TEDDY AFRO – ናዕት (እያመመው ቁጥር ፪) – [New! Official Single 2022] – With Lyrics

June 21, 2022

እያመመው መጣ ቁጥር ሁለት /ቴዲ አፍሮ/
ዶፍ ዶፍ…
ግርም እያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ
ኡኡ ሬጌ ናዕት
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ማን ሊታደም ከድግሱ
ብልጭልጭ ቢሆን ድንኳን
አይለውጥ ጎግ የእውነት መልኳን
ቢጋርድ ሀሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌ ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው
ዘውግ ያወረው ድንበር መኃላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አዕላፍ እሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደሞ በነ ኡኡ ሬጌ
ኡኡ…ሬጌ ናዕት…
ኡኡ ሬጌ ናዕት
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ
ማን ሊታደም ከድግሱ…?
287540960 2142912072535037 2820595780965891535 n 1

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Abn
Previous Story

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ስብሰባ ረግጠው ወጡ! ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን አባላት ስብሰባውን አቋርጠው ወጥተዋል

288834028 141798798444586 915168036526131923 n
Next Story

 ለመዳን መታገል  ወይስ እያለቀሱ መሞት ምኞታችን ሕዝብ በአገሩ በሰላም እንዲኖር ወይስ ሞቶ ለገነት እንዲበቃ? – አገሬ አዲስ       

Go toTop