የጎንደር ወጣቶች በአዘዞ አቡበከር ሰዲቅ መስጊድ የዒድ በዓል ማክበሪያ ስፍራን አፀዱ

 በጎንደር ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች አንዷ በሆነችው የአዘዞ ክፍለ ከተማ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ወጣቶች የተለመደ የዒድ በዓል የፅዳት መርኃ ግብራቸውን በአዘዞ አቡበከር ሰዲቅ መስጊድ በመገኘት አከናውነዋል።
የፅዳት መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ሰዎች በጎንደር ወንድማማች የክርስትና እና የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን ለመነጠል የተሴረው ሴራ ዋጋ የተከፈለበት እና የሚወገዝ ነው ብለዋል።
ይህ የፅንፈኞች ድርጊት ሳይበግረን በዓልን አብረን ለመዋል የተለመደ አብሮነታችን እየተወጣን ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የበዓሉ ቀንም ከመስጊድ እስከ ቤት በመገኘት እንደሚያከብሩት ገልፀዋል።
በመስጊዱ ፅዳት መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት አብደላ ኡስማን እና ሐጂ ፈንታሁን አደም ባለፉት ቀናት በጎንደር ሁለቱን እምነቶች አብሮነት ለማጠልሸት የተሠራው ሥራ ያሳዘናቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የዒድ በዓል በፀጥታው ስጋት ምክንያት በየዓመቱ ከሚከበርከት አፄ ፋሲል ስታዲየም መካሄዱ ቀርቶ በየመስጊዱ እንዲከበር በመወሰኑ በዓሉ የሚከበርበት መስጊድን ለማፅዳት የክርስቲያን ወንድሞች በመገኘታቸው የተለየ ትርጉም ያለው ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የጎንደር ሕዝብ ብዙ የሚፈተን፣ ነገር ግን የማይነጣጠል ወንድማማችነቱን በተግባር ያስመሰከረ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።
በፅዳቱ የተሳፉ የኅብረተሰብ ክፍሎችም በከተማዋ በተከሰተው የሽብር ሥራ የተሳተፉ ለሰዎች ሕይወት መጥፋት እና ለንብረት መውደም ሴራ የጠነሰሱ እና ያስተባበሩትን በመለየት መንግሥት አስተማሪ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
1 ሺሕ 443ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በነገው ዕለት በጎንደር በሁሉም መስጊዶች የዕምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ይከበራል።
ሚያዝያ 23/2014
ዋልታ
ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: የብሔራዊ ቡድናችን አማካይ አዲስ ሕንጻ ለሱዳኑ ክለብ ለመጫወት በ$100 ሺህ ዶላር ፈረመ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share