ምዕራብ ጎጃም ጸጉራሙ ውሻ (ይሁኔ አየለ)

June 15, 2022
abiy diskur“እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር”
የሚል ህዝብ ለእውነት ክብር ያለውና ለእውነት ወጋኝ ነው። “ውሸትን ከእውነት መለየት አለመቻል ትልቁ የክስረት ምልክት ነው” ይላሉ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም። ውሸትን አለማውገዝም እንዲሁ የክስረት ምልክት ይመስለኛል።
ስለሆነም ውሸትን አጋልጣለሁ።
የምእራብ ጎጃም ህዝብ ተዋሽቷል። ምእራብ ጎጃም ጸጉራም ውሻ ነው፣ አለ ሲባል ሞቶ የሚገኝ። ምእራብ ጎጃም ከአጼው ሥርዓት ጀምሮ እስካሁን ያለው አስፋልት መንገድ አንድ ብቻ ነው። እሱም ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳርና ጎንደር የሚዘልቀው ነው።
በምእራብ ጎጃም በዋናው በመንገድ ላይ ካሉት ከተሞች ውጭ ያሉ የወረዳ ከትሞች አስፋልት ምን እንደሚመስል የሚያውቁ ። ሌላው ቀርቶ የዘመኑ ኮብል ስቶን እንኳ ገና አልደረሰም። ምእራብ ጎጃም ከአራት ሚሊዮን ህዝብ በላይ የያዘና ብዙ ተማሪዎችን የሚያሳልፍ ቢሆንም እንደ ሌሎች የአገሪቱ ዞኖች ዩኒቨርሲቲ የማግኘት እድል አልገጠመውም። የመብራት ስርጭቱም እንዲሁ ነው። የለም በሚባልበት ደረጃ ያለ ነው።
ቢሆንም ዞኑ በክልሉም ሆነ በፌደራል መንግስቱ ባለስልጣኖች “ትርፍ አምራች” ተብሎ ውሸት ይነዛበታል።
በዚሁ አንድ ትዝብቴንም ላካፍል፣ በዚህ ዓመት የሰቆጣ ቃልኪዳን የሚባለውና የህጻናትን መቀንጨርና ጽኑ ረሃብን ለማስወገድ የተቋቋመ ድርጅት ከዞኑ አንድም ወረዳ አላካተተም። ምክንያቱ ደግሞ ትርፍ አምራች የሚል ፕሮፖጋንዳ ስለተነዛ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በ2012 ዓም ጀምሮ ወረዳዎችን የሚያገናኙ መንገዶች ይሰራሉ ተብለው ለህዝብ ይፋ ሆኖ ነበር። በቅርቡ ካምፖችና አልፎ አልፎ ቁፈራዎች ከመጀመር ያለፍ ይህ ነው የሚባል ስራ አልተሰራም። 3 ዓመታት አልፈዋል ግን ምንም የሚታይ ነገር የለም።
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አጉልቶና አድምቆ ምዕራብ ጎጃም 504 ኪሎ ሜትር መንገድ ተሰርቶለታል ይለናል። ጸጉራም ውሻ ማለት ይህ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Meskerem Abera
Previous Story

መስከረም አበራ በዋስትና ከእስር ተለቀቀች

abiy
Next Story

ለማመን የሚከብዱ – ዓባይነህ ካሤ

Go toTop