ለኢትዮጵያዉያን ስደት እና ሞት ያላባራ የዓማታት መከራ የሚያስደስታቸዉ የዉስጥ እና ዉጭ ጠላቶች ዛሬም በአዲስ ዓይነት ተግተዉ ይሰራሉ ፡፡
ህዝቡም በተለይ የዓማራ ማህበረሰብ በሆደ ሰፊነት እና በአርቆ አስተዋይነት ከግል እና ከማንነት በላይ ህይወቱን ሳይቀር ለብሄራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት መኖር እና መቀጠል ሲባል ሁሉን መቻል መርህ አድርጎ በመጓዝ አሁን ባለበት ሂደት እና ጊዜ ደርሷል ፡፡
ነገር ግን በመላ ኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት በኢትዮጵያዊነት ላይ ሲካሄድ የነበረዉ በማንነት ላይ የሚካሄድ ማሳደድ ፣ ማዋራድ እና ግድያ ተጠያቂነት አለመኖር ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዉያን ልትሆን እንደማትሆን በተግባር እየታየ ኢትዮጵያ ማለት መቆም ይኖርበታል፡፡
በአገራችን በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የጠላት ፍላጎት ለማስፈፀም ሲባል የኢትዮጵያን አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማዳከም የዓማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ አገረ መንግስት ምስረታ፤እና ለአገር ደህንነት እና ሉዓላዊነት ከፍተኛ ድርሻ ክህደት ከተጀመረበት ግንቦት ፳(ሀያ) አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት ዓ.ም. ተጀምሯል፡፡
ለዚህም በኢትዮጵያዊነት ጥላቻ የተቦካዉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የኢትዮጵያን ሁነኛ የረጂም ዘመን ታሪክ ክህደት እና የአማራ ህዝብ የጥላቻ መነሻ እና መዳራሻ ሆኖ በዓማራ ህዝብ ላይ በዓለም የሠዉ ልጂ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አሳኝ የዘር ፍጂት ተከናዉኗል፡፡
ነገር ግን አንድም ሠባዊነት እና ኢትዮጵያዊነት አለኝ የሚል ሠዉ ሆነ ኢትዮጵያዊ ሞት እና ፍዳ በኢትዮጵያ ምድር ይብቃ የሚል ጠፋ ፡፡
ሠዉነት፣ ዕምነት እና ብሄራዊ ማንነት እና ደህንነት ያለ ኢትዮጵያዉያን የግል፣ የቡድን እና የጋራ ነፃነት ባልተረጋገጠበት አገር አገር ማለት በቀቀንነት ነዉ ፡፡
ለአለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት ለተጎዱት ዕልፍ ዐዕላፍ ኢትዮጵያዉያን ለደረሰባቸዉ ዕንግልት ፣ስደት ፣ ድህነት እና ሞት የሚታደግ ዋስትና እና ኃላፊነት የሚወስድ ኃይል እና አካል አለመኖር ፣ለኢህዴግ / ትህነግ የግፍ አገዛዝ ለደረሰዉ መጠነ ሠፊ የዘር ፍጂት የሰማዕትነት መታሰቢያ ሊኖር በተገባ ነበር ፡፡
ይህ ባልሆነበት ብሀራዊ ዕርቅ ለማስገኘትእና ለጋራ መግባባት ዕዉን የሚሆነዉ የተገፉ በመደገፍ ፤ የሚያነቡትን በማበስ ፣ የሞቱትን በመዘከር አስካልሆነ ድረስ በህዝብ የዘመናት ሰቀቀን እና ሞት ዕድሜ መግዛት አገርን እና ህዝብን ከዉድቀት የሚያድን አይሆንም፡፡
በየጊዜዉ በድፍን ኢትዮጵያ በደረሰዉ ማንነት ተኮር የዘር ጭፍጨፋ እና በወረራ በቤታቸዉ ለሞቱ ኢትዮጵያዉያን የህሊና ፀሎት እና ብሄራዊ መታሰቢያ የሀዘን ቀን አለማወጂም ኢትዮጵያዊነት ሆነ ብሄራዊ ፤ህዝባዊ ኃላፊነት እና ስሜት የማይታይበት በዚህች አገር ላይ ለደረሰ እና እየደረሰ ለሚገኘዉ ዘግናኝ ዕልቂት ተጠያቂ እና ጠያቂ አለመኖር የመከራዉን ጉዞ እንደ አገር የሚራዝም ከመሆኑ በተጨማሪ ዕዉነት እና ነፃነት (ሰርቶ በህይወት የመኖር መብት) በማይታሰብበት ኢትዮጵያዊነት እና ሉዓላዊ ክብር ከንግግር የሚሻገር አይሆንም፡፡
ማላጂ
“ ነፃነት ወይም ሞት ”
ንጉሥ ሆይ ፋኖን ማሣደድ ያቁሙ ዕዳው ለርሥዎ ነዉ
—————————–
ሾልኮ የወጣ የጠሚ አብይና የነብይት ብርቱካን የፀሎት የትንቢትና የምክር ድምፅ ቅጂን THM ለቆታል:: ቅጂው ጠሚ አብይ ሴኩላር ሀገርን ለመምራት
ሾልኮ የወጣ የጠሚ አብይና የነብይት ብርቱካን የፀሎት የትንቢትና የምክር ድምፅ ቅጂን THM ለቆታል:: ቅጂው ጠሚ አብይ ሴኩላር ሀገርን ለመምራት
———————————-