የቃብትያ አድህርዲ መንገድ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አብይ ኮሚቴ

ያገር ልማት በአገር ልጅ !

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ከሚገኙት አራት ወረዳዎች መካከል የቃብትያ ሁመራ ወረዳ አስተዳደር አንዱ ነው። ይህ ወረዳ ሰፊና ለም የሚታረስ መሬት ባለቤት ፣ የቃብትያ ሁመራ ብሄራዊ ፓርክ መገኛ፣ ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች በብዛት የሚገኙበት ለመስኖ እርሻ አመቺ፣ የእጣንና ሙጫ የተፈጥሮ ደን በብዛት የተንጣለለበት፣ ዝርያቸው ከፍ ያለ የቤት እንስሳትን ባለሃብት እና ከሁለት የኢትዮጵያ አጎራባች አገሮች ከኤርትራ እና ሱዳን የሚዋሰን ወረዳ ሲሆን ከትግራይ ክልልም ይዋሰናል።

ይህ ወረዳ ከዞኑ አልፎ በአገር ደረጃ የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ ከሚያበረክቱ የአገሪቱ አካባቢዎች በተርታ የተቀመጠ ቁልፍ እና የረዢም ዕድሜ ባለቤት ወረዳ አስተዳደር ነው።

ወራሪውና ተስፋፊው የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት በሃይል ወልቃይት ጠገዴን ለመጠቅለል ባደረገው ግብግብ የቃብትያ ሁመራ ወረዳ ህዝብ በወራሪው ሃይል በፈፀመው አኩሪ ጀብድ በጠላት ሃይል በከፍተኛ ጥርስ የተነከሰበትና በቀል ከተፈፀመባቸው ቁጥር አንድ ነው።

ይህ ተፈጥሮ የተቸረው ወረዳና ህዝብ ከማንኛውም የልማት እንቅስቃሴዎች ተገሎ የኖረ ብቻ ሳይሆን በእጁ የቆየውን ሃብትና ንብረት በሃይል ተዘርፎ ፣ለሞት፣ ለእስርና ስደት የተዳረገበት አጋጣሚ ነበር። ከነፃነት ማግስት ግን ያለፈው ቢቆጭም ለህግ እንተወውና በሚል ቁጭት ፣እልህና ወኔ ተነሳሽነት ከበጀት ተገለንም ቢሆን ባለን ሃብትና አቅም የመሰረተ ልማት ስራዎች እንደ ወረዳ አስተዳደርና አመራር እናስጀምርና ህዝባችንን ይዘን እንጨርሰዋለን በሚል የቃብትያ አድህርድ የከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ አስተዳደሩ ኮሚቴ አዋቅሮ በጨረታ ለተቋራጭ በመስጠት የተሳካ ግንባታ እያካሄደ ይገኛል።

የወረዳው አስተዳደር አመራር፣ የኮሚቴው አባላትና ህዝብ በጋራ የመንገድ ግንባታው ስራ ሂደት በመገምገም የህዝባችንን ድጋፍ ጠይቀን የመንገዱን ስራ ማስፋፋት አለብን በሚል ስምምነት የቃብትያ አድህርዲ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት አብይ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ሕዝባዊ ኅይል (ፋኖ)፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ፣ የአማራ ሚሊሻ፣ እና የአማራ ልዩ ኃይል የጣና ብርጌድ ጥምር ኃይል

ድጋፋችሁ በአብስንያ ባንክ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሶስት ኮሚቴዎች ስም በተከፈተ ሂሳብ ቁጥር ድጋፋችሁን እንሻለን ።

ንግድ ባንክ 1000 486 199 664

አብስንያ ባንክ 10 22 14 207 ናቸው።

— አዛናው አድማሱ

– ይስፋ ላቃቸው

– ግዛቸው መለሰ ናቸው።

የኮሚቴዎቹ ስልክ ቁጥር

1- 09 46 32 04 71

2- 09 48 80 65 10

3- 09 87 89 83 55 ብላችሁ ደውሉ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share