በኢትዮጵያ 26.2 ሚሊዮን ህዝብ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ይፈልጋል፣በድርቁ 1.7 ሚሊዮን እንሰሳት ሞተዋል!

/

ሚሊዮን ዘአማኑኤል
ት-ኢኮኖሚ  /ET- ECONOMY

Current Food Security and Conflict areas in Ethiopia

ርሃብተኞችን በስብዓዊ ጋሻነት አግተው የእርዳታ እህልና መድኃኒት እንዳይደርስ በማድረግ የህፃናት እልቂት በሃገሪቱ እየተከሠተ ይገኛል፡፡ ርሃብን እንደ ጦር መሣሪያ በመጠቀም የዘር ፍጅት የፈፅሙ የፖለቲካ ወንጀለኞች ለፍርድ የሚቀርቡት ጊዜው አሁን ነው፡፡

የህወሓትና ኦነግ ጦር አበጋዞች የዝርፍያ ሲሶ መንግሥት

የትግራይ ህወሓትና የኦሮሚያ ኦነግ ሸኔ አሸባሪ ኃይሎች ሲሶ መንግሥት በግፍ ከአማራና አፋር ህዝብ  የዘረፉት ኃብት ሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት ባንኮች፣ የቴሌኮሙኒኬሽንና የመብራት ኃይል ግዙፍ የቴክኖሎጂ እቃዎች፣ የጦር ግምጃ ቤት ማሣሪያዎች ዘረፋ፣ የመንግሥት የእህል መጋዘኞች፣ የነዳጅ ዲፖዎች፣ የተዘረፉ መኪኖችና ባጃጆች ወዘተ   ተዘርፈዋል፣ በግፍ በተያዙ አካባቢዎች ከሚኖር ህዝብ ግብር መሰብሰብ ከጀመረ አመታት ተቆጥሮል፡፡ የአብይ አህመድ የብልፅግና መንግሥት በህወሓትና ኦነግ የተያዙ ግዛቶችን ማስመለስ  ያልቻለ መንግሥት ነው፡፡ ህወሓት ሽብርተኛ ቡድን መላ ትግራይን በመቆጣጠርና እንዲሁም ከአማራ ክልልና ከአፋር ክልል ግዛቶችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡

እንዲሁም ኦነግ ሸኔ የኦሮሚያ ክልል ገንጥሎ ግብር እየሰበሰበ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡ኦነግ ሸኔ በወለጋ አራቱ ዞኖች፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በጉጂ ዞን ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ በቦረና ዞን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ሞያሌ ከተማ አካባቢ ወደ ኬንያ የንግድ ኬላን ተቆጣጥሮል ይገኛል፡፡ የህወሓትና ኦነግ ጠመንጃ ነካሾች ሃገሪቱን ህዝብ በጠመንጃ አፈሙዝ ለመግዛት ከክልላቸው አልፈው ሌሎች ክልሎችን በመውረር አዲስ ግዛት በመያዝ በመስፋፋት ሥራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ብልፅግና መንግሥት አይቶ እንዳላየ ዝም ብሎቸዋል፡፡

በመሠረቱ የኢትዮጵያ መንግሥት በሃገሪቱ  የርሃብ አደጋ የለም በማለት ይክዳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ‹‹በትግራይ ርሃብ የለም!!!…‹‹ችግር አለ መንግሥት ማስተካከል ችሎታ አለው፡፡ ›› In fact, the Ethiopian government has denied there is any hunger crisis at all. “There is no hunger in Tigray,” Prime Minister Abiy Ahmed said this week. “There is a problem and the government is capable of fixing that.”………….(1)

የወያኔና የብልፅግና መንግሥት ርሃብተኞችን በስብዓዊ ጋሻነት አግተው የዘር ፍጅት የፈፅሙ በሄግ ፍርድ ቤት መቅረባቸው የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ርሃብተኞ ወገኖችን በስብዓዊ ጋሻነት (Human shield) በማገት የዘር ፍጅት የፈፅሙ በሄግ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ!!! ርሃብን እንደ ፖለቲካ ጦር መሣሪያ በመጠቀም ህዝብን አሰቃይቶ በመግደል ወንጀል የሚጠየቁ ፖለቲከኞች የስብዓዊ እርዳታ ለህዝብ እንዳይደርስ ያደረጉ ወንጀለኞች ተጣርቶ ለፍርድ ማቅረብ ዋነኛ አንገብጋቢ የፍትህ ጥያቄ ነው፡፡ የስብአዊ እርዳታና መድኃኒት እንዳይደርስ ህወሓት ብልፅግናን ይከሳል፣ ብልፅግና ህወሓትን ይከሳል፣ ስለዚህ ነፃና ገለልተኛ ወገን ገብቶ እንዲያጣራ የዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ጥያቄን በፀጋ መቀበል የሁላችንም ሃላፊነት ነው፡፡  ያልተገደበ ስብዓዊ እርዳታ ስርጭት በዓየርና፣ በየብስ ትራንስፖርት  እንዳይደርስ በማድረግ ተጠያቂ የሆኑት ማንም ይሁን ማን በነፃና ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ተመርምሮ ለፍርድ ይቀርባል፣ ለህዝብ እልቂት ዋና ተጠያቂዎች  የብልፅግና መንግሥትና ካቢኔው፣ የኤርትራ መንግሥትና ካቢኔው፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥትና ካቢኔው፣የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና ካቢኔው፣የአማራ ክልላዊ መንግሥትና ካቢኔው፣የአፋር ክልላዊ መንግሥትና ካቢኔው ናቸው፡፡ እንዲሁም የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግሥትና ካቢኔው  በአማራ የዘር ፍጅት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ “Food is definitely being used as a weapon of war”…UN Emergency Relief Coordinator Mark Lowcock, in an interview with Reuters, specifically called out Eritrean forces for “trying to deal with the Tigrayan population by starving them,” namely by blocking supplies and looting. “Food is definitely being used as a weapon of war,”

ተጨማሪ ያንብቡ:  አፈናው ቀጥሏል / ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ላይ የደረሰው ጥቃት

አብይ አህመድ መንግሥት መጣል ጊዜው አሁን ነው!!! አብይ አህመድ መንግሥት ከአሜሪካ ሦስት ቢሊዮን ዶላር እርዳት ለማግኘት ሲል ከትግራይ ጦሩን አስወጥቶ፣ የአማራን መሬት ለህወሓት ለማስረከብ ተስማምቶል፡፡ አብይ አህመድ ትግራይን አስገንጥሎ ቀሪዎን ኢትዮጵያ ለመግዛት ደጅ በመጥናት ላይ ይገኛል፡፡  በአራት አመታት የሥልጣን ዘመኑ  በኢትዮጵያ ውስጥ በጦርነትና ግጭት በተለይ በአማራ፣ አፋርና በትግራይ ክልሎች  በህወሓት፣ ኦነግና ብልፅግና ኤርትራ ተዋናዬች ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ህይወቱን አጥቶል፣ አስራ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ቀየውን ለቆ ተፈናቅሎ እርዳታ ጠባቂ ዜጋ ሆኖል፡፡  አንድ ትሪሊዮን ብር ንብረትና ኃብት ተዘርፎል ወድሞል!!! ኢትዮጵያ በጦርነትና በድርቅ ኢኮኖሚ ውስጥ ትገኛለች፡፡

{1} በኢትዮጵያ 26.2 (ሃያ ስድስት ነጥብ ሁለት) ሚሊዮን ህዝብ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ይፈልጋል፣ በጦርነቱ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው የአስቸኳይ ስብዓዊ እርዳታ ጠባቂ ህዝብ ቁጥር ከፍተኛ ሆኖል፡፡ በኢትዮጵያ ዕለታዊ የምግብ ደህንነት (CURRENT FOOD SECURITY) እና በኢትዮጵያ የግጭት ቀጠና (Conflict areas in Ethiopia October 29, 2021) በኢትዮጵያ ካርታዎች ከላይ ማስተዋል ይቻላል፡፡

  • በትግራይ ክልላዊ መንግስት 5.5 ሚሊዮን ህዝብ በ‹‹ደረጃ አምስት›› የአስቸኳይ ስብዓዊ እርዳታ ሲፈልጉ፣ ሦስት መቶ ሃምሳ ሽህ ሰዎችና ህፃናቶች በከፍተኛ ርሃብና እልቂት ውስጥ ይገኛሉ በአስቸኮይ ለህፃናቱ አልሚ ምግቦች ካልደረሰ ብዙ ሽህ ህፃናት ይሞታሉ፡፡ እርዳታው እንዳይደርስ የሚያደርጉ አከላት ርሃብን እንደጦር መሣሪያ  በማድረግ ተጠያቂ የሚሆኑበት ጊዜው አሁን ነው እንላለን፡፡

Right now, more than 5.5 million people — about 60 percent of Tigray’s population — are facing acute food insecurity. As many as 2.1 million are in the “emergency” phase, a level below catastrophe, and 3 million people are in the “crisis” phase. About 350,000 people in Tigray are facing a food “catastrophe,” which means they’re suffering from famine conditions. That classification is based on the Integrated Food Security Phase Classification (IPC), a global index that relies on assessments from United Nations agencies and other regional and international nongovernmental organizations.

  • በአማራ ክልል መንግስት 12.6 (አስራ ሁለት ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን  ህዝብ በተለይም በሰሜን ወሎ በዋግ ህምራ ዞን በድርቅ በጣም የተጠቃ አካባቢ በመሀኑ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡
  • በአፋር ክልል መንግስት 1 (አንድ) ሚሊዮን  ህዝብ ገደማ
  • በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 3.7 (ሦስት ነጥብ ሰባት) ሚሊዮን ህዝብ
  • በሶማሌ ክልላዊ መንግስት 3.4 (ሦስት ነጥብ አራት) ሚሊዮን ህዝብ

የብልፅግና መንግሥት የቅድመ መከላከል የድርቅ ሥራዎች ባለመሥራቱ በኦሮሚያ ክልል 3.7 ሚሊዮን እንዲሁም በሶማሌ ክልል 3.4 ሚሊዮን ህዝብ የአስቸኮይ ስብዓዊ እርዳታ ጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

{2} በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች 1.7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ሚሊዮን በላይ እንሰሳት ሞተዋል

  • በኢትዮጵያ ዕለታዊ የምግብ ደህንነት (CURRENT FOOD SECURITY)
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአዋሽ አርባ: የበረሃው ጓንታናሞ

ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት በተከሰተው ድርቅ በኢትዮጵያ በስተ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ አርብቶ አደር  አካባቢዎች የዝናብ እጥረት ያስከተለው የውኃ ችግር በእንሰሳ ኃብታችን ላይ ጉዳት አስከትሎል፡፡ በዚህም የተነሳ የእንሰሳት ስደትና የእንሰሳት ሞት አስከትሎል፡፡ በመንግሥት መረጃ መሠረት በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች 1.7 ሚሊዮን በላይ እንሰሳትን የገደለውን ድርቅ ለምን አስቀድሞ መከላከል እንዳልቻለ መልስ የለውም፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው በሶማሌ ክልል ውስጥ በሸበሌ፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ኦጎባ፣ እና ዳዋ ዞን  በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በቦረና ጉጂ፣ ምስራቅ ጉጂ፣ ምዕራብ ባሌ ዞን እና በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በዳሸና ወረዳ አርብቶ አደሮች ከፍተኛ የእንሰሳ ኃብት እልቂት ደርሶባቸዋል፡፡ አርብቶ አደሮቹ የሚመገቡት የእርሻ ምርትና የወተት ተዋፅዖ ኃብት ነጥፎል፣ በከብት ሽያጭም ዝቅተኛ ገቢ አግኝተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ Emergency(IPC Phase 4) ‹‹ደረጃ አራት››፣የአስቸይ ጊዜ የምግብ እርዳታ በኦሮሚያ ክልል ለቦረና፣ ለሱማሌ ክልል ዳዋ፣ ሊብንና አፍዴራ ያስፈልጋል፡፡ በተመሳሳይ Crisis (IPC Phase 3) ‹‹ደረጃ  ሦስት››፣ በደቡብ ክልል፣ በስተ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች እንደሚከሰት ተተንብዬል፡፡ ›› …………..(2)

በሰሜን ኢትዮጵያ  ጦርነት በተለይ በአማራና አፋር ክልሎች  ውስጥ በህወሓት አሸባሪዎች ብዙ ሽህ ከብቶች ታርደዋል፣ ተዘርፈዋል ተነድተዋል፡፡ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ክልሎች ውስጥ በኦነግ ሽኔ ብዙ ሽህ ከብቶች  ተዘርፈዋል፡፡  

  • በ‹‹ደረጃ አራተኛ›› የአስቸኮይ ጊዜ የምግብ እርዳታ፣ ስብዓዊ አርዳታ ለ9.6 (ዘጠኝ ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን ህዝብ 153000 (መቶ ሃምሳ ሦስት) ሽህ ሜትሪክ ቶን ምግብ  ከኖቨንበር እስከ ጀንዋሪ 2022እኤአ በትግራይ ክልል የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ አቅርቦት አነስተኛ መሆኑ ምክንያት ሰው ሰራሽ የስብዓዊ እርዳታ ማእቀብ በመደረጉ ነው፡፡የምግብ አቅርቦት እስከ ዲሴምበር 14 ድረስ  በትግራይ ምድር አልደረሰም ፡፡  እንደ የተባበሩተ መንግሥታት የስብዓዊ ጉዳዬች ቢሮ United Nations Office for the Coordination of Humanitarian Affairs. ፌብሪዋሪ አንድ በትግራይ ክልል  ከ1000 (አንድ ሽህ ) ሜትሪክ ቶን የምግብ ዕርዳታ ሲያስፈልግ 300 (ሦስት መቶ) ሜትሪክ ቶን ብቻ ለ 20000 (ሃያ ሽህ) ሰዎች የምግብ አቅርቦት የሚበቃ ብቻ ደርሶል፡፡ በትግራይ የምግብ አቅርቦት ስርጭት የተወሰነ ለመሆኑ አንዱ ምክንያት የነዳጅ እጥረት ችግር  ነው፡፡ በተረፈ ለራህብተኛው ወገን የምግብ እርዳታ እንዳይደርስ ዋነኛው ምክንያት ህወሓት የብልፅግናን መንግሥት ይከሳል፣ መንግሥት ደግሞ ህወሓትን ይከሳል፣አንዱ በአንዱ ላይ እያላከከ እርዳታው ለህዝብ እንዳይደርስ በማድረጋቸው ነፃና ገለልተኛ ወገን አጣርቶ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ለማቅረብ
  • በአማራና አፋር ክልሎች የስብዓዊ እርዳታ ስርጭት ዘለቄታዊና አስተማማኝ ያልሆነ ሲሆን በተለይም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለ5.7 (አምስት ነጥብ ሰባት) ሚሊዮን ህዝብ በወርሃ ኖቨንበርና 534000 (አምስት መቶ ሠላሳ አራት ሽህ) ሰዎች በወርሃ ጀነዋሪ ተመድበዋል፡፡ የስብዓዊ እርዳታ ስርጭት ለሱማሌ ክልል 1.65 (ለአንድ ነጥብ ስልሳ አምስት) ሚሊዮን ህዝብ በአራተኛውና አምስተኛው ዙር የምግብ ክፍፍል ተዳርሶል፡፡ ቀሪው የአራተኛው ዙር የእርዳታ እህል ድልድል ለሦስት ሚሊዮን ህዝብ ግጭት በሌለባቸው ተጎጂዎች በአማራ፣ድሬዳዎ፣ኦሮሚያ፣ሲዳማና በደቡብ ክልል ተከፋፍሎል፡፡  ››

 

{3} የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብዓዊ መብቶች ካውንስል በትግራይ ክልል የተካሄደውን ጦርነት ዳግም እንዲመረመር  በድምፅ ብልጫ አልፎና አዲስ በጀት ፅድቆ ሥራውን ለመጀመር ተዘጋጅቶል፡፡ ካውንስሉ በጦርነቱ ወቅት የተከሰተውን የጦርነት ወንጀል፣ የስብዓዊ መብት ጥስትና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ዳግም መርምሮ ወንጀል የፈፀሙትን አካላቶች ለዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ ያለመ ነው፡፡ በዘር ማጥፍት ወንጀል ለፍርድ የሚቀርቡ ዋና ተጠያቂዎች  የብልፅግና መንግሥትና ካቢኔው፣ የኤርትራ መንግሥትና ካቢኔውና፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥትና ካቢኔው ናቸው፡፡ ካውንስሉ በነፃና ገለልተኛነት ምርመራውን እንዲያጣራ መተባበር አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት አዲሱን ምርመራ ተቃውሞል፣ ለኮሚሽኑ በጀት እንዲታገድ ሁሉ ጠይቆ በድምፅ ብልጫ ከሽፎበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከአንድ ወር በፊት ከቤታቸው በሌሊት ተወስደውና አድራሻቸው ጠፍቶ የቆዬው ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ በአሁኑ ሰዓት ገላን ከተማ ታስረው ተገኙ

የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመሆን በትግራይ ክልል ከተከሰተው ጦርነት ጋር በተያያዘ፣ በተለይ በትግራይ ክልልና በተወሰነ መጠን በሌሎች አካባቢዎች ስለነበረው የስብዓዊ መብቶች ሁኔታ ምርምር በማድረግ የግኝቱን ሪፖርት ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ/ም በገራ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ምርመራ በኢሰመኮና በተመድ የስብዓዊ መብቶች ካውንስል ባለሙያዎች በጋራ የተከናወነ፣ እንዲሁም  በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኘ ቢሆንም በሕወሓት አመራሮችና በኤርትራ መንግሥት ተቀባይነት አላገኘም፡፡

ያለገደብ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ጥያቄ

የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ የአለም ጤና ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት የስብዓዊ እርዳታዎች ማድረስ እንዲችሉ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስብዓዊ እርዳታ የአየር በረራዎች ቁጥር እንዲጨምር፣ ለእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የነዳጅና የጥሬ ገንዘብ እንዲያቀርብ መንግሥትን ያስገድዳል፡፡ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች ከሠመራ፣ በአብአላ- መቀሌ የየብስ ትራንስፖርት መስመር በኩል የስብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መድረስ እንዲችል አስፈላጊውን ትብብር አድርገው ለርሃብተኛው ወገኖች እርዳታው እንዲደርስ ማድረግን ይጠይቃል፡፡  በቡዙ ሽህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የስብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች አማራ፣ አፋርና ኤርትራ እየተጎዙ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች እንዲጠናከሩ ማድረግ ያካትታል፡፡

 

{4} H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች  

በአሜሪካ መንግሥት ባወጣው H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች በሰሜኑ ጦርነት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት ወንጀል፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል የጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ወገኞች ሲቪል ሰዎችን እንደ ከለላ በመጠቀም በመኖሪያ ቤቶችና በከተማ ውስጥ ጦርነት በማካሄድ በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት እንዲከሰት ያደረጉ የኢትዮጵያ፣ ህወሓትና ኤርትራ ባለሥልጣኖች ላይ የንብረት ማምከንና የመጎጎዝ ነጻነትን ማገድ እርምጃ ይወሰዳል፡፡ እንዲሁም የጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች ዓለም አቀፍ የስብዓዊነት ሕግን በመጣስ ከባድ መሣሪያዎችን እንደተኮሱ፣ የዓየርና የድሮን ድብደባዎችን ሲቪል ሰዎች ላይ የፈፀሙ ላይ ተጣርቶ ውስኔ ይሰጣል፡፡

H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች ከጸደቀ በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግሥቶች ላይ በፋይናንስ፣ በደህንነትና በኢሚግሬሽን፣ በመከላከያና በፀጥታው ዘርፍ ራሳቸውን እንዳይችሉ ማድረግ፣ ብድሮችና የብድር ማራዘሚያ እንዳያገኙ ማድረግ፣ እርዳታ እንዳያገኙ ማድረግ እና የቴክኒክ ድጋፎች እንዳያገኙ የሚያደርግ ማእቀብ አዋጁ ይፀናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህም ምክንያት የዲያስፖራውን ድጋፍ ያጣው የአብይ ኦነጋዊ አራጅ መንግሥት የዲያስፖራው እግር ስር ወድቆል፡፡

የኦህዴድ ዘረኛ ወረራና የመስፋፋት ፖሊሲ  በህዝብ ትግል ይከሽፋል!!!

 

ምንጭ

(1) Ethiopia is facing a human-made famine – Vox

(2)Ethiopia – Food Security Outlook: Sat, 2021-10-23 to Mon, 2022-05-23 | Famine Early Warning Systems Network (fews.net)

(3)Ethiopia | Famine Early Warning Systems Network (fews.net)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share