ጎንደር ከተማ ላይ በግፍ የተገደሉት ወንድሞች ቁጥር ሶስት ደርሷል

በአሁኑ ሰዓት መስጅዶች እየተደበደቡ ነው፤ የመኖሪያ ቤቶች በጠራራ ፀሃይ እየተዘረፋና የሙስሊሞች ንብረት እየወደመ እንደሆነ ከነዋሪዎቹ ሰምተናል።
የክልሉ ለመንግስ አስቸኳይ ምላሽ ካልሰጠ ወይም የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ ካላረጋጋው ጥፋቱ በቀላሉ የሚቆም አይደለም።
እባካችሁን ህዝባችን ተጨንቋል።
ኃያሉ ጌታችን ሆይ! ተበድለናልና እርዳን።

በድሩ ሁሴን

ተጨማሪ ያንብቡ:  በ2 ወራት ውስጥ ከ16ሺህ በላይ ወታደሮች ጠፍተዋል፥ የኢሰመኮ ሪፖርት፥ የካናዳ ማስጠንቀቂያ፥ አብይ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ለማስወገድ?

2 Comments

  1. ትግሬዎች፤ አህመዲን ጀበል፤ጁዋር መሃመድ፤ኡስታዝ አቡበከር ሎቶሪ ወጣላችሁ ሰውን ስላም አትንሱት ብዙ ቤተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል ተከባብረን እንኑር አታቀጣጥሉት እናንተም የሰራችሁት ማስረጃዉ አለን።

  2. እብዶች የራሳቸውን ቤት አቃጥለው ድረሱልን ይላሉ ወይም ዘለው እሳቱ ውስጥ በመግባት አብረው ይነዳሉ። ጎበዝ አብደናል። አሁን ሰው በሃይማኖት ሳቢያ በዚህ ዘመን ይጋጫል? ይህ የሚያሳየው እየቆየን ኋላቀር መሆናችን ነው። የምታመልከው አንድ አምላክ የምትሰበሰብበት ሥፍራ የተለዬ መሆኑ ለብቻው ሰውን እስከ መገዳደል ያደርሳል? ግን ይህ ሁሉ ሸር ሃገርን ለማፍረስ ከታቀደው ሴራ ጋር አብሮ ይሄዳል። ለፈጣሪ ማንም ከማንም የበለጠ ቀናኢ ሊሆን አይችልም። የእስልምና እምነት ቤቶች እየነደድ የእኔ አትንኩ ማለትም አይቻልም። ተያይዞ መጥፋትና መንደድ እንጂ። ሲጀመር ሃይማኖት የሰዎች የማሰሪያ ገመድ ነው። በአስተሳሰብ ያስራል፤ ሰውን ያራርቃል፤ ያቀረበውን ያቀርባል የሚያሳድደውን ያሳድዳል፤ የእኔ እምነት ከአንተ ይሻላል በማለት ይለፋል። ይህ ሁሉ መለፋደድ ነው። የማንም ሃይማኖት፤ ወይም እምነት ከማንም አይበልጥም።
    እንዴት ባለ ምድር ነው ሰው ለቀብር ወጥቶ እንደ እንስሳ ተራርዶ ለመኖር ቃል የሚግባባው። የዚህ ሁሉ አትራፊ ሟችም ቋሚም አይደለም። የሃገሪቱን እንደ ጧፍ መንደድ የሚሹ የውጭና የውስጥ ሃይሎች እንጂ። ትላንት እልፍ ሰዎች በወለጋ፤ በአርሲ፤ በሃርርና በልዪ ልዪ ሥፍራ ሲታረድና ሲፈናቀሉ ሰላማዊ ሰልፍ ያልወጣው ሃበሻ አሁን ጎንደር ላይ በተጫረው እሳት ሳቢያ የራሳችውንም ለመጫር እንዲመቻቸው ተሰላፊ ሆነዋል። አይገርምም። እየመረጡ ማልቀስ ይሉሃል እንዲህ ነው። ሰው በዘሩ፤ በቋንቋና በሃይማኖቱ እይታ ብቻ ለሰልፍ ከቆመ ከቄራ ከብት በምንም አይሻልም። በጎንደር ለተፈጠረው ግድያና ዝርፊያ ተጠያቂዎቹ በህግ መጠየቅ አለባቸው። ግን እኮ ምንም ያላረገ ወገኑን የገደለ ፍጡር ለገዛ ቤተሰቡ ደህንነትም አያሰጋም? ውጊያና ፍትጊያ ከፈለጉ ይኸው ወያኔ በ 12 ክፍለ ጦር ራሱን አደራጅቶ ግጠሙኝ እያለ አይደለም። ሂድና ተፋለም እዚያ። የወስላታ ጋጋታ ከተማን ያጨናንቃል እንጂ ለሃገርም ለወገንም ደህንነት አይረባም። ሁሌ አካኪ ዘራፍ፤ ሁሌ ያዙኝ ልቀቁኝ፤ ሁሌ ፉከራና ቀረርቶ አይሰለችም? ህይወት እኮ የምትመዘንበት ሌላ ብዙ አይነት መንገድ አለ።
    I will bear witness: A Dairy of the Nazi years, 1933-1941 በተሰኘው መጽሃፉ ላይ Victor Klemperer እንዲህ ይለናል። ከምርጦቹ የአሪያን ዘሮች ያልሆኑት ከሞትም ቢተርፉ ናዚ ጀርመኒ በምታስዳድራችው ሃገሮች ላይ የሚቆጠሩት እንደ እቃ ነበር ይለናል። ግፈኞች ሲሰፍሩም ሲሰፈርባቸውም ጸጸትን አያውቁም። አብሮ መኖር በዓለም ዙሪያ ለእነርሱ ጥቅም እስካልሆነ ድረስ ዓለም ራሱ አብራ ብትቃጠል ደንታ የላቸውም። በተለይ ደግሞ በሃሰተኛና ያለ ቅጥ በተጋነነ የእምነት ጎዳና ውስጥ የገባ ማንም ሰው አይኑን ገልጦ የሌላውን ችግርና መከራ ለማየት አይቻለውም። ሁሌ በደላችን፤ ሃጢአታችን እያለ ይለፋል። ሰውን የሚበድለው ሰው ነው። ፈጣሪ አይደለም። የችግሩና የመከራው ሁሉ አዝናቢዎች እኛ ነን። በጎንደር የሆነውም ጢቢራቸው በተጣመመ የእምነት ዘይቤ በዞረባቸውና ሃገርን ለማፍረስ በተሰለፉ ቅጥረኞች የተፈጸመ በደል ነው። ነገሩን እንደማርገብ እያራገቡ ነዳጅ ማርከፍከፍም ተገቢ አይሆንም። እውነቱ ከሞቱት፤ ከተቃጠሉት ቤቶችና መስጊዶች ጋር አብሮ ተቃጥሏል። የምንሰማው ወሬ ሁሉ የተዛባ፤ ቅንጫቢና አጨብጫቢ፤ የበለጠ እንድንዳማ ሆን ተብሎ የተለጠፈውንና የተጻፈውን ነው። እውነት በሃበሻ ምድር እንደ ትንኝ እድሜዋ አጭር ነው። ላፍታ ታይታ የምትጠፋ! ከመጠፋፋታችን በፊት ጊዜ እያለ እናስተውል። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share