ኢትዮጵያ ክንዷን ለማዛል በጠላት የተራቆተችዉ በግልፅ በአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ግንቦት ፳ ቀን መሆኑን እና የሞት እና ክህደት አዋጂ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን (ዓማራ) ላይ ነበር ፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮ እና በፊት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኢትዮጵያዉያንን ትጥቅ ፤ ኢትዮጵያን መቀነት ማስፈታት የተጀመረዉ ዓማራን በትጥቅ እንዲቆይ ማድረግ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ዕንቅፋት መሆኑን የኢትዮጵያዉያን ጠላት አሊባባዎች መሪ መጠየቅ እንደሚሻል መተዉ ይሻላል፡፡
በዓማራ የግንባር ቀደም ትግል መስዋዕት “ኢህዲን” አማካኝነት የተገኘዉን ትግል የትህነግ ለማድረግ ከበረኃ አስከ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት መሳሪያ በተለያየ መንገድ በመቀማት መኖሩን ብሎም አዲስ አበባ ከገባ በኋላ የኢህዴን ጦር እንደ በግ ባዶ እጁን ወደ አስር እና አንግልት ተዳርጓል፡፡
በየትኛም ዓለም እና አገር የመንግስት እና ስርዓት ለዉጥ የአንድ አገር መከላከያ ህዝባዊ ፤ብሄራዊ ጦር ፈርሶ በአንድ እና ኢትዮጵያን እና ህዝቦችን አምርሮ በሚጠላ በኢህዴግ /ትህነግ ጦር ተተክቷል፡፡
ይህ ሳይበቃ የዓማራ አርሶ አደር ማህበረሰብ ከሚበላዉ ቆርሶ ፤ ከሚለብሰዉ ቀንሶ የነበረዉን የነፍስ ወከፍ ጦር መሳሪያ በሃይል ( በግድያ፣ በዕስር፣ በዛቻ…) ተቀምቷል፡፡
ለዚህም በተለይ የዕህል መጋዘኖች ፣ ት/ቤቶች ፣ ጤና ጣቢያወች……….ከመደበኛዉ የዕስር ቤቶች በተጨማሪ ይናገራሉ ፡፡
በዚህ አልበቃም በክል አስተዳደር እና በስራ ቅጥር ረገድ በዓማራ ክልል በሚባለዉ ሁሉ የቀድሞ ሥርዓት የህዝብ አገልግሎት የሰጡ ሁሉ ክልከላ እና ዕገዳ እንዲሁም ጡረታ ሲነፈጉ በተቃራኒዉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲሰራ የነበረዉ የህወኃት / ኢህዴግ ጦር ቅድመ አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት በበረኃ ለቆዩበት ጊዜ ጡረታ እንዲከፈል ሆኗል፡፡
ከዚህም በላይ በኢትዮጵያ -ኤርትራ ጦርነት ግንባር ቀደም ሚና የነበራቸዉን ኢትዮጵያዉያን ከጦርነቱ ማብቃት ማግስት ትጥቅ ቀርቶ ያለምንም ጥቅማጥቅም እና ዕዉቅና የተረሱት እና የተካዱት ኢትዮጵያዉያን በተለይም የዓማራ ማህበረሰብ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነዉ፡፡
የጥቅምት ሀያ አራት ሁለት ሽ አስራ ሶስት የክህደት እና ወረራ ጦርነት በትህነግ ሲጀመር ኢትዮጵያዉያን ራሳቸዉን እና አገራቸዉን ለመከላከል ቀርቶ ሊነክስ የሚመጣዉን ተናካሽ ዉሻ ለመመለስ እንደማይችል ስለሚታወቅ ነበር ፤ ነዉ ፡፡
ዕኮ ያኔ ኢትዮጵያ ከአናቷ ስትፈርስ መቀናቷን በግፍ ስትፈታ ፤ ልጆቿ በሴራ እጂ ከወርች ተቀፍድዶ ለሞት ፣ጥቃት እና ስደት ከተዳረጉበት የሰላሳ ዓመታት የመከራ ዘመን በመርሳት ኢትዮጵያን ዛሬ እንደመከነች ባዶ እጇን መሆኗን ዛሬ ዛሬ ማጮኅ ከንቱ ትዝብት ነዉ ፡፡
ትናንት ከጥልቅ የጥፋት ጂምር የኢትዮጵያን ጣራ ከማፍረስ አስከ ስብስቦ መግደል የሚታወቅ ሲሆን ይህም ታሪክን ካለማወቅ እና የራስን ማንነት መርሳት ምልክት ነዉ ፡፡
አንድ የእኛን የቆየ ብሄራዊ የአበዉ ብሂል ዞትር ልንመራበት የሚገባ ሲሆን ይኸዉም “ጂብ አስኪይዝ ያነክስ” የሚለዉን መርሳት ሠዉ አለመሆን ነዉ ፡፡
ይህን ጊዜ ነበር ኢትዮጵያዉያን እንዲሞቱ ሲፈረድባቸዉ የኢትዮጵያ ጠላቶች እንዲኖሩ ሲፈቀድ ኢትዮጵያዉን ትጥቅ የፈቱት፡፡
“ምንጊዜም ኢትዮጵያ ”
ማላጂ