እስከ ግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም ድረስ የሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት ዋና አዛዥ (ሁአሠ) የነበሩት ስመ ጥሩው የጦር ሰው ሜ/ጀ ደምሴ ቡልቶ ነበሩ፡፡
ሜ/ጀ ደምሴ ቡልቶ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ክፍለ ሀገር ፤ በመናገሻ አውራጃ ፤ በአደአ በርጋ ወረዳ አስተዳደር ልዩ ስሙ ቢላቻ ወይም ኪቶ ጠበላ ተብሎ ከሚጠራው መንደር ነበር ውልደታቸው ፡፡
የስመ ጥሩው ጀነራል አባት የማይጨው አርበኛ አቶ ቡልቶ ኤጄርሳ ናቸው ፡፡ አባት ቡልቶ ኤጄርሳ ከጦሩ ሰው ሜ/ጀ ደምሴ ሌላ ልጆችም ወልደው ለቁም ነገር አብቅተዋል ።
አቶ በቀለ ቡልቶ (የገንዘብ ሚንስቴር መሥሪያ ቤት) የግምጃ ቤት ሹም
አቶ ክበበው ቡልቶ ( የኤርትራ ክፍለ ሀገር የE.D.D.C) ቅርንጫፍ ኃላፊ
አቶ ብርሀኑ ቡልቶ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ዳኛ ሲሆኑ በዘመነ ኢህአዴግ ደግሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ
ዶክተር ተስፋዬ ቡልቶ ደግሞ የአለርት የALERT ሆስፒታል ሜዲካል ዲሬክተር
ወይዘሮ ወርቅዬ ቡልቶ ደግሞ ለተወሰነ ጊዜ የጭነት ማመላለሻ ድርጅት(ጭ.ማ.ድ) ሠራተኛ
ወይዘሮ አልማዝ ቡልቶ በንግድ ዘርፍ (አስመጪና ላኪ)
በመሆን ሀገራቸውን በዘመናቸው አገልግለዋል ።
አቶ ቡልቶ ኤጄርሳ ምንም እንኳ በዘመናቸዉ የ19 ጋሻ መሬት (አሁን ሙገር ስሚንቶ ፋብረካ ያለበትን መሬት ጨምሮ ) ባለባት የነበሩ ቢሆንም ልጆቼን የመሬት ወራሽ ከማደርጋቸዉ ባስተምራቸዉ ይሻላል በማለት በዘመኑ ከፍተኛዉን ዉሳኔ በመወሰን ልጆቻቸዉን በማስተማራቸዉና ለከፍተኛ ወግና ማዕረግ አብቅተዋል ።
በአሁን ወቅት ዶክተር ተስፋዬ ቡልቶ ፤ ወይዘሮ ወርቅዬ ቡልቶ (የባሮ ቱምሳ ባለቤት የነበሩ ) እና ወ/ሮ አልማዝ ቡልቶ በህይወት ይገኛሉ ፡፡
የአቶ ቡልቶ ኤጄርሳ ልጆች በአደአ በርጋ ወረዳ አስተዳደር ሥር ቢላቻ ተብሎ ከሚጠራው መንደር የነበራቸውን የገጠር መሬትና ቤት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሥሪያ በፍቃዳቸው ሠጥተዋል ፡፡ በዐለ-እግዚአብሔር የሚባል ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
#አብዮታዊው_ሰራዊት_ገፅ