February 17, 2015
35 mins read

ስለ ዐምሐራ ህዝብ አሰያየምና ትርጉም – በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደኢየሱስ

ስለ ዐምሐራ ህዝብ አሰያየምና ትርጉም ልታዉቁት የሚገባ እዉነተኛ ታሪክ ይህ ነዉ ፡፡ በዚህም የታሪክ አጠራር ምክንያት የአገዉ ህዝብ የሆኑት ህምራ ፤አዊ፤ ቅማንት፤ፈላሻና ብሌን ከ13ተኛዉ ክ.ዘ ጀምሮ በክርስትና እምነት መቀበላቸዉና መጠመቃቸዉ ምክኒያት እንዴት ዐምሐራ ተብለዉ ይጠሩ እንደነበር ያሣያል፡፡ “ዐምሐራ” የሚለዉ ቃል መልእክትና ትርጉም ባለዉ ምክንያት በኢትዩጵያ ምድር ለሚኖረዉ ለአብዛኛዉ የአገሪቱ ነባር ህዝብ የተሰጠ ትዉፊታዊ ስያሜ ነዉ፡፡ ቃሉ ከግዕዝ ተገኝቷል፡፡ በግዕዝ “ዐም” ማለት ሕዝብ ሲሆን “ሐራ” ማለት ደግሞ ነጻ ማለት ሲሆን “ዐምሐራ” የሚለዉ የቃል ለቃል ትርጉም “ነጻ ህዝብ” ማለት ሲሆን ይህም ትርጉም የእዉነተኛ ኢትዩጵያዊን ማንነት ከሚገልጹት ዓበይት ባሕሪያት መካከል አንዱ መሆኑን በግለጽ ያመለክታል፡፡ በአጠቃለይ ቅዱስ ኪዳነ ሃይማኖት እየተማሩና እያወቁ በፈቃዳቸዉ ሲገረዙና ሲጠመቁ ዐምሐራ ወይም ክርስቲያን እየተባሉ የእግዚአብሄር ህዝብ ሆኑ፡፡ በዚያ ጊዜ ያ ግለሰብ ዐምሐራ ሆነ ይባልል፡፡ ነፃ ወገን ሆነ ማለት ነዉ ሲሆን ነፃነቱም ከባዕድ አምልኮ ከዲያብሎስና ከሰዉ ተገዥነት ፤ከኃጢያት ቀንበር ከሞት ባለዕዳነት ተላቅቆ በእግዚአብሄር ልጅነት ለመኖር መብቃት ነዉ፡፡ ቋንቋዉን ፊደሉም ይኸዉ ኢትዩጵያዊ ህብረተሰብ ተስማምቶ የፈጠረዉ ዐምሐርኛ ወይ ኢትዩጵያኛ ይሆናል፡፡
ethiopia flag mapግዕዝ ራሱን የቻለ ፊደል ያለዉ የኢትዩጵያዉያን የመጀመሪያ እናት ቋንቋቸዉ መሆኑ በዓለም ሕዝቦች ዘንድ ሳይቀር በይፋ የታወቀ ነዉ፡፡ የዐምሐራዉ ኅብረተሰብ መነጋገሪዉ ያደረገዉ ቋንቋ ዐምሐርኛ ተብሏል፡፡ የዚህ ኅብረተሰብ የቃል ብቻ ሳይሆን የጽሕፈት መገናኛዉ ጭምር የሆነዉ ይህ ልሳን ግንድ ቢሆንም በጋብቻና በልደት እንደተዋሃደዉ እንደቋንቋዉ ባለቤት ሁሉ ዐምሐረኛም ብሄር አቀፍ ሁኖ በሃገሪቱ ዉስጥ በሚነገሩት አያሌና የተለያዩ በሆኑ ልሳናት ራሱን ሲያበለጽግ የኖረ ቋንቋ መሆኑ የቃላቱ ቤተ-መዛግብት ያረጋግጣል፡፡ ዐምሐራ የሚለዉ ስም ለምሳሌ አገዉ፤አርጎባ፤አፋር፤ኦሮሞ፤ጉራ፤ጋፋት፤ሓዲያ፤ ወላይታ፤ከምባት፤ ኩናማ ወይም ትግሬ እንደሚባለዉ በየጎጣቸዉና በየክልላቸዉ በየእምነታቸዉና በየቋንቋቸዉ ተለያይተዉና ተወስነዉ በየስማቸዉ እንደሚታወቁት ብሄሮች ወይም ሴማዉያን ፤ካማዉያን ያፌታዉያን ተብለዉ በመላዋ ምድር ተሰራጭተዉ እንደሚኖሩት እንደሦስቱ የሰዉ ዘር የትዉልድ ቅርንጫፎች ይህም ኅብረተሰብ “አንድ ነጠላ ጎሳ ወይም ነገድ ነዉ” ተብሎ ለእርሱ መለያና መታወቂያ ይሆን ዘንድ የተሰጠ ስያሜ አይደለም፡፡ በሌላ አገላለጽ ዐምሐራ የአንድ ጎሳ ወይም የአንድ ነገድ ወይም የአንድ ዘር ወገን አይደለም ማለት ነዉ፡፡ የቃሉ ፍቺ እንደሚያመለክተዉ ዐምሐራ በኢትዩጵያ ምድር የሰፈሩ ፤ከተለያዩ ጎሳዎች፤ነገዶች፤ዘሮች፤ ቋንቋዎች፤ባህሎችና ሃይማኖቶች የተዉጣጡ ወንዶችና ሴቶች እርስ በርሳቸዉ በመጋባት በሥጋ አንድ የሆኑበት ህልዉና ነዉ፡፡ በመንፈስ ቀድሞ በኪዳነ ልቦና ፤ቀጥሎ በኪዳነ ኦሪት፤ በመጨረሻም በኪዳነ ምህረት የክርስትና ተዋህዶ ሃይማኖት ከእግዚአብሄር በመወለድ ስጋቸዉና ነብሳቸዉ እነርሱም ሁላቸዉ በአንድ መንፈስ ቅዱስ ፍጽም አንድ የሆኑበት ህይዎት ነዉ፡፡ በአጠቃላይ ኢትዩጵያዊነት የተባለዉን ዘላለማዊ የህልዉና ዓላማ በሕያዉነት ከግብ ለማድረስ መለኮታዊዉ ጥሪ በፈቃዳቸዉ ተቀብለዉ ለእርሱ በጋራ ቃልኪዳን የገቡና ለሰዉም ሆነ ለዲያብሎስ ተገዢ ከመሆን ነጻ ወጥተዉ በእግዚአብሄር ሕገ መንግስት በእኩልነት ፍትሕ በመምራት እየተዳደሩ እንደ አንድ ቤተሰብ የሚኖሩበት ስርዓት ሃገር ነዉ፡፡ ዐምሐራዉ ከላይ እንደተገለፀዉ የእኒያ እያንዳንዳቸዉ የየግላቸዉ ብሔረኝነትና ጎሠኛነት ፤አምልኮና ልሳን በፈቃዳቸዉ ትተዉ ኢትዩጵያዊነትን ከፍጹም ሁለንተናዉ ጋር በፈቃዳቸዉና በሃይማኖት የተቀበሉ ፤ የኢትዩጵያ ጥንታዉያን ባለገሮች ኅብረተሰብ ስለሆነ ቀጥሎ ባለዉ ሐተታ እንደሚያብራራዉ ይህ ኅብረተሰብ እዉነተኛዉ ኢትዩጵያዉ ሆኖ ለመገኘት በቅቷል፡፡ እንግዲህ ማንኛዉም ግለሰብ ወንድ ሆነ ሴት በዚህ ኢትዩጵያዊነት አምኖ የዚህ ኅብረተሰብ አባል ለመሆን በፍጹም ነፃነት ፈቃደኛ ሲሆን የሚፈጸምለት ስርዓት አለ፡፡ ይኸዉም ከመንፈስ ቅዱስ ህይዎት የሚያበቃዉን ፀጋ የሚጎናጽፍበት ልዩ ስርዓት ነዉ፡፡
እርሱም በሃይማኖት እዉቀት በእዉነተኛ ንስሓ በክርስትና ጥምቀትና በቅዱስ ቁርባን ምስጢራ ይፈጽማል፡፡ ለዚያ ግለሰብ ይህ ስርዓት እንደተፈጸመለት ወዲያዉኑ ያ ግለሰብ ዐምሐራ ሆነ ፤ ክርስቲያ ሆነ ወይ ኢትዩጵያዊ ሆነ ማለት ነዉ፡፡ ዐምሐራነት በኃላ በስጋ ጋብቻ ጭምር እስኪዋሃዱበት ድረስ በቅድሚያ እንዲህ በመንፈስ የሚወለዱበት ስለሆነ ጎሳ ወይም ብሄር አለመሆኑ በዚህ ይታወቃል፡፡ በዚህ ጌዜ ያ ግለሰብ ኢትዩጵያዊነት በሚያስተማምን ቃል ኪዳን ለዘላዓለም የሚያጎናፅፈዉን ያን በመለኮታዊ ፀጋ የተገኘዉን ሰብዓዊ ነፃነት እንዳይቀዳጅ ከልክሎት ከኖረዉ ከጠባብ ብሄረኝነትና ከጎሠኝነት ከቋንቋና ከአምልኮ ባዕድ ቁራኝነት፤ ከአጓል አስተሳሰብም ቀምበር ተላቅቆ ከእዉቀት ብርሃን የወጣለትና የነፃነትን አክሊል የተቀዳጀዉ ኅብረተሰብ አባል ለመሆን የበቃ ይሆናል፡፡ ይህ ዐምሐራ የመሆን ምሥጢር ኢትዩጵያዊ ከመሆን ጋር የሚመሳሰልና እንደ ኢትዩጵያዊነት ሁሉ ያልተቋረጠ ትንግርታዊ ሂደት ያለዉ ሆኖ ኖርዋል፡፡ ዐምሐራ ሆነ ማለት ከላይ እንደተወሳዉ ኢትዩጵያዊ ሆነ እንደማለት ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ በፍጥረት ዓለሙ ዘንድ በይበልጥ እዉቅና እንዳገኘዉና በመጨረሻ ዘመን የሰዉን ዘር እንደገና አዋህዶ ፍጽም አንድ እንደሚያደርገዉ እንደ አዲስ ኪዳኑ ስያሜ ክርስቲን ሆነ ማለትም ነዉ፡፡ በዚህ መሠረት ዐይነተኛዉ (ማለት አማናዊዉ ወይም እዉነተኛዉ) ዐምሐራ ይህም ዐይነተኛዉ ኢትዩጵያዊ ወይም ዐይነተኛዉ ክርስቲያንም፤ ዐይነተኛዉ ዐምሐራ ነዉ፡፡እንዲህ ከሆነ እነዚህ ሶስት ስያሜዎች ማለትም ዐምሐራነት፤ ኢትዩጵያዊነት እና ክርስቲያንነት በምስጢርና በትርጓሜ ይዘታቸዉ አንድ ሌላዉን ሊተካ የሚችል የተመሳሳይነትና የተወራራሽነት ባሕርይ ያላቸዉ ቃላት መሆናቸዉ በግለጽ ይረጋገጣል፡፡ ለዛሬዉ ኢትዩጵያዊ ትዉልድ የዘር ግንድ የሆነዉ የጥንቱ የዐምሐራ ኅብረተሰብ የኢትዩጵያ ነባር ባለገሮች ከሆኑ ኀዳጣን (ቁጥራቸዉ አናሳየሆነ) እና ብዙኃን ( ቁጥራቸዉ በርካታ የሆነ) ብሄረሰቦች ተዉጣጥቶና ተዋሕዶ የተገኘ መሆኑ ከላይ ተመልክቷል፡፡ የዚህ ጥንታዊ ኅብረተሰብ አባሎች የሆኑት እንያ አባቶችና እናቶች ለቅዱስ ኪዳን አምላክ ለልዑል እግዚአብሄር ፈቃድ ራሳቸዉን በሐይማኖት በማስገዛት ዘላለማዊ በረከትና ፀጋ ለልጅ ልጆቻቸዉ እንደሚያቀዳጅ የተማመኑበት የኢትዩጵያዊነትን መሠረት በበለጠ አጽንተዉ ለመቀጠል በስምምነት የሠጡት ዉሳኔና ዉሳኔዉን በስራ ላይ በማዋል የፈጸሙት ገድል ለዚህ ግዳጃቸዉ ከከፈሉት መስዋዕትነት ጋር እጅግ ብልሆች ፤አርቆ አስተዋዩችና ቆራጦች ለመሆናቸዉ በቂ ማስረጃ ሆኗቸዋል፡፡ እስቲ ዛሬ የትኛዉ ኢትዩጵያዊ ነዉ ወየም ከላይ በጥቂቱ በተወሱትና ከየራሳቸዉ ጠባብ ብሄረኝነት ጋር ተቆራኝተዉ በሚገኑት ጎሳዎች ዉስጥ አባል ከሆነዉ ግለሰብ መካከል እንኳ ሳይቀር የትኛዉ ነዉ እንኳንስ ከአንድ ነጠላ ጎሳ ይቅርና ከሁለት ወይ ከሶስት ጎሳዎች ብቻ የተወልድኩ ነኝ በማለት በሙሉ አፉ ደፍሮ ሊናገር የሚችል? ማንም ሊኖር ከቶ አይችልም፡፡
ምክኒያቱም ያ ኢትዩጵያዊ ወይም የጎሳ አባል ወንድ ሆነ ሴት በወላጆቹ የትዉልድ ግንድ በኩል በጥቂቱ ወደ ኃላ ሄድ ብሎ አያቶቹን፤ የቅድማያቶቹንና የምንዝላቶቹን የዘር ሐረግ ቢስብ ራሱን የኅብረብሄር ፍሬ ማለት አያሌ ጎሳዎች የተዋሃዱበት ቅይጥ ፍጡር ሆኖ ያገኘዋል፡፡ ዐምሐራ ወይም ኢትዩጵያዊ ከሚያሰኙት ዓበይት ባሕሪያት መካከል ደግሞ ይህ የኅብረ ብሄር ፍሬነት አንዱ አይነተኛዉ ባህርይ መሆኑን በትኩረት መመልከት ነዉ፡፡ የዚህ እዉነት አማናዊነትና እርግጠኝነት ባሁኒ ጊዜ በኢትዩጵያ ምድር እንዲሁም በሃገር ዉስጥ በሚኖሩትና በዉጭ አህጉር ተበትነዉ በሚገኙት ኢትዩጵያዉንና ኢትዩጵያዊዉያን ዘንድ ሰፍኖ በሚታየዉ ሁኔታ ጎልቶና ገዝፎ ይታያል፡፡ ይህዉም ዓይነተኛዉ ( እዉነተኛዉ) የዐምሐራዉ ኅብረተሰብ ኢትዩጵያ በእግዚአብሄር መንግስትነት ስር ተዋህዳ የኖረች የማትከፋፈል አንዲት አካል መሆኑን በማመን በጎሳ ወይም በዘር መለያየትን የሚቃወም በመሆኑ ነዉ፡፡ እንዲያዉም ኢትዩጵያዊነት ከዚህ የበለጠና የመጠቀ የጠለቀ ፤የሰፋም ባህርይ አለዉ፡፡ ይኸዉም ለኢትዩጵያ እንዲሁም ላለፉትና ለዛሬዎቹ ወደፊቶቹም ኢትዩጵያንና ኢትዩጵያዉያት ብቻ ላይ ተለይቶና ተወስኖ የተሰጠ፤ እየተሰጠ ያለና የሚሰጥም አለመሆኑ ነዉ፡፡ ስለሆንም ዐምሐራን በመላዉ ዐምሐራ ወይም በሃገር አቀፍ ደረጃ አማራ ክልል ማለት ዐምሐራን ከመሠረታዊ የኢትዩጵያዊነት ባሕር አዉጥቶ እንደ ጎሣ ማስቆጠር የኢትዩጵያ የደም ጠላቶች በሚያዉጠነጥኑት ሴራና በሚያካሄዱት ዘመቻ ዉስጥ ተባባሪ ደጋፊና መሣሪያ መሆን በግለጽ አረጋግጦ የሚያሳይ የክህደትና የአመጽ ተግባር በመሆኑ ነዉ፡፡ ስለዚህ ዐምሐራ ኢትዩጵያዊነትን ሕያዉ ለማድረግ ለመጠበቅና ለማስፋፋት በድርጅታዊ ሆነ በብሄራዊ ደረጃ የሚታየዉን የተዛበ አሠራርና ጉዳይ የሚመለከታቸዉ ወገኞች በሙሉ በብሩቱ አስበዉበት ስለ እዉነተኛ ኢትዩጵያዊነት ዐምሐራ ማስተካከልና ማብቃት ይገባቸዋል፡፡

አማራ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አማራ ዐማራ የሚለዉን ቃል ብዙዎች የተለያየ ግን ተዛማጅ የሆነ ትርጉም ይሰጡታል፡፡ ከነዚህም መካከል አለቃኪዳኔ ወልድ ክፍሌ- ነጻና ጨዋ ህዝብ ማለት ነዉ ሲሉ ከሳቴ ብርሃን ተሰማ ጨዋ፣ የተመረጠ፣ ነጻ ሕዝብ፤ትርጉሙም አም-ሕዝብ፤ሀራ(ሁር) ምርጥ፤በጥምሩ ዐምሀራ ማለት-ነፃ ሕዝብ፤ በራሱ መገዛት እንጅ የሌሎች ተገዠ የማይሆን ሰዉ ይላሉ፡፡ ሀድሰንና ተከስተ ነጋሽም ዐማራ ማለት ክርሲቲያን ወይንም የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ማለት ሲሆን ዐማሮች ቀድመዉ ክርስቲያን ስለነበሩ በኃላ እስላሞችና ጋሎች ሲመጡ ዐማራ ማለትን ክርስቲያን ማለት አድርገዉ ተቀበሉት ይላል ፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምም የእብራይስጥ ሀገር ጎብኝዎች ከብዙ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን በጎበኙ ጊዜ ተራራ ላይ የሚኖር ህዝብ አዩና በእብራይስጥ ቋንቋ ዐማራ ብለዉ ጠሩት ይላሉ፡፡ ይህም በዕብራይሥጥ አም -ሕዝባ ሃራ -ተራራ ማለት ስለሆነ በጥምሩ ዐማራ ሲሉ ተራራ ላይ የሚኖር ደገኛ ሕዝብ ማለት ነዉ ይላሉ፡፡ እንደሳቸዉ ትንታኔ ከሆነ ደገኛዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቋንቋዉ ቢለይም የአንድ የዐማራ ሕዝብ ክፍል ነዉ ወደሚለዉ ይወስደናል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ አሁን ባለንበት 88%(88 በመቶ) የኢትዮጵያ ህዝብ በደጋዉ ያገራችን ክፍል ኗ ሪ በመሆኑ 88 በመቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐማራ ነዉ ያሰኛል፡፡ወይም ቀሪዉ 12ፐርሰንት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐማራ አይደለም ማለት ይሆናል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ዐማራ ማለት ምን ማለት ነዉ ? የአማራ ብሄር አለ ወይ ? የሚሉ ጥያቄዎች አሁን በብዙዎች ዘንድ እየተነሳ ያለ ጥያቄ ሆኖአል፡፡ አንዳንዶች እንዲያዉም የዐማራ ሕዝብ እንጅ የዐማራ ብሄር የለም የሚለዉን ሃሳብ በማጣመም ዐማራ የለም የሚል መሰረተ ቢስ ተረት ጀምረዋል ፡፡

 

ሌሎች ደግሞ የዐማራዉን ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በመቀነስ አማረኛ ተናጋሪዉን የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለ የለህም ለማለት እሽቅድምድም የጀመሩ ይመስላል፡፡ ወያኔ ስልጣን ከመያዙ በፊት በዓለም ይታወቅ የነበረዉ የዐማራዉ ሕዝብ ብዛት በ1990 እንደ Britannia world data 37.7ፕርሰንት ሲሆን ፤የኦሮሞ ሕዝብ ደግሞ35.3ፐርሰንት እንዲሁም በሌላ መረጃ በ1980-84 የህዝብ ቆጠራ ዐማራዉ38ፐርሰንት የኦሮሞዉ ሕዝብ ደግሞ 35.3ፐርሰንት ነበር (copy 1990 pc Globe Tempe AZ, USA) እንደ1984 ዓመተ ምህረቱም የኢትዮጵያ መንግስት ባወጣዉ የሕዝብ ቆጠራ ደግሞከ 52383100 ሕዝብ ዉስጥ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪዉ (ከኤርትራና ትግራይ)ሕዝብ ጨምሮ 32 ፐርሰንት ነበር፡፡ ሆኖም ወያኔ ስልጣን ከያዘ በኃላ CIA የዐማራን ሕዝብ ከትግረኛ ተናጋሪዉ(ከኤርትራና ትግራይ) ሕዝብ ጋር ጨምሮ 32 ፕርሰንት ነዉ ሲል አወጣ፡፡ (The Swedish institute of international affairs no.2 1993) አማረኛ ተናጋሪዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስትን ከመሰረተ በኃላ ንጉሶቹ አንድ ባላባት ወይም መስፍን በሸፈተ ቁጥር ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ፤ከሰሜን ወደ ደቡብ ከደቡብ ወደ ምስራቅ ወዘተ በመዘዋወር አርፍዉ እንኳን የተቀመጡበት አንድ ማዕከላዊ ከተማና ቤተ መንግስት በቅጡ ሳይገነቡ የሀገርን ድንበር እና የህዝብ አንድነት ለማስጠበቅ የተረከቡትን ሃላፊነት አክብረዉ በጦር ሜዳ ያለፉበት ዘመን ብዙ መቶ ዓመቶች ናቸዉ፡፡ በዚህ ወቅት ከዚያ አካባቢ በምርኮም ይሁን በፍላጎት በወታደርነት የገቡ ወይም ክርስትና ሃይማኖትን የተቀበሉት ዐማሮች የሆኑ ሲባል ፤ንጉሱን ተከትለዉትም ሄደዉ የንጉሱን ስርዓት ለማስጠበቅ ሆነ ወይም በምረኮ በዉዴታም ሆነ ወይም በሆነ ምክንያት በአካባቢዉ የቀሩ ዐማሮች ደግሞ ከአካባቢዉ ጋር ተጋብተዉና ተዋልደዉ ከግዜ ብዛት የሕዝቡን አኗኗር እና ቋንቋ በመልመድ የአካባቢዉ ሕዝብ አካል ሆነዉ ለብዙ ዘመናት ኖረዋል ፡፡ በዚህ መነሻነት አማራ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሁሉም ቦታ አለ፡፡ የኢትዮጵያ ያልሆነች ኢትዮጵያ የለችም፡፡ የወያኔ አልበቃ ብሎ አንዳንድ ቀዠቃዣ የፖለቲካ ሰዎች አወቅን እያላችሁ አማራ ምናምን እያላችሁ መቀባጠራችሁን ብታቆሙ

መልካም ነዉ፡፡ . አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል እንዲ ኢትዮጵያ በተለያዩ ፀሃ•ፍት ዘንድ በተለያየ አጠራርና ስም ስትጠራ ኖራለች:: በዋናነት በኦሪት ላይ “ኩሽ” ትባል ነበር:: እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው 70 ሊቃውንት በጋራ ሆነው ብሉይን ከእብራይስጥ ወደ ፅርዕ/ግሪክ/ ሲተረጉሙ “ኩሽ” የሚለውን ቃል ከግብፅ በስተደቡብ ያለውን አገር ሁሉ ለመጠቆም ይጠቀሙበት የነበረውን የነገድ አባት ስም(“አይቶ ፒያ”) ወይም “Aithio-Pia” ብለው ተረጎሙት:: ይህን ወደ ግዕዝ ሲተረጉሙትም ቃሉን ብቻ እንደወረደ “ኢትዮጵያ” ብለው አሰፈሩት:: ከግዕዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎምም እንደገና ያለ ፍቺ ሆሄውን ብቻ “ኢትዮጵያ” አሉት:: ህዝቡን ደግሞ “ኢትዮጵያዊ” :: የቃሉ ስር መሰረት የት ነው ? ሲባል ግሪክ ሆነ::ትርጓሜውስ ? ተብለው ሲጠየቁ “በፀሐይ የጠቆረ፣ በፀሃይ የተቃጠለ ፊት ያላቸው..” ብለው ነገሯቸው/ዋሹዋቸው::

እንግዲህ ብሉይ ከሂብሩ ወደ ፅርዕ በተተረጎመበት ዘመን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት በ282 ላይ ነበር:: Aithio – Pia የሚሉት እነዚህ ሁለቱ ቃላቶች “አይቶ” ጥቁር፣አደረገ፣አቃጠለ፣ የሚል ትርጉም ሲሰጥ “ኦፕያ” ወይም “ኦጵስ” ፊት የሚል ትርጉም ይይዝና ነዋሪዎች ፊታቸውን ፀሃይ ያቃጠለው በሚል ፀና:: አንዳንዶችም ሲራሩልን “ጠይም” ለማለት ነው ይሉናል:: እንዴት ግሪካዊያን ኢትዮጵያ ማለት “በፀሃይ የጠቆረ” ማለት ነው እንዳሉን እና እንዳታለሉን/እንደዋሹን ይህን ያህል ካየን ይህን ቀልማዳነት ደግሞ እንዲህ እናፈርሰዋለን::

ኢትዮጵያ ማለት በትክክለኛው፣ ፍጹም በጠራው አገላለጽ ባሁኑ “ኢት-ዮጵ”: የአማርኛ አባት በሆነው በግዕዝ = “ኢትኦጵግዮን” የግዕዝ አባት በተባለው በሳባ = “እንቅዮጳዝዮን” ቋንቋ ከመከፋፈሉ በፊት በኖኅና በቤተሰቦቹ ዘመን ኩሽቲክ ሴሚቲክ ተብሎ ከመከፋፈሉ በፊት የነበራት ስያሜ “እንቅዮጳዝዮን” የተባለች አገር ናት:: ስለዚህ በአማርኛ ኢትዮጵያ እያልነው ያለነው በዘመን ብዛት ተወራርሶ እዚህ ደረሰ እንጂ በጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አንድ አይነትና ተመሳሳይ፣ቢገለባበጥ ይዘቱንን የማይለቅ፣በራሱ በፈጣሪ የተሰየመ፣ከነወንዙ የተሰጠ ስያሜ ነው::

+++ “ኢትዮጲስ 1ኛ” እና “ኢትዮጲስ 2ኛ” የሚለው ስም ግሪክ ከመታወቋ ሺ አመት ቀድሞ እዚህ(ኢትዮጵያ) የነገስታት መጠሪያ ስም የነበረ ነው:: “ኢትዮጲስ” በአማርኛም፣በግዕዝም፣በሱባም፣ በእንግሊዘኛም፣ በምንም ቢለዋወጥ ያው “ኢትዮፒስ” ነው:: የአገሪቱ ስም ከግሪክ ብቻ ከተገኘ ንጉስ ኢትዮጲስ ከግሪክ የወሰደው ስም ነውን ? የግዕዝ ቋንቋ በአጋዝያን ዘመን ነበረ:: ኢትዮጵያም ቋሚ ስም፣ ትርጉም ያለው ስም ነበራት:: ምንጩም ፍንጩም ግሪክ አይደለም!!!

ሀበሻ ቆሻሻ መጣያ ማለት ሲሆን ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ያማረ ፣ የተዋበ ማለት ነው። ETHIOPIA = UTOPIA = ጦቢያ ቃሎች ይወራረሳሉ በተለያየ የዓለም ቋንቋዎች። ምንአልባትም ትንሽ የትርጓሜ ልዮነት ሊኖር ይችላል። ግና በደንብ ከተስተዋለ የቃሎቹ ትርጉም ከአንድ ቤተሰብ ይወለዳሉ። ለምሳሌ ያክል ሀበሻን ብንወስድ እንደሚከተለው ይተረጎማል፦ በአረብኛ አባሽ ማለት የተዘበራረቀ፣ አንድ ወጥ ያልሆነ፣ ቆሻሻ የሚገኝበት ቦታ ሁሉ በዚህ ቃል ሲሰየም በእንግሊዘኛ ደግሞ አባሽ ( ABASH ) የሚል ቃል እናገኛለን። ትርጓሜውም annoy, confuse, crush, discomfit, discompose, disconcert, disgrace, dismay, displease, disquiet, dissatisfy, embarrass, humiliate, irk, irritate, mortify, peeve, perturb, shame ማለት ነው። ሀበሻ ወይም በጥቅሉ ቆሻሻ ማለት ሲሆን አረቦች በ624 ዓ/ም በ “ብድር ጦርነት” ጌዜ ፥ ቅድስት እናታችንን መልእክተኛው ልጃቸው ሞሀመድ ትረዳ ዘንድ በፈጣሪ አምላክ ታዛ፣ በ40ሽ ሐረኞች ልጆቻቸውን ክፉኛ ስለተሸነፉ ነው ሀበሽ ፦ ጥርቅምቅማም፤ ታሪክ የሌለው ፤ ቆሻሻ ብለው የጠሩን። ይኸውም እንደነሱ ተመሳሳይ ቀለምና ጠጉር ስላላዩብን ነው። በተጨማሪም በ16ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ አይሁዶች ከኢትዮጵያ ምድር ሲባረሩ አንወጣም ያሉትን ደግሞ እንግልትና ሲደርስባቸው በተንኮል አቢሲኒያ ( Abyssinia )። ቃሉ ቀጥታ ይተገኘው ከAbyss ነው። ትርጓሜውም የስቃይ ቦታ ማለት ነው። ለዚህ ተቀራራቢው ቃል በአማርኛ “አበሳ” ሆኖ እናገኘዋልን። ስለዚህ በኢትዮጵያ ጠላቶች አትታለሉ አትመኑም እራሳችሁን ለጥፋት አታሰናዱ!! በጥቂት አጋንንቶች አውሮጳውያን፣ የኢትዮጵያን ቅዱስነትን ለማጥፋት የለጠፉብንን ሰይጣናዊ “ኩሽ = “ugly & shit” (ለኩሲ ፣ የሴም ልጅ ነው። ኩሲ የቅዱሳን ቅዱስ ማለት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ወይም የኔንሮድ ወዘተ አባት ናቸው። የኢትዮጵስም* አባት ናቸው። የኢትዮጵያም ስም የተገኘው ከዚሁ የአባታችን የዘር ሐረግ ነው እንጂ ቃሉ ከግሪክ ተገኘ በማለት በሀሰትና እውነተኛ ታሪካችንን ለማዳከም ብሎም ለማጥፋት ያቀነባበሩት ሴራ ነው። እንዴው ለመሆኑ ማን ነበር የዚህ ዓለም የመጀመሪያዎቹ ስልጡን? የታወቁት የግሪክ ፊሎዞፈሮች** ትምርታቸውን የቀሰሙት በየትኛው ምድር ሆነና ነው? መላው የአፍሪካ ኢትዮጵያ ተብሎ ይጠራ ነበር። እግዚአብሄር ሲፈጥረን አሳምሮ እንጂ መልካችን ተቃጥሎ አይደለም።

