June 9, 2022
2 mins read

“ሰሞኑን በጎንደር ማክሰኝት ከተማ በመንግስት ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ የተወሰደው የከባድ መሳሪያ እርምጃ ለእኔ መንግስታዊ ሽብር ነው” ሲሉ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሰብሳቢ ሻለቃ ሰፈር መለስ

56455445
56455445“ሰሞኑን በጎንደር ማክሰኝት የተወሰደው የከባድ
መሳሪያ እርምጃ መንግስታዊ ሽብር ነው”
ሻለቃ ሰፈር መለሰ
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሰብሳቢ

“ሰሞኑን በጎንደር ማክሰኝት ከተማ በመንግስት ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ የተወሰደው የከባድ መሳሪያ እርምጃ ለእኔ መንግስታዊ ሽብር ነው” ሲሉ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሰብሳቢ ሻለቃ ሰፈር መለስ በስልክ ባደረጉት ቃለምልልስ ተናገሩ።

“በተለያዮ ግንባሮች ከመንግስት ጋር አብረን ወራሪን ስንመክት ቆይተናል።በቀጣይም፣ በአማራ ክልልም ይሁን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚገጥሙንን ማናቸውም የፀጥታና የሰላም ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ በሰላም እየመከርን በነበረበት ወቅት ይህ መፈፀሙ ክህደት ነው” ብለዋል።
አያይዘውም፣ “አሁን ላይ ህግ በማስከበር ሽፋን በፋኖዎች፣በአክቲቪስቶች፣በጋዜጠኞች እና በፖለቲካ ደርጅት ኃላፊዎች እና አባላት ላይ እየተወሰደ ያለው ጅምላ እስር፣እገታና የንፁሃን ግድያ አሳዝኖናል።በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል” ብለዋል።
“ከሰሞኑን በድርድር ስም የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን እየሰማን ነው። እንቅፋት ሊሆን ይችላል ተብሎ የታሰበውን ፋኖን አስቀድሞ ለማሸማቀቅ እና ለማዳከም የተሸረበ ሴራ መሆኑን ተረድተናል፣ ግን አይሳካም”ብለዋል።
“የአማራ አፅመ ርስት የሆኑትን ወልቃይትና ራያን ከዚህ በኋላ ለህወሓት መስጠት የመጨረሻውን ቀይ መስመር መርገጥ ነው” ብለዋል ሻለቃ ሰፈር መለስ።
ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

1 Comment

  1. ካሁን በሗላ ትግሬን በምንም መልኩ ወደዛ አካባቢ መመለስ ለኢትዮጵያና ለአካባቢው ማህበረሰብ የወደፊት መከራን ማቆየት ነው። በሌላ ቋንቋ ከራቫት አሰርኩ ብሎ እባብን አንገት ላይ መጠምጠም ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Poem
Previous Story

“ ቀጠለ…ወደ እሳቱ” – ጌታቸው አበራ

564554
Next Story

የኦህዴድ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ መንግሥት 71 ቢሊዮን ብር በኦሮሚያ ስም ከበጀቱ ዘረፎል!!! በወያኔ ጦርነት ለተጎዱ የአማራና አፋር ክልሎች ድጎማ የለም!!!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop