የአብይ አህመድ ፊርማ – ፀጋ አራጌ ትኩዬ

March 16, 2022
ነባሩ ሰንደቅ ዓላማ አንድን ፓርቲ የሚወክል ነው ብሏል
Tsegaበዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ፊርማ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆኜ በመመደቤ አንዳንድ ሰወች ቀደም ብየ የታገልኩትንና ሌቦችን ያጋለጥኩበትን ትግል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ታዝዤ እና መጠረግ የነበረባቸውን ሰዎች ለማሰጠረግ የፈፀምኩት ተግባር አድርገው መመልከታቸው አሳዛኝ ነው።
መርህ እንዲከበር ያደረግኩትን ትግል የሴራ አካል ማድረግ ሌሎች ታጋዮች እንዳይፈጠሩ እና ሌቦችና ሙሰኞች እንዲበረታቱ በር የሚከፍት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት እንደነበሩት መሪወች ነቀፋዬን ችላ ከማለት እና በእኔ ላይም የበቀል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የህግና የመርህ ማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው በበጎ የሚታይ ለውጥ ነው። ከዚህ ውጭ የእኔን ነቀፋ ከመጥፎ አተያይ ከማየት ይልቅ በበጎ ወስደውት የበለጠ የሚያበረታታ የኃላፊነት ቦታ ላይ መመደቤ ሌሎች ጓዶችም በየዘርፉ ሌብነትንና ሙስናን እንዲታገሉ የሚያበረታታ ነው።

2 Comments

  1. ጸጋ አራጌ ትንሽ ጠብቅ አብይ ይህንን ለምን እንዳደረገው የሚያዉቀው እሱ ብቻ ነው ትዝብት ዉስጥ አትግባ። የአብይ ሃሳብ ያ ቢሆን ኑሮ አሁንም ሌቦችን የምታሳድድበት የፌደራል ተቋም ዉስጥ በመደበህ ነበር። ተው ከሰው አትጣላ ለማመስገንም ትምህርት ውሰድ ከአገኘሁ ተሻገርም ትምህርት ውሰድ።
    ፍትህ ለታምራት ነገራ

  2. አቶ ጸጋ፦
    ጀግንነትህን አድንቀን ሳንጨርስ በአጭቤው አብይ አህመድ ተጠልፈህ ጠ/ሚ/ሩ ብለሀን “ሹመቱን” ተቀበልክና አረፍከው፡፡ ህዝቡ የሚታገለው እኮ ስርአቱን ነው፡፤ የስርአቱ መሪ ደግሞ የምትላቸው ጠ/ቅላይ ሚንስትርህ ናቸው፡፡ አያሳዝንም??

Leave a Reply

Your email address will not be published.

275976388 2276521065837705 2031677047501494837 n 1
Previous Story

ወደ አማራ ክልል በርሃብ ሰበብ ከትግራይ የሚፈልሰው ህዝብ በአብዛኛው ወጣት ነው

Next Story

አብይ አህመድ ስልጣን የያዘው በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተጋድሎ ነው….።”ግርማ ካሳ

Go toTop