የምድር ሁሉ ቋንቋ፣ፈጣሪ ከፍጡሮቹ በተነጋገረበት ቋንቋ “እንቅዮጳዝዮን” ስትባል ቆየችና ቀስ በቀስ “ኢትዮጵግዮን” መባል ጀመረችና በመሐል ቤት ተሰረቀች:: ከዚያ በኋላ ለሌላ ግልጋሎት ሲጠቀሙበት ኖረው ብንፈልግ፣ብንፈልግ፣ብንዳብስ፣ብንዳብስ አጣነው:: በመጨረሻ “ኢትዮጵ” ሆኖ አገኘነው:: “ኢት” = ስጦታ “ዮጵ” = ብጫ ወርቅ ወይም እንቁ “ግዮን” = ፈሣሽ ወንዝ በጥቅል “ኢትኦጵግዮን” = “የግዮን ወርቅ ስጦታ” ከዚያ በፊት ማን ትባል ነበር ? “እንቅዮጳዝዮን” እውነቱ ይሄ እና ይሄ ብቻ ነው! ሙሉው ምንጭ የተገኘው: “የኢትዮጵያ የ5ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግ ” ከሚለው መጽሐፍ በጋዜጠኛ ፍስሐ ያዜ ካሣ የተጻፈ! መጽሐፉ በሚያስደስት መልኩ ሃተታውን እያተተ እና ድምዳሜውን እየደመደመ ይሄዳል:: እኔ ግን ለጊዜው ይበቃል ያልኩቱን ብቻ ነው

ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከግሪክ ሊገኝ አይችልም ምክንያቱም እንደሚከተለው፦ ፩ ከዓለም መጀመሪያዎቹ ከፍጥረት ጀምሮ እስከ መጀመሪያ የሰው ልጅ ስልጣኔ ኢትዮጵያ ቀዳማዊነትን ትይዛለች። ስለዚህ ግሪኮችን እኛ ኢትዮጵያውያን ማንነታችንን አስተማርናቸው እንጅ እነርሱ አላስተማሩንም። የታወቁን ፊሎዞፎሮችንም ጨምሮ ትምህርታቸውን የገበዩት በኢትዮጵያ ምድር ነው!! ፪ የኢትዮጵያ ስም የተገኘው ከኢትዮጲስ ከሚባለው የኩሲ ልጅ ነው። ትርጓሜውም እጂግ ያማረ የተዋበ ደስ የሚል ለሰብዓዊም ይሁን ለአእምሮ እርካታን የሚሰጥ ሁሉ ኢትዮጵያ ፣ ዮቶፕያ ወይም ጦብያ የሚባለው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የምድር ገነት የምትባለውም። ኢትዮጵያም በእለ ቅእቡላን (ALKABULAN) ትታወቅም ነበር። መላው የ”አፍሪካ” ተብዬው አህጉር በኢትዮጵያ ይጠራም ነበር እስከ 1884 እ/አ። እለ ቅእቡላን = በምድር ገነት የሚኖሩ ቅቡአን ፈጣሪያቸውን የሚፈሩም ማለት ነው። ፫ እግዚአብሔር ሲስራን አስተካክሎና አሳምሮ ሲሆን ጠቆር ያለ መልክ እንዲኖረን የሆነበት ምክንያት የፀሀይን ጨረር (uv) ለመከላከልም እንዲሁም ሰውነታችን ይሚያስፈልገውን uv ተቀብሎ ለአጥንታችን ጥንካሬ ጤነኛ እንድንሆን ነው እንጂ እንደ እነሱ አመልካከት የኢትዮጵያን ምነት ለማጥፋት ከተነሱት የሰይጣንች ቡችላዎች እንደሚያናፍሱት ወሬ አይደለም። እንደትርጓሜው ከሆነማ ሳንወለድ ገና ነጫጭባ በሆንን ነበር።

*ኢትዮጲስ = ግዕዝ ነው ትርጓሜውም ያማረ ማለት ነው። **ፊሎሶፊ = ግዕዝ ነው ትርጓሜውም ፈልሳፊ ማለት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop