የአማራ ሕዝብ ዐብይ ድክመት – መስፍን አረጋ

ጠላቴ ጠፍቶኝ ሳስስ በነፍሴ
ሁኖ አገኘሁት እኔው ራሴ፡፡

ጠላት \የሚገባው\ በደካማ ጎን ስለሆነ፣ የሽንፈት ምንጩ የራስ ድክመት እንጅ የጠላት ጥንካሬ አይደለም፡፡  ፈረንጅና ዐረብ ያልደፈረው ታላቁ የአማራ ሕዝብ በመጀመርያ በወያኔ አሁን ደግሞ በኦነግ ይሄን ያህል ሊዋረድ የቻለው በወያኔም ሆነ በኦነግ ጥንካሬ ሳይሆን በሱ በራሱ ድክመት ብቻ ነው፡፡  የአማራን ሕዝብ ለወያኔና ለኦነግ ጥቃት ያጋለጡት ድክመቶች በርካታ ሲሆኑ፣ ከነዚህ ድክመቶች ውስጥ አንዱና ዋናው ደግሞ ዋና ጠላቱን ለይቶ አውቆ በዚሁ ዋና ጠላቱ ላይ ዋና ትኩረቱን አለማድረጉ ነው፡፡

መለስ ዜናዊ የአማራን ሕዝብ ለሩብ ክፍለዘመን ያህል ሊቀጠቅጥ የቻለው፣ ወያኔን በማጠናከር ሳይሆን አማራን በማዳከም ነበር፡፡  ምክኒያቱ ደግሞ ወያኔ የጠነከረውን ያህል ቢጠነክርም ያልተዳከመን አማራ ሊቀጠቅጥ ቀርቶ ሊቆነጥጥ እንደማይችል በደንብ ስለሚያውቅ ነበር፡፡  ወያኔን ያጠናክሩለት የነበሩትን ወያኔወቹን ኃየሎም አርአያን፣ ሰየ አብርሃን፣ ገብሩ አስራትንና መሰሎቻቸውን ባንድም በሌላም መንገድ አስወግዶ፣ አማራን የሚያዳክሙለትን ብአዴኖቹን አዲሱ ለገሰን፣ ተፈራ ዋልዋን፣ በረከት ስምዖንንና መሰሎቻቸውን ቁልፍ ሰወቹ ያደረጋቸውም ለዚሁ ዓላማው ሲል ብቻ ነበር፡፡

የዘመኑ የአማራ ሕዝብ ዋና ጠላት ደግሞ ሌላ ማንም ሳይሆን የወያኔና የኦነግ ዲቃላ የሆነው ጭራቅ አሕመድ ነው፡፡  ይህ ጭራቅ አማራን በልቶ ለመጨረስ ቆርጦ የተነሳው፣ ልክ እንደ አባቱ እንደ መለስ ዜናዊ አማራን በማዳከም ነው፡፡  ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ ኦነጋዊ አራጅ ሠራዊቱን ያጠናከረውን ያህል ቢያጠናክረውም አማራ ካልተዳከመ ግን የአማራን ሕጻናት ሊያርድ ቀርቶ ዝንባቸውን እሽ ሊል እንደማይደፍርና፣ እደፍራለሁ ካለ ደግሞ የሸዋ ፋኖ ብቻ ልክ እንደሚያስገባው ስለሚያውቅ ነው፡፡  ስልጣን ከያዘበት ዕለት ጀምሮ ሙሉ ትኩረቱን ያደረገው አራጅ ሠራዊቱን የሚያጠናክሩለትን ኦነጋውያን በማሰባሰብ ላይ ሳይሆን፣ አማራን ያጠናክሩብኛል ብሎ የሚፈራቸውን ሰወች በመበታተን ላይ የሆነበትም ምክኒያት ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማን ምክር ጠየቃቸው? - መርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

ስለዚህም የአማራ ሕዝብ መዳኛው መንገድ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡  እሱም ተሟሙቶም ቢሆን ጭራቅ አሕመድን በማናቸውም መንገድ ባስቸኳይ ማስወገድ ነው፡፡  መለስ ዜናዊ ሲከፈን፣ ወያኔ እንደ በነነ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድም ሲወገድ፣ ኦነግም ዐመድ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ባስቸኳይ ጨርቅ ካደረገ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ ሆይ!

ሊገልህ የመጣን ዐልመህ በተለይ

መምታትህን እንጅ ወሳኝ ብልቱ ላይ፣

ጭራሽ አያሳስብህ የመሞቱ ጉዳይ፡፡

በታችም በምድር በላይም በሰማይ

ወንጀለኛ አይደለም አልሞት ባይ ተጋዳይ፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

1 Comment

  1. ችግሩ የአማራ ህዝብ ብቻ አይደለም። የመላ ሃገሪቱም ጭምር እንጂ። ሲጀመር የሃበሻን ህዝብ ማስተዳደር እጅግ ከባድ ነው። ያው አሁን ደግሞ ሰው በዘሩ እየተመነዘረ የሚገደልበት፤ የሚታሰርበት፤ የሚባረርበትና የክፋት ልክ ጣራ የወጣበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። በዘርና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ የክልል ፓለቲካ የሁሉን ዓይን ከእውነት አርቆታል። ለእኔ እንጂ ለእኛ ማለት ቀርቷል። በዚያው ልክ ለሞቫይልና ለአላቂ ቁሳቁስ የሰውን አንገት የሚቀሉ፤ ወላጆቻቸውን የሚዘርፉና የሚገሉ ጉዶች እያበቀለች ያለች ሃገር ናት። የምድሪቱ መናወጥ መሰረቱ ስር የሰደደ ነው። መፍትሄውም በቀላሉ የሚፈታ አይደለም። ከምናየውና ከምንሰማው ይልቅ እንደ ምስጥ ሥር ስሩን የሃገራችንና የህዝባችን አንድነት የሚንድ ሃይሎች በሙሉ ጉልበታቸውና ሃብታቸው ተሰልፈዋል። እነዚህ ሃይሎች በአንድ በኩል አስታራቂ መስለው እየቀረቡ ክብሪትና ነዳጅ እያቀበሉ ሲያገድሉን ኖረዋል ዛሬም ያ እቅዳቸው አልተቀየረም። አሁን ላለው የክልል ስጡኝ ጋጋታም ዋናው የእኛው የጠባብ ብሄርተኝነት ህሳቤና የኢትዮጵያን አንድነት የማይሹ ሃይሎች ያሰመሩት የክፋት መንገድ ነው። እኛ ግን አልነቃንም። የቀረበልን ስንጋትና በዚያው ሳቢያ ህዝባችን ስናስጨንቅ ዘመናት ቆጥረናል።
    የአማራን ህዝብ ያደነዘዘው በላዪ ላይ የሚወርደው ያላሰለሰ መከራና ሰቆቃ ነው። በንጉሱ፤ በደርግ፤ በወያኔ እንዲሁም አሁን በብልጽግና ሃበሳውን የሚቆጥረው ይህ ጨቋኝ፤ ቅኝ ገዢ፤ ነፍጠኛ እየተባለ የሚጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ ነው። በተለይ ሻቢያና ወያኔ ለችግራቸው ሁሉ ምንጩ የአማራ የበላይነት ነው ብለው ህዝባቸውን ስላሳመኑ ጥላቻው ሰማይ ነክቶ መሬት ላይ ወርዶ አሁን የኦሮሞ የዘርና የቋንቋ ፓለቲከኞችን አንገት በጣሽና ነፍሰጡር ገዳይ አድርጓቸዋል። እውቁ የፓለቲካ ሰውና እውነተኛው ኢትዮጵያዊ አቶ አሰፋ ጫቦ በአንድ ወቅት እንዳለው ኢትዪጵያን የማፍረክረክ ሴራ “በሻቢያ የበላይነት ኦነግን አልፎ ተርፎም ወያኔን ያካተተ ነው” ብሎ ነበር። ይህን ወደ ኋላም ሆነ ወደፊት ተራምዶ ነገሮችን ለመረመረ እውነት ነው። የወያኔ በጉልበት መሬትን እየቀማ ካርታውን ማስፋት፤ ኦነግ ከኤርትራ ወደ ሃገር ሲመለስ መቀሌ ላይ ወያኔ ያደረገላቸው አቀባበል አሁን ኦነግ ሸኔ ለተባለው ድርጅትና ለሌሎችም ተለጣፊ ሃይሎች በቀጥታና በስውር የሚደረገው ድጋፍም ከዚህ እውነታ ጋር ይገናኛል። ታዲያ በዚህ ሁሉ ሴራ የአማራ ህዝብ “ኢትዮጵያ” በማለት ለሃገሩ ያለውን ያለውን የማይናወጥ አቋም ተገንጣይና አስገንጣይ ሃይሎቹ ያኔም አሁንም አይወድለትም። ስለዚህ ይህ ህዝብ ተነጥሎ እንዲመታ የተፈረደበት ህዝብ ነው።
    ስለሆነም ወንድሜ መስፍን – የአማራ ህዝብ ራሱን ከሊቅ እስከ ደቂቅ አሰልጥኖ የሚመጣበትን ወረራ መከላከል እስካልቻለ ድረስ አሁን በአማራና በአፋር ክልል ወያኔ ሆን ብሎ ያወደመውን መልሶ ለመገንባት የሚደረገው ሩጫ ሁሉ ዋጋ ቢስ ነው። ለዳግመኛ ወረራ የሚዘጋጀው ወያኔ ባለበት ማቆም እስካልተቻለ ድረስ የዳግም ወረራቸው ከበፊት የከፋ እንደሚሆን ከአሁኑ መገመት ይቻላል። ልክ ነህ “አልችልም” ከማለት ይልቅ ራስን እና ቤተሰብን ከመከራ ለማዳን የጠላትን የጦርነት አቋምና ትጥቅ ስሪትና እቅድ ቀድሞ ማወቅ አስፈላጊ ይሆናል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በዚህ ህዝብ ላይ ለሚደርሰው መከራ ፈጣሪም ሆነ ሌላ ሃይል ተጠያቂ አይሆኑም። ጊዜ እያለ መዘጋጀት፤ መታጠቅ፤ መተባበርና የቅንጅት ጥምረት አስፈላጊነት ከምንጊዜም በላይ ዛሬ ተፈላጊነቱ ጎልቶ ይታያል። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share