ግልጽ አቤቱታ: ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሕግ በመጣስ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው አለምዐቀፍ ፍርድቤት እንዲቀርቡ ስለመጠየቅ

June 21, 2022

ማንም ግለሰብ ከህግ በላይ መሆን አይችልም

288221339 10227874163464065 6092142956036120320 n

ጠቅላይ ሚንስቴሩ ከጦርነቱ በኋላ ገባ ያሉት ለየት ያለውን ክላሽ ፋኖ የመከላከያ አባለትን ገሎ ታጥቋል ካሉና ክላሹ ክልልም ፖሊስም የለውም ከተባለ ። ታዲያ እነኚህ የኦነግ ተዋጊዎች ከዬት አምጥተው ታጠቁ ? ማንስ አስጣጠቃቸው ? ተብለው ሊጠየቁ ይገባል ።

OLF

ግልጽ አቤቱታ ለሚመለከተው ሁሉ ፦

  • ለኢትዮጵያ ርዕሰ ብሄር ለፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣
  • ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክርሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፣
  • ለኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሺን ፣
  • ለኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖርቲ መሪዎች፤
  • ለኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት ሃላፊዎች፤
  • ለሲቪክ ማህበራት ፣
  • ለምሁራን ፣
  • ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣

 

ክቡራትና ክቡራን

ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሕግ በመጣስ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድቤት እንዲቀርቡ ስለመጠየቅ ፣

ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ይኼውና አራት ዓመት አስቆጥረዋል። በባዕለ ሲመት ንግግራቸው የተነቃቃውና ተስፋ የሰነቀው ሕዝብ ከአንደበታቸው የሚወጡ መልካም ንግግሮቻቸው እምነት አሳድሮ ያለፈውን ችግርና መከራ እርግፍ አድርጎ በመተው በተስፋ ተቀበሏቸውና ሙሉ ድጋፍም ሰጧቸው ፤ በዶ/ር አብይ የመጣ በዓይናችንና በኢትዮጵያ የመጣ ነው በሚል “ሺህ ዓመት ይግዛ” እስከማለት ተደረሶም ነበር። ላለፉት አራት ዓመታት አገራችን የገባችበትን ቀውስ ለሕዝባችን መዘርዘር ለቀባሪ እንደማርዳትም፣ እንደ ድፍረትም ስለሚሆንብኝ ወደ ዋናው የዚህ ግልጽ ደብዳቤ ዓላማ በቀጥታ እገባለሁ።

ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በህዝባችን ልብ ውስጥ መግባት የቻሉትና ትልቅ ድጋፍ የተቸራቸው በመልካም ንግግሮቻቸውና በገቧቸው ቃልኪዳኖች ነበር ። እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ መልካም ከሚመስሉ ንግግሮቻቸው በዘለለ በተግባር የሚታየው ነገር ሁሉ አስደንጋጭ ፣ አሳዛኝና አሳፋሪ እየሆነ መጣ። ጠ/ሚንስቴሩ ስራዎቻቸው ብቻ ሳይሆን ከአንደበታቸው የሚወጡ አስደንጋጭ ፣ ከፋፋይና

ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ፣ የሚያዋርዱና የሚያሳቅቁ እየሆኑ መጡ ። ያም ሆኖ ሕዝቡ ‘ለውጥ አመጣሽ ችግር’፣ የውስጥና የውጪ ጠላት የሚፈጥሯቸው ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ ወዘተ በማለት ትዕግስትና ሆደሰፊነትን መርጦ ጥርሱን ነክሶ ወገቡን ታጥቆ “ሊነጋ ሲል ይጨልማል” በሚል ተስፋ  ከነችግራቸውም ቢሆን አብሯቸው ለመዝለቅ የቻለውን ያህል ለፋ፣  ታገለ፣  ዋጋም ከፈለበት። እያደር ግን እየባሰና እየተወሳሰበ እንጂ እየተሻለና እየቀለለ የሄደ ነገር የለም። ጭፍጨፋው፣ መፈናቀሉ፣ ጦርነቱ ፣ እልቂቱና ውድመት የዕለት ተዕለት ህይወቱ ሆነ። ሀገሪቷ በዘር በጥቅም፣ በእምነት ተዘርዝሮ የማያልቅ የግጭቶች መፈልፈያ ጎሬ ሆናለች ።

መንግስት ዝቅተኛ የተባለውን የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ተግባሩን መከወን ተሳነው ብቻ ሳይሆን የችግሮች አካል እየሆነ በመገኘቱ በገሃድ ከችግሩ ሰለባዎች አፍ እየሰማን ነው ። በዚህ ምክንያት የህዝባችን በመንግስትና በህግ ላይ ያለው የቆየ ጥልቅ እምነት እየተሸረሸረ መጥቷል። አስመሳይ መሆናቸውን ያልተጠራጠረው ሕዝባችን በመልካም አንደበታቸው ተማርኮ የዘፈኑለት መሪ ፣ ያለ መታደል ሆነና ችግርና መከራ ሲደርስበት ማስቆም ባይችል መጎብኘት፣ ማስተዛዘንና ማጽናናት የማይፈልግ ልበ ደንዳና ደመ ቀዝቃዛና ጨካኝ መሪ ሆኖ አገኙት። ከመደንገጥ አልፈው ማዘንና ተስፋ መቁረጥ ቢጀምሩም አገር እንዳትፈርስ ፣ በኛ ይለፍ በሚል ህመሙን ለመቻል ሞከረ። ነገር ግን ሁሉም ነገር ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ መጣ። ከሰላም ማጣትና ከኑሮ ውድነት በላይ የጠቅላይ ሚንስትሩ ሃላፊነት የጎደለው፣ ውሸትና ቅጥፈት የተሞላበት ከፋፋይ ንግግር ትልቅ የራስ ምታት ሆነበት። አሁን አሁን እኒህ ሰው ዛሬ ምኑን ይናገሩ ይሆን እያለ መሳቀቅም ተጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በየግዜው ያሻቸውን እየተናገሩ የፈለጉትን ህዝብና ቡድን እየሰደቡ በዝምታ፣ አንዳንዴም በሳቅና በጭብጨባ ታልፈዋል፤ አብዛኛው ህዝብ አገር ቋፍ ላይ በመሆኗ በሆደ ሰፊነት ችሎት ቆይቷል። ነገር ግን ይህ እየባሰባቸው የሄደው አፍ እላፊ የመናገር አባዜ ወይም ልጓም አልባነት በድንገት የመጣ አይደለም። የጤንነት ሁኔታቸውን እስክንጠራጠር ድረስ ለቁጥር የሚያታክቱ ውሸቶች፣ አስደንጋጭና ከፋፋይ ነገሮችና ስድብና ማስፈራሪያ ቃላቶችን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገመንግሥት ፦

  • ምዕራፍ ሁልት አንቀጽ12 የመንግሥት አሰራርና ተጠያቂነትን በተመለከተ በተራ ቁጥር 2 ማንኛውም ኃላፊና የሕዝብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ ይሆናል ይላል ።

1/ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ስልጣን እንደጨበጡ ትልቅ ወንጀል በእርሳቸው ላይ ተደረገ የተባለው የግዲያ ሙከራ እውነት ይሁን ድራማ እስካሁን ድረስ ተዳፍኖ የቀረውን ተከታትለው ፍትህ እንዲያገኝ አለማስደረጋቸው ፣

2/ ታጥቀው እስከ ቤተመንግሥት ድረስ መጥተው በፑሻፕ የተሽኙ የሰራዊቱ አባላት በወንጀል ባይጠየቁ እንኳን የዲስፕሊን እርምጃ ተወስዶ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ አለማስደረጋቸው ፣

3/ የኢንጂኔር ስመኜው ግዲያ ፣ የአማራ ክልል ባለሥልጣናትና የመከላከያ ሚንስቴር ሞት ፈቺ ያልተገኘላቸው ህልሞች ሆነው ያለ ተጠያቂ ፍትህ አልባ ሆኖ ሲቀር ተከታትለው ተፈጻሚ እንዲሆን አለማስደረጋቸው ፤

4/ ከነትጥቁ እንዲገባ የፈቀዱለት የኦነግ ታጣቂ በክልሉ ውስጥ አማራን ለይቶ በየቀኑ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻ እያካሄደ ህጋዊ እርምጃ አለመወሰዱና ለዜጎች ህይወትና ሀብት ንብረታቸው የመንግሥት ጥበቃ አለመደረጉ ፤

5/ በኦሮሚያ ክልል ሰው ተዘቅዝቆ ተገድሎ ፣ሀብት ንብረት ወድሞ አንድም ሰው ተፈርዶበት ለሕዝብ ይፋ አለመደረጉ፤

6/ ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ በትረ ሥልጣኑን ከጨበጡ በኋላ እርሳቸውን ለጠቅላይ ሚንስቴርነት ካበቃቸው ክልል ብቻ 20 ባንኮች በኦነግ ታጣቂዎች ተዘርፈው እስካሁን የተጠየቀ አለመኖሩ ፤

7/ በኦሮሚያ ክልል ወጣት የደንቢዶሎ ዩኒቬርስቲ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ታፍነው ተወስደው መንግሥት ማስለቀቅ ባይችል በህይወት መኖር አለመኖር ትክክለኛ መረጃ ለቤተሰብ ሳይሰጥ ሶስት ዓመት ማስቆጠሩና ወዘተ ወንጀሎች ዶክተር አብይና መንግሥታቸው በህገመንግሥቱ የተሰጣቸውን ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው የተከሰቱና ፍትህም ያላገኙ በመሆናቸው ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ ኃላፊነትን በማጓደል ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድቤት መቅረብ አለባቸው

  • ምዕራፍ ሦስት መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶችን አስመልክቶ አንቀጽ24 የክብርና የመልካም ስም መብት በተመለከተ በተራ ቁጥር 1 ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው ይላል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በየግዜው ያሻቸውን እየተናገሩ የፈለጉትን ህዝብና ቡድን እየተሳደቡ በዝምታ፣ አንዳንዴም በሕዝብ ተወካዮች ጭምር መልካም ተግባር እንዳደረጉ በሳቅና በጭብጨባ ታልፈዋል፤ አብዛኛው ህዝብ አገር ቋፍ ላይ በመሆኗ በሆደ ሰፊነት ችሎት ቆይቷል። ነገር ግን ይህ እየባሰባቸው የሄደው አፍ እላፊ የመናገር አባዜ ወይም ልጓም አልባነት ማንም ከህግ በላይ መሆን ስለማይችል መገታት ይኖርበታል ።

1/ የአዲስ አበባ ከተማ ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግሥት ሆኖ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ያለው መሆኑን በህገመንግሥቱ ምዕራፍ አራት አንቀጽ 49 በተራቁጥር 2 ተደንግጓል ። ይህንን ሕገመንግሥታዊ መብት በመጣስ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከክልሉ ውጭ በአዲስ አበባ መስተዳር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እንዲዘመርና ባንዲራም እንዲሰቀል ማስገደዱ ህግን የጣሰ ጣልቃ ገብነት መሆኑን የተቃወሙና ህገመንግሥታዊ መብታቸውን የጠየቁ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን „ኦሮሞ ጠል“ በማለት ከአንድ ጠቅላይ ሚንስቴር የማይጠበቅ ሕዝብን በሕዝብ ላይ የሚያነሳሳ ፣ የአዲስ አበባን ነዋሪ በዘር ቁና የማይሰፈር ሁሉን አቀፍ መሆኑ እየታወቀ መልካም ስሙን ለማጉደፍ ለሕዝብ በቀጥታ በሚተላለፍ ሚዲያና የሕዝብ ተወካዮች ፊት “ኦሮሞ ጠል“ ብለው መናገራቸው የህግ ጥሰት በመሆኑ ፣ ጠቅላይ ሚንስቴሩን የአዲስ አበባ ነዋሪ ለምን ተቃወመ ፣ „ብሔርተኛ ኦሮሞ ጠል ኃይሎች“ ናቸው ያስባላቸው መዝሙር የሕዝባችንን ታሪክ “እድፍ“ (“የመቶ ዓመት እድፍ በደማችን አጥበንልሽ“) እያለ ታርሪክን የሚያጎድፍ የሀሰተና የውሸት ትርክት ለህጻናት የሚያስተምረውን ነው ። ሌላው ደግሞ አንድን ዘውግ ለይተው በአማራው ላይ ያላቸውን ከፍተኛ የጥላቻ መርዝ ለተውልድ እንዲተላለፍ (“ነፍጠኛ የሰራውን ማሰብ ያንገበግበናል“) የሚል የውሽት ትርክት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ህጻናትን ጭንቅላት በክልላቸው ውስጥ የሚመርዙት አልበቃ ብሏቸው በአዲስ አበባ እንዳይመርዙ ለምን ተቃውሞ ገጠማቸው ብሎ ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር ለማጣላትና አዛኝ መስሎ ድጋፍና መደበቂያ ለመፈለግ መጣር ሕዝብን በሕዝብ ላይ የማነሳሳት ወንጀል በመሆኑ ጠቅላይ ሚንስቴሩ ከህግ በላይ የሚያረጋቸ ህጋዊ መሰረት ባለመኖሩ እንደ ማንኛውም ዜጋ በህግ መጠየቅ አለባቸው ፤

2/ በሀገራችን ውስጥ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም ክልሎች ሰላም ካለመኖሩ የተንሳ የንጹሃን ሕይወት ይጠፋል ሀብት ንብረታቸውም በመውደም ላይ ይገኛል በተለይም በኦሮሚያ ክልል ያለማቋረጥ እለት ተእለት በመፈጸም ላይ ይገኛ ። ስለሆነም በህገመንግሥቱ ምዕራፍ 6 አንቀጽ 55 ተራ ቁጥር 16 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በራሱ አነሳሽነትና ያለ ክልሉ ፈቃድ ተገቢ እርምጃ እንዲወሰድ ለፌደሬሽኑ ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮችምክር ቤት የጋራ ስብሰብ ጥያቄ ያቀርባል በተደረሰበት ውሳኔ መሰረት ለክልሉ ምክር ቤት መመሪያ ይሰጣል ይላል ይህንን በሕግ የተሰጠውን ሀላፊነቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መወጣት ይኖርበታል ። ይህንን ማድረግ ካልቻለ ምክር ቤቱ ኃላፊነቱን እንዳልተወጣ ስለሚቆጠር ከተጠያቂነት አያመልጥም ።

ኃላፊነት የጎደላቸው የጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ንግግሮች ፦

  • በኦሮሞ ክልል ስንት ንጹሀን ዜጎች በአማራነታቸውና በእምነት ተለይተ በኦነግ ታጣቂዎች እየተገደሉ ባሉት ወቅት ወለጋ ለጉብኝት ያልሄዱበትን ምክንያት ጠቅላይ ሚንስቴሩ ሲገልጹ ኦሮሞ ኦሮሞን ገደለው እንዳይባል ነው ብለዋል ፤
  • የተወሰኑ የሰራዊቱ አባላት ከነትጥቃቸው ቤተመንግሥት በመጡ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሲገልጹ አንድ ነገር ቢሆን የሱሉልታ ፣ የለገጣፎና የቡራዩ ገበሬ በተጠንቀቅ ነበር የሚጠባበቀው ማለታቸው የሚመሩትን ሕዝብ አንዱን እንደልጅ ሌላውን እንድ እንጀራ ልጅ በማየት እዚያው

ቅርባቸው አዲስ አበባ ያለውን ሕዝብ የሴራው አካል ማድረግና እንደማያምኑት የሚያሳብቅ ነበር ፤

  • በእምነት አባቶች ስለ ቤትክርስቲያን ማቃጠል ህገወጥነት ተጠይቀው”ቤተክርስቲያን ተቃጠለ

ትላላችሁ የቦሩ ሜዳን ታሪክ ለማያውቅ ሊገርመን ይችላል ቤተክርስቲያን ወደፊትም ይቃጠላል” ፣ እኔ በየቦታው ያለውን ወንጀል ለመከላከል ሚሊሺያ አይደለሁም ብለው ነው እንደ አንድ ጠቅላይ ሚንስቴር የመለሱት ።

 

የጠቃልይ ሚንስቴሩ ጅምላ ፍረጃ ፣ ስድቦችና ስም ማጥፋት ወንጀሎች ፦

  • በሰሜኑ ጦርነት ከትግራይ ወራሪ ኃይል ጋር ተዋግቶ አገሩን የተከላከለና ለመከላከያ

ኃይላችን ጋሻና መከታ ሆኖ የሚሰዋውን ፋኖ ከፍርሀት በመነጨ ለማጥፋትና ለማዳከም ሲባልተፈቅዶለት ማርኮ የታጠቀውን ማሳሪያ መከላከያን ከኋላ ወግቶ የታጠቀው በማስመሰል ፋኖን ከመከላከያ ጋር ለማጣላት ውስጥ ውስጡን የሚያካሂዱትን ሴራ በአደባባይ መናገራቸው ፤

  • የመከላከያ አባላት ምረቃ ላይ ተገኝተው የሰራዊቱን አባላት ለማጀገን ሌላውን ማኮሰስና መሳደብ ጊዴታ ይመስል እናንተ ለሀገርና ለሕዝብ መስዋእትነት ስትከፍሉ ካድሬዎች ግን እየዘረፉ ይሸሻሉ ማለታቸው ፤
  • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት13ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የፍትህና የጸጥታ አካላትን በጅምላ

ደረጃ ሰጥተው ሌቦች እንደሆኑ መሳደባቸውና ወዘተ… የአንድ አገር ጠሚር ሊናገራቸው የማይገቡ አደገኛ ንግግሮች ህዝባችንን ወደ ከባድ ቀውስና ፍጅት ያስገባ በመሆኑ፣ አገር ወደባሰና የማንወጣው ቀውስ ከመግባቱ በፊት ለማስቆም የሁሉም ኢትዮጵያውያን በተለይም የልሂቃን ኃላፊነት ነው የሚል እምነት አለኝ። ሰለዚህ ጠቅላይ ሚንስቴሩ በፍርድቤት ክስ እንዲመሰርትባቸው በትውልደ ኢትዮጵያዊነቴ እጠይቃለሁ።

  • አሁን በወለጋ አማራ ላይ ያነጣጠር የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከፍተኛ የሆነ የንጹሀንን ህይወት እየቀጠፈ ያለው በዶክተር አብይ አህመድና በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ፈቃድ ወይን የመሪነት ብቃት ማጣት በመሆኑ ከተቻለ ለሀገርና ለሕዝብ ሲሉ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ካልፈለጉ ደግሞ በህግ ተገደው የሚወርዱበትን መንገድ ማፈላለጉ ይዋል ይደር መባል የሌለበት ሀቅ ነውና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያስብበት ፣ ሊመክርበትና ለመተግበር የሚነሳበት አጣዳፊ ጉዳይ ነው ።

ሀገርንና ሕዝብን የሚያክል ትልቅ ነገር ለተወሰኑ ግለሰቦችና ቡድኖች አሳልፎ ሰጥቶ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ከህሊናም ሆነ ከታሪክ ተጠያቂንት አያስጥልምና ወጣቱ ትውልድና ምሁራን ነጻነት በልመና ስለማይገኝ ትግሉን ተቀላቀሉ ።

 

ንጉሤ አሊ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

1 Comment

  1. “አዲስ አበባ ውስጥ ከፍተኛ ኦሮሞ ጠል ሃይሎች አሉ” ጠ/ሚር አብይ – ይህ አባባል እብደት እንጂ የጤና አይደለም። አንዲት ሃገርን የሚመራ ባለስልጣን እንዲህ ያለ አነጋገር ምን ያህል እሳት እንደሚያቀጣጥል እንዴት አይገባውም? እኔ የኦሮሞ ጥላቻ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የለም ማለት አልችልም። ግን ለምን? እንዴት ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ወያኔን አክ እንትፍ ያለው ህዝብ እነዚህን የጊዜው ጡሩንባ ነፊዎች መበታተኑ አይቀሬ ነው። የማያቋርጥ የቃል ጋጋታ ህዝቡን የሚግተው ወያኔ ቀመሱ መንግስት ሥራና ተግባሩ እያደር የድርቡሽ እየሆነ እየመጣ ነው። እስከ መቼ ነው ሰዎች እንደ ድር አራዊት እየታደኑ በኦሮሞዎች የሚገደሉት? ዝም ብሎ ፈጣሪ ያወጣናል፤ መንግስት ይደርስልናል ከማለት ይልቅ ገዳይን ገድሎ መሞት ይመረጣል። በሃሽሽና በዘር ፓለቲካ ጢቢራው የዞረው የኦነግ ሸኔም ሆነ የጉምዝ አልፎ ተርፎም የጋምቤላው ገዳይ ሃይል ሞትን እነርሱም መቅመስ አለባቸው። ቤ/ክርስቲያን መስጊድ ብትጠለል በወያኔና በኦሮሞ ፓለቲካ ታድነህ ትገደላለህ እንጂ አተርፍም። ቆም ብለን እናስብ። በሰው ላይ መኪና የሚነድ እርኩሶች ያፈራች ሃገር ናት። ወያኔና የኦሮሞ ሃይሎች አውሬዎች እንጂ የሰውነት ባህሪ የላቸውም።
    በቁጥር ከደርዘን በላይ የሆኑት የኦሮሞን ህዝብ ነጻ እናወጣለን የሚሉት ስመ ታጋዪች በወለጋና በተለያዪ የሃገሪቱ ክፍል በደረሰው እልቂት ያሉት ነገር የለም። ሥራ አስፈጻሚዎቹ ያሉት በውጭ ሃገርና በሃገሪቱ መዲና ነውና! ተናበው ነው የሚሰሩት!
    አቶ በቀለ ገርባና ጃዋር በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ልብ ቢስ ኦሮሞዎችን ሰብስበው ሲለፈልፉና ስሜታዊ ሆነው የወያኔን ጥያቄ ሲያስተናግድ ወለጋ በንጽሃን ደም ትታጠባለች። ይህ ነው የኦሮሞ ነጻነት። ከወያኔ ጋር አንድ የሚያረጋቸውም ለሰው ልጅ ህይወት ምንም ደንታ የማይሰጣቸው ጨካኝ አረመኔዎች በመሆናቸው ነው። ተጨቆን፤ ሃብታችን ተዘረፈ እያሉ ኦሮሞ አይደለም የሚሉትን በሚዘገንን ሁኔታ የሚያጭድት እነዚህ አረመኔዎች ተመክረው አይሰሙም። በቀለ ገርባ የሚናገረውን ለሰማ ይህ ሰው በእርግጥም የጭንቅላት በሽታ አለበት ያስብላል። እልፍ ኦሮሞ በስደት ወጥቶ ሰርቶ በሰላም እየኖረ መሆኑን እያዪ ምላስ የምታክል ሃገር ተይዞ ቁረሰው አባረው ግደለው አስወጣው መጤ ነው ቋንቋዬ ተጨቆነ ገለ መሌ ሲሉ መስማት የሰከነ ጭንቅላት ላለው ኡኡ ያሰኛል። የሃገራችን ቋንቋዎች ለመግባቢያነት እንጂ ሂሳብ ተቀምሮ፤ ሳይንሳዊ ጽሁፍ ተጽፎ ለአለም በረከት የሚሆን ነገር የሚቀርብባቸው አይደሉም። ቢበዛ ይህንም ያንም እያነገቡ ለመዝፈንና ለመጨፈር ይጠቅሙ ይሆናል እንጂ።
    በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የተለጠፈውን ፎቶ ትኩር ብሎ ላየ እንዴት ተስፋ የሌለው ህብረተሰብ እንደሆነ ያሳያል። በተውሶ መሳሪያ፤ በተላላኪነት ሃገርና ወገንን ማበራየት የነጻነት ምልክት ጭራሽ አይደለም። ግን የጅምላ አስተሳሰብን ለሚከተል አንድ ሃይል ምንም አይነት የተናጠል ህሳቤ እንዲኖረው አይፈቀድለትም። የኦሮሞ ሙታን ፓለቲከኞች የሚጠቀሙት ስልት ልክ ወያኔ የሚጠቀምበትን ነው። ያው የሚልካቸው ራሱ ወያኔ ነውና። ለምሳሌ የሸኔ ቃል አቀባይ የሆነው በሶሻል ሚዲያ ሲለጥፍ ግድያውን የፈጸምነው እኛ አይደለንም ይለናል። ይህ ሰው ተፈልጎ በህግ ሊከሰስ ይገባዋል። ከተቀረቀረበት ሃገርም ሊባረርና እዚያው ወለጋ ሂዶ እንዲኖር ማድረግ ነው። ይህ ሲባል የመንግስት ተብዬ ወታደሮች በደል አይፈጽሙም ማለት አይደለም። ግን በወለጋ በመቶ የሚቆጠሩ አማሮችን የፈጀው የኦሮሞው ወልጋዳ ፓለቲካ የፈጠራቸው ሃይሎች ናቸው። እውነትን በውሸት መሸፈን የሃበሻ ፓለቲካ ዋና ዘዴ በመሆኑ ያው ይህም ያም ይለፈልፋል።
    በጣሊያን ወረራ ለሃገራቸው የተዋደቁትን የገደለው፤ እነ ዶ/ር ሰናይ ልኬን የበላው፤ እነ ጄ/ጻረ መኮነን በሴራ የሸኘው ኸረ ስንቱ የስንቱ ደም የፈሰሰባት ያቺ የሃበሻ ምድር ዛሬም በአስረሽ ምቺው የዘር ፓለቲካ ትናጣለች። ግን በዚህ የፈጠራ ታሪክ፤ በዚህ የወያኔና የኦሮሞዎች የፓለቲካ ጥምረት የሚያተርፍ ማንም አይኖርም። አማራ ነኝ፤ ለአማራ ህዝብ ቁሜአለሁ የሚል ማንም ሃይል ግን አቅመ ደካሞችንና መጠጊያ የሌላቸውን እያሳደደ የሚገለውን በተናጠልም ሆነ በህብረት ለማበራየትና አጸፋዊና ፍትሃዊ ምላሽ ለመስጠት ታጥቆ መነሳት አለበት። ያ እስካልሆነ ድረስ በወረፋ ሞት የማይቀር ነው። የህሊና ጽሎት ህሊና በሌላቸው ሰዎች መካከል ቢደረግ ፍሬ ቢስ ነው። መታጠቅ፤ መሰልጠን፤ መናበብ፤ መረዳዳት አስፈላጊ ነው። ከኦሮሞው ታጣቂ ሃይልም ሆነ ከወያኔ ድርቡሻዊ ግድያ መዳን የሚቻለው በጸሎትና በጾም ሳይሆን ራስን በማዘጋጀትና እሳትን በእሳት በመታገል ብቻ ነው። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

287613935 3037034889940244 2713958192887927026 n
Previous Story

እግዜር ይጠይቃል! ትውልድ ይታዘባል! ታሪክ ይዘግባል! – በላይነህ አባተ

289332716 1080337699244664 3499487684740557569 n
Next Story

አቢይና ሽመልስ ኦሮሞን በቁም እየገደሉት ናቸው!! – ይነጋል በላቸው

Go toTop