March 21, 2022
3 mins read

የ”ቅዱስ” አባታችን ፣ የኢትዮጵያ ወይስ የትግራይ ፓትርያርክ ለሌላው ሕዝብ ሌላ የሚቾህለት ፓትርያርክ ሳያስፈልግ አልቀረም

Mathias

ሰሞኑን ቤኒሻንጉል ላይ በትግራይ ተወላጆች ላይ ተፈጸመ የተባለው ጥቃት የሰውን ልጆች ልቦና ሁሉ ያደማል፡፡ በዚህ ልዩነት የለም፡፡ በየትኛውም መልኩ ቢሆን ወንጀል መወገዝ አለበት፡፡
ጥያቄው ግን ፣ የሁሉ አባት ተደርገው የሚታሰቡት አባት (የፓትርያርኩ) መርጦ ለቅሶ ነው፡፡
ፓትርያርክ ማቲያስ፣ የትግራይ ሰዎች ተጎዱ ሲባል ለመናገር ፈጣን ናቸው፡፡ ሚድያ ፈልገው አያጡም ፡፡ ሲፈልጉ በፈረንጅ በኩል፣ ሲፈልጉ በተወገዘው ቲኤሜች በኩል ለመናገር ፈጣን ናቸው፡፡
ወንጀልን ማውገዝ መልካም ነው፡፡ ግ ን ሀገር የሚመራ የሃይማኖት አባት መርጦ ሲያለቅስ ያሣስባል፡፡
አባ ማቲያስ ፣ አፋር ላይ ያ ሁሉ ሰው ሲያልቅ ምነው ድምጻቸው አልተሰማ? አነ ጭና ተክለሃይማኖት የመሰሉ ቦታዎች ላይ ያ ሁሉ ሰው ዘር እየተመረጠ ሲያልቅ ፓትርያርኩ ምነው አፋቸው ተለጎመ፡፡ እነ ማይካድራ ላይ ፣ ወለጋ ላይ ፣ ዘር እየተመረጠ ደም ሲፈስ ምነው አፋቸው አልተላቀቀ፡፡ወይስ ለሌላው ሕዝብ ፕትርክናቸው አይመለከተውም?
እንደ አባት ፣ ለሰው ዘር ሁሉ ይልቁንም ደግሞ ለተሾሙበት ኢትዮጵያ ሁሉ እኩል ማልቀስ ሲገባዎ፣ አባታችን ድምጻቸውን የሚያሰሙት ለአንድ ብሔር ብቻ ነው፡፡
አባታችን የትግራይ ፓትርያርክ ወይስ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ?

277005920 662094348336531 2721623907625901316 n

276165431 108217491822359 5624913832923409665 n

ከፎቶው ላይ ካቦርታ ለብሰው ፊት ለፊት ገጭ ብለው የምታዩአቸው የድሮው አባ ኃይለማርያም የአሁኑ ፓትርያርክ አባ ማቲያስ ናቸው። ፎቶውን የተነሱት ለወታደራዊ መንግስት ደርግ ለፖለቲካ ሥራ ወደ ጎንደር ስሜንኛ በሄዱበት ወቅት ነው። አባ ማቲያስ በሁለት የተለያዩ መንግስታት ሁለት እየቅል የሆኑ ፓርቲወችን (ኢሰፓና ኢህአዴግ) ፖለቲካ ሲያስፈጽሙ የኖሩ ጀግና የሃይማኖት መሪ እንደሆኑ መረዳት ችለናል። ስንቱ አባት ገዳም ተቀምጦ እኚህን አንዴ አሜሪካ ሌላ ጊዜ አውሮፓ፣ ሲፈልጉ ኢሰፓ ደግሞ ሌላ ጊዜ ህወሓት የሚሆኑት ፓትርያርክ ከሰሞኑ ደግሞ አይን ያወጣ ወገንተኝነት ያለው መልክት አስተላልፈዋል።

ነጋሪት – ዜና ጎንደር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop