ስለሀገር – “የመከላከያ አባላት ሚስቶች ናችሁ” በሚል ግፍ የተፈጸመባቸው የትግራይ ሴቶች አሳዛኝ ታሪክ

June 8, 2022

1 Comment

  1. የትግራይ ህዝብ ጠላቱ ወያኔ ነው። ይህ የማይገባው ካለ ደንቆሮና በዘር ፓለቲካ ጢምቢራው የዞረ ብቻ ነው። የትግራይን ህዝብ ለዘመናት በስሙ የሚነግድበት ወያኔ ነው። የእነዚህ ሴቶች ምስክርነት አባይን በጭልፋ እንዲሉ እንጂ ግፉ ሰማይ ጠቀስ ነው። በሃገራችን ረጅም ታሪክ ውስጥ እንደ ወያኔ ያለ ግፈኛና ዘራፊ ተፈጥሮ አያውቅም። የሚገርመው የቀይ መስቀልም ሆነ የተመድ የመቀሌ ቅርንጫፍ የበደሉ ተባባሪ መሆናቸው ነው። ለነገሩ አይዞአችሁ እያሉ የትግራይ ወጣት እንዲያልቅ አሁን ላይ ከኤርትራ ጋር የሚያላትሙን ምዕራባዊያን አይደሉምን? ግን ህዝባችን መቼ ነው የሚነቃው? መቼ ነው ጦርነት በቃ፤ መከራ በቃ ለሰላም እንቁም በማለት እንዘጥ እንዘጥ ማለቱን ትቶ ሰርቶና አርሶ የሚያድረው። አሁን አሁን ላይ ነፍሴ ከምትጠየፋቸው ሰዎች መካከል በዘር ፓለቲካ ቡራ ከረዪ የሚሉ የእድሜ ልክ ፓለቲከኞችና ጠበንጃ አንግተው ላይ ታች የሚራወጡ የቁም ሙታኖችን ነው።
    በቅርቡ ጀዋር እይታውን አስፍቶ ባደረጋቸው ቃለ ምልልሶችና የስብሰባ ዲስኩሮች የተኮፈሰው ኦነግ ባንዲራዬን አትጠቀም ማለቱ የፓለቲካን የልጆች ጫወታ ያሳያል። ለአንድ ህዝብ የሚታገል ወገን በሰንደቅ ሲፋለም ማየት የፓለቲካውን ክሰረት ያሳያል። ግን ኦነግን ከእንቅልፉ የቀሰቀሰው የጃዋር የፓለቲካ ዝንባሌ የሚያሳየን አንድ ነገር አለ። ኦሮሚያን ሃገር እንኳን ቢያረጉ በማግስቱ እንደሚገዳደሉ ሳይታለም የተፈታ ነው። አፍሪቃዊው ታሪካችን የመበላላት ፓለቲካ ነውና። በጥቅሉ የብሄር ፓለቲከኞች ጥርሳቸው አልቆ በድዳቸው ብቻ ቆመው ዛሬም 50 ዓመት ሙሉ ከዚህ ግባ የማይባል ለውጥ ሳያመጡ ይኸው ለዛሬ ደርሰናል። የሃበሻው የፓለቲካ ክርፋት ለዘሩና ለቋንቋው ቆሜአለሁ ለሚለው ብቻ አይደለም ግማቱ የሚተርፈው። ምድሪቱን ሁሉ እንጂ። ባጭሩ ከእውነት የተጠጋ እይታ ያላቸውን ሰዎች አንገት ማስደፋት፤ ያለስማቸው ስም መለጠፍ፤ አልፎ ተርፎም ማሰርና መግደል ሙያ ሆኗል።
    እኔን በጣም የሚገርመኝ ግን የትግራይ ተወላጆች አሁንም ከወያኔ ጎን መቆም ነው። ራሱ ያደራጀውን፤ የሸለመውንና ያሰለጠነውን፤ ለ 20 ዓመታት አብሮት የኖረውን ወገኑን በተኛበት ያረደ፤ ሲኖ ትራክ የነዳ፤ በሳንጃ የሴቶችን ጡት የቆረጠ፤ ገደል ገፍትሮ የከተተ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ለትግራይ ህዝብ የሰላም ምንጭ የሚሆነው? በቪዲዮው ላይ እህቶቻችን ከእንባ ጋር እንዳሉት ከሩቅ ሆኖ ቀረርቶ ማሰማትና ወያኔን መደገፍ ተጨፍኖ ገደልን ለመዝለል እንደመሞከር ይቆጠራል። ወያኔ ያበደ ድርጅት ነው። ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ቆሞ አያውቅም። የትግራይ ህዝብን ሲደላው የሚረሳው፤ ሲከፋው የሚጠለልበት ጫካው ነው። በዓለማችን ላይ ከሚደረጉ ግፎች ዋናውና ምስክርነት የሌለበት በደል የሚፈጸመው በትግራይ ምድር በወያኔ ካድሬዎችና ወታደሮች ነው። አሁን ማን ይሙት ወያኔና ሻቢያ መዋጋት አለባቸው? ይህ የአሜሪካንን ተልኮ ለማስፈጸም ካልሆነ በስተቀር በሁለቱ ህዝቦች መካከል ምንም ጸብ የለም። ሻቢያም በምንም ሂሳብ ትግራይን ልውረር አይልም። ግን ፍትጊያው ለምን? ወያኔ በታሪኩ ውስጥ አሁን እንደ ገባበት ያለ ማጥ ውስጥ ገብቶ አያቅም። ሊወጣ በሞከረ ቁጥር እየሰመጠ እየሄደ ነው። የትግራይን ህዝብ አካለ ጎደሎ አድርጎ ምን አይነት ነጻነት ነው የሚታወጀው? ወያኔ ከክፋቱ የተነሳ ደብዳቤ የሚጽፉ ህቡዕ ክንፍ አዘጋጅቶ የውሸት ደብዳቤ ግንባር በተገደሉ ታጋዪች ስም ለወላጅና ለዘመድ በመጻፍ በማታለል ላይ የሚገኝ እጅግ ናዚ የሆነ ድርጅት ነው። ግን ትንሽ ታገሱ፤ በዚያ ያሉ የርዳታም ሆነ የሌላ ተተኳሽ አቀባይ ቡድኖች መጽሃፍ ይጽፋሉ እውነቱን ያወጣሉ። የአሜሪካው የወያኔ ፍቅርም እንደ አቶ ኢሳያስና እንደ አብይ ፍቅር ቀስ እያለ ይበርዳል። አሜሪካን ያመነ ጉም የዘገነ ነውና። አሁን ለሶስተኛ ጊዜ ለምሥራቅ አፍሪቃ መልክተኛ የሾመቸው አሜሪካ ግራ የገባት ሃገር ሆናለች። የአሜሪካ የውጭ ፓሊሲ በ 60 ዎቹ እንደነበረ ደፋ ቀና እያለ ያለምንም ማሻሻያ ዓለምን ያምሳል። ዪክሬን በራሷ አስባ አሜሪካኖች የሚሉትን አልሰማም ብትል ኑሮ ዛሬ ዪክሬን እንዲህ የጦር አውድማ ባልሆነችም ነበር። ግን በስመ ዲሞክራሲ ሃገሪቷ ስትፈራርስ ዋሽንግተን ላይ ተቀምጠው ዪክሬኖች እያሸነፉ ነው ሲሉ አለማፈራቸው። ግን ግባቸው ሩሲያን ማዳከም ስለሆነ ያው በዚህም በዚያም ሲጠላለፉ መሽቶ ይነጋል። በቪዲዮው ላይ የሚታዪት ሶስቱ እህቶቻችን ተወልደው ባደጉበት የትግራይ ምድር ግፍና መከራ የደረሰባቸው የወታደር ሚስቶች ስለሆኑ ነው። ግን ሌላውም የትግራይ ህዝብ ከእነርሱ የከፋ በደል እንጂ የተሻለ ነገር ከወያኔ አያገኝም። የትግራይ ልጆች የሚነቁትና እውነቱን የሚፈትሹት መቼ ይሆን? ዋ በህዋላ ምድሪቱ ባዶ እንዳትሆን። የእብድ ገላጋዮች ድንጋይ ሲያቀብሉን ስንገዳደል ከዳር ቆመው ይስቃሉ። በወያኔና በሻቢያ መካከል ያለው ፍልሚያ መቆም አለበት። እብደት ነው። ወያኔ ስልጣኑን ህዝብ ለመረጠው አስረክቦ በቃኝ ማለት ካልቻለ የትግራይ/የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ የማይገታ ይሆናል። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

45543dd
Previous Story

በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ተገለፀ

172811
Next Story

በፓርላማ ጥያቄ ያስነሳው የትግራይ እና ወልቃይት በጀት ድልድል ጉዳይ

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop