ለቸኮለ! ሰኞ ሰኔ 13/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

June 19, 2022

1፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ከ200 በላይ ሰላማዊ ሰዎችን እንደገደሉ አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል። የንጹሃን ጅምላ ጭፍጨፋውን የፈጸሙት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች እንደሆኑ እና የጥቃቱ ዒላማዎች በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች እንደሆኑ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። ከግድያው በኋላ መከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው እንደገባ ተገልጧል። የክልሉ መንግሥት ግድያውን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ሲል፣ ቡድኑ ግን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎችን ተጠያቂ አድርጓል።

2፤ ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የሰዎች ሕይወት እንደ ጠፋ አስታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ከግድያው በኋላ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሆኑ እና መንግሥት የጸጥታ ጥበቃ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው እየጠየቁ እንደሆነ ኮሚሽኑ ገልጧል። ኮሚሽነር ዳንዔል በቀለ መንግሥት ሲቪል ሰዎች ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ርምጃዎችን እንዲወስድ፣ ሲቪሎች የጥቃት ዒላማ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልግ አሳስበዋል። Link- https://bit.ly/3nkaBqR

3፤ መንግሥት ከነዳጅ ሽያጭ ላይ የሚሰበስበውን ኤክሳይስ ታክስ እና የቫት ገቢ ለነዳጅ ድጎማ ለማዋል እንደወሰነ ሪፖርተር አስነብቧል። ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት መንግሥት ኤክሳይስ ታክስን እና ቫት ላይ ጭማሪ በማድረግ፣ ከነዳጅ ላይ 15 በመቶ ቫት እና 50 በመቶ ኤክሳይስ ታክስ ለመሰብሰብ ማቀዱን ዘገባው ገልጧል። ሆኖም የቫት እና ኤክሳይስ ታክስ መጨመር የነዳጅ ዋጋን ሊጨምረው ይችላል የሚል ስጋት ያደረበት ንግድ ሚንስቴር፣ አሁን ያለው አሠራር እንዲቀጥል ለሚንስትሮች ምክር ቤት ጥያቄ አቅርቧል።

4፤ የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ የፓርቲው ነባር አመራሮች በአዳዲስ አመራሮች እንዲተኩ ለማዕከላዊ ኮሚቴው ያቀረቡት ሃሳብ ተቀባይነት እንዳላገኘ የአማራ ብዙኀን መገናኛ የፓርቲውን ሕዝብ ግንኙነት ጠቅሶ ዘግቧል። ሊቀመንበሩ በግላቸው ያቀረቡትን ከሥልጣን የመልቀቅ ጥያቄም ማዕከላዊ ኮሚቴው ውድቅ እንዳደረገ ዘገባው ጠቅሷል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ጉዳዩ በሐምሌ ወር በጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንዲታይ ወስኗል ተብሏል። ፓርቲው በጉዳዩ ላይ ያወጣው መግለጫ የለም።

5፤ ቻይና የጠራችው የአፍሪካ ቀንድ አገራት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ እንደሚጀመር ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። በሰላም፣ ልማት እና መልካም አስተዳደር ላይ የሚያተኩረው የመሪዎች ጉባዔለሁለት ቀናት ይቆያል። የመሪዎቹ ጉባዔ ቻይና ለቀጠናው ያዘጋጀችው የመጀመሪያው ጉባዔ ይሆናል። በጉባዔው ስንት የቀጠናው አገራት መሪዎች እንደሚሳተፉ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ማወቅ አልተቻለም። በአፍሪካ ቀንድ የቻይና ልዩ መልዕክተኛ ግን ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል።

6፤ የተመድ ልማት ፕሮግራም በነሐሴ የሚካሄደውን የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሰላማዊ ለማድረግ ከኬንያ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ስምምነት እንደፈረመ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በስምምነቱ መሠረት የተመድ ልማት ፕሮግራም በአገሪቱ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን የሚያስችሉ ሰላም ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን ይሰጣል። የዘንድሮው የአገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውድድር ካሁኑ በተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ ቅራኔ እና ውጥረት የሰፈነበት መሆኑ፣ ከውጤቱ ጋር በተያያዘ ሁከት እንዳይቀሰቀስ ስጋቶች አሉ።

7፤ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ትናንት የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች እንደገቡ ቤተ መንግሥታቸው ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ወደ አቡዳቢ ያቀኑት፣ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ሻክሮ የነበረውን የሁለቱ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማደስ ነው። ላለፉት አራት ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ መሻከር ሳቢያ፣ ኢምሬቶች ለሱማሊያ የምትሰጠውን እርዳታ አቋርጣ ቆይታለች። [ዋዜማ ራዲዮ]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

abiy shirak
Previous Story

የአማራ ፋኖ ላይ የጦር ብርጌዱን ያለሃፍረት ያዘመተው ጠቅላይ ሚኒስትር – ግርማ ካሳ

Dr. Fekadu Bekele
Next Story

“ኋላ-ቀር አስተሳሰብ ባላቸውና በአረመኔዎች የሚመራ ምስኬን ህዝብና አገር” ትችት መልስ! – ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop