ዕድገት ወይስ ዉድመት? – ዶ/ር በቀለ ገሠሠ

ዶ/ር በቀለ ገሠሠ – ሰኔ 2014 ዓ/ም (drbekeleg@gmail.com)

1ኛ/ መንደርደሪያ፡

እጅጉን ግራ ገብቶኛል። እንቅልፍና ዕረፍት አጥቻለሁ። ብዞዎቻችሁም በዚህ ጭንቀት ዉስጥ እንደምትገኙ አልጠራጠርም። ባሁኑ ዘመን ሁሉም ዓለም (ምናልባት ከኢትዮጵያና ከዩክሬን በስተቀር) በዕድገት ላይ እየተረባረቡ ይገኛሉ። የአካባቢ የአየር ብክለት ለመቀነስ እየሞከሩ ይገኛሉ። ከኮሮና ወረርሺኝ ኪሣራ ለመዉጣት እየተፍጨረጨሩ ናቸዉ። የአገር ኢኮኖሚ በማሳደግ የሥራ ዕድሎች ለመክፈት፤ ለወጣቶች የትምህርት ዕድልና እንክብካቤ ለመስጠት፡ ወዘተ፤ በመሯሯጥ ላይ  ይገኛሉ።

በዉዲቷ አገራችን ግን የሚታየዉ ፍጹም ተቃራኒዉ ነዉ። ዘርና ሃይማኖት እየመረጡ መግደልና ማፈናቀል፤ ትምህርት ቤቶችንነና ንብረቶችን ማቃጠል፤ መዝረፍ፤ እስራት፡ ወዘተ እየተበራከቱ ይገኛሉ።

ትምህርት ቤቶችና የተማሪዎች መረጃዎች እየተቃጠሉ፤ ወጣቶችን ለጦርነት ወይም ለስደት እየዳረጉ ትምህርት ማስፋፋት ሆነ ዕድገት ማምጣት እንዴት ይቻላል? እንደዚሁም ንብረቶች፤ ማሳዎችና ከብቶች እየተቃጠሉና እየተዘረፍ እንዴት ስለዕድገት ማሰብ ይቻላል? ዜጋ በገዛ ሀገሩ በነፃ ተዟዙሮ መነገድ ካልቻለ እንዴት ከድህነትና ከእልቂት ሊተርፍ ይችላል? አሁን በዉጪ አገራት በገፍ ተበትነዉ የሚታዩ የኢትዮጵያ ወጣቶችን ስመለከት እንባዬ ይመጣል። እነዚህ በሀያ አካባቢ ዕድሜ ዉስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ተቸግረዉና ጠዉልገዉ በየመንገዱ ሲንገላወዱ ማየቱ እጅግ በጣም ያሳዝናል። በዐረብ አገራት ዉስጥ በባርነትና በእስር ቤቶች ዉስጥ  እየማቀቁ የሚገኙትን ወገኖች ማየቱም እጅግ በጣም ያሰቅቃል። አገራችን ሰፊና ህዝባችን ብርቱ ሠራተኛ በሆነበት ዉስጥ ለምን ለነዚህ መከራዎች ልንዳረግ በቃን? ወገን እንደቅጠል እየረገፈና የአገሪቷ ሕልዉና በከባድ ፈተና ዉስጥ በወደቀበት ወቅት ዝም ብለን ማየት አይኖርብንም።

1ኛ/ አማራ የማንም ጠላት አይደለም

በየደረስኩባቸዉ ሰፈሮች ሁሉ ያየሁት የተለያዩ ጎሣዎች በመጋባት፤ በጉርብትና፤ በዕድር፤ በምዕመንነት፤ ወዘተ በሰላም ተሳስረዉ አብረዉ እንደኖሩ ነዉ። የባላባታዊዉንም ሥርዓት ብንወስድ የአማራ ብቻ እንዳልነበረ ታሪክ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ሥርዓቱ በከፋም፤ በወለጋም፤ በወላይታም፤ በአፋርም፤ ወዘተ የነበረ ነዉ። የጂማዉ አባጂፋር 10000 ዜጎችን አስረዉ በባርነት ወደአረቦች ሊሸጡ ሲሉ አፄ ምኒልክ ተቆጥተዉ እንዳስቆሟቸዉ ታሪክ ይናገራል። በደቡብ አንድ ባላባት ሲሞት ሁለት ድሆች በህይወታዉ በአስከሬኑ ግራና ቀኝ አብረዉ እንደሚቀበሩ የሚናገሩ ታሪኮች አሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ከሰው ያቀያይማል"??? - ጠገናው ጎሹ

ነገር ግን ዶ/ር መረራን ጨምሮ ብዙዎች እንደዘገቡት ለመሬት ላራሹና ለእኩልነት ትግል ከፍተኛዉን የህይወት መስዋዕትነት የከፈለው ዛሬ የተፈረደበት የአማራ ልጅ ነዉ። በዚያ አኩሪ የትግል ዘመን የ14ቱም ጠቅላይ ግዛት/ ክፍለሀገር ልጆች በዘርና በሃይማኖት ሳይለያዩ ባንድነት ነበር ታግለዉ አኩሪ መስዋዕትነት የከፈሉት። በጭቁኑ አማራና ትግሬ፤ አማራና ኦሮሞ፤ አፋርና ትግሬ፤ ወዘተ መካከል ምንም ልዩነትና ጠላትነት አልነበረም። አምባገነኖች ህዝቡን ከፋፍለዉ ለመግዛት በሚጠቀሙበት መርዘኛ ወጥመድ ዉስጥ መግባት የለብንም።

ዳሩ ግን የአምባገነን መሪዎችን ወንጀል ለመሸፈን ሲሉ የዚያን ዘመን ወጣቶችን በሙሉ ባንድ ላይ ለመጨፍለቅ የሚፈልጉ ካድሬዎች ሞልተዋል። በማንኛዉም ዘመን አርበኞች እንዳሉ ሁሉ ባንዳዎችም ሞልተዋል። በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት የእንግሊዝ ወራሪ ኃይሎችን መንገድ እየመሩ ያስመቷቸዉ ባንዳዎች ነበሩ። ለጣሊያ ፋሺስቶች ተገዝተዉ ከፍተኛ ጉዳት ያስደረሱ ባንዳዎች እንደነበሩ ከአርበኛዉ አባቴና ከታሪክ የተማርኩት ሃቅ ነዉ። ከወታደራዊዉ የደርግ አምባገነናዊ መንግሥት ጎን በመሰለፍ የንፁሐን ዜጎችን ደም እንደጎርፍ ያስፈሰሱ ባንዳ ካድሬዎች ነበሩ። ባንዳ ምን ጊዜም ለሆዱ እንጂ ለወገን አይሳሳም።

2ኛ/ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በጎ እምነትና ጥበብ በሰጠ ለምን ተጠላ?

ታሪክ ቁልጭ አድርጎ እንደሚያሳየዉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ለኢትዮጵያና ለዓለምም ጭምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ግሩም ሃይማኖት ነዉ። የሌሎችን እምነት ያከብራል። የተቸገረዉንና የተሰደደዉን ይቀበላል። ለእመነት ብቻ ሳይሆን ለባህልና ለጥበብ እድገትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ዛሬ ግን በባልንጀራህ ላይ በሀሰት አትመስክር ብሎ ባስተማር በራሱ ላይ በሀሰት ሲመሰከርበት እናያለን። እናትህንና አባትህን አክብር ብሎ ባስተማር ዛሬ አባቶችና እናቶች በግፍ ሲገደሉና ሲቃጠሉ እናያለን። አትግደል ብሎ እያስተማረ ይገደላል። አታመንዝር ብሎ እያስተማረ ምግባረ ብልሹዎች በዝተዋል። አትስረቅ ብሎ እያስተማረ የሀገር ሀብት በገፍ ይመዘበራል። ባልንጀራህን እንደእራስህ ዉደድ  ብሎ እያስተማረ የጥላቻና የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲንሰራፋ ይገኛል። የተራበ ማብላትን፤ የተጠማ ማጠጣትን፤ እንግዳ መቀበልን፤ ወዘተ እያስተማረ ህዝባችን ግን ሲፈናቀል፤ ሲሰደድና ሲማቅቅ ይታያል። ስለዚህ ከባዱ ችግሩ ያለዉ ከኦርቶዶክ እምነትና ተከታዮች ሳይሆን ከጨፍጫፊ አረመኔዎች ዘንድ መሆኑ ታዉቆ እርምት እንዲደረግ ማድረግ ይጠበቃል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕዝብ ሆይ! እንደማመጥ እንጅ! ጋሰለ አረሩ፤ አዴፓ ብአዴን፤ ብልጽግናም ይህ አድግ ነው!  

3ኛ/ ካለፉት ጥፋቶችና ወንጀሎች መማር እንዴት አቃታቸዉ?

ካለፉት የዓለም ነዉረኛ ታሪኮች መማር ይኖርብናል። ናዚ ጀርመኒ በተለይ በአዉሮፓ ላይ ያስከተለዉን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ እናዉቃለን። ዛሬ ግን ከስህተቶቻቸዉ ተምረዉ የአዎሮፓ ሕብረትን መስርተዉ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገትና ሰላም ዉስጥ ይኖራሉ። ፋሺስት ኢጣሊያም በወላጆቻችን ላይ ያስከተለችዉን አስነዋሪና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ምን ጊዜም አንረሳዉም። በሩዋንዳ የተካሄደዉ አስፈሪ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ታሪክ አለ። እነርሱ ግን ዛሬ ተታርቀዉ ሰላም አዉርደዉ በጥሩ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ይገኛሉ። ፋሺስቱ ደርግ የአገር መሪዎችን እንዴት አድርጎ እንደገደለ፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በቀይ ሽብር በወላጆቻቸዉ ፊት እንዴት እንደጨፈጨፈና የታወቁ ጄነራሎችን እንዳስረሸነና በመጨረሻ ሥልጣኑን ለሻቢያና ለወያኔ አስረክቦ ጣጣ ዉስጥ ከትቶን እንደፈረጠጠ ስንመለከት በጣም ያማል።  አሁን ከነዚያ ሁሉ አሳፋሪ ታሪኮች ተምረን ወደፊት መራመድ ሲገባን እነዚያን ጥፋቶች መድገሙና ማባባሱ ለማንም አይበጅም፤ ተያይዞ መጥፋትን ያስከትላል፤ ይዋል፤ ይደር እንጂ በሕግም ያስጠይቃል። ስለዚህ ሁኔታዎቹን ለማስተካከል እያንዳንዳችን የየአቅማችንን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርብናል። በጎ ፈቃድ ካለ መፍትሔ መንገድ ይገኛል፤ በእግዚአብሔር ኃይል።

4ኛ/ የዉሸት ትርክቶችን የማረም ግዴታ አለብን

ተስፋዬ ገብረአብን የመሳሰሉት የሻቢያና ወያኔ ካድሬዎች የረጩት የዉሸት ትርክቶች ብዙ ጉዳቶች አድርሰዋል። በዘመነ መሳፍንት ምትክ ታላቅ ሀገር መልሶ የመገንባት ጥረት በእነ አፄ ቴዎድሮስና አፄ ዮሐንስ ተጀምሮ በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት መሳካቱ ግልፅ ነዉ። በሂደቱ አንዳንድ ጉዳቶች የደረሱ ቢሆኑም ተልዕኮዉ ቀላል አልነበረም። ተመሳሳይ የዓለም ታሪኮችም ይሄንኑ ያሳያሉ። ሂደቱ ግን አንድነት መስርቶ ጠንካራ ህዝብ አድርጎ ከዉጪ ወረራ፤ ባርነትና ቅኝ ተገዢነት አዳነን። አፄ ምኒልክ ጡት አስቆራጭ አልነበሩም። ባንድ በኩል አፄ ምኒልክ ጡት ቆራጭ ናቸዉ እያሉ የዉሸት ትርክት እየረጩ ዛሬ በተግባር እየታየ ያለዉ ግን ጡት ሲቆረጥና ማህፀን ሲከፈት ነዉ። ዘርና ሃይማኖት እየመረጡ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች የታዩት በቅርቡ ነዉ። እላይ በተራ ቁጥር 1 ስር እንደተገለፀዉ ጭቁን አማራ የማንም ዘር ጠላት ሆኖ አያዉቅም። ልክ እንደሌሎቹ በገዛ አገሩ በተለያዩ ቦታዎች ሰፍሮ ለብዙ ሺዎች ዓመታት የኖረ ደግ ህዝብ ነዉ። ስለዚህ ባለማወቅ በክፉ ካድሬዎች ተታልላችሁ ጉዳት ያደረሳችሁ ሰዎች ከትክክለኛ ታሪክ በመማር ከወንጀላችሁ ታቀቡ፤ ወጥታችሁ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቁ። ነገር ግን የዉሸት ታሪክ መሆኑን እያወቃችሁ ለርካሽ ፖሊቲካ መጠቀሚያ ያደረጋችሁ የመንግሥት አካላት ብታርፉ ይሻላችኋል፤ ህዝቡ በደንብ እየነቃ ነዉና። በሕግም እንደሚያስጠይቃችሁ ተረዱ። የሞራል ግዳጅም ይኑራችሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እባቡ እየተቃረበ መጣ - ዶ /ር ምህረት ደበበ

5ኛ/ ከዉድመት ይልቅ በእድገት ላይ እናተኩር

ደጋግሜ ለመግለፅ እንደሞከርኩት አገራችን ሰፊ ናት። የወንዙንና የሀይቆቹን ብዛት፤ የብዝሃ ሕይወትን ስፋትና የመልክአ ምድሩን አቀማመጥ ስንመለከት ገነት እራስዋ በኢትዮጵያ ምድር እንዳለች ያስመስላል። እነግብፅ አንድ እንኳን ወንዝ ሳይኖራቸዉ በኢኮኖሚ ከኛ ተሽለዉ ይገኛሉ።

ሆኖም ግን አፈራችን ጥበቃና እንክብካቤ በማጣቱ ምክንያት እየተሸነሸነ ይገኛል። የአካባቢዉ አየር ብክለትም ሁኒታዎቹን እያባባሰ ይገኛል።

ስለዚህ እርስ በርሳችን በመጨራረስ ፋንታ በግንባታ ላይ ብናተኩር ይሻላል። ልጆች ማስተማርና የተማሩ ወገኖችን ማሰለፍ ይጠበቃል። አፈሩንና አየሩን  መንከባከብ ይጠበቅብናል። ወንዞቻችንን በሙሉ በመጠቀም የመስኖ እርሻዎች ማስፋፋት ይኖርብናል።

እነዚህን ለመፈፀም የሰላም መስፈን ተቀዳሚነት የሚሰጠዉ እጅግ አስፈላጊ ጥያቄ ነዉ።

መንግሥት የህዝብን ደህነነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ይጠበቅበታል። የመከላከያ ጦር ድንበርን መጠበቅና መከላከል ይጠበቅበታል። የፀጥታዉ ኃይል የህዝብ ወገን በመሆን የሁሉንም ዜጋ  ደህንነት የማስጠበቅ ታላቅ ኃላፊነት ይጠበቅበታል። የሃይማኖት መሪዎች ሃቁን የመመስከር፤ የማስተማር፤ የተጣላዉን የማስታረቅና ለሀገር ባንድ ላይ ቆሞ የመፀለይ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። የፖሊቲካ ቡድኖች ለሀገር አንድነት፤ ለሰላምና ዕድገት መታገል ይጠበቅባቸዋል። እያንዳንዱም ዜጋ ህዝብ ሲያልቅ፤ ሲፈናቀል፤ ሀገር ሲፈርስ ቁጭ ብሎ ማየት የለበትም። ሁሉም ንስሐ ገብቶ ለህዝቡና ለሀገሩ ሰላምና አንድነት መፀለይና መታገል ይጠበቅበታል። እግዚአብሔር ይጨመርበት።

2 Comments

  1. One Shegitu Dadi, a very forward looking Oromo woman has the following to say on confederation. I’m copying and pastion her write-up without her authorization hoping that she’ll not mind.

    “Here is how to save Amharas, Oromos and the country.

    Once again in our recent history, Amharas have emerged as the holders of the MASTER key to solve Ethiopia’s multifaceted problems . How? By opting for confederation.

    Amharas have no choice but to move for confederation simply because federation in the Ethiopian context does not work.

    As a polirized multi-ethnic country, Ethiopia will not have a fair and free election without the opression of one or another ethnic group. Hence, democracy is an illusion that cannot be realized. The way Oromo rose to power and now control the entire country through proxy regional governments is the proof. Tigreans did it for the last thirty years and Oromos have stepped in Tigreans shoes to impose similar one ethnic group rule. With their number and size of their region, Oromo opressive rule will be much worse than Tigrean`s. Give another ten years to Oromo rule, Ethiopia will be the tail of the world by all standards of measure.

    So, it is time for Amharas to exercise their constitutional right to self-determnation and vote on confederation. If they adopt conederation, it will give them the opportunity to attract direct foreign investment since confederation will enable them to have economic diplomats and even have embasies abroad cutting the Oromo controlled foreign ministry diverting foreign investment to Oromia and other favoured regions. Amharas can also have a defense force which will protect them from foreign invaders including ethnic Oromo organizations.

    The Belgian model of confederation which appears to hep advance Amhara interests is something to explore.

    In any event, Ethiopia needs vast decentralization resembling confederation since the federalism the country has adopted is notheing other than unitarism in disguise. Controlled from the centre, it has miserably failed to develop the country let alone prosper and ensure safety and security of its citizens. The chaos we see in the country right now has much to do with lack of development (in all sectors) and security. Both have proven beyond the capacity of the federal government to provide.Change of government at federal level is not the answer for these problems.

    Tigreans have floated the idea of confederation, Amharas must follow. Tigreans know that they will not be fairly treated under Oromo rule; as a result, their choice of confederation appears just. Amharas must seize the opportunity to decide their destiny via self-determination as well without wasting another decade under incompetent Oromo rule. Despite all the atrocities they have committed, Tigreans are being heard and embraced by the Oromo rule since Oromos now feel tobe the savours of Ethiopia.

    Folks! Don’`t be fooled!. Oromos pretend to be “savours” only if they rule the entire country as one piece. Like any other ethnic group that aspire to oppress and dominate , they are after resources. If Amharas want to be heard and embraced as Tigreans, they have to go for confederation. If confederation does not work, they have to say good bye to the Ethiopian state.

    It is outdated for Amharas to hang on “mama ethiopia” cry since nobody in the country is interested in it any more. What Amharas got from this cry is atrocotoes, redicule and shame. All these on Amhara because they gave Oromos and other ethnic groups a country which they are not ready and willing to let go. If Amhara Insist on confederation, Oromos might call the army on it to protect the unity of the country! That will make them a laghing stock since they were in the forefront to weaken the unity of the country. Now they cannot be alllowed to reverse gear.

    Amhara! Wake up and smell the coffee. Tell Oromos that you want confederation – if not confederation then separation. Oromo crack down will soften even disappear as it did for Tigreans if Amara opt for confederation. But the idea is not to see Oromo softening on Amhara, it is to seek real confederation as a wayout from decades long quagmire. Oromo softeneing does not take Amharas anywhere.

    Try it! It will work and catapult Amhara development and growth to the sky and ensure their security. It will eventually liberate Oromos too from their bloody distructive path poised to takie everybody else down with them.

    For us, Oromos, conederation is also the answer. ”

    GREAT!

  2. Dear Shukuri, Shagitu, OLFite Robot or some anti-African agent,

    Whose land will you be claiming exclusively to yourself and “confederating”? There is no land in Ethiopia to be claimed as the exclusive property of any one ethnic group. Why do you keep reposting this recipe for African disaster again and again as an irrelevant and out of place comment on this media?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share