“ትውልድና ሃገር እየገደሉ የተከበሩ መባል የለም!”

ዜና ቲዩብ አንድ መምህርን ጠቅሶ እንደዘገበው በአንድ ዩኒቨርሲቲ ከመምህራንና አመራሮች ጋር በተደረገ ስብሰባ ላይ የት/ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተገኝተዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ሚ/ሩን ወደ መድረክ ሲጋብዟቸው “የተከበሩ…” ይሏቸዋል። ፕ/ሩም ንግግራቸውን ሲጀምሩ “ማንም የተከበረ የለም። ትውልድና ሃገር እየገደሉ የተከበሩ መባል የለም። ምናል መስዋዕትነት ከፍለን መጪውን ትውልድ ከሞት የታደግን ከሆነ እነሱ የተከበሩ ሊሉን ይችላሉ” ይላሉ። ቀጥለውም የትምህርት ስርዓቱን መበስበስ ምክንያቶች በዝርዝር ከተናገሩ በኋላ የዩኒቨርሲቲው መምህራን የመፍትሄ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ጠየቁ።
ከቀረቡት ሃሳቦች ውስጥ 99% የቤት መስሪያ ቦታ እና የመኪና መግዣ ብድር ጥያቄ ነበር። ሚኒስትሩም ይህን ሲሰሙ በብስጭት ዩኒቨርሲቲውን ጥለው ሄዱ። ይላል ደረጀ ሃ/ወልድ በዘገባው።

Gedewon Teka Abegaz

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከባድ አደጋ ላይ ነን ግጭቱ ወደ መኮንኖች ተሸጋግሯል” አበባው አፈረጠው - “ኦሮሞዎቹ ይታጠቁ፣ ሌሎች ትጥቁን ያውርዱ” አብይ አህመድ

5 Comments

  1. After having successfully used him to consolidate his dictatorship, it looks like Abiy put Berhanu Nega to a worse punishment than Mengistu put Haile Fida to.

    Education is one of the pillars targeted by those who wanted to demolish the Ethiopian state. Berhanu, in the best of circumstances, will not be equipped to solve the problem. The root cause of the Ethiopian educational system is its alienation from the roots and realities of the nation (or its alienating nature). Bringing back the educational system of the fifties (that produced the likes of Meles, Berhanu etc) would not solve the problem, even if it were possible. It would not be desirable as it only produced a generation divorced from the Ethiopian knowledge system – Ethiopian hardware with European software.

  2. አሁን ከብርሀኑ በላይ ትውልድና አገር የገደለ አለ ማን ነው የጻፈለት ይህንን ካሁን በሗላ ማን ይጭበረበራል በዚህ ተልካሻ ፕሮፓጋንዳ?

  3. ደረጀ ያወራው ተረትተረት ይመስላል::ምናልባትም የብርሃኑን ስብዕና ለመገንባት ዳር ዳር እያለ ነው:: ይህ በራሱ አያስከፋም:: ችግሩ ግን ብርሃኑ ያለሙያው በትምህርት መስክ መመደቡ ነው::ሰውየው ሙያው በምጣኔ ሀብት ሆኖ ሳለ ለምን በዚህ መስክ እንደማይሠራ ግራ አጋቢ ነው::

  4. Hailu Yesuneh
    ስለ ብርሃኑ ትክክለኛ ግንዛቤ ያገኘህ አልመሰለኝም ሰውየው ለጥቂት ጊዜ የሆነ ኮሌጅ እንዳስተማረ ይነገራል ከዛ ውጭ ግን አብዛኛው ጊዜውን ያሳለፈው ምርት(ፕሮዳክት) በመሸጥ ወይም ደግሞ ኢኮኖሚክስ የሚጠይቀው ሙያ ላይ በመሰማራት ሳይሆን ፖለቲካን በመሸጥ ነው። በእርግጠኝነት በምትኖርበት አገር ብዙ ዶክተሮች ፕሮፌሰሮች ቢኖሩም ኢኮኖሚክስን በተመለከት የበላይ ሃላፊ የሚሆኑት ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ሳይሆኑ በስራው ጥሩ ልምድ ያካበቱ በስራቸው ምስጉን የሆኑ ዜጎች ናቸው። እነዚህን መስፈርቶች ብርሃኑ ላይ አታገኝም። ዲማ ነገዎ፤አረጋዊ በርሄ፤ዳውድ ኢብሳ፤ሌንጮ ለታ፤ሌንጮ ባቲ…….. እና ይህወአት ሹመኞችን ይጨምራል ስለዚህ ፕሮፌሰርና እኮኖሚስት የሚለው መጠሪያ አያማልልህ ለማለት ነው።ለዛውም የ ሶሻል ሳይንስ ትምህርት በየአመቱ 25% ስለሚቀንስ ዶክተር ብርሃኑ ከእውቀት የጸዳ ነው ብለህ መደምደም ትችላለህ። ከሆነለት ኮሚኒቲ ኦርጋናይዘር ልትለው ትችል ይሆናል ያም ቢሆን ነበልባል ትውልድ ስለሚበዛ አይችላቸውም። እንግዲህ ይመቸው አልመክረው 3 መንግስት ታግዬ ይህንንም በመገዝገዝ ላይ ነኝ ይልሃል። ይመቸው ምን አገባኝ አሁን ባለፈው እንዲሁ ሞቅ ብሎት እንቅልፋም ፓርላማ ብሎ በመሳደቡ አይለመደኝም ብሏል እንግዲህ ብሬ እንዲህ ነው በቦታው ከቆየ ብዙ ታያለህ።

  5. ነፃ ሃሳብን መስጠት ጥሩ ቢሆንም መረጃው እውነት እንዲኖረው መጣር ደግሞ አስተዋይነት ነው፡፡ እንደው በየትኛው አግባብ ነው ሰው በሙያውና በዕውቀቱ በዚህች አገር ስልጣን ላይ ሲሾም፡፡ ምን ሚኒስቴር ለመሆን የፖለቲካ ታምኝነት ብቁ ነው የተባለበት አገር እያለን፡፡ እንደውም ከተቋዋሚ ፓርቲ መምጣቱ ፕሮፌሰሩ ለየት ያደርገዋል ምንም እንኳን መድብለ ፓርቲ/Multi-party system/ በአግባቡ ባይሰራበትም፡፡ እንደው ይህ አባባል እውነት ከሆነ…..
    “ፕ/ሩም ንግግራቸውን ሲጀምሩ “ማንም የተከበረ የለም። ትውልድና ሃገር እየገደሉ የተከበሩ መባል የለም። ምናል መስዋዕትነት ከፍለን መጪውን ትውልድ ከሞት የታደግን ከሆነ እነሱ የተከበሩ ሊሉን ይችላሉ ይላሉ”

    ንግግራቸው ምኑ ላይ ነው ጥፋቱ ትውልድ ከሞተ ቆይቶ የለ!!!!!! ከኃይለ ስላሴ ጀምሮ፣ ደርግ፣ ወያኔ አሁንም ደግሞ ትውልድ በትምህርት ሻጥር ሲገደል፣ ሲዋረድ፣ ሲሰደድ፣ ሲንከራተት እና ቦዘኔ ሲሆን አደል የቆየው ታዲያ ምን ይደንቃል፡፡ አንዴ ማትሪክ ተሰረቀ፣ ፈተና ተጭበረበረ፣ በሙስና ተሰጠ፣ ሌባው አለፈ፣ አልአግባብ ዩኑቨርሲቲ ተመደበ፣ ያአለአግባብ A grade እያገኘ ስንት ዲግሪና ሰርተፊኬት ተሰጠ፡፡ አረ ስንት ነገር ሆድ ይፍጃው፡፡ በወረድ ትምህርት አሰጣጥ እስቲ አዚህች አገር ምን ለውጥ መጣ??????????????????? ከተወሰነ ተጠቃሚ በስተቀር፡፡ ታዲያ ፕሮፌሰሩ ቢናገሩ ምን ይደንቃል፡፡ ሰውየው እኮ በወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በነበሩ ጊዜ የመንግስትን የኢኮኖሚና ፖለቲካ ድራም ሲያገልጡ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተጠቁረው ስንት ችግር እንዳጋጠማቸው ታሪክን መፈተሸ ጥሩ ነው፡፡ ውጪም በትምህርት ዘርፉ የካበተ ልምድና እውቀት እንዳላቸው የተመሰከረ ነው ዝም ብሎ መዘርጠጥ ግን አለመማርን አመላካች ነው፡፡ የመኪናና ቤት መግዣ ብድር መጋነን ከሌለበት እና ወሬው ፍየል ወዲያ ቅዝምዝሚት ……. እንደሚባለው ሆነና ነገሩ እንጂ መንግስት የአገር ውስጥ ምርት ለማሳደግ በሚያደርገው ደካማ እንቅስቃሴ ዘይት 1200 ብር በሚሸጥበት አገር ጥያቄውም ቅንጦት ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን የትምህርትን ችግር ለመፍታት አነዚህ ነገሮች በሃሳብ ደረጃ መቅረባቸው ግን ድራማ ነው የሚመስለው፡፡
    ታዲያ የፕሮፌሰሩ መናደድ የተባለው ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ምንአልባት ነገሩ እውነት ከሆነ ሰውየው as “A CHANGE MAKER” ነገሮችን በአግባቡ በመጋፈጥ ለለውጥ መጣር አለባቸው EDUCATIONAL REVOLUTION የግድ አስፈላጊ ስለሆነ፡፡ በትዕግስት በደንብ መበወዝ አለበት፡፡ ካልደፈረሰ አይጠራም ነውና ነገሩ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share