ኢትዮጵያ በአለም ሻምፒዮናው እስካሁን 10 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በ2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

ኢትዮጵያ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች 4 የወርቅ፣4 የብር እና 2 የነሐስ ሜዳሊያ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ማጠቃለያ እለት በሚጠበቁት የሴቶች 800 ሜትር እና ወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜዎች ላይ ተጨማሪ ሜዳሊያዎች ልታገኝ የምትችልባቸው ውድድሮች ዛሬ ሌሊት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳሉ።
በወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ ኢትዮጵያን የሚወልኩት አትሌት ሙክታር ኢድሪስ፤አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና አትሌት ሰለሞን ባረጋ ሲሆኑ ውድድራቸውን ከሌሊቱ 10 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ጀምሮ ያካሂዳሉ።
በማጣሪያው ድንቅ ብቃቷን ያሳየችው የ800 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ተወካይ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በበኩሏ ውድድሯን ከሌሊቱ 10 ሰዓት ከ35 ጀምሮ የምታካሂድ ይሆናል።
ኢዜአ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ስፐርስ ቤልን ለማቆየት እቅድ ይዟል

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share