አብይ አህመድ ስልጣን የያዘው በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተጋድሎ ነው….።”ግርማ ካሳ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና የወልቃይት አመራሮች በወልቃይት ባጀትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከፌዴራል መንግስት ሃላፊዎች ጋር ለመነጋገር አዲስ አበባ ሄደው ነበር….።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አራት ጊዜ ቀጠሮ ካስያዘ በሗላ አራቱንም ጊዜ አልችልም ብሎ እነ ኮሎኔል ደመቀን ለማግኘት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል….ያም የሆነበት ምክንያት በርግጠኝነት ህወሃቶችን ላለማስቀየም ነው…።

ወልቃይት ህዝቡን እንጠይቃለን ብለው እንዳለፈው እመቱ የጨረባ እንደ አሁኑም የብልፅግና አስቂኝ ምርጫዎች አታለው:አወናብደው ካፍታ ሁመራን በወረዳ ደረጃ ለህወሃት ለመስጠት ህወሃት የሱዳን ኮሪዶር እንድታገኝ ለማድረግ ከህወሃቶች ጋር ነገሮችን ተስማምቶ ጨርሷል……።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትግራይ ክልል እውቅና እይሰጥም የፊዴራል ባጀት ለዞንና ለወረዳዎች ይሰጣል ብሎ ወስኖ ነበር…።

በዚያ መሰረት ለትግራይ ክልል ከተመደበው 10 ቢሊዮን ብር 2 ቢሊዮን ለወልቃይት በገንዘብ ሚኒስቴር መላክ ነበረበት…ግን ዶ/ር አብይ አህመድ ገንዘብ እንዳይላቅ በቅርብ ጏደኟቹ አህመድ ሽዴና እዮብ ተካልኝ በኩል አሳግዷል….።

አሀመድ ሽዴ ከቦረና ኦህዴድ የነበረ በሗላ ሶማሌ ነኝ ያለ ገንዘብ ሚኒስቴር ነው። የሱ ምክትል ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ደግሞ ኦህዴድ ነው…።

ትልቁና አሳሳቢው ጉዳይ ግን አብይ አህመድ ይህንን አይነት አሳፋሪ ጨዋታ ሲጫወት በተለይም በአማራ ክልል ያለው ዝምታ ነው…።

በነገራችን ላይ አብይ አህመድ ስልጣን የያዘው በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተጋድሎ ነው…።

ኮሎኔል ደመቀን አራት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ ለማናገር አለመፈለጉ ትንሽነቱን የሚያሳይ ነው….።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “መሬትን መሸጥ፤ መለወጥ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግር ይፈታል ብዬ ፍጹም አላስብም።” - ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ

1 Comment

  1. Abiy”s giving TPLF a corridor would be suicidal for him. The west would love for TPLF to get a corridor through which it could bring in weapons of war using TPLF’S looted money stashed in foreign banks. If Abiy tries his gamble of allowing the Amhara region to be run-over by TPLF one more time again, there will be no photo ops next time around. He knows that, he is not dumb.

    On the other hand, as long as he sticks to the ethno-linguistic federal system, he cannot equitably solve the Welkait problem. In such a scenario, he may just continue with his typical tactics of confusion and conflict creation..

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share