የወጣትነት ዕድሜውን በማገባደድ ላይ የሚገኝ አንድ ተንከራታች ዜጋ ኑሮ ቢጠምበት፣ መልካም ዕድል ፊቷን ብታዞርበት ጊዜ ወደ አንድ ጠንቋይ ቤት ይሄዳል፡፡ እንደሄደም ወረፋውን ጠብቆ ተራው ሲደርስ እጠንቋዩ ፊት ይቆማል፡፡
ከዚያም ጠንቋዩ፤ “እህ፣ ምን ሆነህ መጣህ?” በማለት ይጠይቀዋል፡፡
እሱም፤”ጌታየ! በርስዎ መጀን፤ ኑሮ ቢመረኝ፣ ቢያንገፈግፈኝ፣ ጓደኞቼ ደልቷቸው እኔ ብደኸይ አንዳች መላ ቢሹልኝ ብዬ ወደርስዎ መጣሁ፡፡” ብሎ ይመልስለታል፡፡
አያ ጠንቋዩም ቀጠለ፤ “ለመሆኑ ዕድሜህ ስንት ነው?”
አስጠንቋይ፤ “በመጪው ትሳስ 28 ዓመት ይሞላኛል፡፡”
ጠንቋይ፤ “አሃ! ጥሩ ነው፡፡ እንግዲያውስ ችግርህ 30 ዓመት እስኪሞላህ ነው፡፡ አይዞህ ወዳጃችን፡፡”
የቸገረው ሰው በተስፋ ሆዱን ለመቀብተት የሚቀድመው የለምና የጠንቋዩን ምላሽ ለማዳመጥ ጆሮዎቹን በጉጉት ቀስሮ፤ “ከዚያስ በኋላ ጌታየ?” በማለት ይጠይቃል፡፡
“ከዚያ በኋላማ ትለምደዋለህ፡፡”
አዎ፣ የአማራና በአማራ ላይ የታወጀው የዘር ፍጂት ነገርም ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ በዚያች ጠማማ ዓመት፣ በ1968 ትግራይ ውስጥ ደደቢት ላይ የተጻፈች “አማራንና ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ ማጥፋት፤ አማራን በተለይ ማኅበራዊ ዕረፍት መንሳት” የምትል ወያኔያዊ ሰነድ ከተቀረጸችና ወደተግባር ከተለወጠች ወዲህ ይሄውና አማራ እስከዛሬዋ መዓልትና እስካሁኒቷ ቅጽበት ድረስ ቁም ስቅሉን እያዬ ነው፡፡ አማራም ከአንድነቱ መለያየቱ፣ ከመግባባቱ መነቋቆሩ፣ ከመተዛዘኑና መተሳሰቡ መነካከሱና መቆራቆሱ የተስማማው ይመስላል በምልዓት ከማንም ሳያንስ ለጠላቶቹ ዒላማነት ምቹ ሆኖ በማለቅ ላይ ይገኛል፡፡ እናም ላለፉት 31 ዓመታት በተለይ ደግሞ ካለፉት 4 የጥልቅ መከራ ኦሮሙማዊ አገዛዝ ወዲህ እየደረሰበት የሚገኘውን የስቃይ ዶፍ ለምዶት እንደቤቶች ድራማ ገጸ ባሕርይ እንደሙሽራው እከ ለሽ ብሎ ተኝቷል፡፡
ከአርባ ጉጉ እስከ ጉራ ፈርዳ፣ ከአሰቦት እስከ በደኖ፣ ከገለምሶ እስከ ሻሸመኔ፣ ከደምቢ ዶሎ እስከ አጣዬ፣ ከከሚሴ እስከ ጊምቢ፣ ከአሶሳ እስከ ጋምቤላ …. በመላዋ ኢትዮጵያ በየቀኑ ስለሚገደለው አማራና ሌላው ኢትዮጵያዊ ለመናገር አይደለም አነሳሴ፡፡ አንድ ችግር ተደጋግሞ ሲነገርና ሲጻፍ እውነትም ይለመዳል፡፡ የሚለመድ ነገር ደግሞ ደስታም ሆነ ሀዘን ተራ ነገር ይሆንና ማስደሰቱም ማስደንገጡና ማሳዘኑም የማይቆረቁረን ስሜት አልባ ድንዙዛን እንሆናለን፡፡ ወደስሜት አልባነት ደረጃ የተለወጠ ግለሰብም ሆነ ማኅበረሰብ ለአደጋ የተጋለጠ ነው፡፡ ለምሣሌ በሥጋ ደዌ (ሌፕረሲ) የተጠቃ ሰው በሽታው የነርቭ ሕዋሳቱን ስለሚያደነዝዛቸው ሰውዬው እሳት ቢፈጀው ወይንም ቢላዎ ቢቆርጠው ህመም አይሰማውም፡፡ በዚያም ምክንያት ሳይታወቀው ሁሉ ለከፋ አደጋ ይጋለጥና የሰውነት ክፍሉን ሊያጣ ይችላል፡፡ በነገርም ይሁን በመጠጥ የሰከረ ሰው በሌሎችም ሆነ በራሱ ላይ አደጋ የሚያስከትለውና የደረሰውንም አደጋ የማያስተውለው በዚህ ሳቢያ ነው፡፡ አማራም ወደዚህ ደረጃ የቀረበ ይመስለኛል፡፡ የኋላ ኋላ ከንቅልፉ መንቃቱና ለመብቱ መነሳቱ ታሪካዊ እውነታ ቢሆንም አሁን ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ በዚህ መልክ መግለጹ ነውር አይደለም፡፡
እናም አማራው ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ይገኛል፡፡ ሰሞኑን – ሰኔ 11/2014 – በአቢይ አህመድና በሽመልስ አብዲሣ በሚመራው ኦነግ-ሸኔ የተባለ የነዚህ ልጆች ፍጡር ከሁለት ሽህ በላይ አማራ ወለጋ ውስጥ ባልተወለደ አንጀት ሲረፈረፍ አንድም ቦታ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አልተደረገም፡፡ ይህ የሚያሳየን ከችግር ጋር መኖርን እንዴቱን ያህል እንደተላመድነው ነው፡፡ የሚገርም ድንዛዜ ነው፡፡
በአንድ የዘር ፍጂት ይህን ያህል ሕዝብ ከአንድ ነገድ ሲታጨድ ሁሉም ዝም ጭጭ ማለቱ በርግጥም በእጅጉ ያስደነግጣል፡፡ “አማራ ሰው አይደለም እንዴ?” የሚል ትልቅ ጥያቄም ያጭራል፡፡ ይሄኔ ከሌላ ነገድ አሥር ሰው ተገድሎ ቢሆን ለሦስት ቀናት ባንዲራ ዝቅ ተደርጎ ይውለበለብ፣ አቢይም በፓርላማና በኢቲቪ ወጥቶ ይቅለበለብ፣ ሚዲያዎችም ሁሉ አለልክ ይቅመደመዱ ነበር፡፡ አማራ ሲሞት ግን በተለይ አቢይና ጓደኞቹ ቤት ዘግተው ፌሽታ ሳያደርጉ አይቀሩም፡፡ ይህ ዓይነቱ ደዌ የለከፈው ሰው ሀገርን እንዲያስተዳድር ዕድል ሲገጥመው ማየት ያሳዝናል፡፡ የአማራ ተወካይ ነኝ ባዩ ብአዴንም የሎሌነት ሚናውን በሚገባ እየተወጣ ነው፡፡ ለአማራ ደግሞ ዋናው ጠላት ኦነግ/ኦህዲድ ሳይሆን በስሙ የተመሠረተው ብአዴን ነው፡፡
አቢይና ሽመልስ የመጡበትን ዓላማ በፍጹም አይዘነጉም፡፡ እባብ የወጣበትን ጉድጓድ እንደማይስት ሁሉ እነዚህ ብላቴናዎችም ያደጉበትንና የተመረዙበትን አማራን የማጥፋት ሤራ ለሰከንድም አይዘነጉም – እንጀራቸውም ነው – ነፍሳቸውን ረክዘው ከዐውሬው ጋር የተፈራረሙበት የሕይወታቸው ትልቁ የስኬት አጀንዳ ነው፡፡ ዓላማቸውን አለመርሳት ደግሞ የተልእኳቸው ዓይነተኛ ግብኣት ነው፡፡ ያም ዓላማ አሁን ብዙው ሰው እንደተረዳው አማራንና የሰሜኑን ሕዝብ በጥቅሉ ከምድረ ገጽ በማጥፋት ታላቋ ኦሮምያን መመሥረት ነው፡፡ ሰሜነኞቹ ግን አልገባቸውም፤ እርስ በርስ መፋጀትንም ሥራየ ብለው ይዘውታል፡፡
ይሁንና የተከበረው የኦሮሞ ሕዝብ በነዚህ የታሪክ ውርጃዎች ማፈርና ኦሮሞን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከእስካሁኑ በባሰ የጠቆረ ገጽ ሳያሰጡት በተቻለ ፍጥነት ማስወገድ እንደሚገባው መጠቆም እወዳለሁ፡፡ አቢይና ሽመልስ ያልታጠቁ አማሮችን፣ ሴቶችንና ገና ሦስት ቀንም ያልሆናቸው ሕጻናትን በጥይትና በሜንጫ ስለረፈረፉ ፍላጎቱ ምንም ይሁን ምን የኦሮሞ ፍላጎት አይሳካም፡፡ በአርባና በሃምሳ ሚሊዮን የሚገመተው የአማራ ሕዝብ ከምድረ ገጽ ጠፍቶ ኦሮሞ የሚያገኘው ነገር ምንም ይሁን ምን ሰፊውን የኦሮሞ ሕዝብ ሊያስደስተውና የኅሊና ሰላም ሊሰጠው አይችልም፡፡ ኦሮሞ በአሜሪካና በአውሮፓ ሄዶ ሀብት ንብረት እያፈራና ባልተወለደበት የባዕድ ሀገር ለመንግሥት ሥልጣንም እየተወዳደረ ባለበት የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አብሮ የኖረና የተዋለደ ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ባልተወለደበት የዘር ሐረግ ወይም ነገድ ምክንያት አንድን ሕዝብ በገዛ ሀገሩ መጨፍጨፍ የጤና አለመሆኑን በተለይ ኦሮሞው ተረድቶ ልጆቹን ሃይ ቢል የመጀመሪያው ተጠቃሚ ሌላ ሳይሆን ራሱ ነው፡፡ አዎ፣ በአማራ ዕልቂት ኦሮሞም ሆነ ሌላ ማንም ወገን አይጠቀምም ብቻ ሳይሆን የዞረ ድምር ሊኖረው እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ እያስፈራራሁ አይደለም፡፡ ነገር እያባባሰኩም አይደለም፡፡ ግን ግን ፈጣሪ ምን ጊዜም ቢሆን ከግፈኞች ጋር ሳይሆን ከተበዳዮች ጋር መሆኑን ከመገንዘብ አንጻር ስለነገው የሚታየኝን የነገሮች የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ በእግረ መንገድ መጠቆሜ ነው፡፡ ተረኝነት ተረኝነትን፣ ቂም በቀልም ቂም በቀልን እንደሚወልድ እንረዳ፡፡
አክራሪ ኦሮሞዎችን አንድ ቁም ነገር ላስታውሳቸው እወዳለሁ፡፡ አሁን የምትጨፈጭፏቸው አማሮች ሰዎች እንጂ ጉንዳኖች ወይንም ዐይጦች አይደሉም፡፡ ሰዎች እንደመሆናቸው የሚፈሰው የእያንዳንዱ ንጹሕ ዜጋ ደም ወደፈጣሪ ይጮሃል፡፡ የውሻን ደም መና የማያስቀረው ፈጣሪ ደግሞ በደልን መካስን፣ ጥጋበኛን ማስታገስን አሳምሮ ያውቅበታል፡፡ ለዚህ ደግሞ የቅርቡን ሕወሓትን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ የነሥዩም መስፍንን፣ የነአባይ ወልዱን፣ የነአባይ ፀሐዬን፣ የነስብሃት ነጋን ዕብሪትና ጥጋብ በምን መልክ እንዳስተነፈሰ ከአቢይና ሽመልስ ወዲያ የሚያውቅ ላሣር ነው – ከቡችላነታቸው ጀምሮ እዚያው ነበሩና፡፡
ስለሆነም ያዋጣናል ካላችሁ በመለሳዊ አገላለጽ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፡፡ እናም በዘረኝነት ፕሮፓጋንዳ ያሰከራችኋቸውን ቄሮዎች አማራን እንዲያጠፉ በደምብ ንገሯቸው፤ ግድያውን አጧጡፉት፡፡ ቶሎ ቶሎ በሉና ታላቋን ኦሮምያ መሥርቱ፡፡ ሁሉንም አማራ በተቻለ መጠን በጥቂት ወራት ውስጥ ለመጨረስ በርቱ፡፡ ደም እንደጎርፍ ይሂድ፡፡ ካዋጣችሁ እንግዲህ በዚሁ ግፉበት፡፡ የአፄዎቹን ግፍ፣ የደርግን ጨፍጫፊነት፣ የወያኔን በደልና በሁሉም ላይ የወረደውን የፈጣሪ የመጨረሻ ፍርድ እንደታዘበ አንድ አንጋፋ ዜጋ የአቢይንና የሽመልስን ጥጋብ መጨረሻ መተንበይ ትልቅ ዕውቀትን አይጠይቅም፡፡ የዱባ ጥጋብ ጥቂት ሰዎችን ብቻ ቢጎዳ ምንም አይደለም ሊባል ይችላል፤ ነገር ግን የወያኔ ዕብሪትና ጥጋብ አንድ ክፍለ ሀገርን ያህል ትልቅ ነገር ለምናውቀው ጉዳት እንደዳረገ ለምንገነዘብ ወገኖች የኦህዲድ ድንቁርና ምን ሊያስከትል እንደሚችል በጣም ግልጽ ነውና የኦሮሞ ማኅበረሰብ ቆም ብሎ የሚያስብበት ጊዜ አሁን መሆኑን ሁላችንም ልገነዘብ ይገባል፡፡ በኋላ “አይቡን ሳያዩት አጓቱን ጨለጡት” እንዳይሆን ነገራችን ሁላ፡፡
በመጨረሻም አማራም ሆነ ትግሬ ወደወለጋና ሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች የሄዱት ወደው ሳይሆን የደርግ መንግሥት በሠፈራ ፕሮግራም አስገድዶ ወስዷቸው ነው፡፡ የያኔው መንግሥት ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ እንዲህ ያለ ኢትዮጵያን ባወጣች ሸጦ የሚበላ ጭራቅ መንግሥት እንደሚመጣ በጊዜው ማንም ባለማወቁ ሠፈራውን በጥልቀት አልተቃወመም፡፡ ባዶና ጠፍ መሬት እየተፈለገ በድርቅ ከተጎዱ አካባቢዎች ሰዎችን በግድ በማፍለስ ወደነዚያ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ ተደረገ፡፡ ስለሆነም እዚያ ሥፍራ መገኘታው የነሱ ጥፋት አይደለም – ጥፋትም ከሆነ፡፡ የራሱን መጨረሻ ለማበላሸት ቆርጦ የተነሳው ኦሮሙማ መፃዒ ዕድሉን ለዘብ ለማድረግ ቢፈልግ ኖሮ ሰዎቹን መግደልና ንብረታቸውን መዝረፍ ወይም ማውደም ሳይሆን በሰላም እንዲለቁ በሩን ከፍቶና ቀነ ገደብ ወስኖ ማሰናበት ነበረበት፡፡ ይህ ዓይነቱ ከሰው ቀርቶ ከለዬለት ዐውሬም የማይጠበቅ ጭካኔና ዐረመኔነት ግን የሰውን ልጅ ተፈጥሮ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፤ንጹሓንን መግደል አንዳችም ትርጉም አይሰጥም፤ ከዕብደትም በላይ ነው፡፡ የለዬላቸው የከተሞቻችን ዕብዶች እንኳን ድንጋይ እያነሱ ሰው ላይ ሲወረውሩ አይታዩም፡፡ የነአቢይ የጭካኔ ተግባር ግን ስም እንኳን ሊወጣለት ያስቸገረ ትንግርታዊ ምትሃት ነው፡፡ መሣሪያ ያልያዘን ሰው፣ ስለነገዳዊ ምንነቱ እንኳን የማያውቅን ገራገር ባላገር፣ በራሱ ላብና ወዝ ለፍቶ መሬት በምትሰጠው ፀጋ የሚኖርን ሰው፣ ከአካባቢው ባህልና ወግ ጋር ተላምዶ በመከባበርና እርስ በርስ እየተጋባና እየተዋለደ የሚኖርን ሰው፣ በሃይማኖትና በባህል ከቀደምት ነዋሪዎች ጋር እምብዝም የማይለያይን ሰው፣ በመልክ በቁመት ወዘተ. አንድ የሆነን ሰው…. ያላንዳች ጥፋቱ አንገቱን መቅላት ከሰው ሳይሆን ከለየለት ሰይጣንም አይጠበቅምና ለጤናማ ኦሮሞ ወንድምና እህቶቼ ይህ መልእክቴ ይድረስልኝ፡፡ ከዘረኝነት አባዜ ወጥተንና ከስሜት አምባላይ ፈረስ ወርደን ይህን ነገር በጥሞና እናስተውለው፡፡ ማንም ቢሆን በነገዱና በጎሣው አይሰቃይ፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔርም ይኑረን፡፡ እርግጥ ነው – የሚገድል ሁሉ ማንም ይሁን ማን የእግዚአብሔር ወገን አይደለምና ለራሱ ሲል ይጠንቀቅ፤ ከሰፊው የሚያማልል መንገድም በአፋጣኝ ይውጣ፡፡ ኅሊናን በትክክል መጠቀም ከኋለኛ ጸጸት እንደሚያድን እንወቅ፡፡