ዐብይ አሕመድ ወይስ ጭራቅ አሕመድ? – መስፍን አረጋ

June 16, 2022

Abiy uglyየዐብይ አሕመድ አንድና ብቸኛ ዓላማ የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ አጥፍቶ የኦሮሞን አጼጌ (oromo empire) በመመሥረት በቀሩት ኢትዮጵያውያን ላይ በግድ መጫን ነው ማለት የአዋጁን በጆሮ ነው፡፡  በዚህ ኦነጋዊ ዓላማው መሠረት ባለፉት ዐራት ዓመታት ይህ ነው የሚባል መሰናክል ሳያጋጥመው በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ የአማራን ሕልውና ከትልቅ የጥያቄ ምልክት ውስጥ ከሚያስገባበት ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ቀባሪውን ማርዳት ነው፡፡  በዚህ ፍጥነት መጓዙን እንዲቀጥል ከተፈቀደለት፣ ኦነጋዊ ዓላማውን ሙሉ በሙሉ የሚያሳካበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ማለት ደግሞ ያልታለመውን መፍታት ነው፡፡

ስለዚህም መሠረታዊው አንገብጋቢ ጥያቄ ዐብይ አሕመድ ፀራማራ ዓላማውን ለማሳካት ምንም መሰናክል ሳያጋጥመው በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ አሁን ከደረሰበት ወሳኝ ደረጃ ላይ ሊደረስ የቻለው ለምንድን ነው የሚለው ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ ለዚህ ደረጃ የበቃው በኦነጋዊ ሠራዊቱ ሊሆን አይችልም፣ የኦነግ ሠራዊት ጨለማን ተገን አድርጎ ቤታደሮችን (civilians) ከማረድ በስተቀር በታሪኩ አንድም ጊዜ ድል ማድረግ ቀርቶ በቅጡ ተዋግቶ የማያውቅ ግሳንግስ ሠራዊት ነውና፡፡  ዐብይ አሕመድ ለዚህ ደረጃ የበቃው ፀራማራ ዓላማውን ከሚጋራው ከወያኔ ጋር ስለሚመሳጠርና ስለሚተባበር ሊሆን አይችልም፣ የወያኔ ሠራዊት እስካፍንጫው ቢታጠቅም በአማራዊ አዛዥ ከሚመራ የአማራ ሠራዊት ፊት መቆም እንደማይችል ቅራቅርና ሌሎች የምዕራብ ጎንደር የጦር ዐውድማወች በግልጽ አስመስክረዋልና፡፡

ዐብይ አሕመድ እዚህ ደረጃ ሊደርስ የቻለው የሕልውና ጠላቱ እሱና እሱ ብቻ መሆኑን የአማራ ሕዝብ በጽኑ ተረድቶ በጹኑ ስላልታገለው ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ዐብይ አሕመድን ከጫንቃው ላይ ካወረደ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡  መለስ ዜናዊ ሲሞት ወያኔ እንደፈራረሰ፣ ዐብይ አሕመድም ሲወገድ ከመሬት አንስቶ ሰማይ ያደረሰው ኦነግና፣ ከሞት አፋፍ አንስቶ እንዲያንሰራራ ያደረገው ወያኔ ሁለቱም ፍርስርሳቸው ይወጣል፡፡

የአማራ ሕዝብ ዐብይ የሕልውና ጠላቱ የሆነውን ዐብይ አሕመድን ማስወገድ የሚችለው ግን በጽኑ ሲታገለው ብቻ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ዐብይ አሕመድን በጽኑ የሚታገለው ደግሞ ዐብይ አሕመድ የአማራን ሕዝብ በጽኑ የሚጠላውን ያህል የአማራ ሕዝብም ባጸፋው ዐብይ አሕመድን በጽኑ ሲጠላው ነው፣ በጽኑ ያልጠላኸውን በጽኑ አትታገለውምና፡፡  የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን ማስቀጠል የሚችለው ዐብይ አሕመድን በጽኑ ጠልቶ በመጸየፍ አር እንደነካው እንጨት አሽቀንጥሮ ሲጥለው ብቻና ብቻ ነው፡፡

ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሕልውና ያሳስበናል የምትሉ የሚዲያ ሰወች፣ ይህን እኩይ ፀራማራ ግለሰብ ዶክተር፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ እሳቸው እያላችሁ በማይገባው ክብር በመጥራት የአማራ ሕዝብ ጽኑ ጠላቱን በጽኑ እንዳይጠላ አታድርጉት፣ በክብር የሚጠሩትን በጽኑ አይታገሉትምና፡፡

ዐብይ አሕመድ ለአማራ ሕዝብ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሳይሆን በላዔ አማራ ጭራቅ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ የአማራን ሕዝብና አማራዊ አመራሮቹን በግፍ ከጨፈጨፈና ካስጨፈጨፈ በኋላ ከፍተኛ ደስታውን አበባ በመትከልና ሕንፃ በመመረቅ በይፋ የሚገልጽ ኦነጋዊ አረመኔ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ እኔን ብትነኩ መቶ ሺወቻችሁ ባንድ ጀምበር ትታረዳላቸሁ እያለ በግላጭ የሚዝት፣ ባራጅ ሠራዊቱ የሚተማመን ኦነጋዊ አራጅና አሳራጅ ነው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ይህን ኦነጋዊ አውሬ በማናቸውም መቸት (መቸና የት) ላይ መጥራት ያለበት ዐብይ አሕመድ ብሎ ሳይሆን ጭራቅ አሕመድ ብሎ ነው፡፡  ግራኝ አሕመድ ዛንተራ ላይ ወደቀ፡፡  ጭራቅ አሕመድስ የሚወድቀው የት ይሆን?  ሰንጋተራ?

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

5 Comments

 1. መስፍኔ (የአሳምኔ ሠፈር ልጅ)፣
  የአገርህ ልጅ የሽዋስ ዶ/ር ዐቢይ አእምሮው ልክ አይደለም ብሏል። አንተ ደግሞ “በላዔ አማራ ጭራቅ” ነው ብለሃል። ሁለታችሁ የሚታያችሁ ነገር ቢኖር ነው። ለካንስ ማታ ማታ የምሰማው ጅብ ዶ/ሩ ናቸው! ብዙ ጊዜህን በዚህ ጒዳይ እንደምታጠፋ ስላስተዋልኩ፣ ምናልባት ሥራ ፈት የሆንክበትን ምክንያት ልረዳ ፈልጌአለሁ። ለመሆኑ፣ ከሽዋሴ ጋር አብራችሁ ነው የምትኖሩት? አደራ ቶሎ መልሱን ፃፍልኝ።

  • Yes, Alem, you are disturbed by the laugh of hyenas while trying to enjoy your evenings.

   Sorry for that. However, no wonder! The country, in particular our ADDIS, is infested by DONKEYS. What can the hyenas do?

 2. Abiy Ahmed’s vision for Ethiopia are more aligned with IFLO (Islamic Front for the Liberation of Oromia) than OLF (Oromo Liberation Front) and he is heading towards the establishment of the Islamic Oromo State. The 4-year reign of terror in Wellega is in line with weakening the Christian Wellega Oromo that was at the helm of the OLF movement in the previous century. Wellega has been encircled by Muslim Somali Oromo, millions of them settled by June’idi Sado. Addis Ababa has been run over by a million of the same (Abiy-Lema operation). The Shewa Christian-majority OFC was hijacked and infiltrated by Jawar and Co. Connect the dots and you will see where the Oromia ship, waving the flag of radical Islam, is being guided to.

 3. ይህ ያስቅ ይሆን ወይስ ያሳዝናል? በንዴት ስትንጨረጨር ፅሁፍህን የጠላ ቤት ወሬ አደረከው grow up man ዐቢይ አሕመድን ሚሊዮኖች አማሮች መርጠውታል ጥቂት በጥባጭና ባለጊዜዎች በጉልበት ስልጣን ለመንጠቅ ቢዋትሩም ጤዛ ሆነው ይቀራሉ:: እኔ 100% አማራ ነኝ ዐቢይ አሕመድ ፀረ አማራ ነው ብዬ እራሴን አላጃጅልም ይህ የፈረደበት ዐቢይ ያንተ ቢጤ ፅንፈኛው ኦሮሞ ነፍጥኛ ነው እያሉ ሊያጠፉት ይፈልጋሉ እናንተ ደግሞ ፀረ አማራ ነው ውንጀላችሁ ተገናኙና የሚያስማማችሁን ምረጡ:: ኢትዮጵያውያን ዐቢይን መርጠዋል ድምፃቸው ይከበር

 4. እውነቱና አለም የጠላ ቤት ወሬ ሁኖባችሁ ነው ማስታወሻ እየወሰዳችሁ ያነበባችሁት? በናንተ ቤት ሞራል መጣላችሁ ነው መስፍን ቀለብ ይሰፍርላችኋል እራስችሁን አታዋርዱ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ezema 1 2
Previous Story

የኢዜማ ሚዛን ለባለቤቶቹ ትመለስ! – ከኡመር ሽፋው

Abiy Wusha
Next Story

የአንድ አገር መሪ በዘር ማጥፋት ፍጅት ማነሳሳት ሊከሰሱ ይገባል

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop