March 22, 2022
3 mins read

የኦነግ ታጣቂ ጦር የ100 ዓመት ሽማግሌን በአሰቃቂ ሁኔታ በቤታቸው ውስጥ እንደገደለ ኢሰመጉ ገለፀ

257c681624d5b80fca56a62ee0f6a673የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሽላቸው መግለፃቸውን ገለፀ፡፡ ውጤቱ የተማሪዎቹን ስነ ልቦና የጎዳ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ተገቢውን ማብራሪያ እንዲሰጥና የእርምት እርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል፡፡
እንዲሁም፣ በፈንታሌ ወረዳ፣ አልጌ ቀበሌ ውስጥ ልዩ ቦታው መልቲ ፋብሪካ አካባቢ መጋቢት 9/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ወጣቶች ተገድለዋል ሲል ኢሰመጉ ገልጿል፡፡
እንደሚታወቀው፣ የአካባቢው ነዋሪ ጥቃቱ የተፈፀመው በኦነግ ሸኔ መሆኑንና ብሔር ተኮር እንደሆነም ይናገራል፡፡ ኢሰመጉ ባይገልፀውም፣ በፈንታሌ በተፈፀመው ጥቃት 9 ሰዎች በጥይት ተደብድበው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ 7ቱ አማሮች፣ 2ቱ የደቡብ ተወላጆች እንደሆኑ በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ስርዓተ ቀብራቸውም በአንድ ጉድጓድ ውስጥ በአልጌ ተፈጽሟል፡፡ ህይወታቸው በግፍ የተቀጠፉት ፡-
1. ዘሪሁን ደምሴ
2. ጌትነት ታምራት
3. ደባልቄ እሸቴ
4. ተስፋጽዮን ዳንኤል
5. ልዑልሰገድ መለሰ
6. ታደለ ኤልያስ
7. ቢኒያም ወንዜ ናቸው፡፡
እንዲሁም፣ ኢሠመጉ ባወጣው ሪፖርት ላይ፣ በምዕራብ ሸዋ መጋቢት 9/2014 ዓ.ም፣ አርብ ቀን፣ ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት፣ አምቦ ወረዳ፣ ኢላም ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ቄስ አምደጽዮን የተባሉ የ55 አዛውንት እና አቶ ተፈራ ኃይሉ የተባሉ የ100 አመት እድሜ ባለፀጋ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን ማረጋገጡን አትቷል፡፡ በሌላ በኩልም፣ በምዕራብ ወለጋ በርካታ ሕዝብ መፈናቀሉን፣ ንፁሐን መሞታቸውንና ንብረት መውደሙን ገልጿል፡፡
በመጨረሻም ባቀረበው ጥሪ፣ የፌደራል እና የሚመለከታቸው የክልል መስተዳድሮች በታጣቂዎች እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ፣ እንዲሁም የዜጎችን በሕይወት የመኖር እና የአካል ደህንነት መብቶችን እንዲያስከብሩ ጠይቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop