June 27, 2022
4 mins read

በአማራ ደም ላይ የሚሰነዘሩ ቧልቶች – ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ አማሮች ላይ የሚካሄደው የዘር ማፅዳት እና ማጥፋት ዘመቻ በኦህዴድ ከፍተኛ የመንግስት አመራር አካላት አቅጣጫ ሰጪነት በእቅድ የሚፈጻም ለመሆኑ ብዙ ጠቋሚ ምልክቶች አሉ።

289607297 324046126605564 713037739839701108 n

እነዚህ የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ለሰላሳ አንድ ዓመታት የተካሄዱ ሲሆን በተለይ ላለፉት አራት ዓመታት በተወሰነ የጊዜ ርቀት ሲፈፀሙ ቀይተዋል፡፡ ድርጊቶች ከተፈፀሙ በኃላ  የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለተጠቂዎች ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት ከሚሰነዘሩ የፖለቲካዊ ቧልቶች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

  • የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ ኃይል በኦነግ ሸኔ ተይዘው የነበሩ አካባቢዎችን አስለቀቀ፣
  • የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኦነግ ሸኔን ደመሰሰ፣
  • በኦነግ ሸኔ ላይ የፀጥታ ኃይሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፣
  • የሸኔ የታችኛው አመራር ተመታ፤ተገደለ፣
  • የኦነግ ሸኔ የተሸነፈ ኃይል ተስፋ ቆርጦ እየሸሸ እያለ በንፁኃን ላይ ጥቃት አደረሰ፣
  • የአማራ እና የኦሮሚያ የክልል ፕረዘዳነቶች አብረው መግለጫ ይሰጣሉ(የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት አብሮ የኖረ ወንድማማች ህዝብ ነው እያሉ ዲስኩራቸውን ይነዛሉ)፡፡ ፖለቲከኞች ለያዩት እንጅ ህዝቡ ወንድማማች እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ከግድያው በኃላ የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነተኛ ፍላጎት ላይ የተመሰረት እንዳልሆነ ጥሬ ሃቅ ነው። ከወንጀሉ በኃላ የሚወጡ መግለጫዎች የዜጎችን የቁጣ ስሜት ለማብረድ ድውያን ፖለቲከኞች የሚጠቀሙበት ቁማር ነው፡፡ ስለዚህ የአማራ ህዝብ እና የአማራን ህዝብ ህመም የሚጋሩት ኢትዮጵያውያን ዛሬም እንደ ትናንቱ ቁጣን አሰምቶ መመለስ ሳይሆን መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዲመለሱ መታገል ነው፡፡ የስርዓት ለውጥ ተደርጎ ህገ መንግስቱ እስከሚቀየር ድረስ እነዚህ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው፡

1ኛ. የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ መንግስት ስልጣኑን እንዲያስረክብ፤

2ኛ. በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን እንዳለው ሁሉ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል  ክልሎች የአማራ ልዩ ዞኖች እንዲፈጠሩ እና ከክልሉ ውጭ የሚገኙ አማራዎች እራሳቸውን የሚያስተዳድሩበት እድል እንዲፈጠር ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በደራ፣ በአሶሳ፣ በወለጋ፣ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በጉራ ፈርዳ፣ እና በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ አማራዎች እራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ንቅናቄ ሊፈጠር ይገባል፡፡ ትግሉ መቀጠል አለበት፡፡ ያለበለዚያ እነርሱም በሞታችን እየቀለዱ እኛም እያለቀስን እንኖራለን፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop