June 19, 2022
3 mins read

የአማራ ፋኖ ላይ የጦር ብርጌዱን ያለሃፍረት ያዘመተው ጠቅላይ ሚኒስትር – ግርማ ካሳ

abiy shirak
abiy shirak“ሱቅ እየገቡ ዕቃ ይሰርቃሉ የሚል የፌዝ ክስ በማቅረብ የጦር ብርጌዱን የአማራ ፋኖ ላይ ያለሃፍረት ያዘመተው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፣ ዘመነ ካሴን ለመያዝ በምድር አንድ ክፍለጦር ያዘመተ እና በሰማይ የጦር ድሮኖቹን ለሰዓታት በጎጃም ሰማይ ላይ እንዲበሩ ያደረገ ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ ሕወሓት ጋር በተደረጉ ውጊያዎች የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ጭምር ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ ለማድረግ መወሰን የደፈረ ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ በሶማሌ ክልል አብዲ ኢሌ ላይ እና በደቡብ ክልል ወላይታ ላይ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ የወሰን ጠቅላይ ሚኒስትር በየዕለቱ ዘግናኝ የሆኑ ግድያዎች የሚፈፀምበት ኦሮሞ ክልል ላይ መጨከን እና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንዴት ተሳናቸው ? ኦሮሞ ክልል ሲሆን ለምን ያመነታሉ ?”
ብሎ ይጠይቃል፡፡ እርምጃ ለመውሰድ ያመነታ አይመስለኝም፡፡ እርምጃ ለመውሰድ ሞክሯል፡፡ ነገር ግን ፡
1ኛ እርሱ መንግስት ውስጥ ፣ ደህንነት መስሪያ ቤት፣ መከላከያ ውስጥ ፣ እንዲሁም የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይል ውስጥ ኦነጎ አሉበት፡፡ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሲወሰን፣ ኦነግ አስቀድሞ መረጃ ይደርሰዋል፡፡ ስለዚህ የአብይ መንግስት ራሱን ኦነግ ስለሆነ፣ ራሱን ማሸነፍ አልቻለም፡፡ ጦርነትን የሚወስደው ደግሞ በዋናናነት ወታደራዊ መረጃ ነው፡፡
2ኛ የወታደራዊ አመራር ብቃት የለውም፡፡ ማውራት እንጂ የጦር ስትራቴጂ አያውቅም፡፡ አንዴ አቁሙ ይላል። አንዲ ቀጥሎ ይላል፡፡ የርሱ የጦር አዝማችነት ታች ያሉ መኮንኖችም ግራ ያጋባበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
3ኛ የፖለቲካ ውሳኔዎቹ ህዝቡን የሚያቅፍ ሳይሆን የሚገፋ፣ አምባገነናዊ በመሆኑ፣ ወጣቶችን ማሰር፣ ማወክ፣ ማሸበር ስለበዛ ነው፡፡ ኦህዴድ ከሕወሃት የባሰ አፋኝ ስለሆነ፣ ኦነግ አራት እጥፍ ጭራቅ ቢሆንም፣ ብዙ ተከታዮችን ለማግኘት ችሏል፡፡ በወለጋ በተለይም በርካታ የወረዳና የዞን አመራሮች ሁለት ኮፍያ ያላቸው ናቸው፡፡ ቀን ቀን የኦህዴድን ኮፍያ ያደርጋሉ፣ ማታ ማታ የኦነኝ ኮፍያ ያደርጋሉ፡፡ አብይ በፖለቲካው ረገድ የሕወሃት ሶስት እጥፍ አፋኝ መሆኑ ቀርቶ ህዝቡን ቢያከብር ኖሮ፣ ኦነግ የትም አትደርስም ነበር፡፡

1 Comment

  1. ግርማ ካሳ ያልከው እንዳለ ሁኖ በአደባባይ “ኦሮሞ ኦሮሞን አይገድልም” ብሎ እንደ ነገረን ኦሮምያ ክልል ብለው በጠሩት የሚላከው ወደ ሰማይ የሚተኩስ ሳይሆን አይቀርም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Wolega
Previous Story

ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሲቪል ሰዎች ላይ ስለደረሰው ጥቃት

pro government militias or military forces in the amhara region of northern ethiopia ap
Next Story

ለቸኮለ! ሰኞ ሰኔ 13/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop