June 16, 2022
12 mins read

የኢዜማ ሚዛን ለባለቤቶቹ ትመለስ! – ከኡመር ሽፋው

ezema 1 2

የኢዜማ ሚዛን ለባለቤቶቹ ትመለስ!
(ከኡመር ሽፋው – May 16, 2022)

ezema 1 2የኢዜማ አርማ የሆነችው ሚዛን በዜግነት ፖለቲካ፣ በነፃነትና በማህብራዊ ፍትህ ስም ያልተፈፀመባት ወንጀል የለም። ይህ አስተያየቴ የኢዜማን ተራ አባሎች ላይመለከት ይችላል። ዘግይቶም ቢሆን በቅርቡ መናገር የጀመረውን  አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ አመራሮቹን ግን በሙሉ ይመለከታል። ሚዛን የፍትህ ምልክት ናት። ስለሆነችም በየትም ዓለም በፍርድ ቤት ሕንፃዎች ላይ እናያታለን። የኢዜማ አመራሮችም ፓርቲያቸውን ሲመሠርቱ ሚዛንን እንደአርማ የመረጧት የፍትህ ምልክትነቷን እሳቤ ውስጥ በማስገባት ነው ብዬ ለማመን እወዳለሁ። ነገር ግን ባለፈው ሦስት ዓመት በተግባር ያስዩት ሚዛኗ የቆመችለትን የሚያንፀባርቅ አይደልም ብቻ ሳይሆን ወገናችንን ለብዙ መከራና ሥቃይ የዳረገ ነው። (የኢዜማን ፀረ ሕዝብ አካሄድ በተመለከተ “የኢዜማ መኢሶናዊ ጉዞ” (May 5, 2022) በሚል ርእስ የጻፍኩትን እንድትመለከቱ እጋብዛችኋላሁ።)

የኢዜማ አመራሮች ለሕዝብ የገቡትን ቃል ረስተው የፍትህ ፀር የሆነውን የአብይ አህመድን ዘረኛና ተረኛ መንግሥት ዙፋን ላይ ተደላድሎ እንዲቀመጥ በማገዛቸውና አይተው እንዳላዩ በመሆናቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ከቄያቸው ተፈናቅለዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ቤተእምነቶች፣ የታሪክ ቅርሶች፣ መሰረተ ልማቶችና ከተማዎች ወድመዋል። በተለይ አማራ በማንነቱ እንደበግ ታርዷል። በአጭሩ በቀጥተኛ ቋንቋ የኢዜማ አመራሮች ይቅርታ የማይቸረው ክህደት ፈጽመዋል። የቆምነው ለሕዝብ ነው፣ ለነፃነት ነው፣ ለዜግነት ፖለቲካ ነው፣ ለፍትህ ነው ካሉ በኋላ የኢዜማ አመራሮች ፍፁም ተጻራሪውን በሚተገብር መንግሥት ጎን በፈቃደኝነት ስለቆሙ ሌሎቹ በማኒፌስቷቸው ያወጡትን ተንተርሰው ወገን ቢጨርሱ፣ ሕዝብ ቢያፈናቅሉ፣ ከተማ ቢያቃጥሉና ሃገር ቢያወድሙ ለምን ይደንቀናል እንድንል አድርገውናል።

ሰሞኑን ለኢዜማ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረው የፓርቲው ም/ፕሬዚዳንት አቶ አንዱዓለም አራጌ ለሪፖርተር፣ ለአንድ አፍታና ለኢሳት ኢትዮጵያ ቃለ ምልልስ ሰጥቷል። በቃለምልልሶቹ ላይ ኢዜማ የከሸፈ ፓርቲ መሆኑን አምኖ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የፓርቲውን አሳፋሪ ጉዞ የደፈደፈው በሊቀመንበሩ በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ላይ ነው። እርግጥ ነው ዶ/ር ብርሃኑ ወገናችንን የበደለው በደል ታሪክ አይረሳውም  ብለን ብቻ የምናልፈው ባይሆንም ሌሎቹም የኢዜማ አመራሮች ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ የወገናችን ግንዛቤ ነው። በሌላ አነጋገር፣ የሰማዩን ለፈጣሪ እንተወውና፣ ጊዜና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ዶ/ር ብርሃኑ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች ጭምር በምድር ላይ ለፍርድ እንዲቀርቡ የምንመኝ ጥቂቶች አይደለንም።

ግንቦት 7 ጓዙን ጠቅልሎ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ ብቅ ሲል እንደአንድ የሃገር መሪ በትልቅ አዳራሽ ውስጥ ትልቅ ዝግጅት ተደርጎ በጭብጨባ፣ በመዝሙር፣ በዋካታና እልልታ እንቀበለው ነበር። ዛሬ ግን የአምባገነኑ አብይ አህመድ ቀኝ እጅ በመሆኑ  ያጨበጨብንበትን እጃችንን እና የዘመርንበት አፋችንን እየረገምን እንገኛለን። ልክ ጠ/ሚ አብይ አህመድ በሕልማችንም ሆነ በእውናችን ባልጠበቅነው ቦታ በመዋል ወገናችን ክፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለለትን ትንሳኤ እንዳልነበር እንዳደረገው ሁሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም ባላሰብነው ቦታ ተከሰቶ የተረኞች መሣሪያ በመሆኑ ዛሬ ሃገራችን በጣር ላይ ትገኛለች!

አቶ አንዱዓለም አራጌ ለአንድ አፍታ በሰጠው ቃለምልልስ ላይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከቤተሰቡ ይልቅ የብልጽግና ፓርቲ ይበልጥበታል፣ ብልጽግና ከሚተችበት ቤተሰቡ ቢተችበት ይመርጣል ብሎ ነግሮናል። አቶ አንዱዓለም አራጌ የራሱን የሦስት ዓመት ዝምታ ተውኔታዊ በሆነ መንገድ ሠብሮ ለመውጣት አስቦም ይሁን ወይም የኢዜማ ፕሬዚደንትነትን ለማሸነፍ ብሎ፣ ሃቁን በማውጣቱ ግን ሊመሰገን ይገባዋል። ዝም ያልኩት የፓርቲው ዲሲፕሊን ይዞኝ ነው ያለው ግን ፍጹም ተቀባይነት የለውም። ለመሆኑ እሱ ዛሬ ስለፓርቲ ዲሲፕሊ ሲጨነቅና ዝምታን ሲመርጥ ከአራት ዓመት በፊት እሱ ከእሥር እንዲፈታ ብዙዎች ሕይወታቸውን እንደገበሩ እንዴት ዘነጋው? የሆነው ሆኖ በዝምታው ተጠያቂነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ስለፕሮፌሰር ብርሃኑ የተናገረው ግን ጥያቄ የሚነሳበት አይደለም። ያም ሆነ ይህ ፕሮፌሰሩ እንደገና የኢዜማ ሊቀመንበር ሆኖ ቢመረጥ በቀየሰው ድንበር የለሽ ግንኙነት ኢዜማ የብልጽና አጎብዳጅ ሆኖ እንደሚቀጥል ሳይታለም የተፈታ ነው። እዚህ ላይ ጥያቄው መሆን ያለበት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ቢያሸንፍ አቶ አንዱዓለም አራጌ የፓርቲውን ዲሲፕሊን በማክበር እንደአለፈው ሦስት ዓምት እንደገና አርምሞ ውስጥ ይገባ ይሆን ወይስ ፓርቲውን ጥሎ ይወጣል የሚለው ነው።

አቶ አንዱዓለም አራጌ ኢትዮጵያ ከአብይ ሌላ አማራጭ የላትም ብሎ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ያምናል ያለው  ፕሮፊሰሩን እንደሚያውቅ አንድ ግለሰብ ማመን ነው ያቃተኝ። እውን ኢትዮጵያ እንደዚህ መካን ናት?! በጣም ያስደነግጣል! ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንደ አቶ አንዱዓለም አራጌ ይመለስ ይሆናል የምትሉ ተስፈኞች ካላችሁ እርማችሁን አውጡ! አዎ አብይ አህመድ የአብኑን በለጠ ሞላንና ፕሮፌሰር ብርሃኑን አውሮፓ ይዟቸው በመጓዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ አለ ለማስባል ሲነግድባቸውና ሲተውንባቸው ባየሁ ጊዜም ደንግጬ ነበር።

በነገራችን ላይ ፕ/ር ብርሃኑ ሰሞኑን ወደዋሺንግተን ዲሲ ብቅ ባለ ጊዜ ከላይ በአቶ አንዱዓለም አራጌ የቀረበበትን ክስ አረጋግጦልናል ማለት ይቻላል። የትምህርት ሚንስትር እንደመሆኑ መጠን ትምህርት ነክ ጉዳዮችን ለማወያየት በሚል ሽፋን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸውን ብቻ ሰብስቦ ዘረኛውን የአብይ አህመድን መንግሥት መደጋፋቸውን እንዲቀጥሉ እንደተማፀናቸው ሰምተናል። እንዲሁም ቀደም ሲል ከዲሲ ግብረሃል አስገንጥሎ ያስወጣቸውን ስብስቦች የማነቃቂያ ንግግር ((Prep Talk) አድርጎ ስለለቀቃቸው በአብይ አህመድ አምላኪዎች እየተደገፉ “የሰከነ ፖለቲካ” የሚል መፈክር አንግበው የሱን ገጽታ ለመገንባት ሰሞኑን በማህበራዊ ሚድያ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ከፍተዋል። በአንዱዓለም አራጌ ላይም ያላቸውን ሁሉ እያራገፉበት ነው።

ወደጽሁፌ ርእስ ልመለስና ኢዜማ አሁን ባለበት እጅግ አሳፋሪ ቁመናው እንደአርማ የሚጠቀምባትን የፍትህ ሚዛን ፈጽሞ አይመጥንም። ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ ኢዜማ በዶ/ር ብርሃኑ መሪነት ከአብይ አህመድ ጋር ተጣምሮ በመሥራቱ በወገናችን ላይ የደረሰው መከራ ባለፈው 200 ዓመት ፈጽሞ አልታየም።  ስለሆነም የኢዜማ አርማ መሆን ያለበት ሸክም የሚችል እንሰሳ፣ የጭነት መኪና ወይም ሌላ ነገር እንጂ ለዘመናት የፍትህ ምልክት ሆና የቆየችው ሚዛን መሆን የለባትም። ሚዛኗ የምታምርባቸው በታፈኑት ጋዜጠኞች በነታድዮስ ታንቱ ላይ፣ በነተመስገን ደሳለኝ ላይ፣ በነመአዛ መሐመድ ላይ፣ በደራሲና መምህርት መስክረም አበራ ላይ፣ በኢኮኖሚስቱና ተንታኙ ሰሎሞን ሹምዬ ላይ፣ አብይ አህመድ በሚያሳድደው  የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ እና ሌሎችም ላይ ነው። ስለዚህ ኢዜማ የፍትህ ሚዛኗን ለባለቤቶቹ ይመልስ!

በመጨረሻ ኢዜማ እንደፓርቲ ባስቸኳይ ቢከስም ለሁሉም ይበጃል የሚል እምነት አለኝ። ኢዜማን ማስቀጠል ማለት የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም የአማራውን ስቆቃ ማስቀጠል ማለት ነውና!

2 Comments

  1. ስለነ ብርሃኑ ነጋ ተጨማሪ ምስጢሮች፤
    እነ ብርሃኑ ነጋ ህብረትን አፍርሰዉ ቅንጅትን መስርተዉ ወደ97ቱ የዉሸት ምርጫ ዉስጥ የተሳተፉት በገንዘብ ስለተገዙ ነዉ የሚባል ምስጢር አለ፤ ብርሃኑ 50 ሚሊዮን፤ ሃይሉ ሻወል 70 ሚሊዮን በብድር መልክ እንደተቀበሉ ይሰማል። ብርሃኑ ሆቴሎቹን ሲያስፋፋ ሀይሉ ደግሞ በልጁ ስም የምህንድስና ኩባኒያ እኢነደከፈተ ይነገራል። ታዲያ አሁን ችግር ቢፈጥሩ ብድሩን መልሱ ስለሚባሉ ሊሆን ይችላል መንግሥትን በጭፍን የሚደግፉት።

  2. Regarding Berhanu a lot have been said, his Merkatos experience is clearly reflected on his political life. Deceit, lie, inconsistencies,opportunism are some of his personal trade mark. With his friend Andargachewu they are good in motivating people who have intellectual deficit. Him,Aregawi Berhea,Dawud,Ibsa, Lencho bati leta are the ???? of Ethiopia. Unlike others Berhanu is regarded as a professor ,in reality we haven’t heard any intellectual statements from him, he even didn’t get the courage to stand infront of Ledetu for political debate. He will keep messing up the country as long he has weak followers like him.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

abiy shirak
Previous Story

የጠቅላያችን ንግግር እና የአእምሮ ህመም ምልክቶቾ – የሽዋስ ዘወልድያ ሚካኤል (የስነ አእምሮ ባለሙያ)

Abiy ugly
Next Story

ዐብይ አሕመድ ወይስ ጭራቅ አሕመድ? – መስፍን አረጋ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop