“በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመውን ግፍ፣ አማራ ፈፅሞት ቢሆን ኖሮ ስንት አኖሌ ሀውልት ይሰራ ነበር?” – አቶ ዮሐንስ ቧያለው

በኢትዮጵያ 3 አይነት ዜጋ አለ። አማራ በአሁኑ ሰዓት 3ኛ ደረጃ ዜጋ ነው። በወያኔ ጊዜ 2ኛ ደረጃ ዜጋ ነበር። አንደኛ ደረጃ ዜጋው ጊዜው የእኛ ነው የሚለው አካል ነው። ሁለተኛ ደረጃ ዜጋው ደግሞ ሌላው ብሄር ነው። በሶስተኛ ደረጃ የአማራ ህዝብ ነው። አሁን ላይ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ የሚኖረው ከሱዳን ስደተኞች፣ ከኤርትራ ስደተኞች፣ ከሶሪያና ከየመን ስደተኞች በታች ነው።
በጦርነት ጊዜ ያልተባለ፣ ከጦርነቱ በሗላም ያልተነሳ … ድንገት ሰሞኑን ፋኖ ከመከላከያ ላይ ጥቁር ክላሽ ቀማ የሚለው እንዴት መጣ? አትሞኙ፣ ይሄ አዲስ የአማራ ጥላቻ ትርክት እየተፈጠረልን ነው። ነባሩ ትርክት አልበቃቸው ስላለ ነው። የጥቁር ክላሽ ትርክት የመጣው፣ የኦሮሚያ ብልፅግና ተረኛ አመራሮችን ጥቁር ታሪክ ለመሸፋፈን ነው። በእነዚህ አመራሮች መሪነት አማራ ታርዷል። የ15 ቀን ህፃን ከእነ እናቷ ተገድላለች። ታዳጊ ህፃን ሁለተኛ አማራ አልሆንም ብላለች። ጥቁር ታሪካቸው ተዘርዝሮ አያልቅም።
በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመው ግፍ፣ አማራ ፈፅሞት ቢሆን ምን ይፈጠራል? ኦሮሚያ ውስጥ የታረዱትን ያህል፣ አማራ ውስጥ ሌላ ብሄር ታርዶ ቢሆን ምን ሊፈጠር ይችላል? ብላችሁ አስቡት። በበቀል አፀፋ ኢትዮጵያ የደም ጎርፍ ትሆን ነበር። ሀገር ሙሉ በሙሉ ይፈርስ ነበር። ስንት አኖሌ ሀውልት ይሰራ ነበር።
(አቶ ዮሐንስ ቧያለው – ፋኖነት በሚለው የመፅሐፍ ምርቃት ላይ የተናገረው)
ተጨማሪ ያንብቡ:  በአማራ ክልል ውስጥ በተካሄዱት ሰልፎች ላይ ለምን “በኦህዴድ” በተለይ በዶ/ር አብይ ክህደት ተፈፅሞብናል -

6 Comments

  1. I do not think these brain children of EPRDF , now renamed this or that ethnic group Prosperity Party have any credible political rhetoric and personalities . This guy particularly who was not courageous enough to speak his mind when Abyi was on a stage of the meeting of Prosperity and got himself elected is now barking a very cheap popularity rhetoric on the Amharas ! He is still sitting in that very dirty chair of the Amhara Regional State Council as a honorable representative but just feeding his good for nothing rhetoric which sounds very opportunistic and hypocritical ! If he is genuine enough about the untold sufferings of the people because of the criminal political system he belonged and still belongs to , he must show the people some sort of action including leaving the very dirty chair he is still sitting on; not just keep telling the the horrible story as if it is not the day to day life experiences of the people .

    I hate to say but I have to say that these types cadres are more dangerous than the ones whose political stupidity and crime is clear and straightforward !!!

    You members of this generation who are serious and determined enough to make a historic difference in making democratic system a reality must wake up and do something big and long lasting! You should not allow yourselves to keep being fooled by the very opportunistic and cynical cadres of a criminal political system !!!

  2. በመጀመሪያ ይሄንን በማውጣታችሁ ዘሐበሻን አመሰግናችኋለሁ።
    ቀጥሎ፤ አንባቢያንን ላሳስበው የምፈልገውን ልዘርዝር። ይሄን እንድጽፍ ያነሳሳኝ፤ ከላይ በእንግሊዝኛ የተሠጠው አስተያየት ነው። ጥቂት ሰዎች ራሳቸውን የኅብረተሰቡ ሚዛን አድርገው፣ በደልዳላ ሶፋቸው ተቀምጠው፣ የሂደቱ ሁሉ አድራጊ ፈጣሪ በመሆን፤ ሌሎች የሚያደርጉትን አስተዋፅዖ ማንቋሸሽ ወጋቸው ነው። “እኔ ምን ሠራሁ?” ብለው ራሳቸውን አይጠይቁም ወይንም በሚዛናቸው ላይ አያስቀምጡም። የአገርን ፖለቲካ ስንመለከት፤ ሁሉም ግለሰብ በአንድ ደረጃ አንድ የፖለቲካ አቋም ላይ አይደርስም። እንዳንዶች ቀደም ብለው ለትክክለኛው መንገድ ይሰለፋሉ። ሌሎች ደግሞ በራሳቸው ሰዓት ይደርሳሉ። ያን ጊዜ፤ ቀደም ብለው የተሰለፉት፤ አባሪ አገኘን፣ የጠላቶቻችን ቁጥር ቀነሰ፣ የኛ ቁጥር በዛ፣ የጠላቶቻችንን ተግባር ብቻ ሳይሆን የውስጥ አሰራራቸውንም ለኛ ዕውቀት የሚጨምር መጣልን፤ ብለው በአድናቆትና በፍቅር ይቀበሏቸዋል። ይህ ለተራቀቁት የጦርነት ዐቃጆች ብቻ የተሠጠ ሚና አይደለም። ማንኛችንም ብንሆን ይሄንን ልንረዳ ይገባናል።
    በቅዱስ መጽሕፍት የተመለከተውም፤ የጠፋን በግ ፍለጋ መሄ ነው። በደለኛን አለሳልሶና በቀላሉ ቀጥቶ መመለስና የመሳሰሉት ናቸው። እኔ የሃይማኖት ሊቅ ስላልሆንኩ ዝርዝሩን ወይንም ቀጥተና አባባሉን አላስቀመጥኩም። ሆኖም ግን፤ ከሌላው ወገን ወዳንተ ወገን የሚመጣን ማንኛውም ደጋፊ፤ እጅን ዘርግቶ መቀበል፤ ሃይማኖታዊ፣ ኅብረተሰባዊ፣ ፖላቲካዊ ፀጋ ነው።
    አቶ ቧያለው ዮሐንስ፤ የብልጽግናን ዕድገትና አሠራር ከማወቃቸውም በላይ፤ በውስጥ ያሉትን ሙሉ አባላት አቋምና የዕውቀት ደረጃ ያውቃሉ። በአማራም ሆነ በኦሮሞ ብልፅግና ያሉትን ግለሰቦች ደካማና በጎ ጎን ያውቃሉ። የርሳቸው ወደ ሕዝቡ ወገን መምጣት ታላቅ ድል ነው። እናም መታየትና መከበር ያለበት በዚህ ዐይን ነው። ርሳቸው ወደ ሕዝቡ በመምጣታቸው፤ ብልፅግና ተጎዳ የሕዝቡ ትግል ገዘፈ። መመርመር ያለበት፤ ከትግሉ አኳያ እንዴት ሊረዱ ይችላሉ? ነው። አንባቢያንን የምጠይቀው፤ ራሳችን ምን አድርገን ነው ሌሎችን፤ “ይሄን ያድርጉ ወይንም ያንን ያድርጉ ወይንም እንዲያ ነበሩ፣ እንዲህ ናቸው?” የምንለው?

  3. ልጅ እስከ መቼ፦
    በገባህና ባመንክበት መጠን የሰጠኸውን አስተያየትና ትችት አነበብኩት ።
    አመሰግናለሁ።
    የኢህአዴግ/የብልፅግና ካድሬዎች አንተ በአመንክበትና በተበረታታህበት አኳኋን (በተግባራዊ ይዘት) ቢሆን ኖሮ ትችቱን ከይቅርታ ጋር በተቀበልኩት ነበር። መከረኛው ህዝብም በታደለ ነበር። ምክንያቱም አንቅቶና አደራጅቶ እጅግ እየከፋ ከሄደው ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት መንጥቆ የሚያወጣው የእውነት መሪ (ፖለቲከኛ) ከሰማይ እርቆበታልና ። ግን አልተሳካለትም።
    እንደ ምኞት ቢሆነማ ኖሮ እነ ዮሐንስ ቧያለው በአሽከርነት ያገለገሉት ህወሃት/ኢህአዴግ በኦህዴድ/ኢህአዴግ (አሁን ኦህዴድ/ብልፅግና) ሲተካ አብይ አህመድ የተናዘዘው ኑዛዜ፣ የጠየቀው ይቅርታና የገባው ቃል እንኳን ለኢትዮጵያ በክፉ አገዛዝ ለተያዘ ህዝብ ሁሉ በተረፈ ነበር።
    የማሰቢያና ጊዜን ሁኔታን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ከምሁር ተብየ ጀምሮ የመማር እድል እስካላገኘው የአገሬ ሰው “ሙሴ ፣ ከሰማይ የተላከ የኢትዮጵያ መድህን ፣ ወዘተ” በሚል ውዳሴ አቅሉን (ሚዛናዊ ህሊናውን) በመሳቱ ምክንያት በሸፍጠኛ፣ ሴረኛ ፣ ፈሪና ጨካኝ ገዠ ቡድኖች (የኢህአዴግ አንጃዎች) የደረሰውና ማቆሚያ ያጣው አስከፊ መከራና ውርደት ለምንና እንዴት ትምህርት እንደማይሆነን ለመረዳት ያስቸግራል።
    እነ ዮሐንስ ቧያለውና ፀጋ አራጌ የነገሩንና የሚነግሩን ነገር ፈፅሞ አዲስና አስገራሚ ባይሆንም መናገራቸውን የሚጠላ ወይም የሚቃወም ጤናማ ሰው አይኖርም።
    ጥያቄው ዲስኩራቸው እስካሁን የተዘፈቁበትን ወንጀለኛ ሥርዓት (የፖለቲካ ካንሰር) በመሠረታዊነት ሊለውጥና ዴሞክረአራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን የሚያግዝ ነው? ወይንስ “ቢሚረንም ሃሳብን በነፃነት ማራመድ የውስጥ ዴሞክራሲያዊ ባህሪያችንና አሠራራችን ነው” የሚል የብልፅግናዎች ርካሽ የፖለቲካ ጨዋታ? ወይንስ ደግሞ በሥርዓቱና በህዝብ መከካል የሚደረግ የአድርባይነት ፖለቲካ ዳንስ?
    መቸም መሪሩን ሃቅ መጋፈጥ ሲያቅተን የሚቀናን ሰበብ እየደረደርን የመሸሽ ክፉ ልማድ ሆኖብን ነው እንጅ መሬት ላይ የነበረው ፣ አሁንም ያለው፣ እና በእውነተኛ ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እስካለተገታ ድረስወደ ፊትም የሚቀጥለው ግዙፍና መሪሩ እውነታ ይኸው ነው።
    ስንቱ ንፁህ የነፃነትና የፍትህ ተሟጋች ለምን ፃፍክብንና ተናገርክብን ተብሎ ህይወቱን እያጣ ባለበት ፣ በየማጎሪያ ቤት በሚሰቃይበት ፧ በፍትህ ስም የፖለቲካ ቁማር ሰለባ በሆነበት መሪር እውነታ ውስጥ ኦህዴዳዊያን/ኢህአዴጋዊያን /ብልፅግናዊያን እርስ በርሳቸው የተወራረፉና የተጨካከኑ የሚመስልና የሚያስመስል አጀንዳ እየሰጡ መሳቂያና መሳለቂያ አድርገውናል ።
    አብይ አህመድ በአስመራጭነትና በተመራጭነት በመራውና እጅግ የወረደ የፕሮፓጋንዳ ጋጋት በተስተጋባበት የብልፅግና ተብየ ጉባኤ ላይ ምላሱን ቆልፎ ከወጣ በኋላ ተወካዩ ነኝ በሚለው መከረኛ የአማራ ማህበረሰብ ላይ የእወቁልኝ አካኪ ዘራፍ ምን የሚሉት የተራማጅነት ፖለቲካ እንደሆነ ለመረዳት ይቸግራል።
    ከምር ለህዝብ የሚቆረቆር ሰው በእውን ከስህተቱ ከተመለሰ ለዘመናት ከተዘፈቀበትና ጨርሶ ሊድን ከማይችል የፖለቲካ ካንሠር ጋር ምን ያሽመደምደዋል?
    እዚያው ከአካፋዎች ጋር አካፋ ሆኖ ደርጊት አልባ “የቃላት ነጎድጓዴን ስሙልኝ” የማለት ፖለቲካ ጨርሶ ስሜት አይሰጥም።
    ከዮሐንስ ቧያለውም ሆነ ከፀጋ አራጌ አንድም ቀን ” ችግሩ የሥርዓት መበስበስና መከርፋት ችግር ስለሆነ የሚያስፈልገውም መሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ነው” የሚል የፖለቲካ ና የሞራል ደፋርነት ሰምቼ አላውቅም ። መላልሰው የሚነግሩን እነርሱ ተዘፍቀው የቀጠሉበት ወንጀለኛ ሥርዓት የሚያደርሰውን የመከራና የውርደት ዶፍ እየመጠኑና እየተጠነቀቁ እንጅ ከአስከፊው መከራና ውርደት ስለሚያወጣው መሠረታዊና ዘላቄ መፍትሄ አይደለም ።
    የገዳይና የአስገዳይ ሥርዓት ባልደረባ (የሥልጣን ወይም የጥቅም ተጋሪ ሆኖ) ህዝብ በፖለቲካ ምክንያት እንዲገደልና እንዲገዳደል ተደረገ እያሉ በሰላ አንደበት አካኪ ዘራፍ ማለት ፈፅሞ ስሜት የሚሰጥ የፖለቲካና የሞራል ስሜት የለውም።

  4. TG
    ሀሳብህ ጥሩ ነው ፡፤ ነገር ግን ሁሉም ነገር ቦታ ቦታ አለው፡፡ አሁን አቶ ዮሀንስ ቧ ያለውም ሆነ አቶ ጸጋ አራጌ የነበሩበትንና አሁንም ያሉበትን የፖለቲካ ድርጅት ስህተቶች ለህዝቡ ይፋ ማድረጋቸው ጉዳቱ ምንድን ነው??
    እንደዚያ ብለው ሀቁን በይፋ ማውጣታቸውና ህዝቡ አውቆተየኖረው ያለ ሀቅ ቢሆንም ይህንኑ ለህዝቡ የሚሰማቸውን በመናገራቸው ይሄዉና አንተም እኔም ሌሎችም በተለይም የአማራው ህዝብ ነገሩን ይበልጥ ሲያጤነውና ሲያስተነትነው ሲነጋገርበት እየተስተዋለ ነው፡ ታዲያ ጉዳቱ ምኑ ላይ ነው?? በእርግጥ አንተ እንዳልከው ከዚህም መረር ያለ አቋም ወስደውፓርቲያቸውንም ለቀው ወጥተው ….ወዘተ ምናምን ልትል ከጅሎሀል፡፡
    አሁን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ውስጥስ ሆነው ድርጊታቸው እዚያው ውስጥም ከዚያው ውጭምባለው ላይ ምን ሊያስከትል እንደሚችናን ምንስ እያስከተለ እነሆነ አስበሀዋልን፡፡
    የእነ አብይ አህመድ ተላላኪ ሆነህ ተንኮል አስበህ ነው ለማለት ቢያሰችግረኝም ድርጊታቸውን ሙሉ በሙሉ መንቀፍህ የጤና አልመሰለኝም፡፤ የእነርሱ አይነቶቹ ( ከአማራ ብልጽግና ውስጥ ሌላ ዮሀንስ ቧያለውና ሌላ ጸጋ አራጌ አይነቶች ማለቴ ነው) ይብዙልንና ይህንን የኦሮሙማ የተረኖችና የግፈኞች አገዛዝ በተገላገልነው ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share