የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ስብሰባ ረግጠው ወጡ! ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን አባላት ስብሰባውን አቋርጠው ወጥተዋል

June 21, 2022
Abnየአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጮች ዛሬ የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ አቋርጠው እንደወጡ በምክር ቤቱ የአብን ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። የፓርቲው ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ ምክር ቤቱ በመደበኛ አጀንዳዎች ላይ ከመወያየቱ በፊት፣ ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ክልል እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እየተፈጸሙ ባሉ ጅምላ ጭፍጨፋዎች እና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች ላይ በቅድሚያ እንዲወያይ አጀንዳ እንዲያዝላቸው የምክር ቤቱን አፈ ጉባዔ መጠየቃቸውን አብራርተዋል።
ሆኖም የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ ምክር ቤቱ ቀደም ብሎ ባልተያዘ አጀንዳ ላይ ሊወያይ እንደማይችል ገልጸው ጥያቄውን ስላልተቀበሉት፣ ራሳቸውን ጨምሮ በምክር ቤቱ የፓርቲው ተመራጮች ስብሰባውን አቋርጠው መውጣታቸውን ደሳለኝ ገልጸዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው መደበኛ ስብሰባው ለውይይት የያዘው አጀንዳ፣ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችን የ2013 ዓ፣ም በጀት ዓመት ሒሳብ፣ የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት እና የክንውን ኦዲት ሪፖርቶችን ማዳመጥ እና መወያየት ነው። የፌደራል መንግሥት ኦዲት ሪፖርቶችን ለምክር ቤቱ ያቀረበው ፌደራል ዋና ኦዲተር ነው።
[ዋዜማ ራዲዮ]
——————-
“….በህይወቴ እንደዚህ የአራጅ ዘመን ላይ እንደርሳለን ብዬ አላስብም ነበር። በህግ ማስከበር ስም ብዙ ሰው ተለቀመ፣ ገዳይ ግን በነፃነት ያርዳል..!!!”
ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ …
ሁልህም ንቃ ፋኖ አሳዳጁ ኦሮሙማ በግላጭ ዘር እያጸዳ ነው፤መፍት ሄው ዓይንን ላወጣ ዓይኑን መመንገል ብቻና ብቻ ነው…።

1 Comment

  1. በለጠ ሞላ ምነው አብሯችሁ አልቆመም በርቱ ወንድሞቻችን የእውነት ጸሃይ መውጣቱ አይቀርም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

288834028 141798798444586 915168036526131923 n
Previous Story

አቢይና ሽመልስ ኦሮሞን በቁም እየገደሉት ናቸው!! – ይነጋል በላቸው

teddy afro new official sing
Next Story

TEDDY AFRO – ናዕት (እያመመው ቁጥር ፪) – [New! Official Single 2022] – With Lyrics

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop