የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ

ግንቦት 28 ቀን 2014 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም.  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review) ምክረ ሃሳቦች አፈጻጸምን ከማስተዋወቅና ከመቆጣጠር አንጻር የሲቪል ማኅበራት ያላቸውን ሚና የተመለከተ ሁለተኛ ዙር ስልጠና አዘጋጅቷል።

ሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review – UPR) በመንግሥታት የሚመራ፣ አሳታፊና በፍላጎት/ትብብር ላይ የሚመሰረት ሂደት ሲሆን፣ ሁሉም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገራት በሀገራቸው ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል እና የሰብአዊ መብቶች ግዴታቸውን ለመወጣት የወሰዱትን እርምጃዎች በማስመልከት ሪፖርት እንዲያቀርቡ ዕድል የሚሰጥ ነው። የግምገማውን ሂደት ተከትሎ በግምገማው የተለዩ ክፍተቶችንና ጉድለቶችን ለማሻሻል ምክረ ሃሳቦች ይሰጣሉ። ኢትዮጵያ በሦስት የ UPR ዙሮች (2002፣ 2006 እና 2011 ዓ.ም.) ባቀረበችው ሪፖርት ላይ አስተያየት ተቀብላለች። በ2011 ዓ.ም. በተደረገው ግምገማ ላይ ከ132 ሀገራት 327 ምክረ ሃሳቦች ለኢትዮጵያ የቀረቡ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል ኢትዮጵያ 270 ምክረ ሃሳቦችን ተቀብላ 57ቱን ሳትቀበል ቀርታለች።

ከጥቅምት 17 እስከ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት (Office of the High Commissioner for Human Rights) የሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review) ምክረ ሃሳቦች፣ እንዲሁም የተ.መ.ድ. የሰብአዊ መብቶች ተቋማት የሚሰጡትን ምክረ ሃሳቦች አፈጻጸም ከመቆጣጠር አንጻር የሲቪል ማኅበራት ያላቸውን ሚና የተመለከተ ስልጠና አዘጋጅተው ነበር። የክትትል ስብሰባውም ይህንን ስልጠና ተከትሎ የተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማው የሲቪል ማኅበራትን የሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review) ምክረ ሃሳቦች አፈጻጸም የመከታተል አቅምን የበለጠ ማሳደግ እና ለመከታተል የወሰዷቸውን እርምጃዎች ከሲቪል ማኅበራት ለመስማት ነበር።

የኢሰመኮ የሴቶችና ሕፃናት መብቶች ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ በመክፈቻ ንግግራቸው “የምክረ ሃሳቦች አፈጻጸምን አስመልክቶ መንግሥት ሪፖርት የማቅረብ ተቀዳሚ ኃላፊነት ያለው ቢሆንም የሲቪል ማኅበራት የምክረ ሃሳቦቹን አፈጻጸም አስመልክቶ የራሳቸውን ምልከታ ሪፖርት ለማቅረብ ልዩ ዕድል አላቸው” ሲሉ አስረድተዋል። ኮሚሽነሯ አክለውም የሲቪል ማኅበራት እና ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት በሀገራቸው ስላለው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ተዓማኒነት ያለው መረጃ በመስጠት በመንግሥት እና በአህጉራዊ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዙ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራዎች የተጨፈጨፉባቸው በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የጥናት ቡድኑ ገለጸ

የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት በተባበሩት መንግሥታት ሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review) ላይ ካላቸው ተሳትፎ ጋር በተገናኘ፤ በ2011 ዓ.ም. በተካሄደው የሦስተኛው ዙር የግምገማ ወቅት፣ እነዚሁ ማኅበራት የተቀናጀ ጥረት በማድረግ ወደ 10 የሚሆኑ ሪፖርቶችን አቅርበው እንደነበር ተገልጿል። የሲቪል ማኅበራት ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ቢኖርባቸውም ተግዳሮቶችን በመቋቋምና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሲቪል ማኅበራት አዋጅ መሻሻልን ተከትሎ ለኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት የተፈጠረውን የበለጠ ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም  ከሌሎች ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ጋር በመተባበር ጭምር አስተዋጾአቸውን ሊያጎለብቱ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት በአሁኑ ወቅት አገልግሎት ላይ ያሉ የሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review) የመረጃ ቋቶችን በመጠቀም እንደ ኢሰመኮ፣ የተ.መ.ድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት (Office of the High Commissioner for Human Rights) እና የብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርኃ ግብር ጽሕፈት ቤትን (National Human Rights Action Plan Office) ከመሰሉ እና ድጋፍ ሊሰጡ ከሚችሉ ተቋማት ጋር ተቀራርበው እንዲሰሩ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል። በስብሰባው የሲቪል ማኅበራት የሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review) ምክረ ሃሳቦች አፈጻጸምን በተመለከተ ሪፖርት እንዲያቀርቡ የሚያስችል እንዲሁም ተጨባጭ ውጤቶች እና የጊዜ ሰሌዳዎችን የሚያካትት ረቂቅ-እቅድ ተነድፏል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አልባብ ተስፋዬ በመዝጊያ ንግግራቸው፣ “ኢሰመኮ የኢትዮጵያን የሲቪል ማኅበራት የተባበሩት መንግሥታት ሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክን ምክረ ሃሳቦች አፈጻጸም ለመከታተል እንዲሁም ከዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ጋር እንዲሰሩ ለማገዝ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከፍተኛ ባልስልጣናትን ገድለዋል የተባሉት ከ15 ዓመት- እድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተሰጠ፡

3 Comments

  1. ያየህ ሰው ሽመልስ እንኳ በዚያ ሁኖ የስለላ ስራውን እንዲሰራ የተመደበ ነው እሱን ከዚያ ይፈታ ማለት ገቢ የሚያገኝበት ስራውን ማስተጓጎል ይሆናል እሱም ደስ የሚለው አይመስለኝም። ሌሎቹ ግን ለእኛም ለኢትዮጵያ አንድነትም የታሰሩ በመሆናቸው ልንጮህላቸው ይገባል። ጠቅላዩ ግን በጤናው ነው ቦካሳን በልጦ የተገኘው? ያች ክፉ ቀን ስትመጣ ነብዩ ጩፋ ያስጥለው እንደሆን ይታያል።

  2. የኦነግ አውሬያዊ መብት ጠባቂ አትሉትም? አማራው ላይ የሚወርደው የመከራ ዶፍ ደስታ የሚሰጠው ይመስላል። 2000 ከታረደ 2, 20000 ከአካባቢው ከተባረረ አንድ 20 ሰው ይልሀል ደሞዙን ፈረንጅ የሚከፍለው ይመስላል።

  3. Somewhere, Daniel Bekele says :

    “Federal and regional security forces should refrain from arresting suspects before criminal investigations and imprisoning journalists because of their work and arresting people irrespective of a court warrant and notify family members when individuals are arrested as well bring them before a court.”

    This is not the first time Daniel B. tells the government to refrain from violation of the constitution and other laws, but the government does not “refrain” from any of its illegal activities. Let alone refrain, t’s not even responding to his statements; it simply ignores him.

    If the government does not listen to its human rights officer, what the hell is Daniel B. doing as head of the institution? Isn’t his repeated empty cry of foul simply enabing the government to do what it wants to do more and more? If he stays as the top human rights officer who make statement with no consequences, how is he different from the arresting and torturing agents and judges that cooperate with the agents? At some stage, he should say enough.

    I feel that Daniel B. should resign from his position. He might claim that he better stay in his postion to further expose the illegal activites of the governemt. That argument might have made sense when he was appointed for the positon to verify the widely held opinion at the time that human rights situation is improvingi n the country. Two years after, it’s more than clear that the government is the worst violater of human rights the country has ever known.

    Daniel is supposed to know what to do under the prevailing situation: RESIGN.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share