“በ HR6600 ረቂቅ መሰረት በአማራ ላይ የዘር ፍጅት የፈፀሙ አካላት በሙሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል” ቴዎድሮስ ትርፌ

“በ HR6600 ረቂቅ መሰረት በአማራ ላይ የዘር ፍጅት የፈፀሙ አካላት በሙሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል።” ይህን ያሉት የአማራ ማህበራት በሰሜን አሜሪካ ሰብሳቢ ቴዎድሮስ ትርፌ ናቸው። በጉዳዩ ዙሪያ ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመው ንግግራቸው ቀጥሎ ቀርቧል።
~~
1. “ረቂቁን ተቃወሙ” የሚሉ ባለስልጣናት ጭንቀታቸው ኢትዮጵታያ እንዳትጎዳ ሳይሆን በሰሩት ወንጀል ልክ ተጠያቂ እንዳይሆኑ ነው፤ የኢትዮጵያ መጎዳት ቢያሳስባቸው ኖሮ ከ HR6600 ይልቅ ሀገሪቱ ውስጥ የሚፈሰው ደም ያስጨንቃቸው ነበር።
2. የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሉዓላዊነት ትዝ የሚላቸው ስለ ማዕቀብና ቅጣት ሲሰሙ ነው ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈፀሙ ግድያዎች ተጠያቂ ላለመሆን በሀገር ሉዓላዊነት ስም ለመደበቅ ይሞክራሉ።
3. የዘር ማጥፋትን የሚፈፅም መንግስት የሚቀጣው አካል ሊኖር ይገባል፤ እንደ HR6600 አይነት ረቂቆች የማይኖሩ ከሆነ ያለ ጠያቂ የሚፈፀመው የአማራ ህዝብ መፈናቀልና ጅምላ ግድያ ይቀጥላል ማለት ነዉ። ስለዚህ የግድ አሳሪ ረቂቅ ተግባራዊ መደረግ አለበት።
4. የኢትዮጵያ መንግስት የ HR6600 ን መፅደቅ በድጋፍ መቋረጥ ስም ማስፈራሪያ አድርጎ ለመጠቀም ይሞክራል፤ እውነታው ግን ከውጪ የሚላኩ ድጋፎች የካድሬ ምሳና ራት ከመሆን አልዘለሉም። ዛሬ ድረስ የተፈናቀሉ ወገኖች በከፍተኛ ርሃብ ውስጥ ናቸውና። ስለዚህ ድጋፎች ባይቋረጡም ለአማራ ህዝብ አይደርሱም፤ ቢቋረጡም የተለዬ ነገር አይኖርም፤ የተለዬ ነገር ካለም ለካድሬው፣ ለጆሮ ጠቢውና ለገዳዩ የሚከፈል ገንዘብ እጥረት ነው።
5. HR6600 ረቂቅ ጉዳቱን ብቻ የማጉላት አዝማሚያ ይታያል። ከአማራ ህዝብ አንፃር ካየነው ከHR6600 ረቂቅ ይልቅ የአብይ አስተዳደር የሚፈፅመው ግፍ አውዳሚ ነው።
6. እኛ HR6600 የአማራን ህዝብ በማይጎዳ እና በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት የፈፀሙ አካላትን ተጠያቂ በሚያደርግ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰራን ነው።
7. የHR6600 ረቂቅ የኢትዮጵያ መንግስትን ያዳክመዋል፤ ብሄር ለይቶ የሚጨፈጭፍ መንግስት መዳከሙ እንጂ መጠናከሩ ምን ይጠቅማል? መሳሪያ ያጣል? ይጣ፤ መሳሪያ ኖሮት የትኛውን ህዝብ ከየትኛው ግድያ አዳነ?
8. ሌላው የባለስልጣናቱ ጭንቀት መንስኤ የHR6600 በዘር ፍጅት ወንጀል የሚከሰሱ ባለስልጣናት ክስ የሚመሰርት መሆኑ ነው፤ ይሄንን ነው “አሜሪካ ሉዓላዊነታችንን ተዳፈረች፣ እጅ ጠመዘዘች” እያሉ የሌለ ምስል ለመፍጠር የሚሞክሩት።
9. ያም ሆነ ይህ በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረግ ግድያ፣ መፈናቀልና መገፋት በማንኛውም መንገድ መቆም አለበት፤ ይህንን የአብይ አስተዳደር ሊያደርገው ስላልቻለ የሚገደድበትን መንገድ ማዘጋጀት ግድ ነው፤ ከዛ መንገድ ውስጥ አንዱ HR6600 ነው።
የኢትዮጵያዊያን የአንድነት ኃይሎች የውይይት መድረክ
በአብይ አሕመድ የሕጻን ውሳኔ የተበተነው ዲያስፖራ ዛሬ ብትፈልገው ከየት ይምጣ?
በውጪ ያለው ዲያስፖራ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት ተሰባስቦ #NoMore ብሎ የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት ሲቃወም፣ የትህነግን አካሄድ ሲኮንን፣ ገንዘቡን አዋጥቶ ለተጎዱ ሲልክ ከርሞ ወደ ሀገር ቤት ከገባ በኋላ ጋሽ አያልቅበት(አብይ አሕመድ) በገና ዋዜማ የንቀቱን ውሳኔ አስተላልፎ ዲያስፖራውን አስቆጣ። ውጪ ሆነው ይይዙት የነበረውን ባንዲራ አዲስ አበባ ላይ ማውለብለብ አትችሉም ብለው በፖሊስ ያሳድዱ ጀመረ።
#NoMore የሚለው እንቅስቃሴ እንዳበቃለት አድርገው ከጦርነት በኋላ ስላለ ነገር መደስኮር፣ ዋጋ የከፈሉ ፋኖዎችን በጠላትነት መፈረጅ ወዘተ ጀመሩ። አሁን አሜሪካ “ማዕቀብ እጥላለው” ስትል ዞር ብለው አውግዙልን ተቃወሙል ይሉ ጀመር። አብዛኛው ዲያስፖራ ግን ከገና ዋዜማ በኋላ ነገሩን ቶታል። በአብይ አሕመድ አላዋቂነትና የሕጻን ሥራ የተበተነው ዲያስፖራ ማንም ሊሰበስበው አይችልም።
በግል ንቀትህ አላስፈላጊ ያደረከው ዲያስፖራ ዛሬ ከየት ይምጣ? የተቀጣጠለውን የተቃውሞ እሳት ሆን ብለህ ካጠፋህ በኋላ ማን መልሶ ይቆስቁስልህ?
Abenezer B.Yisihak

ንጉሥ ሆይ ፋኖን ማሣደድ ያቁሙ ዕዳው ለርሥዎ ነዉ

—————————————–
ንጉሥ ሆይ ፋኖን ማሣደድ ያቁሙ ዕዳው ለርሥዎ ነዉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ማን ያርዳ የቀረበ ማን ይናገር የነበረ ነውና ወንድማችን አርቲስት ዱባለ መላክ በራያ ግንባር ተገኝቶና ተሳትፎ ያየየውንና እየሆነ ያለውን በአሻራ ሚዲያ ቀርቦ ገልጾታል።


—————————–

ሾልኮ የወጣ የጠሚ አብይና የነብይት ብርቱካን የፀሎት የትንቢትና የምክር ድምፅ ቅጂን THM ለቆታል:: ቅጂው ጠሚ አብይ ሴኩላር ሀገርን ለመምራት


ሾልኮ የወጣ የጠሚ አብይና የነብይት ብርቱካን የፀሎት የትንቢትና የምክር ድምፅ ቅጂን THM ለቆታል:: ቅጂው ጠሚ አብይ ሴኩላር ሀገርን ለመምራት
———————————-

1 Comment

  1. ቴዲ፣
    ጄኖሳይድ ጄኖሳይድ ብላችሁ ሌላውን ለመወንጀል ስታስቡ ወደ እናንተው እንዳይመለስ!
    ፋኖ ብዙ እልቂት ብዙ ዘረፋ የሴቶች መድፈር ውስጥ ተሳትፏል፣ እንደ ወያኔው ማለቴ ነው።
    አላርፍ ያለች ጣት ማለቴ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share