በፓርላማ ጥያቄ ያስነሳው የትግራይ እና ወልቃይት በጀት ድልድል ጉዳይ

የፌደራል መንግስት የ2015 ረቂቅ በጀት ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ግንቦት 30 ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት ወቅት፤ ለትግራይ ክልል የተመደበው 12 ቢሊዮን ብር በጀት እና ለወልቃይት የሚመደበው በጀት ጉዳይ ከፓርላማ አባላት ጥያቄ ተነስቶበታል። ለጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፤ መስሪያ ቤታቸው በጀቱ ያዘጋጀው “ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ተከትሎ” እንደሆነ አስታውቀዋል።

“በጀት የሚበጀተው ለህዝብ ነው። በጀቱ ተግባራዊ የመሆኑ ጉዳይ ግን የህጋዊነትና የሰላም እና በጀቱን ማስፈጸም የሚያስችል ህጋዊ ሁኔታ ከመኖር ከህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ጋር የተገናኘ ጉዳይ ስላለው፤ በጀትን ማጽደቁ ህገ መንግስታዊ ስዓቱን ተከትሎ የሚደረግ ነው። የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው። በጀቱን ማስፈጸም ሲመጣ ግን ህገ መንግስታዊ፣ ህጋዊ ስርዓቱ መሟላት አለበት ማለት ነው” ሲሉ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ዘንድሮ ለትግራይ የተመደበው በጀት ወደ ክልሉ አለመተላለፉን የገለጹት አቶ አህመድ፤ በጀቱ ቢጸድቅም አፈጻጸሙ ግን “ህጋዊነት ከመሟላት እና “ከሰላም ሁኔታ ጋር አብሮ የተገናኘ” መሆኑን አስረድተዋል። የገንዘብ ሚኒስቴር ለወልቃይት አካባቢ የበጀት አስተዳደሩን የሚያስፈጽመው “ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን” ተከትሎ መሆኑን የገለጹት አቶ አህመድ፤ የበጀት ድልድሉ የሚፈጸመውም የተወካዮች ምክር ቤት በሚሰጠው መመሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

“ቀመር የሚዘጋጀው በነበረው ህገ መንግስታዊ ስርዓት ስለሆነ ከዚያ ጋር በተገናኘ የአካባቢው ማህብረሰብ ተቸግሯል። ችግሩን እናውቃለን። ችግሩ ከህግ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች አሉት። ከህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች አሉት። ይህንን በጠበቀ መልኩ ምን መደረግ ይችላል የሚለው ተጨማሪ ውይይት የሚፈልግ ይሆናል” ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
* በፓርላማ የነበረውን ጥያቄ እና ምላሽ ለማድመጥ ከታች የተያያዘውን ቪዲዮ ይጫኑ። በ2015 በጀት ላይ ለቀረቡ ሌሎች ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾችን ለመመልከት ደግሞ እነዚህን ሊንኮች ይጫኑ፦

ተጨማሪ ያንብቡ:  እጅግ አሳዛኝ... ሄዋን ወልዴ ትባላለች የተወለደችዉ ጎንደር ከተማ ነዉ።

Ethiopia Insider 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share