ በከዓለም አቀፍ የቦንድ ገበያ የኢትዮጵያ መንግሥት አንድ ቢሊዮን ዶላር በብድር ማግኘቱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ከዚህ ቦንድ ሽያጭ የተገኘው ብድር አገልግሎቱ ለምን ጉዳይ ነው ? በአገሪቱ የብድር ጫና ላይ የሚያሳርፈው ጫና ምንያህል ነው? ይሄንን እንዴት መቌቌም ይቻላል? ተብው በሥራ አስፈፃሚው የተጠየቁት  የገንዘብ ሚኒስር ብድሩን በተመለከተ መንግሥት   ‹‹የተሸለ ዕይታ›› እነዳለው ጫናውም የሚያሰጋ መሆኑን ብድሩም  ሊጠናቀቁና ወደ ሥራ ሊገቡ ለደረሱ ለስኳርና ሌሎቸ የውጭ ምንዛሪ ሊያስገኙ የሚችሉ ፕሮጀክቶች የሚውል መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡ ይህ ብድር ለስኳር ፋብሪካዎች  ማጠናቀቂያ እንዳልዋለ ከጊዜ በኃላ ማወቅ ተችሏል፡፡››

  • የኢትዮጵያየገንዘብ ሚኒስቴር የዕዳ መግለጫ ሰነድ መረጃ መሠረት፤ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ ከጁን 30 ቀን 2021 እኤአ ድረስ4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ሆኖ መመዝገቡን ይፋ አድርጎል፡፡ አጠቃላይ የአገሪቱ የዕዳ መጠን በውጭ ምንዛሪ ሲሰላ ደግሞ 55.6 (ሃምሳ አምስት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ   የዕዳ መግለጫ ሰነድ ያመለክታል፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው አንድ አመት ባደረገው የብር ምንዛሪ ተመን ለውጥ ምክንያት የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በመውረዱ ፤ በብር የምንዛሪ ተመን ማሽቆልቆል ሳቢያ አጠቃላይ የአገሪቱ ውዝፍ እዳ በ221.5 (ሁለት መቶ ሃያ አንድ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኖል፡፡
  • ከጁን30 ቀን 2020 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ929 (አንድ ነጥብ ዘጠኝ መቶ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 918.9 (ዘጠኝ መቶ አስራ ስምንት ነጥብ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.01 (አንድ ነጥብ ዜሮ አንድ )ትሪሊዮን ብር ነበር፡፡ መንግሥት 64.03 (ስልሳ አራት ነጥብ ዜሮ ሥስት) ቢሊዮን ብር ወይም ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለውጭ አበዳሪዎች ከፍሎ ነበር፡፡
  • ከጁን30 ቀን 2021 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር ሆኖል፡፡መንግሥት በዘንድሮው በጀት አመት 73.1 (ስባ ሦስት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ብር ወይም 1.8 (አንድ ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ዶላር ለውጭ አበዳሪዎቹ ከፍሎል፡፡………………………………….………..(3)

{7} የፋይናንስ ሴክተሩን ሪፎርም ማድረግ:-

‹‹ የፋይናንስ ሴክተሩ ባለፈው ዓመታት በሀብት በትርፍና በቅር ብዛት ውጤታማ የሆነ እድገት አስመዝግቦል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተር ቴክኖሎጂ ዕድገቱ እዚህ ግባ የማይባል ከዚህ በተጨማሪ ‹‹ባህላዊ›› የባንክ አገልግሎቱና አሠራሩ  ሊቀየር  አልቻለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፋይናንስ ሴክተሩ በተለይም የመንግሥት ባንኮች አሳሳቢ ተግዳሮቶች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ይህ ጹሑፍ በሁለት የመንግሥት  ባንኮች ላይ በቻ ያተኩራል፡፡ (ቀሪውን ከድህረ ገፁ ላይ ያንብቡት) ››

  • የአብይአህመድ መንግሥት በአራት አመታት ውስጥ3 (ስድስት መቶ ዘጠና ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድሯል፡፡ ከእናት ባንክ እየተበደሩ አዲስ የእንጀራ እናት ባንኮች መክፈት የኦሮሙማ አዲሱ የባንክና ፋይናንስ ስልት ነው፡፡ ፅንሰ ሃሳቡን ለመረዳት ካሻህ እንደ አሸን የፈሉትን የዘር ባንኮች ቢዝነስ በማንነት ላይ የተመሠረቱ የኦሮሞ፣ አማራ፣ ሲዳማ ወዘተ የማንነት መታወቂያ እየሰጡ  የሚቆቆም የባንክ ስርዓት ነው፡፡ ከፌዴራል መንግሥቱ ስር ያሉ የክልል መንግሥቶች ይሄን የጥሬ ብርና ዘር የማንነት መታወቂያ በማደል የዘር ባንኮች በመመስረት ላይ ይገኛሉ፡፡
  • የብልፅግናመንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳ14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት ) ትሪሊዮን ብር ከብሄራዊ ባንክ ብድር ያለ ገደብ መበደር የኑሮ ውድነቱንና (ከ35 በመቶ እስከ 45 በመቶ) የዋጋ ግሽበቱን አባብሷታል፡፡ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደው የቀጥታ ብድር ጣሪያ  እስካልተወሰነ ድረስ የተዛባ ኢኮኖሚው ይቀጥላል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ላይ የአስራአምስት በመቶ ጭማሪ ተደርጎበት እንዲሸጡ መቆጣጠር ኃላፊነቱን በመዘንጋቱ የእቃዎች ዋጋ በእየለቱ ሲያሻቅብ ይታያል፡፡ ብሄራዊ ባንኩ የተቌቌሙት አዲስ ባንኮች በዘርና በኃይማኖት ላይ የተመሠረተ አክሲዩን ግዢ ሲፈፀም እያየ ዝም በማለቱ በዘር የተደራጁ ባንኮች እንደአሸን ፈልተዋል፡፡ ብሄራዊ ባንኩ በጦርነቱ ወቅት በህወሓትና በኦነግ ሸኔ ስለተዘረፉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አንድም ነገር ትንፍሽ ብሎ አለማወቁ የህዝብ ገንዘብ ሲዘረፍ ዝም ማለት አንድ ቀን ያስጠይቃል እንላለን፡፡
  • በህወሓትኢህአዴግ ዘመን ወጋገን ባንክ በኦዴፓ ብልፅግና ዘመን  ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ዘረኛና ተረኛ አወቃቀርና ጠባብ አመለካከት በመውጣት፣  የሃገሪቱን የባንክና ፋይናንስ ዘርፉ ዓለም አቀፍ  አሠራርና ተወዳዳሪነት የውጭ ባንኮችን አገር ውስጥ በማስገባት የክልላዊነትና የጠባብነት የባንክ አሠራር ጠራርጎ ማስወገድ ሳንወድ በግድ አለም አቀፍ ንግድ The World Trade Organization (WTO) ሥርዓት አባል ለመሆንና ለመሳተፍ የባንክ ዘርፉን በማዘመን የውጭ ባንኮች ማስገባት ግዴታ ሆኖል፡፡ The World Trade Organization (WTO) is the only global international organization dealing with the rules of trade between nations. At its heart are the WTO agreements, negotiated and signed by the bulk of the world’s trading nations and ratified in their parliaments. The goal is to ensure that trade flows as smoothly, predictably and freely as possible.
  • የኢትዮጵያንግድ ባንክ በ1934 ዓ/ም የዛሬ ሰማንያ አመት እንደተቌቌመ ታሪክ ይመሠክራል፡፡ ባንኩ 1700 (አንድ ሽህ ሰባት መቶ) ቅርንጫፍ ባንኮችና4 (ሠላሳ አንድ ነጥብ አራት) ሚሊዮን ደንበኞች አሉት፡፡ በተጠናቀቀው የ2013 ዓ/ም ሒሳብ አመት ከታክስ በፊት 20 (ሃያ) ቢሊዮን ብር ማትረፉን ያስታወቀ ሲሆን፣ አጠቃላይ የባንኩ ንብረት አንድ ትሪሊየን ብር ይገመታል፡፡ “The state-owned giant Commercial Bank of Ethiopia (CBE) has recorded total assets worth close to a trillion Birr, making it the country’s richest entity. The Bank’s management also announced that they have managed to register a record-breaking 20 billion Br in gross profits for the fiscal year 2020/2021.Jul 11, 2021…. Bank of Ethiopia currently has 1,700 branches and 31.4 million customers.”

ምንጭ

(1) https://online.fliphtml5.com/qhkn/nmft/ (ቅጽ 23 ቁጥር 1894 / እሑድ ሰኔ 17 ቀን 2010)

ሪፖርተር ጋዜጣ እሁድ ሰኔ 17 ቀን 2010ዓ/ም በዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ

(2) Ethiopia’s Top 10 Budget Expenditures in 2022-23 fiscal years – Business Info Ethiopia

(3) መንግሥት ከአገር ውስጥና ከውጭ የተበደረው ውዝፍ የዕዳ መጠን 2.4 ትሪሊዮን ብር ደረሰ/ ሪፖርተር ጋዜጣ / 1 ሴፕቴምበር 2021

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop