የኦህዴድ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ መንግሥት 71 ቢሊዮን ብር በኦሮሚያ ስም ከበጀቱ ዘረፎል!!! በወያኔ ጦርነት ለተጎዱ የአማራና አፋር ክልሎች ድጎማ የለም!!!

/

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

ኮነሬል አብይ አህመድ ‹‹ስለ ትንሽ ወጪዎች ተጠንቀቅ፣ ትንሽ ቀዳዳ ትልቁን መርከብ ከውኃ ውስጥ ታሰምጠዋለችና!!!››

ህወሓት ኢህአዴግ ከ1983ዓ ም ጀምሮ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ልዩ ድጎማ በሚል ስበብ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ልዩ ተጠቃሚ በማድረግ ለብዙ አመታት በበጅትና በውጭ በሚገኝ እርዳታን ወደ ትግራይ ፈሰስ በማድረግ ክልሉን ሲጠቅሙ መቆየታቸውን እንኮን ፓርላማ ተመራጮች ህዝብ ያውቃል፡፡

  • የአማራክልላዊ መንግሥት መረጃ መሠረት በአማራ ክልል 380 ቢሊዮን ብር ንብረት መዘረፉንና መውደሙን ዳግም ለመገንባትም ብዙ አመታት እንደሚፈጅ በተደጋጋሚ አሳስበው ከፌዴራል መንግሥቱ የበጀት ድጋፍ  እንዲደረግላቸው ጠይቀው ኦህዴድ ብልጽግና የዝሆን ጆሮ ሠጥቶል፡፡  የአፋር ክልላዊ መንግሥት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት መዘረፍና ውድመት የበጀት ማካካሻ አልተደረገላቸውም፡፡ ትላንት በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ልዩ ድጎማ በሚል ስበብ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ ድጋፍ ይደረግ ነበር፡፡  ዛሬ በጦርነት ለተጎዱ የአማራና አፋር  ክልሎች ድጋፍ ቀርቶ የኦህዴድ ብልፅግና የበጀት ዘረፋ ለምን? 
  • የትምህርትሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በህወኃት አሸባሪ ድርጅት በአማራ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 100 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ለፓርላማ አባላት ገልፀዋል፡፡ ከወደሙት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1200 ትምህርት ቤቶች በጦርነትና በሌሎች ምክንያት የወደሙ፣ 5000 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ ሶሰት ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፣ መቶ ሃምሳ ሽህ መምህራን ከመማር ማስተማር አገልግሎት ውጪ ሆነዋል፣ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች በከፊልና በሙሉ ወድመዋል በማለት የደረሰውን ጉዳት ገልጸዋል፡፡ በአማራ ክልል ብዙ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ብዙ6 ሚሊዮን ህዝብ በጦርነቱ ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ ዜጎች ሆነዋል፡፡ በሌላ በኩል የብአዴን/አዴፓ ብልጽግና ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች 60 ሚሊዮን ብር ተከፋፍለው ለመጥፋት በዝግጅት ላይ እንደነበሩና መቶ ሚሊዮን ብር እንደተዘረፈ ተገልፆል፡፡
  • የጤናሚኒስትሮ ዶክተር ሊያ ታደሰ በአማራና በአፋር ክልሎች ለተዘረፉና ለወደሙ 36 ቢሊዮን ብር መልሶ ለማቆቆም እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል በህወኃት የተዘረፉ የጤና ተቆማት ተፈታትተው የተዘረፉ የህክምና መሣሪያዎችና የላብራቶሪ እቃዎች ግምት 36 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ታውቆል፡፡በአፍር ክልል እስከ አምስት መቶ ሽህ ህዝብ በጦርነቱ ተፈናቅሎ ይገኛል፡፡
  • የኦነግሸኔ  የአማራ የዘር ፍጅት፣የንብረት ዘረፋና ውድመት በተመለከተ በኦነግ ሸኔ በሁሩ ጉድሩና በምስራቅ ወለጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2563፣ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር 68፣ የተዘረፉ የቀንድ ከብቶች 145000፣ የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያኖች 68፣ የተቃጠሉ መስጊዶች 46፣ የተቃጠሉ ወፍጮዎች 84፣ የተቃጠሉና የተዘረፉ መኪኖች 18 መሆናቸው ተገልጾል፡፡
  • ኦነግሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሜ ወረዳ 168 ንጹሃን ሰዎች መግደሉ ተገልፆል፡፡  በኦነግ ሸኔ በቄለም ዞን 30 የመንግሥት ተቆማቶች ወድመዋል፣ 45 አንደኛ ደረጃ ተምህርት ቤቶች፣ 4 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣  6 ጤና ተቆማት፣ ሃያ ሽህ ሃምሳ አራት የመንግሥት ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ተገልለዋል፣ የቄለም ዞን ወደ መደበኛ የመንግሥት ተቆማት ለማደራጀት 15 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሎል፡፡
  • በሌላበኩል የኦነግ ሸኔ ጥቃት በምዕራብ ሸዋ ዞን 647 ንፁሃን ዜጎችን መግደሉ ተገላፆል፡፡ 1252 (እንድ ሽህ ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት) ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቆል፡፡ 85000  (ሰማንያ አምስት)  ሽህ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ኦነግ7 (ሃያ ስድስት ነጥብ ሰባት) ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረና ኃብት ዘርፎል፣ አውድሞል፡፡ ባለፈው ጊዜ ኦነግ የዘረፈው የሻሸመኔ ከተማ፣ አርሲ፣ አጣዬ፣ ጂማ፣ ዘረፋና ውድመት ልብ ሊሉ ይገባል፡፡

የኦህዴድ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ መንግሥት 71 ቢሊዮን ብር ከበጀቱ ዘረፈ!!!

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የ2015ዓ/ም ዓመታዊ በጀት 786.61 ቢሊዩን ብር በጀት በጅቶል፣  ይህም በዩኤስ 15.23 ቢሊዩን ዶላር ይተመናል፡፡ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ51.84 ብር ሂሳብ ገደማ የተሰላ ነው፡፡ በጥቁር ገበያ አንድ የአሜሪካ ዶላር 80 ብር ደርሶል በዛ ከተሰላ ደግሞ በጀቱ 9.8 ቢሊዮን ዶላር ይወርዳል፡፡

  • ኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2015 ዓ/ም የተያዘው ዓመታዊ በጀት 786.61 ቢሊዩን ብር ውስጥ የመደበኛ በጀት ወጪ 345.1 ቢሊዩን ብር ሲሆን ይህም በዩኤስ 6.25 ቢሊዩን ዶላር ይተመናል፡፡
  • የ2015 ዓ/ም የሃገሪቱ አጠቃላይ በጀት 786.61 ቢሊዩን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት 218 ቢሊዩን ብር ይህም በዩኤስ 4.2 ቢሊዩን ዶላር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡
  • የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች የሚሠጥ ድጋፍ ደግሞ 209 ቢሊዩን ብር ይህም በዩኤስ 4.0 ቢሊዩን ዶላር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡
  • የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች ለዘላቂ ልማት ግብ 14 ቢሊዩን ብር ሲሆን ይህም በዩኤስ 230 ሚሊዩን ዶላር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:     ጠ/ሚ አብይ እንደ አሽሞዳይ

 “Ethiopia’s Executive body, the Council of Ministers announced on Friday it has approved a proposed budget of 786.61 billion Ethiopian birr (15.23 billion U.S. dollars) for the upcoming 2022/2023 fiscal year, which will start on July 8…..”6.25 billion U.S. dollars has been set aside for regular spending while 4.2 billion U.S. dollars has been set aside for capital spending and support for regional administrations,” the Council of Ministers disclosed. “Four billion U.S. dollars has been set aside for implementation of sustainable development goals and 230 million U.S. dollars has been set aside for the federal government,” the Council of Ministers further disclosed. The Council of Ministers statement also disclosed the 2022/2023 fiscal year proposed budget is an increase of 16.59 percent, when compared to the current 2021/2022 fiscal year”.………….(1)

በ2015ዓ/ም ለክልሎች ድጋፍ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት ለኦሮሚያ ክልል 71 ቢሊዮን ብር በመመደብ ዘረኛና ተረኛ መንግሥትነቱን በተግባር አረጋግጦ፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች የበጀት ድጎማ መሠረታዊ ደንብና መመሪያ ሲኖረው የኢኮኖሚውን እድገት ቱሩፋት በፍታዊነት ለማከፋፈል ዋናው መሥፈርቶች መኃል፤    (1) የክልሎች የህዝብ ብዛት፣(2) የክልሎች የእድገታቸው ደረጃ፣(3) የክልሎች የገቢ ምንጫቸውና (4) የክልሎች ከካፒታል ባጀት ጋር ያለው የንፅፅር ድርሻ፣ በማስላት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት መንግሥታዊ ሽብር በአፈናና ግድያ በመላ ሃገሪቱ ጋዜጠኞችን፣የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶችን የሥርዓቱን ሌብነት እንዳያጋልጡ በመፍራት በማፈንና በማሰር ላይ ይገኛል፡፡ አንባቢዎች የ2015 ዓ/ም በጀት ከ 2007 ዓ/ም ጋር በማነፃፀር ከወያኔ የባሰ የኦህዴድ የቀን ጅብ ዘረኛና ተረኛ አድሎዊ የበጀት ድልድልን በመቃወም የሦስት ቀናት የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ በመላ ኢትዮጵያ በተቃዋሚ ፓርቲዎች መጠራት አለበት እንላለን፡፡ ህዝባዊ እንቢተኛነትና አመፅ ከአጥናፍ አጥፍ ማቀጣጠልና ለጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት መመሥረቻ መታገል  ጊዜው አሁን ነው፡፡

  • በ2015ዓ/ም ለክልሎች ድጋፍ ወይም ለክልሎች ድጎማ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት የፀደቀው ባጀት 209 ቢሊዩን ብር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ኦህዴድ ተፅዕኖ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባፀደቀው ቀመር መሠረት ለክልሎች የተመደበው ባጀት ተከፋፍሎ በረቂቅ የባጀት ሰነድ ላይ አድሎዊ ድልድል ተመልክቶል፡፡ በዚህም  መሰረት የኦሮሚያ ክልል 71 ቢሊዩን ብር፣ የአማራ ክልል 44 ቢሊዩን ብር፣የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል 26.5 ቢሊዩን ብር፣የሶማሌ ክልል 20.5 ቢሊዩን ብር፣ትግራይ ክልል 12 ቢሊዩን ብር፣የአፋር ክልል 6.2 ቢሊዩን ብር፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3.7 ቢሊዩን ብር፣ለጋምቤላ ክልል 2.4 ቢሊዩን፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 1.8 ቢሊዩን፣ ለሃራሪ ክልል 1.5 ቢሊዩን ብር፣ለአዲስአበባ 3.2 ቢሊዩን ብር፣ ለሲዳማ ክልል 8.4 ቢሊዩን ብር፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 6.4 ቢሊዩን ብር ሲሆን ጠቅላላ 209 ቢሊዩን ብር ለክልሎች ድጎማ የቀረበ መሆኑ ይታወቃል፡፡
  • በ2007 እኢአ ዓ.ም ለክልሎች ድጋፍ ወይም ለክልሎች ድጎማ ህወሓት ኢህአዴግ ዘመን የፀደቀው ባጀት 51.52 ቢሊዩን ብር መሆኑ ይታወቃል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባፀደቀው ቀመር መሠረት ለክልሎች የተመደበው ባጀት ተከፋፍሎ በረቂቅ የባጀት ሰነድ ላይ ተመልክቶል፡፡  በዚህም  መሰረት የኦሮሚያ ክልል 16.69 ቢሊዩን ብር፣የአማራ ክልል 11.95 ቢሊዩን ብር፣የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል 10.34 ቢሊዩን ብር፣የሶማሌ ክልል 4.1 ቢሊዩን ብር፣ትግራይ ክልል 3.67 ቢሊዩን ብር፣የአፋር ክልል 1.6 ቢሊዩን ብር፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 1.1 ቢሊዩን ብር፣ለጋምቤላ ክልል 771 ሚሊዩን 535 ሽህ ብር፣ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 596 ሚሊዩን 653 ሽህ ብር፣ለሃራሪ ክልል 514 ሚሊዩን 356 ሽህ ብር፣ለአዲስአበባ 84 ሚሊዩን 721 ሽህ ብር ሲሆን ጠቅላላ 51.52 ቢሊዩን ብር ለክልሎች ድጎማ የቀረበ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የ2015 ዓ/ም የበጀት ድልድል የኦህዴድ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ አድሎዊና የበጀት ድልድልን የሁሉም ክልሎች ህዝብ ይቃወማሉ፡፡ እንኳን ኦህዴድ ብልፅግና ህወሓት ኢህአዴግን በህዝባዊ እንቢተኛነትና አመጽ ጥለናል፣የኢትዮጵያ ህዝብ ኦህዴድ ብልፅግናን ለመጣል ታጥቀህ ተነስ !!!

‹‹ለኦሮሞው፣ለአማራው፣ ለከንባታው፣ ለጉራጌው፣ ለዶርዜው፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣ ፍትህና ርትዕ፣  ዴሞክራሲና እኩል ብሔራዊ ዕድል ከወያኔ ኢህአዴግ የፍትሕ አደባባይ፣ ከቢሮክራሲ መዋቅሩና ከኢኮኖሚ መንበሩ ይፈስስልናል ብለን አናስብም፡፡ ወይስ ከፖለቲካ ዲስኩሮቹ ምንጮች ይፈልቅልናል ብለን አንጠብቅም፡፡………….. ሚሊዮን በሚሊዮን የሆነውን ህዝብ ጥያቄ የፕሮፓጋንዳ ቌንቌ  በመሰለ ጫጫታ (ሬቶሪክ) ለመሸንገል ያስቸግራል፡፡ ፍትህ እንፈልጋለን፡፡ አላገኝናትም፡፡ መብት እንሻለን፡፡ የለንም፡፡ እኩልነት እንላለን-እየራቀን የሄደ ‹‹ሸቀጥ›› ሆኖአል፡፡ ከቶውንም ‹‹ ኦርዌላዊ›› በሆነ ፌዝ ‹‹ ሁሉም እንስሳት እኩል ናቸው፡፡  አንዳንድ እንስሳት ደግሞ ከሌሎቹ ይበልጥ እኩል›› ሆነዋል፡፡ አንድ ሕዝብ ከዚህ የባሰ ውርደት በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ፍፃሜ ላይ ሊደርስበት አይችልም፡፡ ስለዚህ የፍትሕ ጥያቄ – ከወያኔ(ኦህዴድ ብልፅግና) ፍርድ ቤት የማይገኘው፣ የስብአዊ መብት ጥያቄ -ከወያኔ (ኦህዴድ ብልፅግና) ፖሊስ የማይገኘው፣ የእኩልነት ጥያቄ -ከእነሱ የፖለቲካ መድረክ የማንጠብቀው የዴሞክራሲ ጥያቄ- ከምን ጊዜውም የበለጠ ይነሣል፡፡ አይቀርምም፡፡›ከፕሬስ ነፃነት አባታችን ከአቶ ሙሉጌታ ሉሌ ከጻፍት የተቀነጨ፣ ከዛሬ ሁለት አስርታት በፊት የተፃፈ ትንቢት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንደ ዘበት ያለፉት ነፍሶች - (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)

ለክልሎች የሚደረግ የበጀት እርዳታ/ድጎማ

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች የበጀት ድጎማ የሚያደርግበት ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት የክልሎች መንግስታት ያላቸውን የተፈጥሮ፤ የሰው ሃይልና ካፒታል ሃብቶችን በአግባቡ ማደራጀት ባለመቻላቸው የተነሳ፣ አስተዳደራዊ ወጫቸውን መሸፈን ባለመቻላቻ ምክንያት ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ መንግስት በሁሉም ክልሎች እኩል የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ማምጣት ሃላፊነት ስላለበት ነው፡፡ መንግስት በሁለተኛው ምክንያት የተነሳ እኩል ያልሆነ የሃብት ክፍፍል ፖሊሲ በመንደፍ በክልሎች መኃል እኩልነት መፍጠር ይሻል፡፡

የመንግስት ለክልሎች የሚያደርገው የእርዳታና ድጎማ ስርዓት ለክልሎች እድገት ጠቃሚ መሣሪያ በመሆን የኢኮኖሚና የማህበረሰብ እድገት ለማፋጠን ታላቅ ጠቄሜታ ሳያስገኝ ቀርቶል፡፡ በዚህም ምክንያት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታትና አስተዳደር የሚደረገው ጠቅላላ የካፒታል ባጀት ክፍፍል ድጎማ በየግዜው እየጨመረ ቢሄድም በክልሎች መኃል የተፈጠረው ያልተስተካከለ ዕድገት በተለይም በትምህርት፣ በጤና፣ በመብራት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በመሠረተ-ልማት ማለትም በመንገድ ሥራ፣ በባቡር መስመር፣ በኤርፖርት፣ በግድቡ፣ በኢንዱስትሪያል ዞኖች ግንባታ አይን ያወጣ አድሎ እንደአለ ገሃድ ሆኖል፡፡ የትግራይ ሽብርተኞች በአማራና አፋር ከልሎች ያደረሱት ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በበጀቱ ማካካሻ አልተሰጠውም፡፡ እንዲያውም በጦርነቱ ምንም ጉዳት ያል የኦሮሚያ ክልል በኦህዴድ ካድሬዎች የ71 ቢሊዮን በጀት ተችሮታል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች የበጀት ድጎማ መሠረታዊ ደንብና መመሪያ ሲኖረው የኢኮኖሚውን እድገት ቱሩፋት በፍታዊነት ለማከፋፈል ዋናው መሥፈርቶች መኃል፤የክልሎች የህዝብ ብዛት፣የእድገታቸው ደረጃ፣የገቢ ምንጫቸው ከካፒታል ባጀት ጋር ያለው የንፅፅር ድርሻ፣በማስላት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን አጥኝዎች ይገልፃል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት አጠቃላይ ባጀት (Regional Government Budget)፤ የፌዴራል ገንዘብ ክፍፍል ለክልሎች ባጀት በመቶኛ (Federal money as % of total) እና የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ ድርሻ ( Percapita share of Federal Money) ከአዲስ አበባ በስተቀር ሁሉም ክልሎች የፌዴራል ገንዘብ ተደጎሚዎች እንደሆኑ ማስተዋል ይቻላል፡፡ለክልሎች የበጀት ድጎማ መሠረታዊ ደንብና መመሪያ ቢኖረውም በፍትሃዊና እኩልነት ላይ የተመሠረተ ቢመስልም፤በሌላ ገፅታው ሲታይ በሌሎች ተለዋዋጭ ምክንያቶች የክልሎች የፌዴራል ገንዘብ ክፍፍል ኢፍትሃዊነትና አድሎን ያሳያሉ፡፡

  • አንደኛ በለጋሺ ሃገራት ተጨማሪ የባጀት ድልድል በሚያገኙ ክልሎች ክፍፍሉን የተዛባ ያረገዋል፣ዝቅተኛውን የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ ድጋፍ ያገኘ ክልል ሌላ የገንዘብ ምንጭ ስለሚያገኝ የመንግስት ድጎማን ኢፍታዊና አድሎዊ ያደርገዋል፡፡
  • ሁለተኛ የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ፣ወይም አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት የገንዘብ እርዳታ ድምር ሂሳብ በማየት ፍትሃዊነትና እኩልነት መኖሩን ማረጋገጥ አይቻልም፡፡ ውስጣዊ ክፍፍልና ዳግማዊ ክፍፍል ጥቅምና የጥቅሙን የማግኛ መድረሻና መግቢያ ዘዴ መንገድ ማወቅ  ትልቅ ተፅዕኖ  ያደርጋሉ፤በክልሉ ህዝብ በእኩልነት የኢኮኖሚ እድገቱን ቱሩፋት ለመቆደስ አይቻልም፡፡ በኢትዩጵያ ኃላቀር ክልሎች በተለይ የጋምቤላ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በጣም ኃላ ቀር የኢኮኖሚ እድገት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም የተነሳ ባለፉት 26 ዓመታት አንባገነናዊ አገዛዝ፣ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ፍትሃዊ የበጀት ክፍፍል በፌዴራል ሥርዓቱ እንደሌለ ህዝቡ ተገንዝቦል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስትና ክልላዊ መንግስት ባጀት

በኢትዩጰጵያ ያልተመጣጠነና ያልተስተካከለ የክልል መንግስታት ኢኮኖሚያዊ እድገት

በኢትዩጰጵያ የተስተካከለ የክልል መንግስታት ኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እቅድ በጋራ መንደፍ አስፈላጊ ነው፡፡ የክልሎችን የኢኮኖሚ እቅድ ለመንደፍ ለፖሊሲ አውጭዎች ፈታኝ የሆኑ ችግሮች መኃከል አንደኛ ለክልሎች ፍትሃዊና እኩልነት ላይ ያተኮረ፣ ፈጣን እድገትና ልማት አስፈላጊነት ሁለተኛ በክልሎች አድሎ አልባ የኢንደስትሪያላይዤሽን  እድገት አስፈላጊነት ሶስተኛ የክልሎች የውሃ ኃብት ልማት እድገት አራተኛ የክልሎች የኢኮኖሚ ዘርፍ እድገትና የግብርና ምርቶች፣ የውጭ ንግድን የማስፋፋት አስፈላጊነት ያካትታል፡፡ በክልሎች የኢኮኖሚ ስትራቴጂ መርሃ ግብር ውስጥ የሚካተቱ ውስጥም የገቢ ንግድን የሚተኩ ኢንደስትሪዎችን በሃገር ውስጥ መገንባት፣ የውሃ ተፋስስ ልማትና የኮሜርሻል እርሻዎችን በክልሎች ማስፋፋት ለተጠቀሱት ችግሮች ማቃለያ ፖሊሲ እንደሆኑ አጥኝዎች ያሳስባሉ፡፡  እነዚህ ፖሊሲዎች ብቻቸውን የተስተካከለ የክልሎች እድገት ያመጣሉ ማለት አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት ያልተመጣጠነ የክልሎች እድገት በሃገሪቱ ይከሰታል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የክልል የፖለቲካ ፖሊሲዎች በዋናነት የሚያጠነጥኑት 1ኛ/ sንs ተኮር /ዘውግ ተኮር ፖለቲካዊ የክልል ፖሊሲ በመንደፉ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲን መዘንጋት  2ኛ/ ያልተማከለ የኢኮኖሚ እቅድ ስርአት መዘርጋት( decentralized planning systems) ኢፍታህዊነት 3ኛ/ በክልሎች ውስጥ የኃብት ክፍፍል ስርጭት አመዳደብ( inter-regional allocation of resources) ፍትሃዊ አለመሆን 4ኛ/ የመዋለ ንዋይ /ኢንቨስመንት ፖሊሲዎች ፍትሃዊ አለመሆን 5ኛ/ክልላዊ የስልጠናና እውቀት ክህሎቶች አለመኖር 6ኛ/የውሃ ተፋስስ ልማትና የኮሜርሻል ገበያ ተኮር የግብርና ምርቶች (ቡና ፣ሠሊጥ፣የቅባት እህሎች፣ጫት፣ቅመማ ቅመም ወዘተ)አምራች ለሆኑ ክልሎች አስፈላጊውን የመንገድ ፣የባቡርና  የዓየር ትራንስፖርት አገልግሎቶች መሠረተ-ልማቶች በቅድሚያ በመዘርጋት በዓለም አቀፍ ንግድ የውጭ ንግድ ዘርፉን በማጠናከርና በመሳተፍ  የውጭ ምንዛሪ (ዶላር፣ ዩሮ፣ ፓውንድ ወዘተ)በማግኘት ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ  አስፈላጊ የሆኑ የምርት መገልገያ እቃዎች/የካፒታል  ጉድስ(ማሽነሪዎች፣ፋብሪካዎች፣ ትራክተሮች፣ነዳጅ፣ ማዳበሪ ወዘተ)ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ብሄራዊ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ መገንባት ይቻል ነበር፡፡ ማለትም ብሄራዊ የሃገሪቱ እድገት ከክልሎች እድገት በላይ ትኩረት ማግኘት አለመቻሉና የክልላዊ ዘውግ ተኮር ፍቅር ከብሄራዊ የኢትዩጵያዊ ሃገር ፍቅር በላይ መሆን የኢኮኖሚ እድገት ኃላ ቀር እንዲሆን አድርጎታል፡፡  የክልላዊ ዘውግ ተኮር ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ክልሎች የግብርና ምርቶች (ቡና ፣ሠሊጥ፣የቅባት እህሎች፣ጫት፣ቅመማ ቅመም፣ የቁም እንሰሳት ወዘተ) ወደ ጎረቤት ሃገሮች በመላክ የውጭ ምንዛሪ ያግበሰብሳሉ ብሎም ገንዘቡን ወደ ባህር ማዶ ሀገራት ያሸሻሉ፡፡ ትላንት የህወሃት /ኤህአዴግ ዛሬ የኦህዴድ ብልፅግና የፌዴራልና ክልላዊ መንግስታት የፖለቲካ ካድሬዎችና የጦር አበጋዞች  ሓብት ማግበስበስ ሲያፋጥን የክልሉን ህዝብና  የብሄራዊ ኢኮኖሜችንን እድገት ያቀጨጨ መሆኑን የሚጠራጠር ካለ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ያልተገነዘበ ምሁር ነው፡፡ በሃገሪቱ የሠፈነው የፌዴራልና የክልል መንግስታት የሞኖፖሊ ኢንፓየር የግሉ ዘርፍ ባለኃብት ስራን በመንጠቅ ኢኮኖሚውን በእዝ ኢኮኖሚ ጠርንፎ የያዘና የመሬት ኃብትን በመንግስት ስም በፓርክ ስም፣ በሙዚየም ስም፣ በቤተመንግሥት ስም፣ በስንዴ እርሻ ስም ወዘተ ትላንት የህወሃት /ኢህአዴግ ዛሬ የኦህዴድ ብልፅግና ሹማምንቶች ንብረት በማድረግ ሰፊውን የኢትዩጵያ ህዝብ ጭሰኛ ያደረገ የክልሎች የጦር አበጋዞች ስርአተ አገዛዝ ነው የሰፈነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሶስቱ የህወሃት ቀለበቶች ታወቁ! ዳገት ላይ ሰው እንዳይጠፋ ይሁን !

‹‹በሥልጣንን ለማቆየት ‹‹በቀን ሦስቴ አስደንብረው፣ በወር አንዴ እሰረው››

ኮነሬል አብይ አህመድ ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት ከህወሓት ኢህአዴግ ጋር ለመታረቅ ቆምጦል፣ ለህወሓት የ12 (አስራ ሁለት) ቢሊዮን ብር በጀት አፀድቆል፣ ለወልቃይት ምንም በላጸደቀም፡፡  ኦህዴድ  71 ቢሊዮን ብር  በኦሮሞ ስም ለመመንተፍ በህገወጥ መንገድ ለመዝረፍ  አይኑን በጨው አጥቦል፣ የሚቀጥለው አመት  መንግሥታዊ ሽብርተኛነት ዘለቄታዊ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ የህዝብ ተከራካሪ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ የፖለቲካ ሰዎች፣ እንደ ከርከሮ የሚታደኑ የህዝብ ልጆች፣ የአማራ ፋኖ አርበኞች የህዝብ ድጋፍ ካልተለያቸው በድል አድራጊነት የሚኒሊክ ቤተ-መንግሥትን ይቆጣጠራሉ፣ ቃል ለምድር ለሠማይ!!! ኮነሬል አብይ አህመድ በአራተኛ ዓመቱ በዓለ ሹመቱ፣የዴሞክራሲን ጭላንጭል አጠፋው፣ የፐሬስ ነፃነትን ለጎመው፣ ማህበራዊ ሚዲያን ሸበበው፣ ሃገሪቱን በጦርነት እሳት ለኮሳት፣ ወጣቶች አለቁ፣ አካላተ ስንኩል ሆኑ፣ ህዝብ ከቀየው ተፈናቀለ፣ ከብቶች ተዘረፉ፣ተነዱ፣ የወያኔ ዘራፊ ሌባ እንደ አሸን ተፈለፈለ በነፃነት ስም፣ በዴሞክራሲ ስም እየማሉ የቦዘኔ ወፍዘራሽ መንግሥት በኢትዮጵያ ነገሠ፡፡ ፍትህና ርትህ ዓይኑ ጠፋ፣ ሴት ደፋሪዎች በአደባባይ ነገሱ፣ ሰዉ የሚያርዱ አደባባይ ዋሉ፣ ይህ ቀን ያልፋል ታገሉ ያሉ የህዝብ ልጆች ለድምጽ አልባው ወገን ጮሁ፡፡ ስንታየሁ ቸኮል ከባልደራስ፣ በቃሉ አላምረው ከአልፋ ቲቪ፣ ያየሰው ሽመልስ ከኢት ፎረም፣ መዕዛ መሃመድ ከሮሃ ሚዲያ፣መሥከረም አበራ፣ ተመስገን ደሣለኝ ከፍትሕ መጽሄት በመንግሥት ታፍነው እየታሠሩ ይገኛል፡፡ የዛሬ ሁለት አስርት በፊት በጦቢያ መፅሄት ላይ ‹‹በሥልጣንን ለማቆየት ‹‹በቀን ሦስቴ አስደንብረው፣ በወር አንዴ እሰረው›› የሚሉ ምክር የሚሰጡ ምርጥ ዜጎች ይፈለፈሉ ይሆናል፡፡ ከፍርድ አወቅ መሸሻ ብለው ነበር፡፡ ትንቢቱ ደርሶል፡፡ በኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት፣የታሰሩት የፖለቲካ እሰረኞች ሁለተኛ ዜጋና የእንጀራ ልጆች በመሆናቸው የሚደርስባቸውን በቀል ለአንዴና ለዘለቄታው የኦህዴድ ብልፅግና የጦር አበጋዞች መንግሥት መንግሎ መጣል አማራጭ የለውም፡፡ የህሊና እስረኞች በትግላችን ይፈታ፣ ዳግም በትግላችን ነፃነታቸውን ያገኛሉ፡፡

እንኳን የመሶቡን የጄን ተውኩላችሁ!!!

ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ!!!

ምንጭ

(1) Ethiopia’s Council of Ministers approves budget for 2022/2023 fiscal year

Source: Xinhua| 2022-06-03 21:12:44|Editor: huaxia

(2) Ethiopia sees 231.4 billion birr budget deficit for the next fiscal year /June 7, 2022

 

1 Comment

  1. ኮሎኔል ዐቢይ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ያስተዳድራል በጉልበት ስልጣን መንጠቅ ያለፈበት የጨለማ ጊዜ ነው:: የትግራይ ክልል ሚጢጢ 12 ቢሊዮን ሳያንጨረጭርህ አልቅረም ተመስገን ለሶማሌ ክልል 20.5 ቢሊዮን መሆኑ ደስ ብሎናል:: ስለአማራ ስትቆረቆር ያስቀኛል

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share