ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
የኢትዮጵያወታደራዊወጪከሃያ አምስት ቢሊዮን ብር ወደ መቶ ቢሊዮን ብር ተመነደገ!
የ2022/ 2023 እኤአ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ገንዘብና ፋይናንስ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አጠቃላይ በጀት 785 (ሰባት መቶ ሰማንያ አምስት) ቢሊዮን ብር እንዲሆን ለሚንስትሮች ምክር ቤት አቅርቦል፡፡ ከባጀቱ ውስጥ የወታደራዊ ወጪ 100 (መቶ) ቢሊዮን ብር መሆኑ ባልጸደቀው ሪፖርት ተገልፆል፡፡ በባጀቱ የቢሮ ባጀት በአርባ በመቶ መቀነሱ ሲገለፅ በአንፃሩ 64 ቢሊዮን ብር ከውጭ ምንጭ እንደሚገኝ ቢታሰብም እስካሁን ገንዘቡ አልተገኘም፣ ሆኖም መንግስት የበጀቱን ጉድለት ከሀገር ውስጥ ምንጭ መሸፈን እንደሚቻል ገልፆል፡፡ “The Ministry of Finance has prepared a total budget of 785 billion birr for 2022/2023 and submitted it to the Council of Ministers, The Reporter reported. According to the report, $ 100 billion has been allocated to the Defense Forces from this draft budget. This year, 22 billion birr has been allocated to the Defense Forces. With the government’s new draft budget, budget offices have been cut by up to 40 percent. Expected 64 billion birr from foreign sources has not been completed yet, and the government intends to cover the budget deficit from domestic sources”……… ……………………….(1)
በ2021 እኤአ የዓለም አገሮች ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ወጪ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ድርሻ ጋር ሲነፃፀር Military expenditure as percentage of gross domestic product (GDP) in highest spending countries 2021 ያላቸው አገራቶች ውስጥ የሳውዲ አረቢያ 6.6 በመቶ፣ ራሽያ 4.1 በመቶ፣ አሜሪካ 3.5 በመቶ፣ እስራኤል 2.8 በመቶ፣ ሳውዝ ኮርያ 2.8 በመቶ፣ ህንድ 2.7 በመቶ፣ ኢራን 2.3 በመቶ፣ ዩናይትድ ኪንግደም 2.2 በመቶ፣ አውስትራሊያ 2 በመቶ፣ ፈረንሳይ 1.9 በመቶ፣ ቻይና 1.7 በመቶ፣ ጣሊያን 1.5 በመቶ፣ ጀርመን 1.3 በመቶ፣ ካናዳ 1.3 በመቶ፣ ጃፓን 1.1 በመቶ መሆኑ የዓለም ወታደራዊ ወጪ ከጂዲፒ ድርሻን ስታቲሰታ መረጃውን በድርገፁ ይፋ አድርጎል፡፡……………….(2)
የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ድርሻ ጋር ሲነፃፀር Military expenditure as percentage of gross domestic product (GDP) in 2020 እኤአ 0.5 (ዜሮ ነጥብ አምስት) በመቶ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ከ2021 እስከ 2023 እኤአ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከጂዲፒ ድርሻ ጋር ሲነፃፀር ከ 0.5 እስከ 1.5 በመቶ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ (የኢትዬ360 ወዳጆች የወታደራዊ ወጪ ከጂዲፒ ድርሻ 25 በመቶ ነው የተባለው ስህተት መሆኑን በዚህ አጋጣሚ በመግለፅ እርምት እንዲያደርጉ በማክበር እናሳስባለን፡፡) “GDP in Ethiopia is expected to reach110.00 USD Billionby the end of 2021, according to Trading Economics global macro models and analysts expectations. In the long-term, the Ethiopia GDP is projected to trend around 112.00 USD Billion in 2022 and 115.00 USD Billion in 2023, according to our econometric models.”
የኢትዮጵያ አጎራባች አገራቶች ወታደራዊ ወጪ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ድርሻ ጋር ሲነፃፀር የኤርትራ በ2003 እኤአ 20.9 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ ግብፅ በ2020 እኤአ 1.2 በመቶ፣ ጅቡቲ በ2008 እኤአ 3.7 በመቶ፣ ሱዳን በ2020 እኤአ 1.1 በመቶ፣ ኬንያ በ2020 እኤአ 1.1 በመቶ፣ ሱማሊያ በ1989 እኤአ 1.5 በመቶ፣ ደቡብ ሱዳን በ2019 እኤአ 3.6 በመቶ ወታደራዊ ወጪ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ድርሻ እንደነበር የዓለም ባንክ መረጃ አስገንዝቦል፡፡………………………….(3)
በ2022 እኤአ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ከ142 አገራቶች ወስጥ የ65ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ For 2022,Ethiopia is ranked 65 of 142 out of the countries considered for the annual GFP review. It holds a PwrIndx* score of 1.0798 (a score of 0.0000 is considered ‘perfect’).
{1} የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል (Ethiopian National Defense Force’s (ENDF)
ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ የዓለም የማክሮ ሞዴሎችና ትንተና ግምቶች መሠረት ኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ በ2021 እኤአ መጨረሻ ድረስ ወታደራዊ ወጪዋ 502 (አምስት መቶ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር ወይም ሃያ አምስት ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ ተተንብዬ ነበር:: የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከጂዲፒ ድርሻው ሲሰላ (502ሚሊዮን /110ቢሊዮን x 100= 0.456= 0.5)፡፡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከ2011 እስከ 2022 እኤአ ከ466 ወደ 502 ሚሊዮን ዶላር እንዳደገ ይስተዋላል፡፡ በዚህም መሠረት እድገቱ በ2011 (466) ሚሊዮን ዶላር፣በ2012 (437) ሚሊዮን ዶላር፣በ2013 (438) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2014 (477) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2015 (489) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2016 (537) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2017 (545) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2018 (560) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2019 (545) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2020 (460) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2021 (502) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2022 (475) ሚሊዮን ዶላር፣ እንደሚሆን የመረጃው ምንጭ ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ዶት ኮም ዘግቦል፡፡ “Military Expenditure in Ethiopia is expected to reach 502.00 USD Million by the end of 2021, according to Trading Economics global macro models and analysts expectations. In the long-term, the Ethiopia Military Expenditure is projected to trend around 475.00 USD Million in 2022, according to our econometric models”……………………………………………..{4}
- Top Five Fighters to Modernise Ethiopia’s Air Force: From theF-16Vand J-10C to a Next Generation Su-57 Jet. Ethiopia today deploys on of the most capable armed forces on the African continent, with its Air Force today ranked fourth in Africa after Algeria, Egypt and Angola.Oct 13, 2020
- Zwijnenburg estimates that the Ethiopian government currently has a fleet of10 Chinese Wing Loong drones, “at least 4” Turkish Bayraktar TB2 drones and 2 other Iranian ones called Mohajer-6.Jan 25, 2022
- Most of the Ethiopian National Defense Force’s (ENDF) heavy weapons are ofSoviet/Russian and Ukrainian origin, including T-72 tanks and Su-27 and MiG-23 jet fighters.Nov 1, 2021
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል፡- የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት ከሠላሳ አመታት ውጊያ በኃላ 1983 ዓ/ም በህወሓትና ሻብያ ጦር ተሸነፈ፣ ግማሽ ሚሊዩን የሠራዊቱ አባላት ከስራ ገበታቸው ተበተኑ፡፡የመከላከያ ሠራዊቱ ከባባድ መሳሪያዎች፣ ታንኮች፣ መድፎች፣ ሚሳኤሎች፣ ቢኤሞች፣ ሞርታሎች ወዘተ ተዘረፉ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል ተዋጊ ጀቶች ተማረኩ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የጦር መርከቦችወያኔና ሻብያ ተቀራመቱት፡፡በወያኔና ሻብያ የተዘረፉትን የጦር መሳሪያዎች ዓይነትና ብዛትን የዘገበ ፀሃፊ የለም፡፡ ህወሓትበዘር ላይ የተመሰረተ የሠራዊት አደረጃጀት በጫካ በመጡት ሽምቅ ተዋጊ ሓይሎች ተገነባ፣ የወታደራዊ ሳይንስ በአፍጢሙ ተደፋ፡፡ ዘር ተኮር የጦር መኮንን ጀነራሎች ሹመት እንደ ጠበል በመለስ ዜናዊ ተርከፈከፈ፡፡ የኢትዮጵያ መለዩ ለባሽ አይቶት በማያወቀው የዘር ክፍፍል ታመሰ፣ የወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት የሌላቸው ሽምቅ ተዋጊዎች ትከሻቸውን ለጀነራል መኮንንነት ማዕረግናና ደረታቸውን ለኒሻን ሰጡ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል፡- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመከላከያ መርሆዎች :- (1) ‹‹የሀገሪቱ የ መከላከያ ሠራዊት የብሔሮች፣ የብሔረሰቦች እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋፅዖ ያካተተ ይሆናል፡፡››
- ህወሓት ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት አመታት አገዛዙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል በትግርኛ ቌንቌተናጋሪዎች ከፍተኛና መኃከለኛ ጀነራል መኮንኖች 95 በመቶ ስልጣኑን ተቆጣጥረው ነበር፡፡ ዝቅተኛው የበታች የሠራዊቱ አባላት በአመዛኙ ከአማራና ከኦሮሞ ቌንቌ ተናጋሪዎች የተመለመሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡
- ኦህዴድ ብልፅግና የአራት አመታት አገዛዝ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል የኦሮሙኛ ቌንቌተናጋሪዎች ከፍተኛና መኃከለኛ ጀነራል መኮንኖች 75 በመቶ ስልጣኑን ተቆጣጥረዋል፡፡ ዝቅተኛው የበታች የሠራዊቱ አባላት 75 በመቶ በአመዛኙ ከኦሮሞ ቌንቌ ተናጋሪዎች እንደተመለመሉ የኢትዮጵያ ህዝብና ሠራዊቱ ይመሠክራል፡፡ በዚህም መሠረት ኦህዴድ ብልጽግና ከህወሓት ኢህአዴግ ምንም ያልተማረ ዘረኛና ተረኛ የአገዛዝ ሥርዓት አራማጅ ሆኖል፡፡
- በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል ሚዛናዊ ተዋፅኦ ስለሌለ ትግራዩ የሰሜን ዕዝን መሳሪያ ዘርፎ በመታጠቅ የትግራይን ክልል ገንጥሎ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡ የሕወሓት ደብረፂዩንና የአብይ መንግሥት ስውሩ ድርድር በትግራይ አሸናፊነት እንደሚጠቃለል በአሜሪካ ትዕዛዝ ስምምነት ተደርሶል፡፡ ትግራይ ስብዓዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ ተስማምተዋል፣ በትግራይ የወደሙ መሠረተ-ልማት ግንባታ መብራት ፣ውኃ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ባንክ አገልግሎት በአስቸኮይ መገንባት፣ ወልቃይት፣ ሁመራ፣ ራያ ወዘተ ወደ ትግራይ ግዛትነት መመለስ፣ የትግራይ መከላከያ ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ በክልሉ እንዲንቀሳቀስ፣ የትግራይ የእራስን በእራስ የመወሰን መብት እንዲከበርላቸው በአሜሪካ ትዕዛዝ ስምምነት ላይ ተደርሶል፡፡
ኦህዴድ ብልፅግና (የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል)
በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ፣ የኦህዴድ ብልፅግና ከሶስተኛ ወደ አንደኛ ተገዳዳሪ ኃይል መሆን ሲችል ህወሓት ወደ ሁለተኛ ተገዳዳሪ ኃይል መሆን ችሎል፡፡ ብአዴን ብልፅግና ከሁለተኛ ወደ ሦስተኛ ተገዳዳሪ ኃይልነት ዝቅ ብሎል፡፡
የኦህዴድ ብልፅግና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል መልሰን አቆቁመናል አዲስ የሠራዊት መመሪያ አውጥተናል በሚል የኦሮሙማን ዘረኛና ተረኛ ሥርዓትን ለማስቀጠል አብይ አህመድና ብርሃኑ ነጋ ሽር ጉድ ያሉበት የቴሌቪዥን ትዕይንት ለታሪክ ማስረጃ ይሆናል፡፡ ኦህዴድ ብልፅግና የፖለቲካ ሴራ መሠረት የብሔር ብሔረሰብ ተዋፅዖን አሽቀንጥሮ በመጣል በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አራት እዞች ውስጥ ሦስቱን ዕዞች ኦሮምያ ክልል ውስጥ በማድረግ የኦህዴድ ብልጽግና ቡድን ዓይን ያወጣ የሃገርና የህዝብ ክህደት ፈፅመዋል፡፡
- የሰሜን መከላከያ ዕዝ፡-የኮነሬል አብይ መንግሥት በትግራይ ክልል የነበረውን የሰሜን ዕዝ መከላከያ በወያኔ መብረቃዊ ጥቃት ከተፈፀመበት በኃላ ሦስት መቶ ታንኮችና ከባባድ መሣሪያዎችን ኢትዮጵያ አጥታለች፡፡ ህወሓት የትግራይ ክልል መንግሥት የሰሜን ዕዝ መከላከያ እዝን ገንጥሎ በመግዛት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አስተዳደር ተገንጥሎል፡፡ ህወሓት የትግራይ መከላከያ ኃይል በመመሥረት የራሱ ተገዳዳሪ ኃይል ገንብቶል፡፡
- የደቡብ መከላከያ ዕዝ፡- የኦህዴድ ብልፅግና የደቡብ መከላከያ እዝን ከጥቁር ውኃ ወደ ቆጋ ካንፕ ኦሮሚያ ክልል አዘዋውሮል፡፡
- የምስራቅ መከላከያ ዕዝ፡- የኦህዴድ ብልፅግና የምስራቅ ዕዝ ከሐረር ወደ ቁልቢ ካንፕ ኦሮሚያ ክልል አዘዋውሮል፡፡
- የምዕራብ መከላከያ ዕዝ፡- የኦህዴድ ብልፅግና የአማራ ክልል የምዕራብ መከላከያ ዕዝን ከባህር ዳር ነቅለው ወደ ወለጋ ዕዝ ኦሮሚያ ክልል አዘዋውሮል፡፡
{2} የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (Oromo Liberation Army (OLA)
- ኦነግ ሸኔ ከኤርትራ ምድር ወደ ትግራይ በወያኔ ተባርኮ ወደ ወለጋ ጫካ የኦነግ መሪ ዳውድ ኢብሳና ጃል መሮና የአብይ ትያትር መሳሪያውን ሳይፈታ ከኤርትራ ጫካ ወደ ወለጋ ጫካ የገባ ስመ ብዙ ኦነግ፣ ኦነግ ሸኔ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በመባል የሚታወቅ ዘረኛና ሽብርተኛ ቡድን ነው፡፡ ኦነግ ሸኔና ኦነሠ የመሳሪያ ምንጭ የኦዴፓ ብልፅግና መንግሥትና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እንደሆኑ ይጠረጠራል፡፡ የመንግሥት የመከላከያ በጀት የመሳሪያ ግዥ ድርሻ ለኢትዮጵያ ሠራዊትና ለሽምቅ ተዋጊዎቹ ህወሓት እና ኦነግ እንደሆነ ይታመናል፡፡
- ኦነግ ሸኔ (የኦሮሞ ) እና የትግራይ መከላከያ ኃይል (TigrayDefence Forces (TDF) የጋራ ጦርነት ግንባር በመመስረት ወደ አዲስ አበባ በመገስገስ ወረራው ባይሳካላቸውም ህብረታቸው የፀና ነው፡፡
- ኦዴፓ ብልፅግና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሽመልስ አብዲሳ፣ ጃል መሮ፣ ጁሃር አህመድ የሻሸመኔ ጥቃት፣ አርሲ ነገሌ ጥቃት፣ የወለጋ ጥቃት ወዘተ በአመዛኙ ፀረ አማራ ሲሆን አማራን ከኦሮሚያ ክልል የማስወጣት ድብቅ የጋራ አጀንዳ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የአማራ ላይ የሚከናወነውን የዘር ፍጅት የግድያና የማረድ ድርጊት ኦነግም፣ ኦፌኮም፣ ኦዴፓ ብልፅግናም አንድ ቀንም ሲያወግዙ አልተሰሙም፡፡ እነዚህ የዘር የጦር አበጋዞች በዴሞክራሲ ስምና በነጻነት ስም የሚምሉ ጭንቅላታቸው የነቀዘ የአደንዛዝ ዕፅ ሠለባዎች ናቸው፡፡
{3} የትግራይ መከላከያ ኃይል (TigrayDefence Forces (TDF)
ህወሓት ኢህአዴግ በትግራይ መከላከያ ኃይል ስም ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶችን በጦርነት የማገደ ዘረኛ የጦር አበጋዝ ቡድን ሲሆን ሃያ ሰባት አመታት የስልጣን መንበሩ አክትሞ ዳግም ለመመለስ ሲል ሚሊዮኖች ቢያልቁ ደንታ የሌለው መሣሪያ አፍቃሪ የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ደንቆሮ የቦዘኔ ስብስብ ከትግራይ ህዝብ አናት ላይ ካልወረደ ሰላም አይመጣም፡፡ ትግራይን ህዝብን በስብዓዊ ጋሻነት በመያዝ በአንድ አውራ ፓርቲ ብቻ እንዲመራ በማድረግ ጸረ- ዴሞክራሲ አቆሙን ያሳየ ድርጅት ነው፡፡ ህወሓት የትግራይን ህዝብ ከኢትዮይያ ወገኖቹ ጋር ከአማራ፣ አፋር፣ ኤርትራ ህዝብ ጋር በማጣላት ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ፈፅሞል፡፡ ወያኔ በአማራ ክልል አድርቃይ፣ ፀለምትና አበርገሌን ወሮ በመያዝ ህዝቡን በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ ወያኔ በአፋር ክልል መጋሌ፣ በርሃሌ፣ አባላና ኮኖባ ወሮ በመያዝ ህዝቡን በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡፡
ምዕራባዊያን አገራት ትህነግን በመደገፍና ለማዳን አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአረብ ሊግ ፣ ግብፅ፣ ሱዳን ወዘተ በአንድ ረድፍ ቆመዋል፡፡ ምዕራባዊያን አገራት ለትህነግ በሱዳን በኩል ኮሪደር ለማስከፈት፣ በእህል እርዳታ ማቅረብ ስም የጦር መሣሪያ ለማስታጠቅ፣ የመገናኛ ሳተላይት ስልኮችና ዘመናዊ የመገናኛ ሬዲዩን ለማቅረብ፣ መድኃኒቶች ለማድረስ፣ ከሱዳን ያሉ አርባ ሽህ የትህነግ ሠራዊትን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ወዘተ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የማይፈነቅሉት ድንጊያ የለም፡፡
የህወሓትኢህአዴግ የቀን ቅዥት:-ወያኔ ያሰባሰባቸው የህብረት ኃይል እነሱን የመሰላል መወጣጫ አድርጎ ዳግም ወደ ሥልጣን መንበሩ ለመመለስ ያላገላበጠው ድንጊያ አይገኝም፡፡ ህወሓት ኢህአዴግ በመሠረተው የህብረት ግንባር ያሰባሰባቸው ድርጅቶች ‹‹የኢትዮጵያ ፈዴራሊስትና ኮፌዴራሊስት ኃይሎች›› ህብረት ውስጥ (1) የአፋር አብዬታዊ ዴሞክራቲክ የህብረት ግንባር Afar Revolutionary Democratic Unity Front (2) አገው ዴሞክራቲክ ንቅናቄ Agaw Democratic Movement (3) ቤኒሻንጉል ህዝባዊ የነጻነት ንቅናቄ Benishangul People’s Liberation Army (4) ጋምቤላ ህዝባዊ የነጻነት ንቅናቄ Gambella People’s Liberation Army (5) ዓለም አቀፍ የቅማንት ህዝብ መብትና ፍትህ ንቅናቄ/ ቅማንት ዴሞክራቲክ ፓርቲ Global Kimant People’s Right and Justice Movement/Kimant Democratic Party (6)የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ የነፃነት ሠራዊት Oromo Liberation Front/ Oromo Liberation Army (7) ሲዳማ ብሔራዊ የነጻነት ግንባር Sidama National Liberation Front (8) ሱማሊያ መንግሥት ተገዳዳሪ Somali State Resistance (9) የትግራይ ህዝባዊ ነፃነት ግንባር Tigray People’s Liberation Front በነፃነት ስምና በዴሞክራሲ ስም የተሰየሙ የዘር የጦር አበጋዞች እንኳን ለሌላው ዘር ለእራሳቸውም ዘር የማይበጁ የታሪክ አተላዎች ናቸው፡፡ ወያኔ የትግራይን ህዘብ በሁሉም አቅጣጫ የድንበር ግጭት በማድረግ ጠላት ፈጥሮለታል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግናም የኦሮሞን ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ የድንበር ማስፋት ግጭት ከፍቶ ከአጎራባች ህዝብ ጋር በሠላምና በፍቅር እንዳይኖር በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የወያኔ ህገ መንግሥት፣ አንቀፅ 39ና የክልሎች ካርታ በመቀየርና በማሻሻል የመለስ ዜናዊ የፖለቲካ ሴራ መበጣጠስ ያስፈልጋል፡፡
{4} ፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል (Fano Amhara Defence Force)
የኦህዴድ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ ስርዓት በዴሞክራሲ ስም፣ በእኩልነት ስም፣ በነፃነት ስም የሚሰራው አጸያፊ አድሎና አግላይ ስርዓት በቃህ ሊባል ይገባል፡፡ የአማራ ክልል ወጣቶች ሃገሩንና ህዝቡን ለመጠበቅ ያለደሞዝ፣ ያለ ትጥቅና ስንቅ (ሎጅስቲክ) አቅርቦት ለእናት አገሩ ዘብ የቆመ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው፡፡ ፋኖ በሬውን ሸጦ ክላሸን ኮቭ መቶ ሽህ አራት መቶ ብር እየገዛ የእራሱን ህልውና ያስጠበቀ ህዝባዊ ሠራዊት ነው፡፡ ፋኖ በእራሱ ሰልጥኖና ታጥቆ ወያኔንና ኦነግን በመፋለም ላይ ይገኛል፡፡ በሽብርተኛነት የተፈረጁት ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ትጥቅ ሳይፈቱ፣ ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ትጥቅ አይፈታም፡፡ ፋኖ እልፍ አእላፍ ወጣቶችን አስተባብሮ የአማራ ህዝብ አሌንታና መከታ ሆኖል፣ ተወደደም ተጠላ፣ በውድም ሆነ በግድ ሦስተኛ ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖል፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል በአማራ ክልል በህወሓት የተያዘውን የአማራ ግዛት አድርቃይ፣ ፀለምትና አበርገሌን እስኪለቀቁ ድረስ ትጥቁን ያጠብቃል እንጂ አይፈታም፡፡ በተመሳሳይ ወያኔ በአፋር ክልል መጋሌ፣ በርሃሌ፣ አባላና ኮኖባ ወሮ እንደያዘ ይገኛል፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል በአማራ ህዝብ ላይ ኦነግ ሸኔ የሚያደርስበትን ጭፍጨፋና የዘር ፍጅት፣ ሳያጠፋ ትጥቅ እንደማያወርድ እነ ዝናር በቅፌ ሊረዱት ግድ ይላል፡፡ ምክንያቱም የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ነውና፡፡
ኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል:-የኢትዮጵያ ህዝብ ግብርና ታክስ በመክፈል ለሠራዊቱ ደሞዝ በመክፈል፣ ቀለብ በመስፈር፣ እያኖረው እያለ ሃገሪቱ በሱዳን ወረራ ግዛቶ ተይዞ ዝም ማለት የወያኔ ኢህአዴግና የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት የፖለቲካ ሴራ ነው፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል በሱዳን የተወረረውን የአማራ ግዛት በደሙ ከፍሎ ለማስመለስ ብሶት የወለደው የቁርጥ ቀን ልጅ ነው፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል በህወሓት የተያዘውን የአማራ ግዛት አድርቃይ፣ ፀለምትና አበርገሌን እስኪለቀቁ ድረስ እየታገለ ሳለ ኦህዴድ ብልፅግና መንግስት ትጥቅ ለማስፈታት የጀመረው መንግሥት መር የአፈና ሽብርተኛ ድርጊት በህዝባዊ እንቢተኝነትና አመጽ ይቀለበሳል፡፡
- የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወታደራዊ ዩኒፎርም ዓይነት በመልበስ የኦሮሚያ ክልል ኃይል ኦሮሙኛ ተናጋሪ ወታደሮች በጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ ህዝብ ላይ በማዝመት የአማራና ኦሮሞ ህዝብ በማጣላት የፖለቲካ ሴራ ላይ ይገኛሉ፡፡
- የእርሻ ጊዜ ሆኖ ፋኖ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን እንዳይሠሩ በማድረግ በክልሉ ርሃብና ቸነፈር ሊከሰት እንደሚችል መንግሥት በእርሻ ወቅት የጦር ዘመቻ ማድረግ ውለታ ቢስነት ነው፡፡
- የፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል የአማራ ህዝብ በኢህዴን፣ ብአዴን፣ አዴፓ ብልፅግና ወዘተ የአማራ ክልል ግዛቶችን ወልቃይት፣ ሁመራ፣ ራያ፣ መተከል፣ ደራ፣ አዲስ አበባ ወዘተ ለትግራይና ለኦሮሞ ክልል አስተላልፎ የሸጠ የሞግዚት አስተዳደርን በቃኝ በማለት ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ሦስተኛ ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ መውጣት ለህወሓትና ለኦህዴድ የማይዋጥ የማይተፋ የጉሮሮ ላይ አጥንት ሆኖባቸው፡፡
- አብን የአማራን ትግል ለማጨናገፍ በብአዴኖች በበረከት ስምኦን ፍቃድና የፖለቲካ ሴራ የተቌቌመ የአማራ ነጭ ለባሽ የኦዴፓ ብልፅግና ፊርማቶሪ ድርጅት መሆኑን ለህዝብ አስመስክሮል፡፡
- የፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቶች ለማስጠበቅ በኢትዮጵያ ውስጥ በሠላም የሚኖሩ አማራዎች መታረድ፣ መገደል፣ መሰደድ ይቆም ብሎ ለነፃነት የቆመ ኃይል ነው፡፡
ማጠቃለያ
ኢትዮጵያ ሃገራችን በህገወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውርና ስርጭት በተለይ ከግብፅና ሱዳን በኩል ወደ ሃገርቤት የሚጫን ስፍር ቁጥር የሌለው የጦር መሣሪያ አንዱን ዘር ከአንዱ ዘር ጋር በማጋጨት እንዲሁም በኃየማኖት ግጭት በመቀስቀስ ሃገሪቱን በማያባራ ጦርነት ውስጥ እንድንኖር ተፈርዶብናል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በዴሞክራሲ፣ በነፃነትና እኩልነት ላይ የተመሰረተ ህዝባዊ መንግሥት በመመስረት ሁሉም የዘር ታጣቂ ኃይል ትጥቁን ፈትቶ አንድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማቌቌም የመጭው ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት ፍኖተ ካርታ አንኳር ይሆናል እንላለን፡፡ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ‹‹የማን ዘር ጎመን ዘር ›› እያሉ የዘር የጦር አበጋዞች እየተፈለፈሉ ሃገሪቱን የጦርነት እርሻ አደረጎት፡፡ አንድ ዓይና አልሞ ተኮሽና ደጋን የእጅ ጣቶች ያላቸው የሽምቅ ተዋጊዎች ሰው ከመግደል ስራ ወጥተው ዶሮ እያረቡ እንዲኖሩ፣ እርሻ እያረሱ በሠላም እንዲኖሩ ማድረግ የመጭው ትውልድ መፈክር ‹‹መቼም የትም አይደገም!!!›› Never and Ever Again!!! መሆን አለበት እንላለን፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ 640 ሚሊዮን ህገወጥ አነስተኛና ቀላል የጦር መሣሪያ በመላው ዓለም ውስጥ በህቡዕ ይዘዋወራል፡፡ ከዚህ ውስጥ 100 ሚሊዮኑ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በስውር ይተላለፋል፡፡ ከሳህራ በታች ባሉ አፍሪካ አገራቶች ቀጠና ውስጥ ደግሞ 30 ሚሊዮኑ በህገወጥ መንገድ ይሠራጫል፡፡ የሱማልያ አል-ሸባብ፣ የየመን ሁቲ፣ የናይጀርያ በካሃራም፣ የኢትዮጵያ ሻብያ፣ ህወሓት፣ ኦነግ፣ ወዘተርፈ የግማሽ ክፍለ ዘመን የህገወጥ የመሣሪያ ዝውውርን በማድረግ ጥርሳቸውን ከነቀሉበት ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ ከገዳዬችና አራጆች ይሠውረን !!! እንበል አስራሁለት፡፡
የታሠሩት የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ!!!
ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት ይቌቌም!!!
ምንጭ
(1) Ethiopia government to increase military budget by 500%/ByAddis Insight/May 28, 2022
(2) Military spending as GDP share by country 2021 | Statista
(3) Military expenditure (% of GDP) | Data (worldbank.org)
{4} Ethiopia Military Expenditure – Forecast (tradingeconomics.com)
https://tradingeconomics.com/ethiopia/military-expenditure#:~:text