July 27, 2022
2 mins read

ፍርድ ቤቱ የታዴዎስ ታንቱን የክስ መቃወሚያ ሳይቀበል ቀረ

294302855 5401020023294611 5806656652684659572 n
294302855 5401020023294611 5806656652684659572 n
አዛዎንቱ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሐፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ዛሬ ረቡዕ ሀምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ችሎቱ ለዛሬ ቀጥሮ የነበረው የክስ መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ እና ፖሊስ ሁለተኛ ተከሳሽ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን በተገኘበት አስሮ እንዲያቀርብ ነበር። ሆኖም በከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ተቃውሞ የክስ መቃወሚያቸውን ማቅረብ አለመቻላቸውን ጠበቃቸው አቶ አዲሱ ጌታነህ ገልጸዋል። ዓቃቤ ሕግ ሁለተኛ ተከሳሽን ፖሊስ ፈልጎ እስከ አሁን አለማግኘቱን ጠቅሶ ጌጥዬ ያለው ሳይያዝ የክስ መቃወሚያቸውን እንዳያቀርቀቡ በማለት ተቃውሟል።
ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ የፊታችን ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ረፋድ 4 ሰዓት ላይ የክስ መቃዎሚያቸውን አባሪያቸው ሳይያዝም ቢሆን እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የፌዴራል ፖሊስ እስከ ነሐሴ 2 ጌጥዬ ያለውን በተገኘበት አስሮ እንዲያቀርብም አዝዟል። በዚህ ዕለት ይዞ ካልቀረበ ግን ሁለተኛ ተከሳሽ እንዲሰናበት ወይም በሌለበት ዶሴው እንዲቀጥል ብይን እንደሚሰጥ ገለጿል።
የታዴዎስ ታንቱ የክስ መቃወሚያ እንዳይቀርብ ሲስተጓጎል ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም የክስ መቃወሚያቸውን በሚያቀርቡበት የቀጠሮ ቀን ችሎቱ ቢሰየምም ፖሊስ ሳያቀርባቸው በመቅረቱ ተስተጓጉሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋሽ ታዴዎስ ነገ ሀምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይቀርባሉ። በዚህም ችሎቱ የእስር ፍርድ ቤቱ የፈቀደላቸውን የ15 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ያጸናል ወይም ይሽራል።

ዜና —  ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ 

1 Comment

  1. አረ ግፉ በዛ ዶ/ር አብይ ብቻህን ስትሆን እራስህ ጋር ፍልሚያ ሳትገጥም አትቀርም ስብሃትና ጓደኞቹን ለቅቀህ እኝህን ምስኪን አዛውንት ማንገላታት ምን የሚሉት ነው ይህ ግፍ ተጠራቅሞ ሊያመጣ የሚችለውን ሳትረዳው አትቀርም። ሃገርና ህዝብን የዘረፉ፤የገደሉ፤ያዋረዱ እያሉ እንደ አቶ ታዲዮስ ታንቱን አይነት ዜጋ በክብር ማስቀመጥ ሲገባህ ማንገላታት ምን ይሉታል? አይ የኢትዮጵያ ባለ ስልጣናት ምን ብንበድል ነው እናንተን የመሰሉ ሹመኞችና ባለ ስልጣናት አምጥቶ የዘራብን። አሁን ማን ይሙት የ ሓይለ ስላሴን ዘመን እንተወው በደርግ ዘመን ታከለ ኡማ፤አዳነች አቤቤ፤ታየ ደንዳ፤ሽመልስ አብዲሳ፤ አረጋዊ በርሄ፤ብርሃኑ ነጋ ፤ቀጀላ መርዳሳ፤ ….. እንኳን አሁን ላሉበት ስልጣን ቀርቶ የመዘገብ ቤት ሃላፊነት ይበዛባቸው ነበር አገሪቱ በዘር መሸንሸኗ ለንደዚህ አይነት የአእምሮ ድኩማን ስራ እንዲያበላሹ አገር እንዲገድሉ ሁኔታውን ያመቻችላቸዋል። አጼ ሐይለ ስላሴ የሚሆንላችሁ ከሆነ ደህና ነገር ግን ይህ አገር በትልቅ ጥበብ ላይ ነው የቆመው ብለው በመጨረሻው ሰአት ስጋታቸውን እንደገለጹት ዛሬ ማይክ ይዘው አዳምጡን የሚሉት ጁዋር መሃመድ፤አዳነች አቤቤ፤መአዛ ቅጣው፤አገኘሁ ተሻገር፤ስዩም ተሾመ፤ አጎቱ ዳውድ ኢብሳና መሰሎቻቸው በመሆኑ ለነገሩ ምክንያት ከመፈለግ ፊታችንን ወደ ፈጣሪ እንድናዞር የማስጠንቀቂያ ደወል ይመስላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Abiy 71
Previous Story

ንስሐ በሌለበት የሚያርግ ምስጋና የለም – ዓባይነህ ካሤ – ዲን

176295
Next Story

አብይና መግለጫው – አብይና ተግባር

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop