የሀጂ ሙፍቲ መልእክት

May 1, 2022

279465543 524124942695360 51720046658015468 n5 ነገሮች ከማምለጣቸው በፊት ሥሩባቸው። ዝረፉባቸው። ገብዩባቸው አትርፉባቸው።’ ብለዋል። ወጣትነትን፥ ሽምግልና ሳይመጣ፤ ክብረትን ድህነት ሳይመጣ፤ ሀያትን ሞት ሳይመጣ፤ ፈርያትን ደግሞ ጊዜያትን ያገኘ ሰው በግዚያቱ መስራት ነው። […] አሁን ወጣት እና ሥራ የያዘ ሰው እኩል አይደለም። ሥራ የያዘ ሰአት የለውም። ወላጅ ሰአት የለውም። ወጣት ሰአት አላው። ሰአታችሁን። ክብረትን፣ ወጣትነትን፣ ጤንነትን በሽታ ሳይመጣ፣ ህይወትን ሞት ሳይመጣ ሥሩባቸው።

ሁሉም ጊዜያዊ ነው። ሁሉም ጠፊ ነው። ኗሪ አይደለም። ወጣትነቱ ኗሪ አይደለም። ክብረቱ ኗሪ አይደል። ሰይጣኑ ኗሪ አይደል። የማይኖር ምን ያጣላናል? ይሄን እኮ አለመረዳት፣ ይሄን አለማወቅ ነው። የሰው ልጅ አብዛኛው አርቆ ባለማየት ነው የሚሞኘው። ጊዜያዊ ብቻ እየተመለከተ። ሌላው ደግሞ አብዛኛው በሰበካ ነው።

በተለይ የከተማ ሰው ሰበካ ይነዳዋል። አሁን የገጠር ሰው ተመልካች ነው። አላህን የሚፈራውንና የማይፈራውን ያውቁታል። ጠንካራውን እና (ደካማውን?) ያውቁታል። የከተማ ሰው ደግሞ የሚገርመው ነገር፣ እንዲያው ሰባኪ ካገኘ ተከትሎ መሄድ ነው። ይሄ ጥሩ አይደለም። ይሄ ነገር ይጠቅማል አይጠቅምም ብሎ ማወቅ አለበት አይደል?

ከእንስሳ የተለየንበት ነገር እኛ አቅል የሚባል ነገር ኖሮን ነው። ያንን ካላሰራ ሰው ከእንስሳ ልዩነት የለውም። ከእንስሳ ጋር እኩል ነው ማለት ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ አርቆ ማየት አለበት። “እሞታለሁ፣ ይህ ነገር ሁሉ ይቀራል።” (ብሎ ማሰብ አለበት።)

ጥሩ ስራ ለልጅም ይበጃል። ዘር ይወጣለታል። ልጅ ይወጣለታል። መጥፎ ስራ ሰርቶ ቢሄድ ሰውዬው በሕይወቱም ይረገማል፣ ይጠላል፣ ይዋረዳል፤ ከሞተም በኋላ ታሪኩ የተበላሸ ነው። ጥሩ የሰራ ሰው ግን በሕይወቱም ተከብሮ ተወዶ ይኖራል። ሲሞትም ደግሞ ታሪኩ ያምራል።

ሰው እንደው እንደ ቀልቡ፣ ነጋዴው እንደ ቀልቡ፣ አመራሩ እንደ ቀልቡ፣ ጥሩ ሰው ከሆነ ችግር ከየት ይመጣል? ደህንነት ከጠበቀ፣ ፖሊስ ከጠበቀ፣ አስተዳደር ከጠበቀ፣ ሁለት ሰው ሲጣላ ሕዝቡን ማብረድ ይቻል የለም እንዴ? በሺህ ሚቆጠር ሰው ሲፈናቀል አገር ጠባቂው ጎሳ ከሆነ ማነው የሚጠብቀው? አገር ጠባቂው ለአገር አሳቢ ካልሆነ ማነው ሚጠብቀው? ለሕዝብ አሳቢ ካልሆነ ማነው የሚጠብቀው? …

እኛ ደህና መሆን አለብን። በመጀመሪያ ደረጃ የሀይማኖት አባቶች የሀይማኖት አባት መሆን አለብን። ከላይ እስከታች ደግሞ አመራር ላይ ያሉ ሰዎች ሕዝባዊ አመራር ሊኖራቸው ይገባል። ሕዝባዊ አመለካከት፣ አገራዊ አመለካከት… እነሱን ለመጥቀም አይደለም እኮ ስልጣን የሚያዘው። ሕዝብ ለመጥቀም፣ አገር ለመጥቀም፣ እንጂ ነፍሱን ለመጥቀም አይደለም።

ከስልጣን ላይ የወጣ እንደሆነ በወር በሁለት ወር ልብሱ ይለወጣል። ኑሮው ይለወጣል። ይሄ አይደለም። ኑሮውን ሊለውጥ፣ ቤተሰቡን ሊለውጥ አይደለም ስልጣን የሚይዘው። አገር ሊለውጥ፣ ሕዝብ ሊለውጥ፣ ሕዝብ ሊያስተዳድር ሊመራ ነው እንጂ ለራሱ እና ለቤተሰቡ አይደለም። ይህንን ማወቅ እያንዳንዱ ይገባዋል። ሰላም አላህ ያድርግልን። አገራችንን ሰላም አላህ ያድርግልን።”

~ ሀጂ ሙፍቲ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

279657636 5388300227917381 5746710353305444625 n
Previous Story

የጎንደር ወጣቶች በአዘዞ አቡበከር ሰዲቅ መስጊድ የዒድ በዓል ማክበሪያ ስፍራን አፀዱ

279372485 296344456022350 2789295017710492672 n
Next Story

አዲስ የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop